Telegram Web Link
እስልምና እና ተፈጣሪያዊነት
Eslamic creationism thought

የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች እንደሚሉት የሚታየው እና የማይታየውን ኹሉ የፈጠረው አላህ ነው፡፡ በሰማይ ሆነ በምድር ያሉ ፍጡራን በሙሉ መኖር የሚመሰከሩት ዋነኛው ነገርም ህልውናውን ነው፡፡ ፀሐይ ሆነች ጨረቃ እንዲሁም ከዋከብትን የተፈጠሩትም ሆነ የሚታዘዙት ለአላህ ነው፡፡ ፈጣሪ በዓለም ላይ ያሉ ፍጡራንን ተዛማች ጥንድ አድርጎ የፈጠረው ማለትም ሰማይ እና ምድር፣ ሞት እና ሕይወት፣ ደስታ እና ሀዘን፣ የሚንቀሳቀስ እና የማይንቀሳቀስ አድርጎ ያበጀው የምንም እና የማንም ፈጣሪ እሱ እንደሆነ እንድንገነዘብ ዘንድ ነውም ይሉናል የሃይማኖቱ የሥነ መለኮት መምህራን፡፡ የሰማይን ከፍታ፣ የሌሊትን አጨላለም፣ የቀኑን መልክ፣ የምድር መዘርጋት በሙሉ የተደረገው በአላህ ይሁን ቃል ነው፡፡

እንደ እስልምና ሀይማኖት አስተሳሰብ አለም የተፈጠረችው በስድስት ቀን አፈጣጠር ትረካ ቢሆንም ብዙዎቹ የሀይማኖቱ መምህራን እንደሚሉት "ቀን" የሚለው ትርጉም የሰው የጊዜ አቆጣጠርን ("24 ሰዓት") አይገልፅም ይልቅ በአላህ የጊዜ አቆጣጠር ይወሰናል ይህም ማለት አንዱ ቀን ሚሊዮን አመታት ሊሆን ይችላል የሚል አስተምህሮ አለው።

የሰውን አፈጣጠር ከቅዱስ ቅራዓን አንፃር ምን መልክ እንዳለው ሳጠና ከገረመኝ ነገሮች አንዱ የሰዎች መልክ(የቆዳ ቀለም መለያየት) ምክንያት ምን እንደሆነ ያገኝውት ምላሽ ነው፡፡

"መልካችን የተለያየው፣ የቆዳ ቀለማችን አንድ
ያልሆነው አደም የተፈጠረበት አፈር አንድ ዓይነት ባለመሆኑ ነው።"ይላሉ

“አላህ አደምን ከወሰዳቸው የምድር አፈር አይነቶች ኹሉ ፈጠረው፡፡ የአደም ልጆችም በዚህ የምድር አፈር አይነት (መልክ) የተለያዩ ሆነው መጡ፡፡ ከነሱም ውስጥ ቀይ፣ ነጭ፣ ጥቁር፣ በዚህ መሀል የሆነም በመሆን መጡ...” (አቡ ዳዉድ 4695፣ ቲርሚዚይ 2955)

@zephilosophy
ፍልስፍናን እወዳለሁ' የሚል ግለሰብ እንደ ሃይማኖት ጠይ፣ በሌላ በኩል ሃይማኖቴን እጠብቃለው የሚለው ደግሞ ጥበብ የማይወድ፣ ፍልስፍናን' የሚሸሽ ወይንም ሊጠየቁ እና ሊመረመሩ ያልተገቡ እሳቤዎችን “አሜን” ብሎ የተቀበለ ሞኝ አድርጎ ሊወሰድና ሊታሰብ አይገባውም፡፡ ስህተት ነው። ዓማኝ መሆን ፍልስፍናን ከመውደድ የሚያግድበት አንዳችም ምክንያት የለውም፡፡ እንዲሁም አንድ ግለሰብ የፍልስፍና ወዳጅ ሰለሆነ ብቻ ኢ-አማኝ እና እምነትን የጅሎች መጫወቻ ካርድ አድርጎ የሚቆጥር ነው ብሎ መውሰድም ተገቢ አይደለም፡፡እንዲሁም ኢ-አማኝ ስለሆነም ምግባረ - ብልሹ  ነው ተብሎ ሊታሰብ አይገባውም።

@zephilosophy
የፍልስፍና ምንነት

ፍልስፍና የሰው ልጅ አካባቢውንና የራሱን ማንነት የሚረዳበት መንገድ ነው፡፡ ግምታዊ፣ ባህላዊ፣ ሳይንሳዊ ወይም ሐይማኖታዊ ከሆነው የግንዛቤ መንገድ በተለዬ ሁኔታ ነገሮችን ለመረዳትና ለመግለጽ የሚረዳ የእውቀት አይነት ነው ።

ከዚህ በተጨማሪ ፍልስፍና የምንለው የሰው ልጅ ማወቅ የሚፈልገውን ነገር ሙከራ ሣያደርግ፣ ልኬትንና ስሌትን ሣይጠቀም በህሊናዊ የመረዳትና የማመዛዘን ሁኔተ ብቻ ተጠቅሞ ነገሮችንና ሁኔታዎችን ለማወቅ የሚያስችለው መንገድ ነው::

የፍልስፍና እውቀት የተመሠረተው በህሊና  የመገንዘብ አቅም ላይ ነው፤ በአጭሩ የፍልስፍና እውቀት ህሊናዊ እውቀት ነው፡፡ ህሊናዊ እውቀት የሚገኘው ደግሞ በህሊናዊ ተግባር (rational enterprise) ነው፡፡

በህሊናዊ ተግባር እውነትን ከሀሰት፣ ትክክል የሆነውን ስህተት ከሆነው መለየት የሚያስችለን አዕምሯዊ ሥራ ነው፡፡ አዕምሮ ሠራ የምንለው መጠየቅ ሲጀምር ነው፡፡ ሲመራመር ነው፤ እውነትን ሲፈልግ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ህይወቱን የሚመራ ሰው ፈላስፋ እንለዋለን፡፡

ሚለር ተመሣሣይ ሀሳብ አላቸው::
“ፍልስፍና ህሊናዊ ተግባር በመሆኑ በአመለካከቶቻችን ሥር ሊኖሩ የሚችሉ ድንቁርናን፣ ጭፍን አምላኪነትን፣ ወገንተኛነትን፣ የሌሎችን ሀሳብ በጭፍን መከተልን ፤ አዕምሮቢስነትን ለማስወገድ ይሻል።የምንከተላቸው ሀሳቦቻችን መጠየቅ ፤ መመርመርና በማስረጃና በአመክንዮ መደገፋቸውን መፈተሽ ያስችለናል።

ፍልስፍና እውነትን ይፈልጋል፣ ትርጉምን ይፈልጋል፣ ሰው እየኖረበት ያለውን የኑሮ ዘይቤውን ጠንካራና ደካማ ጐኑን፣ የሚበጀውንና የማይበጀውን፣ መልካሙንና መጥፎውን ለመለየት ዕለት ዕለት ይፈልጋል፡፡ ፈላስፋም ፍለጋ ካልወጣ የኖረ ያህል አይሰማውም፤ ህሊናው እውነትን በመፈለግ ሱስ የተለከፈ ነው፤ ለፈላስፋ መኖር ማለት እውነትን ማወቅ ማለት ነው፡፡

ለዚህ ይመስላል ሜሪ ግሬስ (Mary Grace) የተባሉ ፈላስፋ የካቫኑ (John F.. Kavanaugh)  የሚለውን ጽሑፍ ተመስርተው የሚከተለውን ለመናገር የተገደዱት፡፡

"ፍልስፍና ሰዎች ደስ ብሏቸው እንዲኖሩ መነቃቃት ይፈጥርላቸዋል፤ ብዙ መጠየቅ፣ መመለስ፣ መረዳት፣ መማር ያለብህ ነገር አለ በሚል አስተሳሰብ ተገፋፍተው መኖር እንዲችሉ ያደርጋቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ምንም እንኳ ሥቃይ የሚፈጥሩ ፈተናዎች በየመንገዱ ላይ ቢኖሩም ፍልስፍናን መከተልና መያዝ ዋጋው ከፍ ያለ፣ አስደሳች፣ ህሊና የሚሰጠው ሃሴትም ተወዳዳሪ የሌለው ነው፡፡

የፍልስፍናን ምንነት ለመረዳት ባደረግሁት ጥረት በብዙ ነገር ብስለትን (ዕድገትን) እንደጨመርሁ አምናለሁ፤ እናም ራሴን ከፍልሰፍና ውጭ አደርጌ ማሰብ የማልችል ነገር ሆኖብኛል፡፡"
ትለናለች

ለመሆኑ ፈላስፋ ምን አይነት ባህሪ አለው?

ይቀጥላል
@zephilosophy
የፈላስፋ ህይወት በምን ይገለፃል?

የአማርኛው መዝገበ ቃላት “ፈለሰፈ” እንዲሁም “ፍልሰፋ” የሚሉትን ቃላት ልዩ ልዩ ብልሃትንና ጥበብን ከአእምሮ እያመነጨ አስገኘ፣ ያልነበረውን የጥበብ ሥራ ፈጥሮ አገኘ፣ ያልተገለጠውን (ያልታወቀውን) እንዲታወቅ አደረገ፣ ጥበብን(እውቀትን) ወደደ በማለት ትርጉም ሰጧቸዋል፡፡

የሚከተሉት ባህሪዎች ደግሞ ፈላስፋዎች የሚኖሩትን ህይወት ሊያመለክቱ የሚችሉ ዋና ዋና መገለጫዎች ናቸው።

1.ፈላስፋዎች የእውቀት ሱሰኞች ናቸው፤ አዲስን ነገር ለማወቅ የተራቡ ናቸው:: ነጋም መሸም ያው ነው - እውቀትን መፈለግ የጊዜ ገደብ የለውም፡፡ ለፈላስፋ ጊዜ፣ ቦታ፣ ሁኔታ እውቀት ማስገኘት አለባቸው፡፡ ለፈላስፋ እውቀት በልተው የማይጠግቡት የሚጣፍጥ ምግብ ነው፣ ጠጥተው የማይረኩት ጣፋጭ ወይን ጠጅ ነው፡፡ ሰዎች፣ ተፈጥሮ. ሌላም ሌላም... እግዚአብሔርም ይሁን ለፈላስፋ ሁሉም እውቀት ናቸው፡፡ ተፈጥሮ የያዘችው የሚያስደምም ህብርና ሥርዓት ምስጢር ማወቅ ጉጉታቸው መጠን የለውም፡፡ የሰውን ግላዊ፣ ማኅበራዊና ተፈጥሯዊ ማንነቱን፣ ተስፋውንና ጭንቀቱን ለማወቅ ሥሥት ያደረባቸው ናቸው፡፡ ፈላስፋ ለማንም አይገዛም ቢባል የተጋነነ አይሆንም፣ ግለ - ታሪካቸው ይመስክራልና፡፡ ነገር ግን ለማንም የማይረታው ልቦናቸው ለአንድ ነገር ተሸናፊና ባሪያ ነው - ለእውቀት!

2.ፈላስፋዎች ሌላው የሚታወቁበት ነገር ለሰው ልጅ እጅግ አሳቢዎች መሆናቸው ነው:: ከማንም በላይ ህብረተሰብ የሚሠቃይባቸው ችግሮች ይሰማቸዋል፡፡ ህብረተሰብን ለከፋ ህመም የዳረጉ ቁስሎች እነርሱንም ይጠዘጥዛቸዋል፡፡ ህብረተሰብ ገመናውን በይስሙላ ከበሮችና ወዳሴዎች መሸፈኑ ያንገበግባቸዋል፡፡ ለፈላስፋ የሰው ልጅ በእውነተኛ ማንነቱ መኖር እስካልቻለ ድረስ ህሊናቸው ረፍት አያገኝም፡፡ ሰው ተስፋ ያጣበት ነገር ፈላስፋን አንገቱን ያስደፋዋል፤ ከትካዜውም አይመለስም፡፡ ፈላስፋ ሰው ከሀዘኑ፣ ከጭንቀቱ፣ ከችግሩ የሚያወጣ እውቀት እስካላገኘ ድረስ የሚበላውን፣ የሚለብሰውን፣ የሚኖርበትን፣ ወዘተ እስኪረሳ ድረስ በሀሳብ ይናወዛል፡፡

የሰው ልጅ ተስፋ ማጣት ጩኸት በቀንም በሌሊትም በጆሮው ያቃጭልበታል፣ «ምን ልሁን? ተስፋ ቆረጥሁ፣ ታደገኝ እያለ የሚጠራው ይመስለዋል፤ ነፍሱ በህዝቡ ሰቆቃ መሃል ሁና ትዋትታለች፡፡ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሥርዓቶች በሰው ልጅ ላይ የሚያደርሱት በደል መታገስ የሚችልበት ጉልበት የለውም - ነፍሱ ከተበደሉት ጋር ናት - ሲያለቅሱ ታለቅሳለች፣ ሲታራዙ፣ ሲራቡ፣ ሲሰደዱ አብራቸው ትሰደዳለች፡፡

3.ፈላስፋነት አማጺነት ነው፡፡ፈላስፋ መጥፎ ሥርዓት ላይ አማጺ ነው፡፡ ተፈትኖና ተመርምሮ ባልተረጋገጠ አስተሳሰብና እምነት ጋር አብሮና ተመሣስሎ ላለመኖር እንቢተኛ ነው፡፡ በአጓጉል ማኀበራዊ ሥርዓቶች ተጨፍልቆ ላለመኖርና ራሱን ነፃ ለማውጣት ይጥራል፣ በራሱ ህሊና ለመምራትና የራሱን ማንነት ይዞ ለመገኘት ህሊናው በማይቀበላቸው እምነቶችና አስተሳሰቦች ላይ ያምፃል፡፡ ህሊናውንና ማንነቱን አሳልፎ ሳይሰጥ በተረዳውና በአመነው ነገር ላይ ብቻ ህይወቱን ለመምራት የስብዕና ጥንካሬ ያለው ፈላስፋ ነው፡፡

4.ፈላስፋ ራሱን የሚቀድስ ሰው ነው፡፡ ግለሰቦችና ማኅበራዊ ሥርዓቶች ከሚያደርሱት በደል ራሱን በእውቀት እያበቃ ተካፋይ ላለመሆን የእውነት መንገድን እየፈለገ የሚኖርና ከህብረተሰብ  ‌እድፍ ራሱን የሚያነፃ ፈላስፋ ነው፡፡ ስሜታዊነትን፣ አድሏዊነትንና ወገንተኛነትን ከህይወቱ በማስወገድ ስብዕናውን የሚቀድስና በእውቀት የቅድስና ህይወት መኖር የሚችል ፈላስፋ ነው፡፡ፈላስፋ ምድራዊ ለሆነው ማንነት (ለሥጋዊ ደስታ፤ ለክብር፣ ለዝናና ለሐብት) ብሎ ህሊናውን የማይሸጥ እና ላመነበት ነገር እስከ ሞት ፅዋ ድረስ የሚጋፈጥ ነው።

ረ/ፕሮፌሰር ዋለልኝ እምሩ
@zephilosophy
“የተነገራችሁን ሁሉ በቀጥታ እንደወረደ አምናችሁ አትቀበሉ፡፡ ከዚያ ይልቅ እውነትን በብልሃትና በንቃት ለማግኘት ሞክሩ፡፡ እውነት ሁልጊዜ ተሞክሮ ነው፡፡ የኔ እውነት የእናንተ ሊሆን አይችልም፤  እውነትን ልንጋራው አንችልም፡፡ እኔ የምሰጣችሁ ግንዛቤ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ እያንዳንዱ ሰው እውነትን ደጋግሞ በራሱ ማግኘት አለበት፡፡ ስለሆነም ለመመራመር፣ ለመጠየቅ፣ ለመሞከር ፣ለመተገበር ትጉ፡፡”
ኦሾ
@zephilosophy
ብቸኝነትን የመረጥኩት....
ካህሊል ጂብራን

"ከአለም ተነጥለህ ብቻህን ለመኖር እንዴት መረጥክ ?"
ብዬ ጠየኩት

በሀሳብ ተውጦ በዝምታ ከቆየ በኋላ እንዲህ አለ

‹‹በፍጥረቶቹ መካከል እየኖርኩ እግዚአብሔርን ማምለክ እችል ነበር፤ ማምለክ ለብቻ ተነጥሎ መኖርን አይጠይቅምና! ሰዎችን የተውኳቸው እግዚአብሔርን ለማግኘት ስል አልነበረም፡፡ በአባትና በእናቴ ቤት ሆኜም አገኘው ነበር፡፡ ከሰዎች የተገለልኩበት ምክንያት ተፈጥሯቸው ከእኔ ተፈጥሮአዊ ባህርይ ጋር ስለተጋጨ እንዲሁም ህልማቸው ከህልሜ ጋር ባለመስማማቱ ነው፡፡

‹‹ብቸኝነትን የፈለግሁት ራሳቸውን ሽጠው በተመሳሳይ ዋጋ በመንፈሳዊም ሆነ በቁስ አካላዊ መስፈርት ከእነሱ ያነሰች ነገርን የሚገዙ ሰዎችን ፊት ላለማየት ስል ነው...

‹‹ብቸኝነትን የፈለግሁት የዕውቀትን መንፈስ በህልሞቻቸው ውስጥ አይተው ግባቸውን እንደመቱ ከሚያምኑት ከእነዚያ በራሳቸው ከሚረኩት ሰዎች እራሴን ለመሸሸግ ስል ነው...

‹‹ከማህበረሰቡ የሸሸሁት እውነትን ባያዩም መንፈሱን ባይገነዘቡትም እና ለዓላማቸው መሳካት ሲሉ ብቻ የእውነትን ፍሬ ነገር ሙሉ ለሙሉ እንዳገኙት አድርገው ከሚለፍፉት ለመራቅ ነው::

‹‹ከዓለም ተነጥዬ ብቸኝነትን የፈለግሁበት ምክንያት ትህትናን ደካማነት፣ ምህረትን ፍርሃት፣ ትምክህትን ደግሞ የጥንካሬ መገለጫ እንደሆነ አድርገው የሚያምኑትን ህዝቦች በይሉኝታ መቅረቡ አሰልችቶኝ ነው፡፡

‹ብቸኝነትን የመረጥኩት ነፍሴ ከነዚያ ፀሐይ፣ ጨረቃ እንዲሁም ከዋክብት በገንዘብ ካዝናዎቻቸው ውስጥ ቢሆኑ ኖሮ እንደማይወጡና በእነሱ የአትክልት ስፍራዎች ውስጥ ካልሆነ በስተቀር እንደማይጠልቁ ፅኑ እምነት ካላቸው ጋር አብሮ መኖሩ ስላንገፈገፈኝ ነው...

‹‹እናም በዓይኖቻቸው ላይ ወርቃማ አቧራ እየጨመሩና ጆሮቻቸውን ትርጉም አልባ በሆኑ ወሬዎች እየሞሉ የህዝቦችንን ምድራዊ ዕጣ ፈንታ ከሚበጠብጡት የስልጣን ጥመኞች ሸሸሁ

‹‹እንደስብከታቸው የማይኖሩትን እና ህዝቦችን እነሱ የማይፈጽሙትን ነገር እንዲያደርጉ የሚመክሩትን (የሚያስገድዱትን) ቀሳውስት ለመሽሽ ስል ትቻቸው ሄድኩ...

‹‹ሰዎች ስልጣኔ ብለው የሚጠሩትን  ትቼ እዚህ የምኖረው ስሮቹ መሬት ስር ተሸሽገው የተቆላለፉ ቅርንጫፎቹ ከደመናው በላይ ከፍ ብለው ፈክተው፣ የበቀሉት አበቦቹ ግን ስስት፣ ክፋት እና ሰቃይ የሆኑ ብልሹ የሆነ ጠንካራ አስቀያሚ ዛፍ ሆኖ ስላገኘሁት ነው፡፡

‹‹ብቸኝነትን የፈለግሁት እዚህ በውስጡ ለመንፈስ፣ ለልብና ለአካል የሚሆን ሙሉ ህይወት ስላለ ነው:: እናም የፀሐይ ብርሃን የሚያርፍባቸውና መጨረሻ የሌላቸው አበቦች መዓዛቸውን ወደ ህዋ የሚተነፍሱበት እንዲሁም ጅረቶች እያዜሙ ወደ ባህር የሚያቀኑበትን የሳር መስክ አግኝቻለሁ፡፡ የፀደይ ወራትን ትኩስ ግንዛቤ፣ የክረምትን ቀለመደማቅ ናፍቆት፣ የመኸርን ጣፋጭ መዝሙሮች እና የበጋ ወራትን ውብ እንቆቅልሽ ያገኘሁባቸውን ተራሮች ደረስኩባቸው፡፡ ወደዚህ ርቆ ወደሚገኝ ግዛት የመጣሁት የዓለምን ሚስጥሮች ለማወቅ ስለተራብኩ ነው፡፡

Book: Between night and morn
Author :Khalil Jibran

@zephilosophy
ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
ብቸኝነትን የመረጥኩት.... ካህሊል ጂብራን "ከአለም ተነጥለህ ብቻህን ለመኖር እንዴት መረጥክ ?" ብዬ ጠየኩት በሀሳብ ተውጦ በዝምታ ከቆየ በኋላ እንዲህ አለ ‹‹በፍጥረቶቹ መካከል እየኖርኩ እግዚአብሔርን ማምለክ እችል ነበር፤ ማምለክ ለብቻ ተነጥሎ መኖርን አይጠይቅምና! ሰዎችን የተውኳቸው እግዚአብሔርን ለማግኘት ስል አልነበረም፡፡ በአባትና በእናቴ ቤት ሆኜም አገኘው ነበር፡፡ ከሰዎች የተገለልኩበት…
"በህይወት ውስጥ ካሉት ነገሮች መካከል እጅግ አስደናቂው ግንዛቤ"
ካህሊል ጂብራን

....የቀጠለ

‹‹ስልጣኔ ብላችሁ የምትጠሩት ያ አሰቃቂ ማጭበርበር ነው። ግብዝነት የጧቷ ጫፎች በቀለም ቢወለወሉም ሁልጊዜም ትኖራለች:: ማታለልም ምንም ስስ እና ለስላሳ ብትሆንም በጭራሽ አትለወጥም፡፡ ሀሰትም ብትሆን የሀር ልብስ አልብሰሀት በቤተ መንግስት ብታኖራትም እንኳ በፍፁም ወደ እውነትነት አትቀየርም፡፡ ስስትም እርካታ አይሆንም፡፡ወንጀልም እንደዚያው ደግነትን ሊሆን አይችልም፡፡እናም በትምህርት፣በልማድ እና በታሪክ ውስጥ ያለችው ዘላለማዊ ባርነትም ፊቷን ቀለም ብትቀባም ድምጽዋን ብትቀይርም ባርነት ሆና ትቀራለች፡፡

አዎን ስልጣኔው ከንቱ ነው፡፡ በውስጡ ያሉትም ነገሮች ከንቱ ናቸው፡፡ ፈጠራዎች እና ግኝቶችም ቢሆኑ አካል ሲደክም እና ሲዝል መደሰቻ እና ምቾት ማግኛዎች እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡ ርቀትን መማረክ እና በባህሮች ላይ ድል መቀዳጀት ነፍስን የማያረኩ፣ ልብን የማያጎለምሱ፣ መንፈስን ከፍ የማያደርጉና ከተፈጥሮ  የራቁ ሀሰተኛ ፍሬዎች እንጂ ሌላ አይደሉም።

‹‹በተጨማሪም ሰው እውቀትና ጥበብ እያለ የሚጠራቸው ቅርፆችና ንድፈ ሃሳቦችም ቢሆኑ የሰው ልጅ የሚጎትታቸው የእግር ብረቶችና ወርቃማ ሰንሰለቶች ከመሆናቸው ባለፈ በአብረቅራቂ ነፀብራቃቸውና በሚቅጨለጨል ድምፃቸው የሚፈነጥዙባቸው ከመሆናቸው ውጪ ባዶ ናቸው:: የሰው ልጅ ከረጅም ዘመናት በፊት ፍርግርግ የብረት ግድግዳዎቻቸውን ከውስጥ ሆኖ እየገነባቸው መሆኑን ልብ ሳይል ደክሞባቸው ለዘለአለሙ የራሱ እስረኛ እንደሆነ አልተገነዘበም፡፡ አዎን የሰዎች ተግባራት በሙሉ ዋጋ ቢስ ሆነዋል:: አላማዎቹም ዋጋ የላቸውም!!›

ንግግሩን ገታ አድርጎ ቆየና ከዚያ በቀስታ
‹‹እና በህይወት ውስጥ ካሉት ነገሮች መካከል መንፈስ የሚወደውና የሚጓጓለት አንድ ነገር አለ፡፡ አንድ አስደናቂና ብቸኛ ነገር አለ በማለት ጨምሮ ተናገረ፡፡

‹‹ምንድን ነው?›› ብዬ ጠየቅሁት በሚንቀጠቀጥ ድምጽ፡፡

ለረጅም ጊዜ ትክ ብሎ ተመልክቶኝ ሲያበቃ ዓይኖቹን ጨፈነ፡፡ ከዚያ ፊቱ ፈካ ብሎ እጆቹን ደረቱ ላይ እያሳረፈ ጥርት ባለና ከልቡ በሆነ ድምጽ መናገር ያዘ፡፡

‹‹በመንፈስ ውስጥ ያለ አንድ ግንዛቤ ነው፡፡ ይህ ድንገት በሰው ህሊና ላይ ወርዶ ህይወትን ራስን በሚያዞር ግሩም ሙዚቃ መካከል በታላቅ ብርሃን ዙሪያውን ተከባ ሰውም እንደ ውበት አምድ በመሬት እና በጠፈር መካከል እንደቆመ የሚታይበትን አይን የሚገልጥ እጅግ አስደናቂ የሆነ ኃይል ነው፡፡ ድንገት በመንፈስ ውስጥ ተንቀልቅሎ ልብን በመለብለብ የሚያነፃ፣ ከመሬት በላይ ከፍ ብሎ በመውጣት በሰፊው ሰማይ ላይ የሚነቅፍበትን የአንድን ግለሰብ ልብ የሚጠቀልል እና ታላቅ ፍቺውን ለመረዳት እምቢ ያሉት ላይ የሚያምፅ ርህራሄ  ነው:: በቤተሰቦቼ፣ በወዳጆቼ እና በሀገሬ ሰዎች መካከል ሆኜ የማህበረሰቡ አባል በነበርኩበት ጊዜ ከአይኖቼ ላይ አይነ ርግቡን ያስወግደልኝ ሚስጥራዊ እጅ ነው...

‹‹ብዙ ጊዜ ‹ይህ ዓለም ምንድን ነው? እኔስ ከሚመለከቱኝ ሰዎች ለምን ተለየሁ? እንዴትስ እነሱንስ አውቃቸዋለሁ? የትስ አገኘሁዋቸው? በእነሱ መካከል የምኖረውስ ለምንድን ነው? በዚህች ቁልፎችን በአመኔታና በአደራ ጭምር በሰጠችኝ ህይወት በተገነባችው ዓለም (ምድር) ውስጥ እኔ በእነሱ መካከል የተገኘሁ እንግዳ ፍጡር ነኝ? ወይስ እነሱ ናቸው እንግዳ ፍጡሮቹ?› እያልኩኝ ከራሴ ጋር በመነጋገር ለበርካታ ጊዜያት አሰላስያለሁ::››

ድንገት ከረጅም ጊዜ በፊት ያየውን አንድ ነገር እንዳስታውሰ እና ሊገልፀው እንዳልፈለገ ሁሉ ዝም አለ፡፡ ከዚያም ክንዶቹን ወደፊት ዘርግቶ ‹‹ከአራት አመታት በፊት በእኔ ላይ የደረሰው ይሄ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ነበር ዓለምን ትቼ በህይወት ግንዛቤ ውስጥ ለመኖር ወደዚህ ባዶ ስፍራ በቀና ሃሳቦች እና በማራኪ ፀጥታ ለመደሰት የመጣሁት፡››

ኃይለኛውን ነፋስ ለማነጋገር ተዘጋጅቶ እንደሚጠብቅ ሁሉ ወደ ድቅድቅ ጨለማው እየተመለከተ ወደ በሩ ተራመደ እና በሚስረቀረቅ ድምጽ

‹‹መንፈስ ውስጥ ያለ አንድ ግንዛቤ ነው፡፡ ይህንን ያወቀ በቃላት ሊገልፀው አይችልም:: የማያውቀው ደግሞ በጭራሽ ስለ አስገዳጁ እና ማራኪው የመኖር እንቆቅልሽ አስቦ ውጤት ያለው ነገር አያመጣም፡፡››
አለ

Book :Between night and morn
Author : Khalil Jibran

@Zephilosophy
አምላክ እና ልብ

"አምላክ በመለኮታዊው ሀይሉ ያነጠረውና ያረቀረቀው ነገር ቢኖር ልብ ነው፡፡ "
ሼህ ሙዛፊር

“ልቦናችን ላይ ያለውን ህግ የሚቃረን ሀይማኖታዊ ትምህርትና ህግ ሁሉ ከአምላክ ሊሆን አይችልም፡፡”
ዘርዓያእቆብ

@zephilosophy
ሐተታ ዘርዓ ያዕቆብ.pdf
171.1 KB
#ሐተታ_ዘርዓያዕቆብ
ደራሲ፦ ዘርዓ ያዕቆብ
ስለ መፅሃፉ
(ፍቃዱ ቀነኒሳ ፅፎት አዲስ አድማስ ላይ የወጣ)

[...ዘርዓያዕቆብ በጥንታዊት ኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት፤ በንባብ ቤት፣ በዜማ ቤትና በቅኔ/ሰዋስው ቤት ያለፈ ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ፈላስፋ ሲሆን እርሱ በነበረበት ዘመን የነበሩ ሃይማኖታዊ፣ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ሥነምግባራዊ አስተሳሰቦችን በአመክኗዊ ሐተታ (rational inquiry) በመታገዝ ይመረምርና ይተች ነበር፡፡ የዘርዓያዕቆብ ፍልስፍና የፈጣሪ ህግን ከሰው ህግ፣ የተፈጥሮ ሥርዓትን ከሰብዓዊ ሥርዓት፤መለየትንና በአንድ አምላክ አማኞች ሃይማኖት ውስጥ የሚገኙ ተገቢ ያልሆኑ የሰው ሥርዓቶችን አስወግዶ በእውነተኛው የተፈጥሮ/የፈጣሪ ህግ ብቻ መመራት ላይ ያተኩራል። በተፈጥሮ ህግና በምክንያታዊነት መነጽር በመታገዝ ስለሃይማኖት መከፋፈል፣ስለሙሴና ነቢዩ መሀመድ ህጎች፣ ሐሰተኛ እምነትን ስለመለየት፣ ስለአምላክና ስለሰው ህግ፣ስለ እውነተኛ እውቀት ምንጭ እንዲሁም ስለጋብቻና ምንኩስና ተፈላስፏል፡፡ በአፍሪካ የጽሁፍ ፍልስፍና መገኘት የውስጥ እግር እሳት የሆነባቸው ምዕራባውያን፤ የዘርዓያዕቆብ ፍልስፍና የኢትዮጵያውን ስራ አይደለም ሲሉ ሞግተዋል፡፡...]

@zephilosophy
ግሩም_ትረካ_-_ጥፊህ_ተመልሶ_ይመጣል፣_የካርማ_ሕግ፣_ነፃነት_እና_ሀላፊነት_Girum_Te (3)
<unknown>
"ጥፊያችሁ ተመልሶ ይመጣል!!"
ኦሾ
አዘጋጅና አቅራቢ- ግሩም ተበጀ

"የኦሾ ድንቅ አስተምህሮ በግሩም ውብ የአተራረክ ጥበብ ቀርቧል።"
@zephilosophy
ዘመነ አብርሆት፣ ዘመናዊነት እና ድህረ- ዘመናዊነት
(Enlightenment,Modernity and Postmodernity)

ምንጭ ፦ የፍልስፍና ትምህርት ቅፅ ፩
አርታኢና አዘጋጅ ፦ ብሩህ አለምነህ

የሰው ልጅ ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እርስ በእርሳቸው በሚቃረኑ የሐሳብ ታሪኮች ውስጥ አልፏል። እነዚህም የመካከለኛው ወይም የጨለማው ዘመን (Dark age)፣ ዘመነ ትንሳኤ (Renaissance)፣ ዘመነ አብርሆት (Enlightenment)፣ ዘመናዊነት (Modernity) እና ድህረ ዘመናዊነት (Post modernity) ናቸው።

እነዚህ የሐሳብ ታሪኮች እርስ በእርሳቸው የተያያዙ እና ለአንዱ የሀሳብ ታሪክ መፈጠር ሌላው አስፈላጊ ነበር። ለምሳሌ፦ ዘመነ አብርሆት እንዲፈጠር ዘመነ ትንሳኤ መነሻ ሲሆን ዘመናዊነት እንዲፈጠር ደግሞ ዘመነ አብርሆት አስተዋፅኦ አድርጓል።

የጨለማው ዘመን ወይም የመካከለኛው ዘመን (Dark Age) የምንለው ከ5ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ቶማስ አኳይነስ በ13ኛው ክፍለ ዘመን እስኪነሳ ድረስ ያለው ነው። በዚህ ዘመን ገዥ የነበረው አስተሳሰብ ‹‹ይሄ ዓለም ‹‹ጥላ፣ ጊዜያዊና ፈራሽ›› ስለሆነ ከእሱ ጋር መወዳጀት አያስፈልግም›› የሚል ነበር፡፡ ሰውም አስተምህሮቱን በመከተል ይህ ዓለም ጥላ መሆኑን አምኖ ‹‹ከዚህ ዓለም ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለኝም›› ብሎ የደመደመበት ዘመን ነው፡፡ እናም አውሮፓውያን በዚህ መልክ አስር ክፍለ ዘመናትን (ከ5ኛው 15ኛው ክ/ዘ ድረስ ያሉትን 1000 ዓመታት) አመክዮን እያሳደዱ ነው የኖሩት፡፡ በመሆኑም፣ በዚህ የጨለማው ዘመን ላይ የፕሌቶናውያን ሐሳብ የበላይነት ነበረው፡፡

ቶማስ አኳይነስ የተባለው ካቶሊካዊ መነኩሴ በ13ኛው ክ/ዘ ‹‹ምክንያትና እምነት (faith and reason) አይጋጩም፤ ራሱ ህሊና/አመክንዮ የእግዚአብሔር ፍጥረት ስለሆነ በምክንያት እውነት የሆነ ነገር እምነት ላይ ውሸት ሊሆን አይችልም›› በማለት አሪስቶትልን ከተጣለበት ይዞት ተነሳ፡፡ የፕሌቶ ሐሳብ ገዥ በነበረበት ዘመን ላይ እምነትና አመክንዮ ‹‹ተፃራሪ›› ተደርገው ሲወሰድ የነበረውን አስተሳሰብ በመናድ አኳይነስ አዲስ የእርቅ ሐሳብ ይዞ ተነሳ፡፡

እንደ አኳይነስ አስተሳሰብ

አመክንዮ ዓለምን እንዲያይ፣ እንዲበረብርና እንዲረዳ ነውና በእግዚአብሔር የተፈጠረው፣ በዚህም ምክንያት አመክንዮ አሰላስሎ የሚደርስበት መደምደሚያ ‹‹እውነት›› ከሆነ፣ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ሄዶ ውሸት ሊሆን አይችልም፡፡

ይቺ ሐሳብ ቀላል ትመስላለች፤ ሆኖም ግን በጣም አደገኛ ነች!! ይቺ የአኳይነስ ሐሳብ ‹‹ፕሌቶናውያን አናንቀው ‹‹ጥላ›› ላሉት ዓለም ትኩረት እንድንሰጥ ከማድረጉም ባሻገር ህሊናችንን/አመክንዮአችንን በመጠቀም በዙሪያችን ያሉትን ነገሮች መርምረን እውነት ላይ መድረስ እንችላለን›› የሚል አዲስ በር ከፈተ፡፡ በዚህም ቶማስ አኳይነስ ሃይማኖቱንም አልጣለም፣ አመክንዮንም አልጣለም፡፡

በዚህ መንገድ፣ በጨለማው ዘመን ውስጥ አመክንዮ ለ800 ዓመታት አጥቶት የነበረውን ቦታ አኳይነስ በዚህ መልክ መልሶታል፡፡ አኳይነስ በዚህ መልኩ አመክንዮን ከወደቀበት ሲያነሳው ‹‹ትንሳኤ (Renaissance)›› የሚል ዘመን ተጀመረ፡፡ በዚህም ሰዎች አካባቢያቸውን ማጥናትና መመርመር ጀመሩ፡፡ በዚህ የሬኔሰንስ መንፈስ ከተነሱ ግለሰቦች መካከል ሊኦናርዶ ዳቬንቺ፣ ኒኮላስ ኮፐርኒከስና ሼክስፒር ዋናዎቹ ሲሆኑ፤ በተለይ የኮፐርኒከስ መነሳትና ‹‹መሬት በፀሐይ ዛቢያ ተሽከርካሪ መሆኑዋን ማብሰሩ›› ትልቁ የተሐድሶ ዘመን ክስተት ሆነ፡፡

ነገር ግን እዚጋር መታወቅ ያለበት የአርስቶትል ሐሳብ ገዢ ሆኖ የወጣው ከ12ኛው እስከ 14ኛው ክፍለ ዘመን ወይም የመካከለኛው ዘመን ማብቂያ አካባቢ (late medival period) ዘመነ ትንሳኤ እስኪነሳ ድረስ ሲሆን በዘመነ ትንሳኤ የኘሌቶ ሀሳብ ተመልሶ ገዢ ሀሳብ ነበር። ዘመነ ትንሳኤ አልፎ ዘመነ አብርሆት ሲተካ ደግሞ ተመልሶ የአርስቶትል ሀሳብ ገዢ ሀሳብ ሆኖ ይወጣል። ይህም ክስተት ታላቁ ሀተታ (the grand narrative) ይባላል።

ይህ ታላቁ ሀተታ በፕሌቶ ሲነገር

‹‹ትክክለኛው ዓለም እዚህ ምድር ላይ እንዳልሆነና አሁን የምንኖርበት ይህ ዓለም የእውነተኛው ዓለም ጥላ እንደሆነ፤ እንዲሁም፣ ወደ እውነተኛው ዓለም ለመሸጋገር የህይወት ጉዞ እንደሚያስፈልገንና ይሄም ጉዞ ነፍሳችንን ከስጋ ማላቀቅ እንደሚገባን፤ ይሄንን ለማድረግ ደግሞ መንገዱ እራሳችንን ከስጋዊ ፍላጎቶች (ከምድራዊ ፈንጠዝያ፣ ከምግብ፡ ከመጠጥና ከፍትወት) መቆጠብ እንደሆነ›› ይሰበካል፡፡

ይቺ ‹‹የምንደርስበት ሌላ ዓለም አለ›› የምትለዋን ፕሌቶናዊ ተምኔት (Utopia) በተለያየ ቅርፅ ሁሉም ሃይማኖቶች ውስጥ እናገኛታለን፤ ፖለቲካ ውስጥም (ለምሳሌ · ሶሻሊዝም ውስጥ) እናገኛታለን፡፡ የአንዱ ከሌላው የሚለያየው ‹‹ምን ዓይነት ዓለም?›› በሚለው ሐሳብ ላይ ብቻ ነው፡፡

አሪስቶትል የታላቁ ሐተታ አካል የሆነው ደግሞ በሌላ መንገድ ነው፡፡ ምንም እንኳ አሪስቶትል ትክክለኛው ዓለም ይሄኛው አይደለም ባይለንም ‹‹የነገሮችን ትክክለኛ ተፈጥሮ (The Essence of Things) የምናገኘው ከፍተኛ የሆነ የአሰላስሎት (Contemplation) ‹‹ደረጃ›› ላይ ስንደርስ ነው›› የሚለው ንግግሩ ግን የታላቁ ሐተታ አካል ሆኗል፡፡ በሌላ አነጋገር፣ አሪስቶትል ‹‹እውነተኛው ዓለም ይሄ አሁን የምንኖርበት ዓለም ነው›› ቢልም፤ ሆኖም ግን ‹‹ይሄንን ዓለም ለማንኛውም ሰው ታዋቂ አለማድረጉና ዓለሙን ለማወቅ ውስብስብ ሂደት (process) ማስቀመጡ›› ፍልስፍናውን የታላቁ ሐተታ አካል አድርጎበታል፡፡

‹‹የምንደርስበት ሌላ ዓለም አለ›› የሚለውን የፕሌቶን ሐሳብ በሃይማኖትና በፖለቲካ ውስጥ እንደምናገኘው ሁሉ፣ ‹‹እውነተኛው ዓለም ይሄ አሁን የምንኖርበት ዓለም ነው›› የሚለውን የአሪስቶትልን የሐሳብ ቅርፅ ደግሞ በሳይንስ ውስጥ እናገኘዋለን፡፡

በአጭሩ፣ እነዚህ ሁለት ታላላቅ ፈላስፎች (ፕሌቶና አሪስቶትል) በተጋጩበት ነገር አንድ አስታራቂ ሐሳብ ላይ ሳንደርስ ፕሌቶ ሲያሸንፍ ፊታችንን ከዚህ ዓለም ወደ ሌላ ዓለም እያዞርን፤ አሪስቶትል ሲያሸንፍ ደግሞ ፊታችንን ከዚያኛው ዓለም ወደዚህኛው ዓለም እየመለስን ነው የኖርነው።

ይቀጥላል

@zephilosophy
@zephilosophy
ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
ዘመነ አብርሆት፣ ዘመናዊነት እና ድህረ- ዘመናዊነት (Enlightenment,Modernity and Postmodernity) ምንጭ ፦ የፍልስፍና ትምህርት ቅፅ ፩ አርታኢና አዘጋጅ ፦ ብሩህ አለምነህ የሰው ልጅ ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እርስ በእርሳቸው በሚቃረኑ የሐሳብ ታሪኮች ውስጥ አልፏል። እነዚህም የመካከለኛው ወይም የጨለማው ዘመን (Dark age)፣ ዘመነ ትንሳኤ (Renaissance)፣…
...ካለፈው የቀጠለ

የዘመነ ትንሳኤ አነሳስና ምንነት

‹‹ዘመነ ትንሳኤ›› በ1350 አካባቢ በፍሎረንስ (ሰሜን ጣሊያን) በሚኖሩ ጥቂት ሥነ ሰብዓውያን (Humanists) የተጀመረ ‹‹የጥንት ትምህርቶችና የሥነ ፅሁፍ ዳግም ልደት ነው (Renaissance means a rebirth of literature and a devotion to classical learning)፡፡›› የዘመን ርዝማኔውም እስከ 16ኛው ክ/ዘ ድረስ ያሉትን የፕሮቴስታንትና የካቶሊክ ተሐድሶዎችን (Protestant Reformation and Catholic Counter Reformation) እንዲሁም የሳይንስ አብዮትን ያጠቃልላል፡፡ አንዳንድ ፀሐፍት ደግሞ ዘመኑን እስከ 17ኛው ክ/ዘ ድረስ ያደርሱታል፡፡

‹‹Renaissance›› የሚለው ፅንሰ ሐሳብ የኢኮኖሚ አሊያም የፖለቲካ ፅንሰ ሐሳብ ሳይሆን የባህል ፅንሰ ሐሳብ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ‹‹Renaissance›› በ14ኛው ክ/ዘ የነበሩ ምሁራን (ሥነ ሰብዓውያን) የጀመሩት የሥነ ፅሁፍ ንቅናቄ (Literary Movement) ነው፡፡ በመሆኑም፣ ‹‹ዘመነ ትንሳኤ›› በሁሉም መስክ ያሉ የአውሮፓ ምሁራን ህይወት ላይ ተፅዕኖ የሳረፈ የባህል ንቅናቄ (Cultural Movement) ነው የጥንት ግሪካውያንንና ሮማውያንን የሥነ ሰብዕ ሥራዎችን (Humanities) በድጋሜ የማንሳት ሥነ ፅሁፋዊ ንቅናቄ ነው፡፡ በዚህ ንቅናቄ ያልተነካ የሙያ መስክ የለም ኪነ ጥበቡ፣ ሥነ ፅሁፉ፣ ፖለቲካው፣ ፍልስፍናው፣ ሳይንሱ... ሁሉ ተፅዕኖ አርፎበታል፡፡

ዘመነ ትንሳኤ በባህሪው ፀረ ሃይማኖት ንቅናቄ አልነበረም፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛዎቹ ሥነ ሰብዓውያን የቤ/ክ ሰዎች ስላልነበሩ ለሥነ መለኮት (Theology) አነስተኛ ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም፣ በአቋማቸው ግን ፀረ—ሃይማኖት አልነበሩም፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን፣ ለመካከለኛው ዘመን ‹‹የጨለማው ዘመን (Dark Age)›› የሚለውን መጠሪያ የሰጡትም በዚያው ዘመን የነበሩ እነዚህ ሥነ ሰብዓውያን ናቸው፡፡ ይሄንንም ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመው Petrarch ነው፡፡

የካቶሊክ ቤተ ክርስትያንም የሥነ ሰብዕ ንቅናቄው ተቃዋሚ አልነበረችም፡፡ እንዲያውም በተቃራኒው ቤተ ክርስትያኗ በርካታ የሥነ ሰብዕና አርት ሥራዎችን ስፖንሰር ስታደርግ ነበር፡፡ ለዚህም ጥሩ ተጠቃሽ የሚሆነው ቤ/ክኗ በወቅቱ ታዋቂ ሰዓሊ የነበረውን ራፋኤልን (Rapahael) በ1509 ኮሚሽን በማድረግ በቫቲካን ለጳጳሳት መኖሪያ የተሰራው ቪላ ቤት ግድግዳ ላይ የጥንት ግሪክ ፈላስፎችንበአንድነት እንዲሳል ማድረጓ ነው። ይሔም ስእል "school of Athens" ይባላል።

በመሆኑም፣ በወቅቱ የሥነ ሰብዓውያን ዋነኛ ፍላጎት የነበረው በክርስትና አውድ ውስጥ የጥንት ግሪካውያንና ሮማውያን የሥነ ሰብዕ ትምህርቶች በድጋሜ እንዲያቆጠቁጡና ከመንፈሳዊው ህይወት ጎን ለጎን ለዓለማዊው ጥበብም ትኩረት እንዲሰጠው የማድረግ ጥረት ነው፡፡

በርግጥ፣ የጥንት የሥነ ሰብዕ ትምህርቶች ከመንፈሳዊነት ይልቅ ዓለማዊ ይዘት ያላቸው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከ1000 ዓመታት በፊትም ክርስትና ‹‹አያስፈልጉኝም፤ የአህዛብ ሥራዎች ናቸው›› በማለት የቀበራቸው ናቸው፡፡ በ14ኛው ክ/ዘ የተነሱት ሥነ ሰብዓውያን ግን ‹‹ያስፈልጉናል›› በማለት ከተቀበሩበት እንዲወጡ ማድረግ ጀመሩ፡፡ ይሄ እንግዲህ ፊት ለፊት የማይታይ በክርስትናና በሥነ ሰብዓውያን መካከል ያለ ውስጣዊ ተቃርኖ ነው፡፡

ይሄ ውስጣዊ ተቃርኖ በጊዜ ሂደት ምን ይፈጥር ይሆን? ወይም ደግሞ በሌላ አነጋገር፣ ዓለማዊ የሆኑት የጥንት የሥነ ሰብዕ ትምህርቶች መንፈሳዊ ከሆነው ክርስትና ጋር መሳ ለመሳ ሲቀመጡ፣ ይሄ መስተጋብር (dynamism) ክርስትናን ቀስበቀስ ወዴት ይወስደው ይሆን? ይሄ ጥያቄ ወደፊት ከ100 ዓመታት በኋላ በProtestant Reformation እና በካቶሊክ ‹‹Counter Reformation›› የሚመለስ ይሆናል፡፡ እስከዚያው ድረስ ግን፣ የዘመነ ትንሳኤ ምሁራን የጥንት የሥነ ሰብዕ ትምህርቶች እንዲያብቡ ከመፈለግ ውጭ ክርስትናን የመቃወምም ሆነ የማደስ (Reform የማድረግ) ሐሳብ እንዳልነበራቸው መታወቅ አለበት፡፡

በአጠቃላይ ዘመነ ትንሳኤ

👉ከመንፈሳዊው ህይወት "ብህትውና" ጎን ለጎን ሀይማኖቱን ሳያጠፋ ለአለማዊው ህይወት (ለጥንት ግሪካውያንና ሮማውያን እውቀት) ትኩረት መሰጠት የጀመረበት

👉የፕሌቶ ፍልስፍናዊ ሀሳቦች ገዢ ሆነው ዳግም የተነሱበት

👉የካፒታሊዝም ስርአት መፈጠር ጋር ተያይዞ በመካከለኛው ዘመን (በፊውዳል) ከነበረው የሕዝባዊ ህይወት ይልቅ ግላዊ ህይወት እያየለ መምጣት የዚ ዘመን መገለጫዎች ናቸው።

የዘመነ አብርሆት አነሳስና ምንነት

ዘመነ አብርሆት የሳይንስ አብዮትን (Scientific Revolution) ተከትሎ በአውሮፓ ከ17ኛው ክ/ዘ መጨረሻ እስከ በ18ኛው ክ/ዘ መጨረሻ ድረስ የተከሰተ ምሁራዊና ፍልስፍናዊ ንቅናቄ ነው፡፡ ንቅናቄው ከፈረንሳይ ጀምሮ ወደ ጀርመን፣ ስኮትላንድና ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች የተስፋፋ ነው፡፡ ልክ በዘመነ ትንሳኤ ጊዜ በፍሎረንስ (ጣሊያን) እንደሆነው ሁሉ፣ ዘመነ አብርሆትም በፈረንሳይ ከዩኒቨርሲቲ ውጭ ያሉና ራሳቸውን በንባብ ያበለፀጉ ምሁራን የጀመሩት ፍልስፍናዊ ንቅናቄ ነው፡፡

ዘመነ አብርሆት በአብዛኛው ከፍልስፍና አንፃር የሚተረጎመው ‹‹አመክንዮ ወይም ምክንያታዊነት በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ›› አንፃር ነው፡፡ በሌላ አነጋገር፣ ፍልስፍና ዘመነ አብርሆትን የሚተነትነው ከአመክንዮ የዕድገት ሂደት አንፃር ነው፡፡ ለዚህም ነው ዘመነ አብርሆት ‹‹The Age of Reason›› ተብሎም የሚጠራው፡፡

ምንም እንኳ ‹‹ዘመነ ትንሳኤ›› ለፍልስፍና ያበረከተው አስተዋፅዖ አነስተኛ ቢሆንም፣ በአብርሆት ዘመን ግን በርካታ ፈላስፎችና የፍልስፍና ሥራዎች የተገኙበት ወቅት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ 18ኛው ክ/ዘ ‹‹የፍልስፍና ምዕተ ዓመት (The Century of Philosophy)›› እስከመባል ደርሷል፡፡

‹‹ሆኖም ግን፣ በፈረንሳይ የዘመነ አብርሆት ምሁራንና ፈላስፎች በዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህራን አልነበሩም፡፡ ይሄም የሚያመላክተን በዘመነ አብርሆት መሰረታዊ የፍልስፍና ዕውቀት ለሁሉም ሰው ያስፈልገዋል የሚል አመለካከት በዘመኑ የነበረ መሆኑንና የፍልስፍና ዕውቀት በዩኒቨርሲቲ ላሉ መምህራን ብቻ የተተወ ሙያ ገና መሆን እንዳልጀመረ ነው፡፡››

በአጠቃላይ ዘመነ አብርሆት

👉 የአመክንዮ በብቸኝነት የበላይ ሆኖ የታየበት ይህም በፊት የእውነት ፣ የስነምግባርና የስልጣን ምንጭ ተደርገው ሲታዩ የነበሩትን ሃይማኖትንና ባህልን የሚገዳደር ነው።

👉የአርስቶትል ፍልስፍናዊ ሀሳቦች እና ሳይንስ የገነነበት

👉ተጠራጣሪነት(skepticism to tradition) አመክንዮ የበላይ መሆኑን ተከትሎ በተለያዩ ባህላዊ አስተሳሰቦች እና ልማዶች ላይ የሰፈነበት

👉ግለሰባዊነት (Indivisualism)፦ ግለሰብ የማንንም ሞግዚት ሳይፈልግ በራሱ ውሳኔ ሰጪ የሆነበት

👉ዴይዝም (deism) የአርስቶትል ሜታፊዚካል ፍልስፍና የታየበት ነው። በዚህ ፍልስፍና መሰረት ፈጣሪ አለ ግን ፈጣሪ ይችን ምድር ፈጥሮ ከጨረሰ በኋላ በራሷ ሜካኒካዊ ህግጋት እንድትመራ ትቷታል ወይም ፈጣሪ እዚህ ምድር ላይ ምንም አይነት መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት የለውም የሚል ፍልስፍና ነው። በዘመነ አብርሆት የነበሩ አብዛኞቹ ፈላስፍች ዴይስት ነበሩ።

በቀጠይ ስለ ዘመናዊነት እና ድህረዘመናዊነት እናያለን
ይቀጥላል
@zephilosophy
ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
...ካለፈው የቀጠለ የዘመነ ትንሳኤ አነሳስና ምንነት ‹‹ዘመነ ትንሳኤ›› በ1350 አካባቢ በፍሎረንስ (ሰሜን ጣሊያን) በሚኖሩ ጥቂት ሥነ ሰብዓውያን (Humanists) የተጀመረ ‹‹የጥንት ትምህርቶችና የሥነ ፅሁፍ ዳግም ልደት ነው (Renaissance means a rebirth of literature and a devotion to classical learning)፡፡›› የዘመን ርዝማኔውም እስከ 16ኛው…
.....ካለፈው የቀጠለ

ዘመናዊነት እና ድህረ ዘመናዊነት (modernity and postmodernity)

የዘመናዊነት እሳቤዎች

ከመካከለኛው ዘመን ተነስተን፣ በዘመነ ትንሳኤና በአብርሆት በኩል አልፈን ዘመናዊነት ላይ ደርሰናል፡፡ ይሄም ባጠቃላይ የአውሮፓ የ1500 ዓመታት የሐሳብ ታሪክ (History of Ideas) ነው፡፡ እነዚህ ዘመናት ሲመሩበት የነበረውን ዋነኛ ጭብጥ መግለፅ ካስፈለገ፣ እንዲህ በማለት ማስቀመጥ ይቻላል፤

👉መካከለኛው ዘመን - የክርስትና አስተምህሮ የበላይነት የነበረበት፣

👉ዘመነ ትንሳኤ – የጥንት ግሪክና ሮማውያን ሥነ ፅሁፍ ንቅናቄ፣
👉ዘመነ አብርሆት - ነፃነት (ከውጫዊ ስልጣኖች - ባህል፣ አጉል እምነትና ዘውድ ነፃ መሆን)፣

👉ዘመናዊነት - ምክንያታዊ ማህበረሰብ ግንባታ፣ ምክንያታዊነት እያደገ ሲሄድ ደግሞ የህዝቡ የኑሮ ሁኔታ እየተሻሻለ ይሄዳል የሚል ተስፋ፤

‹‹ዘመናዊነት›› ምክንያታዊ የሆነ የማህበረሰብ ግንባታ ከሆነ ሂደቱ የጀመረው ቀደም ብሎ ነው ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ምሁራን ይሄንን ሂደት ‹‹ከዘመነ ትንሳኤ ጀምሮ የመጣ ነው›› ይሉታል፡፡ ሌሎች ምሁራን ደግሞ ‹‹ዘመናዊነት ‹‹የጥንቱን ባህል ማንሰራራት›› የሚለው የዘመነ ትንሳኤ ርዕይ ከተሳካ በኋላ የመጣ ቀጣዩ ፕሮጅክት ነው›› በማለት ይገልፁታል፡፡ በዚህ ትርጉም ከሄድን ‹‹ዘመነ አብርሆት›› የዘመናዊነት አካል ይሆናል ማለት ነው፤ ምክንያቱም ‹‹የአብርሆት እሴቶች ግልፅና ጉልህ ሆነው የወጡት በዘመናዊነት ነው፡፡

ዘመናዊነትን በአውሮፓ ለተከሰተው አዲስ ነባራዊ ሁኔታ የተሰጠ የአመለካከት ግብረ መልስ አድርገው የሚመለከቱትም አሉ፡፡ ይሄም አዲስ ነባራዊ ሁኔታ የሚገለፀው በዘመናዊ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ የብሔር መንግስታት መመስረት፣ በገንዘብ ኢኮኖሚ፣ በካፒታሊዝም እና በኢንዱስትሪ መስፋፋት ነው፡፡ ይሄም አዲስ ነባራዊ ሁኔታ በህጎች፣ በመመሪያዎች፣ በመለኪያዎችና በቁጥሮች የሚመራ ቢሮክራሲና የህይወት ዘይቤ እንዲኖር አድርጓል፡፡ ከዚህም በመነሳት ነው ጀርመናዊው ሶሲዮሎጂስት ማክስ ቬበር (Max Weber) ‹‹ዘመናዊነት ማለት በህጎች፣ በመመሪያዎች፣ በመለኪያዎች፣ በቁጥሮችና በቢሮክራሲ የሚመራ የህይወት ዘይቤ ነው›› በማለት ትርጉም የሰጠው፡፡

በአጠቃላይ ዘመናዊነት

💡በድሮው ላይ ማመፅ ነው፤ ይሄም አመፅ ጎጂና ኋላ ቀር ከሆኑ የድሮው (የመካከለኛው ዘመን) ልማድ፣ አሰራርና አስተሳሰብ መነጠልን የሚያመላክት ነው፤ ከእነሱም ተነጥሎም ህይወትን በዕውቀትና በአመክንዮ መዘወር ነው፡፡ ለምሳሌ፣ በዘመናዊነት ውስጥ ‹‹ድርቅ የተከሰተው የሰው ኃጢያት ስለበዛና እግዚአብሔር ስለተቆጣ ነው›› አይባልም፤ በዘመናዊነት ውስጥ ‹‹በሽታ የሰይጣን ሥራ ነው›› አይባልም፤ ‹‹እንደዚህ የሆንኩት የ40 ቀን ዕድሌ ስለሆነ ነው›› አይባልም፡፡ በዘመናዊነት ውስጥ ከእንደነዚህ ዓይነት አስተሳሰቦች እንነጠልና፣ የምናምነው ሳይንስ የሚነግረንን የመንስኤ ውጤት ህግጋትን ነው፡፡

💡የፕ/ር መሳይ ከበደን ‹‹ዘመናዊነት ማለት ከድሮው ባህልና አስተሳሰብ መነጠል ሳይሆን፣ እንዲያውም የድሮው ባህሎችና እሴቶች እንደገና እንዲያብቡ ማድረግ ነው››የሚለውን ሐሳብ ከወሰድን ደግሞ ‹‹ዘመናዊነት ማለት ለጥንት ባህላችንና እሴቶቻችን አዲስ አመክኖያዊ መሰረት መስጠትና ዘመናዊ አሰራርን ማላበስ ነው›› በማለት መተርጎም እንችላለን፡፡ ለምሳሌ፣ የዘመን መለወጫ በዓል በጣም የቆየ ባህል ነው፡፡ በበዓሉ ውስጥ እርድ፣ ጠላ መጥመቅ፣ ዳቦ መድፋት፣ ባህላዊ ልብሶች መልበስ፣ ቤተ ዘመድ መሰባሰብ፣ አንድላይ መመገብ...ይከናወናል፡፡ በዘመናዊነት ውስጥ ይሄንን ባህል አልተውነውም፤ እንዲያውም የበዓሉን አከባበር በዘመን አመጣሽ አልባሳት፣ ምርቶችና የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች በመጠቀም በዓሉን ይበልጥ ደማቅ እየሆነ ነው፡፡

የድህረ ዘመናዊነት እሳቤዎች

ከ1970ዎቹ ጀምሮ የተነሳው ድህረ ዘመናዊነት ሁለት መገለጫዎች አሉት፡፡

በአንድ በኩል፣ አሁን በተጫባጩ ዓለም ላይ ያለውን እውነታ የምናሳይበት መንገድ አድርገን ልንመለከተው እንችላለን፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ፣ ድህረ-ዘመናዊነት ‹‹ሞደርኒቲ ከሽፏል፤ አልፎበታል›› የሚል አስተሳሰብ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

ሊዮታርድ ‹‹The Postmodern Condition: A Report on Knowledge›› በተሰኘ መጽሐፉ ውስጥ ድህረ-ዘመናዊነትን ሲተረጉመው እንዲህ ይላል፣

‹‹ድህረ-ዘመናዊነት በታላላቅ ትረካዎች አለማመን ነው

በዘመናዊነት ውስጥ የነገሮችን ተፈጥሮ እና ምንነት የምንረዳባቸው እንዲሁም እውነትን፣ ዕውቀትንና ግብረገብነትን የተመለከቱ ህይወታችንን የምንመራባቸው ቅቡል የሆኑ ታላላቅ ትረካዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ የዘመናዊነት ትረካዎች ውስጥ የተወሰኑት እንዲህ የሚሉ ናቸው፣

👉ሁሉንም ሰው የሚያስማማ እውነት አለ (There is Universal Truth)፤

👉ሁሉንም ሰው የሚያስማማ ሥነ ምግባር አለ (There is Universal Morality)፤

👉ዕውቀት ማግኘት ደስተኛ ያደርጋል፤

👉ዕውቀት ማግኘት ነጻነት ያለው ህይወት እንድንኖር ያደርገናል፤

ድህረ-ዘመናዊነት እንደነዚህ ዓይነቶችን ትረካ አይቀበልም፡፡ በመሆኑም፣ ድህረ- ዘመናዊነት ማለት፣

በእነዚህ የዘመናዊነት ትረካዎች የማናምንበትና የማንስማማበት፣

ሰዎችን ሁሉ እኩል በሆነ መንገድ የሚያስማማ የጋራ እውነት የሌለበት፣

እውነትና ሥነ ምግባር አንፃራዊ የሆኑበት፣

ሰዎች ሁሉ ትክክል የሆኑበት፣

ሁሉም ባህሎችና ሃይማኖቶች ትክክል የሆኑበት፤

ሰዎች እውነትን ገሃዱ ዓለምውስጥ ወጥተው የሚፈልጉበት ሳይሆን በዲስኩር፣ በቋንቋና በፖለቲካ ላይ ተሞርኩዘው የእውነትን ተፈጥሮ የሚረዱበት አዲስ ዓለምነው፡፡

በዘመናዊነት እና በድህረ-ዘመናዊነት አስተሳሰብ መካከል ያለውን ልዩነት የሚከተለውን ጥያቄ በማንሳት ማየት እንችላለን፡፡

💡አንድ ማህበረሰብውስጥ አላዋቂነት መኖሩ ነው ማህበረሰቡ እንዳይዘምን የሚያደርገው (The sleep of reason produces monsters)? ወይስ

💡የአዋቂዎች መብዛት ነው ማህበረሰቡ ውስጥ ችግር የሚፈጥረው (The dream of reason produces monsters)?

የመጀመሪያው፣ ‹‹አንድ ማህበረሰብ ውስጥ አላዋቂነት መኖሩ ነው ችግር የሚያመጣው የሚለው አስተሳሰብ ‹‹የሰው ልጅ የበለጠ ለባህልና ለሃይማኖት ራሱን በሰጠ ቁጥር፣የሰው ልጅ በዘፈቀደ ህይወቱን በመራ ቁጥር ነጻነትን ማግኘት አይችልም፣ ደስተኛ ህይወትን መምራት አይችልም››ወደሚል ድምዳሜ ይወስደናል፡፡ እንደ ካንትና ሄግል ያሉ ፈላስፎች ይሄንን አስተሳሰብ ተከትለው ነው ዘመናዊነት ምን እንደሆነ የሚነግሩን፡፡

ሁለተኛው፣ የድህረ-ዘመናዊነት ፍልስፍናን የሚያቀነቅኑ ፈላስፎች ደግሞ በተቃራኒው የሚሉን ‹‹የአዋቂዎች መብዛት ነው ማህበረሰቡ ውስጥ ችግር የሚፈጥረው፡፡ ይሄም ማለት በጣም ማለምም፣ በጣም መጠየቅም፣ በጣም ዘመናዊ መሆንና ምክኒያታዊነትን ማዳበርም አንድ ማህበረሰብ ውስጥ ተቃርኖን ይፈለፍላል፡፡ ለዚህ መደምደሚያ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ ሉላዊ በሆነው ዓለም ውስጥ፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተመንድጓል በምንልበት፣ የግለሰብ ነፃነት እስከ ጥግ በደረሰበትና ቁሳዊ ዕድገት ባለበት ዓለም ውስጥ እንደ ጀኖሳይድ እና ሆሎኮስት ያሉ እልቂቶች፣ የእርስበርስና የዓለም ጦርነቶች እንዲሁም የህይወት ትርጉም አልባ ስሜቶች ውስጥ መዘፈቃችን ነው፡፡

@zephilosophy

እስኪ እናንተ ጋርስ ያለው ሀሳብ ምንድነው ተወያዩበት
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"የላባቸው ዋጋ ይከፈላቸው!!"

የፍልስፍና ቻናላችን የጤና ባለሙያዎች ብሔርና ሀይማኖት ሳይለያያቸው ለመብታቸው መከበር በአንድነት ሆነው ያነሱትን የመብት ጥያቄ እና ትግል ይደግፋል።

የጤና ባለሙያዎች የመንግስት ውክቢያ እና እስር ሳይስፈራቸው ለመብታቸው በድፍረት ና በፅናት መቆማቸው መብቱ ቢጣስም በፍርሀት ለደነዘዘው የህብረተሰብ ክፍል ምሳሌ በመሆን መነሳሳትን ፈጥረዋል።

ሆኖም ግን ህዝቡ ተገቢውን እውቅናና ድጋፍ ባለመስጠቱ ምክንያት የመብት ጥያቄው በሀይል የመዳፈን ጥላ አጥልቶበታል። መንግስት በሚያደርገው  የጭካኔ ድርጊት ምክንያት ከዶክተሩ የባሰ ችግር ያለበት የህብረተሰብ ክፍል የመብት ትግሉን እንዳይቀላቀል "ስራዬን አጣለሁ" የሚል ስጋት አድሮበታል።

ይህ ጥያቄ የጤና ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን የአብዛኛው የመንግስት እና የግል ዘርፍ ሰራተኞች ጥያቄ ነው።መምህራኖች፣ የፍትህ ባለሙያዎች፣ ኢንጂነሮች ተገቢውን ደሞዝ እያገኙ አይደለም።

በ6 አመት ውስጥ ነዳጅን ጨምሮ አብዛኛው ምግብ እና መሰረታዊ ፍጆታ  በሶስት እጥፍ(300%) ጨምሯል ለሰራተኛው የደሞዝ ጭማሪ የተደረገው ግን ከ30% በታች  ነው።በዚህም ቤተሰቡን ለማስተዳደር ይቅርና የራሱን የእለት-ጉርስ እንኳን ለመሸፈን በቂ አይደለም።

ለልጆቹ  የተሻለ ትምህርት የሚፈልግ ህዝብ መምህራኖች የተሻለ ደምወዝ እንዲያገኙ ማድረግ አለበት። ይህ ካልሆነ ፈፅሞ የትምህርት ጥራትን ሊጠብቅ አይገባውም መምህሩም ስራውን እንደተከበረ ስራ (profession) ሳይሆን  እንደመጠባበቂያ (ጊዜ ማሳለፊያ) ስራ ሊቆጥረው ይገደዳል።

ከሙስና የፀዳ እውነተኛ ፍትህ ለማግኘት የሚፈልግ ህዝብ መጀመሪያ  የዳኛ፣ የአቃቢ-ህግ ፣የፖሊስ ደሞዝ በቂ አይደለም  ብሎ ሊታገል ይገባል።

ስርዓተ -አልበኝነት እንዲኖር የማይፈልግ ህዝብ ሰራተኛው ተገቢውን የላቡን ዋጋ እንዲከፈለው  ማገዝ ይኖርበታል።አለበለዚያ ነጥቆ እና አጭበርብሮ  የሚበላን ሰው እያበረታታ ነው ማለት ነው።

የዜጎች የመብት ጥያቄ የሚመለሰው ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አንድ ሆኖ በመተባበር ድምፁን ሲያሰማ ነው።በተናጠል የሚደረግ ትግል ነጥሎ ለመምታት ያመቻልና ...

የህዝብን ሀብት ፈጣን ገቢ በሚያሰገኙ ፕሮጀክቶች ላይ ከማዋል ይልቅ የሀገሩ ህዝብ እንኳን በነፃነት የማይንቀሳቅስበት አገር ላይ ለቱሪዝም ገቢ ተብሎ ቢሊዮን ብሮችን በማውጣት የቅንጦት ሪዞርቶችና መናፈሻዎች መስራት ትክክል አይደለም።

በጦርነት የተጎዳውን ኢኮኖሚ መልሶ እንዲያገግም ከማድረግ ይልቅ ቢሊዮን ዶላሮችን አውጥቶ በአንድ አገር ሁለት ቤተ-መንግስት የሚሰራ መንግስት ህዝባዊ ተቃውሞ ካልገጠመው በስተቀር ይህን ስራውን ይቀጥላል።

በማጭበርበር እና በሙስና በአንድ ጀንበር ሚሊዮን ብሮችን በማጋበስ ሀገርቱ ላይ በነፃነት የሚርመሰመሱ ሰዎችን ከማሰር ይልቅ መብቱን በሰላማዊ መንገድ የጠየቀውን ዜጋ ማሰር እና ከስራ ማፈናቀል ፍትሀዊ አይደለም።

@zephilosophy
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ራስን ማጥፋት መብት ወይስ ጥፋት
ፍሬው ማሩፍ

ፈላስፋ ለመሞት ሁሌም ዝግጁ ቢኾንም በምንም መልኩ ግን ራሱን ሊያጠፋ አይገባም  አማልዕክቶቹ እሰከአልጠሩን ድረሰ በራስችን ፍቃድማ ህይወታችንን አንነጥቅም ይላል ሶቅራጦስ።

ራሱን ማጥፋት የደካማነት ማሳያ ሲሆን፤ አንድ ሰው ራሱን ካጠፋ ጨካኝ እና ለመኖር ብቁ ያልሆነ በመሆኑ ነው የሚለን ደግሞ አርስቶትል ነው፡፡ ለዚህ ፈላስፋ ራስን የማጥፋት ድርጊት ሊወገዝ የሚገባው ድርጊቱን ስለሚፈጽመው ግለሰብ ተብሎ ሳይሆን በማኅበረሰቡ ላይ ከሚፈጥረው ጉዳት አንፃር ነው፡፡ የዚህ ምክንያትም ይህ ድርጊት በማኅበረሰቡ ላይ የሚፈጥረው መልካም ያልሆነ ተጽዕኖ መፍጠሩ አይቀሬ በመሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም የማኅበረሰቡ አካል የሆነ ግለሰብ የማኅበረሰቡን ሕግና መመሪያ ሊያከብር ይገባል፤ ማኅበረሰቡ ደግሞ ራስን የማጥፋት ድርጊትን የሚከለክል በመሆኑ ድርጊቱ የሚፈጸም ግለሰብም የቀብር ሥርዓቱ በክብር ሊደረግ አይገባም ይላል አርስቶትል፡፡

ከጥንታውያኑ የግሪክ ፈላስፎች(ከላይ ከተመለከትናቸው) በተቃራኒ የሮማን እና የግሪክ ጸሐፍት እና ፈላስፎች ራስን የማጥፋት ድርጊትን ደግፈው ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ሉክራተስ ሕይወት በእጃችን ለመጥፋት ካሻት ለምን እንከልክላት ይለናል፡፡ ይህ ፈላስፋ ነፍስያው ራሱን ያጠፋ ዘንድ ሽታም ራሱን አጥፍቷል ይባላል። ሌላኛው የሮማን ዜጋ የነበረው ሲስሮ በበኩሉ ሰው በኑሮ ደስተኛ ካልሆነ እና ከምቾት ከተራራቀ ለምን ይኖራል የሚል እሳቤ ነበረው። የግሪኩ ፈላስፋ ኢፕክረስ ደግሞ ማናችንም ከስቃይ የሚገላግልንን የትኛውም ተግባር የመፈፀም መብት እስካለን ድረስ እና ከመፍተሄዎቹ መካከል አንዱ ራስን ማጥፋት ከሆነ፣ ማንም ሰው ራሱን በማጥፋቱ ሊወገዝ አይገባም ይለናል፡፡

አብዛኞቹ የሊብራል (ibertarian) የፓሊቲካ ፍልስፍና አራማጆች በበኩላቸው ሰው ራሱን የመግደል ሞራላዊ መብት አለው ይላሉ።የዚህ ፍልስፍና አራማጆች አንድም የአካላችን ባለቤት ከኛ ውጪ ማንም ስላልሆነ ባሻን ኹኔታ የማስወገድ መብት ስላለን፣ በሌላ በኩል የትኛውም ግለሰብ በሞቴ ደህንነትን አገኛለው ካለ ሊከለከል ስለማይገባ  የሚሉ መከራከርያዎችን በማንሳት ራስን ማጥፋት በሕግ ሊደገፍ የሚገባ ድርጊት ነውም ይላሉ።

ራስን መግደል በተፈጥሮ ራሳችንን የመንከባከብ እና የመውደድ ተገቢነትን የሚቃረን ነው የሚለን ደግሞ አኪውናስ ነው። “ራስን መግድል ግለሰቡ አባል የሆነበትን ማኅበረሰብ ላይ ጉዳት ከማድረሱ ባሻገር ህይወታችን የፈጣሪ ስጦታ የመሆኗን ሃቅ ይቃረናል፤ እንዲሁም የምድር ቆይታችንን በእሱ ፍቃድ ላይ መመርኮዙን የሚክድ ድርጊት በመሆኑ ራስን የማጥፋት ድርጊትን እቃወማለሁ" ይለናል የሥነ መለኮት መምህሩ።

የተፈጥሮ ሕግ ጽንስ ሓሳቦች አራማጆችም እንደሚሉት ራስን የማጥፋት ድርጊት የተፈጥሮ ሕግ ከሆነው የመንስዔ-ውጤት ግንኙነት ጋር የሚጋጭ ሲሆን፤ በተጨማሪም ራስን ማጥፋት የትኛውም ፍጡር ራሱን ከአደጋ ሊከላከል እንጂ ጉዳት ሊያደርስ አይችልም ከሚል የሥነ ኑባሬ ሥርዓት ጋር የሚጣረስ ድርጊት ነው የሚል ክርክርን ያነሳሉ።

ከተፈጥሮ ሕግ አንጻር የሚነሳውን መከራከርያ የሚቃወመው ዲቪድ ሁም “Of Suicide” በሚለው ጽሑፉ ላይ እንደሚለው ሰዎች በስቃይ ላይ ሆነው ሞት ብቻ ማምለጫቸው ኾኖ በተገኘ ጊዜ ራስን ማጥፋት ፈጣሪ አይፈቀድም ብሎ መከራከር አስገራሚ ነው፡፡ ይህ እምነት እና አስተሳሰብ የሰው ልጅ በሕይወቱ ላይ ምንም የማድረግ መብት የለውም እንደማለት ነው፡፡"

ከዴቪድ ሁም በተቃራኒ ቆሞ ኢማኑኤል ካንትን እናገኝዋለን። “The Metaphysics of Morals" በሚለው ስራው ላይ ካንት ራስን ማጥፋት ከአውሬነት ለይቼ አላይውም ይላል። አንድ ሰው ራሱን ለመግደል ሞክሮ ካልተሳካለት እንደ አውሬ አሊያም እንደ ቁስ ነገር ነው ልንመለከተው የሚገባው የሚል እሳቤም አለው፤ እንደ ውሻ አሊያም እንደ ፈረስ ለስፖርታዊ ጨዋት ልንገልገልበትም እንችላለን ይለናል። እንዴት ብትሉት “ሰውዬው ራሱን ለማጥፋት አቅዶና ወጥኖ ከሞከረው ሰው የመሆን ክብርን በራሱ ፍቃድ ነስቷል” የሚል ምላሽ ይሰጣችዋል።

ራስ የማጥፋት ድርጊትን በተመለከተ ከተነሳ የኢሜል ዱርካይም ስም እና “Le Suicide” የሚል ስራው ሳይጠቀስ ሊታለፍ አይችልም፡፡ ዱርካይም እንደሚለው ራስን የማጥፋት ድርጊት ስለሚፈጽሙ ግለሰቦች ጥናት እና ምርምር ሊደረግ ከተፈለገ መሰረታችንን የግለሰቡን ግላዊ ጠባያት ብቻ ላይ ካደረገን ትክክል አይደለም የሚለው ዱርካይም፤ ባይሆን ትኩረት ማድረግ ያለብን ግለሰቡ የሚገኝበት ማኅበረሰብ ላይ ነው የሚል ድምዳሜ ነበረው፡፡ የዚህም ምክንያት ራስን የማጥፋት ድርጊት የሚፈጸምበት ምክንያት ድርጊቱን በሚፈጽመው ግለሰብ እና አባል የሆነበት ማኅበረሰብ መካከል ያለው መሰተጋብር ጋር የተያያዘ በመሆኑ ነው፡፡

ለምሳሌ በእኔ ጥናት መሰረት ብሎ ዱርካይም እንደሚያስቀምጠው ከካቶሊኮች ይልቅ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮዎች ራሳቸውን ያጠፋሉ፡፡ የዚህም ምክንያት ካቶሊኮቹ ዓማኞቻቸውን የሚቆጣጠሩበት መንገድ ጥብቅ በመሆኑ ነው ይለናል። እንዲሁም ከሴቶቹ ይልቅ ወንዶች፣ ካጋቡትም ላጤዎቹ፣ ከወለዱት ያልወለዱት በይበልጥ ራስን የመግደል ድርጊትን ይፈጽማሉ።

እንዲሁም ከሰላሙ ይልቅ በጦርነት ወቅት ይበልጥ ድርጊቱ ይባብሳል። ይህ የዱርካይም ጥናት ራስን የማጥፋት ድርጊትን ከግላዊ ችግር ብቻ ተያይዞ ብቻ ሲታይ የነበረውን እሳቤ በብዙ መንገድ ለውጧል፤ እንዲሁም አዲስ የሥነ ማኅበረሰብ የጥናት መስክን በተለይም ከሥነ አእምሮ ጥናት በመነጠል የራሱን መሰረት እንዲኖረው አድርጎታል ይባላል፡፡

ዱርካይም ራስን የማጥፋት ድርጊትን ከድርጊቱ ፈጻሚ እና አባል ከሆነበት ማኅበረሰብ ጋር ካስተሳሰረ በኃላ፣ በመቀጠል ድርጊቱ የሚፈጸምበትን አራት ምክንያቶች ያስቀምጣል፡፡ እነሱም ከመነጠል የተነሳ (egostic suicide) ፣ “ለመሰዋትነት' (Altruistic suicide) ፣ “በመቃዋስ ምክንያት (Anomic suicide) እና “በመወጠር (Fatalistic suicide) በሚል ይከፈላሉ።

በኢትዮጵያ ውስጥ በቅርብ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በየአመቱ ከ8000 በላይ ኢትዮጵያዋን ራሳቸውን ያጠፋሉ፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት በ2018 ባወጣው ጥናት መሰረት በኢትዮጵያ የሞት ምክንያት ከሆኑት መካከል ራስን የማጥፋት ድርጊት 1.2% የሚሽፈን ሲሆን፤ ይኽም ማለት ከ100,000 ኢትዮጵያን መካከል 1.38 የሚሆኑት ድርጊቱን ይፈጽማሉ፡፡ አሁን አሁን ደግሞ ተባብሶ ቀጥሏል እገሌ ራሱን አጠፋ የሚል ወሬ ጆሯችን እየለመደው መጥተዋል፡፡ ትኩረት ቢደረግበትና መፍትሄ ቢሰጠው አይበጅም ትላለቹሁን!

የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የግጥም እና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ፈላስፋ የሆነው ኤልያስ መልካ ራስን የማጥፋት ድርጊት ልክ አለመሆኑን የገለጸበትና በዘሪቱ ከበደ፣ በአብነት አጎናፍር እና በጆኒ ራጋ ድምጽ "መኖርህን ሰዎች ይሻሉ” በሚል ርዕሰ የተቀነቀውን ሙዚቃ  በመጋበዝ እናብቃ።

@zephilosophy
Audio
መኖርህን ሰዎች ይሻሉ

ብትወድቅ ብትከፋ የያዘችህ ቤትህ አለም
ሳታሰናብት መሰናበት በራስ የለም

መች መብቴ ብለህ ወደህ መርጠህ መጣህባት
መብቴ ነው ብላለች አንተን ማኖር መች ጠበባት!!
Audio
ዋጋህን አስታውስ
ግሩም ተበጀ
@zephilosophy
Audio
አስደናቂ ውብ ታሪኮች ከመላው አለም

ተራኪ- ግሩም ተበጀ
@zephilosophy
2025/06/27 10:27:41
Back to Top
HTML Embed Code: