Telegram Web Link
በተለይ ሰኞ ሰኞ ገና ሲነጋ በጠዋት 12:30 ላይ ደዉላ ብር ላክ የምትል ታናሽ እህት አለችኝ

ደዉላ "ቀሰቀስኩህ? ተኝተህ ነበር እንዴ?" ትለኛለች

"አይ አልተኛሁም! ፀሐይ እስክትወጣ ጠብቅ ተብዬ እየጠበኩ ነዉ። ምን ፈልገሽ ነዉ?"

"ብር ላክ!"

"ሳምንት ላኩልሽ አይደል እንዴ?"

"ጨረስኩኮ እሱን። አሁን በዚህ ሳምንት የጓደኛዬ ልደት ነዉ በዚያ ላይ የትምህርት ቤት ክፍያ አለብኝ። በዚያ ላይ እንትን ጨርሻለሁ። በዚያ ላይ እንትን. . ."

"በቃኝ! በቃኝ! ስንት ነዉ ምልክልሽ?"

"እኔ እንጃ ስንት ይበቃኛል?"

"እንዴ እኔ ምን አዉቃለሁ?"

"በቃ ዝምብለህ 4 ላክልኝና ከተረፈ እመልስልሃለሁ"

"4 ምንድነዉ? መቶ ነዉ?"

"ኧረ ባክህ?! አትቀልድ በናትህ"

"የለኝም! ማዘርን ለምን አትጠይቂያትም?"

"ባክህ ለሷ ገና እስካስረዳትና እስካሳምናት እራሱ የልጅቷ ልደት ያልፋል"

"አንቺ በጣም ትቀልጅያለሽ"

"On God ነዉ የምልህ bro three to four business days ይፈጃል ከሷ ጋር ለመግባባት"

"እሺ በኃላ ደዉላላዉ"

"ከረሳኸዉ ደግሜ ደዉላለዉ እወቅ!"

"በኃላ ስልኬ ይጠፋል። መገናኛ ሌባ ይሰርቀኛል"

"አይቀርም በቢሮም ስልክ ቢሆን እደዉላለዉ"

"ቻዉ እሺ"

"በወጣ ይተካ ብለናል"

"በጣም 😏"

ስልኩ ይዘጋል። እግዜር ጤናና እድሜ ይስጠን እንጂ እሄዉ ስልክ ምክንያቱ ተቀይሮ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይደገማል 😁😁
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በኃላ አመሻሹ ላይ እንዳታስቸግርህ ቺኳን እንደኔ በጠዋት አግኛት 😁😂 ከ12 ሰዓት ጀምሮ ከጀማዉ ጋር ኳስ መተንተኛ ስለሆነ ሰዓቱ አይበቃም። ደግሞ ምክንያቱን ንገራት አሉህ . . . ከኔና ከቻምፒዮንስ ሊግ ምረጥ ከምትባል ጊዜ ሰጥተሃት በጊዜ ተሸብለል 😂😁

ሰናይ ቅዳሜ!!
ደማቁ የቻምፒዮንስ ሊግ ዕለት!!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🇩🇪🇩🇪🇩🇪🇩🇪🇩🇪
🇪🇸🇪🇸🇪🇸🇪🇸🇪🇸

ዉጤቱን በትክክል ይገምቱ... የሁለት መቶ ብር ካርድ ተሸላሚ ይሁኑ!!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዶርትሙንድ መምራት የነበረባቸዉ የመጀመሪያዉ አጋማሽ (1st half) ነበረ። እድል ከነሱ ጋር አይደለችም እስካሁን
THE #CHAMP15NS!!

🇪🇸🇪🇸🇪🇸🇪🇸🇪🇸
🇪🇸🇪🇸🇪🇸🇪🇸🇪🇸
🇪🇸🇪🇸🇪🇸🇪🇸🇪🇸

HALA MADRID!!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እዚህ ላይ ነዉ እንግዲህ ምባፔ የሚጨመረዉ
🏆🏆

🔥🔥🔥🔥🔥

ደህና እደሩ!!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ምን አይነት ምድራዊ ቃል ያፅናናሽ ይሆን ከዚህ ስብራት? ከባድ ህመም!! 🥺😔 እግዚአብሔር ያፅናናሽ!! 💔
ቺርስ!! 🥂

መልካም ቃል ለማይጎድልባቸዉ
ፉክክር ሳይሆን ህብረት ለሚታያቸዉ!!
አንገት ስንደፋ አይዞን ለሚሉ
አብረዉን ለመሆን ዋጋ ለሚከፍሉ
ስንፈልጋቸዉ ከጎናችን ለማይጠፉ
ዋጋችንን ከማንም በላይ አግዝፈዉ ላዩ

አቦ ቺርስ በያሉበት

ማደጋችን አይናቸዉን ለማያቀላ
እጅ ስንሻ እያዩ ለማይሉን ችላ
ቺርስ!!

የኔ ለማለት ለማያፍሩብን
ለኔ ለማለት የማይቸኩሉብን
ሸር ለማይተበትቡ
ወጥመድ ለማይዘረጉ
ጉድለታቸዉን ሙላታችን ለሚያስረሳላቸዉ
ተንኮል እንደቅቤ ያልጠገቡ
ጎበጣዉን መዘዉ ለማያወጡ
ከእግዜር ደግ ልብ ለተጋሩ
በመቆማችን እንደቆሙ ለሚኮሩ
ስንወድቅ ለማየት ቀመር ለማይቀምሩ
ቺርስ አቦ!

ቀናቸዉ ይለምልም!
ፀዓዳቸዉ ይመር!
አበባቸዉ ይጎምራ
የተከሉት ያፍራ
በትንሹ ስኬታችን እንደጨፈሩ
እልፍ እጥፍ ድርብ ያፍሩ
በረከትን በበረከት ላይ ይስፈሩ!!
እኔን ባሉበት አንደበት
እልል ይበሉ በደስታ ብዛት
እረፍት አይራቃቸዉ
ሐዘን ይታወርባቸዉ
አይያቸዉ ክፉ
ይጠበቁ በአንዲዬ በእቅፉ!

ቺርስ ለበጎዎቹ!
የዘመኑ በሽታ ላልያዛቸዉ
ሲመሽ ሲነጋ በቀል ለማይታያቸዉ
ቅናት ያላጠወለጋቸዉ
አርፈዉ የሚያሳርፉ እንደጥላ ለተዘረጉ
ብርሃን ተሞልተዉ ብርሃን ለሚያበሩ
አፅናኝ አንደበትና የሚጋባ ደስታ ለተሞሉ
አቦ ቺርስ!! ቺርስ!! ቺርስ!!

ምቀኛዉን ያርቅላቸዉ
ቅን ልቦናቸዉ አይነጠቅ
ከመርዘኞች ይሰዉራቸዉ
ጨለማ አይዋጣቸዉ
ሙሉ ይሁን ህይወታቸዉ
አይደብዝዝ ሳቃቸዉ!!
Dawite Mekonnen Mee Xiq...
90's Music With Lyrics
🎼  Mee Xiqo
🎤 Dawite Mekonnen

ከኔ ማህደር
ለናንተ

#አንድ_ለመንገድ
#ዝንቅ
6 ሴትን ማስፎንቀቂያ መንገድ አለ። 4ቱ ነገ ጠባ ስለsex አታዉራት ነዉ 😁

ለየት በል ከአብዛኞቹ!

ከዚያ ምን የመሰለች ዉብ አበባ 🌹 ቸከስ የራስህ ታደርጋለህ 😄
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Zumbara
Asni Abate & Dimoned Melkamu
🎼  Zumbara
🎤 አስኒና ዳዬ

ከኔ ማህደር
ለናንተ

ቀኑ ተወዳጁ ቅዳሜ ነዉ
በያላችሁት እየተፍታታችሁ 🤙
ፏ ብላችሁ ዋሉልኝ!!

#አንድ_ለቅዳሜ
#ዝንቅ
የድሃ ሀገር ዜጎች ሀብታም ለመሆን ዋናዉን ስራ ብቻ አይሁን እንጂ የትኛዉንም አይነት አቋራጭ መንገድ ታትረዉ ይጠቀማሉ¡

ርዕሱም ሀሳቡም ነዉ!!

ስትሰሩ ዋሉ!!
Monday, Money Day!!
መልካም ሰኞ!!
Every የከተማ girl has ናቲ's touch

ዱባለ ደግሞ is like ናቲ of የገጠር ሺኮች 😁😂

Every chick has story with Duብye 😄😂

አሁን ከግቢ ስወጣ አንዷ በስልክ "ሊሄድ የተነሳን ማዘግየት እንጂ ማቆየት አይቻልም" ስትል ትዝ ብሎኝ ነዉ 😂😁
Kuku Sebsebe - Leman Lenigere.mp3
🎼  ለማን ልንገር
🎤 ኩኩ ሰብስቤ

ከኔ ማህደር
ለናንተ

#አንድ_ለመንገድ
#ዝንቅ
ባለፈዉ ከሐረር ይዤ የመጣሁት ቡችላ መሳቅ ጀምሯል አላለኝም። በል አንተ ማልቀስ ሳትጀምር በጊዜ ሸኘዉ።

😁😂
ዒድ ሙባረክ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

ዝንቅ
ለአባቴ

(በዕውቀቱ ስዩም)

ሰው ብቻ አይደለህም፣ ካፈር ወጥተህ ላፈር
መላክ ነህ፣ ሉሲፈር
ክብርህ ማንነትህ ባመጽ የሚታፈር፡፤
የማትንበረከክ
የማትርመጠመጥ
ከባለጌ ዙፋን
በርጩማ የምትመርጥ፡፡
ያለ ባህር ሰርጓጅ ያለ ሙሴ በትር
በመታገስ ብቻ ፣ባህር የምትመትር፡፡
ካዘልከኝ ጀምሮ ፣እንኮኮ ጫንቃህ ላይ
ከፍታውን እንጅ፣ ዝቅታውን ሳላይ
እንደ ንሥር መጠቅሁ፣ እንደ ምስራቅ በራሁ
የገዛ ክንፎቼን ፣እንደ ዳንቴል ሠራሁ፡፡
በርግጥ ደሀ ነበርህ…
ከሰላምታ በቀር የማታበረክት
ነጠላህ መናኛ፣ሰውነትህ የክት
በርግጥ ድሀ ነበርህ
የነጣህ፣ የጠራህ
ከጦርሜዳ ይልቅ ገበያ ሚያስፈራህ፡፡
ቤሳ ባታወርሰኝ አወረስከኝ ትግል
የትም እንዳይጥለኝ ፣ሕይወት እንደ ፈንግል፡፡
አባየ ብርሀን
አባ የምስራቅ በር
ገመና ሸሻጊ፣እንደ ካባ ገበር
አባቴ ባትሆን ይጸጽተኝ ነበር!
ዛሬ አለም አቀፍ የሙዚቃ ቀን ነበረ።

ሙዚቃ መዝናኛ፣ ሀሳብን፣ ደስታን፣ ፍቅርን፣ ሀዘንን መግለጫ የሆነ አለምአቀፍ መግባቢያ ነዉ። ብዙ የድብርት ቀናትን ሙዚቃ አፍክቶታል። ብዙዎች ፍቅራቸዉን ሌሎች ስብራታቸዉን መግለፅ ተስኗቸዉ ሙዚቃ ጋብዘዋል፤ በሙዚቃ ተነጋግረዋል። ሙዚቃ ትዝታ ነዉ፤ የበጎና መጥፎ ጊዜ ማስታወሻ! ሙዚቃ ቴራፒ ነዉ፤ የተሰበረን መንፈስ ማከሚያ። ሙዚቃ ጉልበት ነዉ፤ በሞራል መስሪያ።

ትኑር ሙዚቃ
ስሜት አምቃ
ደምቃ አሸብርቃ
❤️💔🤍
Eketelehalwe
Tsedenia G - Topic
🎼  እከተልሃለሁ
🎤 ፀደኒያ ft Marcos

ከኔ ማህደር
ለናንተ

#አንድ_ለመንገድ
#ዝንቅ
የቅዳሜ ዉሎ

ፋራ ሆኛለሁ ስላችሁ ፋራ ግምብ ፋራ ነዉ የሆንኩት 😂😁😂😂

ቺክ ምልክት ስታሳየኝ ማንበብማ ታዉሬያለሁ 😂 ኧረ አምላኬ እንደድሮዉ ቀይረኝ 😂😂 እነሱ ደግሞ አፈሉ 😂 ወንድ ልጅ ጨዋ መሆን አይችልም በቃ?
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/06/28 12:39:57
Back to Top
HTML Embed Code: