Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በ9 አስጀምሮሃል በ7 ያስወጣህ እንደንጉሱ!!

🫡👌
"አበባነትሽን ለመቅሰም ብዙ ወንዶች ዙሪያሽን ነዉ የሚዞሩት። ካሁኑኑ ስለ ቁም ነገር ማሰብ መጀመር አለብሽ" እያላት ነዉ ገቢና ዱቅ አርጓት። ምንም አታወራ ጭንቅላቷን ብቻ "አዎ ልክ ነህ" እያለች ትነቀንቃለች። እናንተ የናንተን ላይፍ ቀጭታችሁ ስታበቁ ቆንጆ ቸከስ ባያችሁ ቁጥር ምክር ቢጤ የሚያምራችሁ ሼባዎችና የወጣት ሼባዎች ምናችሁን ነዉ የሚያመዉ? 😁😂

እዚህ ሀገር ሁሉም ቆንጆ ላይ ይበረታል ምንሸት? ባህል ወጓን እንድታከብር ሁሉም ህግ የሚያከረዉ ቆንጆዋ ላይ፣ ስትቦርቅ ስትደሰት አታግቢና እያለ ሁሉም ወላጅ ወላጅ የሚያጫዉተዉ ቆንጂዬዋ ላይ፣ የሚያፈጋ ስራ ስትሰራ አንቺን የመሰለች ቆንጆ እንዴት የሚለዉ ቆንጂዬዋን፣ ስራ ሳትሰራ ቢያያት ሹገር እያጨወተች የምትኖር የሚለዉ ቆንጂዬዋን፣ ወዘተ ተዘርዝሮም አያልቅም። ለዚህ ነዉኮ ቆንጆ ቸከሶች የማይቀርቧችሁ። እነሱም ሰዉ መሆናቸዉን ትረሱና ራሳቸዉን እንዲሆኑና ፈታ እንዲሉ አትፈቅዱላቸዉም። ለመወደድ ቺክ መምከር አይጠበቅብህም ወንድማለም 😂 እዉነተኛ ሁን! ለመጥበስ ከፈለክ ጀንጅን እንጂ አትምከር! ፍሬንድ ዞን ዉስጥ ዘጭ የምትሉት እኮ ለዚህ ነዉ 😄

እኔ ተናግርያለሁ
✌️ ፒስ!!
Yosef Gebre aka Jossy - ...
kuchu
🎼  መጣዋ
🎤 ጆሲ

ከኔ ማህደር
ለናንተ

#አንድ_ለቅዳሜ
#ዝንቅ
"በተመረቅንበት የትምህርት መስክ ሥራ ፈጣሪ በመኾን ሀገርን የሚጠቅም ሥራ እንሠራለን" ተመራቂዎች 😂😁😂

በሉ ስራ ፈጣሪዎች ስትሰሩ ዋሉ!
ሰኞ የስራ ቀን!
ላይፍ ቦይ - ከማነሷ የልብ ማድረሷ!
Channel photo updated
ቸከስህን ለጓደኞችህ ስታስተዋዉቅ "ዋናዉ አንተ ደስተኛ መሆንህ ነዉ" ካሉህ እንግዲህ የጠበስካትን እየነገሩህ ነዉ 😂😁😂

ግን የትኛዉ መሪጌታ ጋር ነዉ ያሰራኸዉ ካሉህ ደግሞ you know what you bagged 😂👌
Channel photo updated
Channel photo updated
መስቀልና በዓላት ሲደርሱ፣ ለዘፈን ክሊፕና ለቫኬሽን ወደ ጋሞና ጎፋ ደጅ የሚሮጡ እግሮች ዛሬ ዳር ቆመዉ ከንፈር እየመጠጡ ነዉ። ቴዲና ያሬድ ብቻ ሁለት ጊዜ ሳያስቡ ምላሻቸዉን ሰጥተዋል። የዘገየ እርዳታ ከሹፈት አይተናነስም። ታሞ የሚማቅቅን ሰዉዬ ህመሙ እንደጠናበት ስታዉቅና ሰዉ ሁሉ እንደጠየቀዉ አንተ ብቻ እንቀረህ ስታዉቅ ሄደህ መጠየቅ ርህራሄና እርዳታ ሳይሆን የይሉኝታ ፍራቻ ነዉ። ብዙዎች አስቸኳይ መልስ የማይሰጡት ራሳቸዉን ችለዉ መቆምና ማሰብ የማይችሉ፣ የዉሳኔ አቅም የሚጎድላቸዉ ስለሆኑ ነዉ። ቢሆንም ግን ሁሉም የየአቅሙን ሳይረፍድ ለሰዉ ብሎ ሳይሆን ሰብዓዊነት ተሰምቶት ቢተጋገዝ የጠፋዉን ባንመልስ እንኳን የተረፈዉን የተጎዳዉን ማበርታትና ማፅናናት እንዲሁም ተስፋ ማስረፅ ይቻላል።

እግዚአብሔር ያፅፅናናችሁ!!
🖤🖤🖤🖤🖤
Hailu Mergia & The Walias - Woghenei
AbeokutA MusiC
🎼  ወገኔ (Instrumental)
🎤 ሐይሉ መርጊያና ዋሊያ ባንድ

ከኔ ማህደር
ለናንተ

#አንድ_ለቅዳሜ
#ዝንቅ
የሆነ ቀን አንድ ጓደኛዬን እያወራሁት

"አንተ ሁልጊዜ እሁድ ይመስልሃል የፍቅር ቀን። የሚወደዉን ላገኘ ሰዉ ሁሉም ቀን እሁድ ነዉ። አንተ ምናልባት በእሁድ ስላስለመድክ ይሆናል እሁድ የፍቅር ቀን የመሰለህ። ግን ቀን ቀን ነዉ። ሰኞ ከሆነ የምታፈቅራትን ልጅ የምታገኘዉ ሰኞም የፍቅር ቀን ይሆናል" አለኝ

እዉነት ነዉ! ቀንን ዉብ የሚያደርጉልን ዉብ ሰዎች ናቸዉ። እሁድም ዉብ እንድትሆን የምትወዱትን ሰዉ አግኙ።

እሁድ የፍቅር ቀን!
በፍቅር ተሞሉ!!
በፍቅር ዋሉ!!
የተረጋጋ ነፍስያ ዉስጥ ስትሆን አንዳንድ ነገሮች ትርጉማቸዉ ይገዝፋል። ሰዎችን ትወዳለህ። ስርዓትን ታደንቃለህ። ታላቁ መፅሐፍ እምነት ተስፋ ፍቅር ፀንተዉ ይኖራሉ፤ ፍቅር ግን ከሁሉ ይበልጣል ያለዉ ይገባሃል። አየህ ምንም ያህል የተማርክ ብትሆን፣ የፈለገ ገንዘብ ቢኖርህ፣ ዉበት ቢደፋብህ አለምን የምታየዉ በሰዉ ዉስጥ ነዉ። አጠገብህ ያሉት ሰዎች ጭለማ ከሆኑ አለም በሙሉ የጨለመ ይመስልሃል። ደጋግና መልካም ሰዎች ህይወትህን ሲከቡ ግን አመስጋኝ ትሆናለህ። ቀና ቀናዉን ታያለህ። ደግ ትሆናለህ። ለሚቀርቡህ አትመርም ትጣፍጣለህ። በሰዎች ዉስጥ የፍቅርን ኃያልነት ታያለህ። ገንዘብ፣ ዉበት፣ ዝና፣ ስልጣን፣ ክብር፣ ስጦታና እድሜ ከፍቅር እንደማይበልጡ ትገነዘባለህ። ከፍቅር ዉጪ ያለዉ ህይወት ሁሉም ይለመዳሉ። ሁሉም ቀነ ገደብ አላቸዉ። ሁሉም ያረጃሉ። ሁሉም ይጠገብና ይሰለቻሉ። ፍቅር ብቻዉን ይኖራል። ፍቅር ብቻ አይጠገብም!! ሁሉም በቃኝ ሊባል ይችላል። ፍቅር ግን ማብቂያ የለዉም።

ኢዮብ መኮንን እንዲህ ይላል

ልሁን ሞኝ የሚወደዉን ካገኘዉ፣
ፍቅርን ያጣ ብልጥ እስኪ ደስታዉ ምንድነዉ?
ዝቅ ልበላ ከግምታቸዉ በብዙ፣
ምን ጥቅም አለው ከፍታ ፍቅርን ካልያዙ!

እሁድ የፍቅር ቀን፤ የፍቅር ምሽት!
መልካም አዳር!
ሳትሸጥ ሳትለዉጥ ተኝተህ ስትነቃ የምትከስርባት ሀገር!!


አንድ ጊዜ 95 በመቶ የሚሆነዉ አካዉንት የከፈተዉ ህብረተሰብ የቁጠባ ሂሳቡ ዉስጥ ያለዉ ከ100,000 ብር በታች ነዉ የሚል ዜና አይቼ ነበረ። አስቡት ከ130 ሚሊየን ህዝብ መሃል 95%? አሁን ይኸዉ የዶላር ምንዛሪዉ ደግሞ ብዙዎች አከሰረ እጅግ በጣም ጥቂቶችን ደግሞ አክብሮ አድሯል። ደሞዝተኛ የሆነ በሙሉ 30% ከሰረ። እንግዲህ በዚህ መኃል ነዉ ብዙዎች ሰርተዉ ለመለወጥ የሚደክሙት። የሚያግዝ መንግስት ሳይሆን ጭላንጭል ተስፋን የሚያደበዝዝ መንግስት ይዘን ወደ ስራ 😒😔

ሰኞ፣ ክረምት፣ ደመና፣ ጭጋግ፣ ስራ!
ስትታትሩ ዋሉ!!
በጠዋት የቀሰቀሰኝ ስልክ የሷ ነዉ

"ዛሬኮ ቀኔ ነዉ" አለችኝ

"ልደትሽ ነዉንዴ?"

"አይደለም!"

"እና ኦዉ ያ ነገር ጀማምሮሽ ነዉ? ቸኮሌት ልግዛልሽ?"

"እሱም አይደለም ግን ቸኮሌቱን ግዛ"

"እና ምንድነዉ ታዲያ?" 🤔

"እኔ ላንተ ምንድነኝ?"

"ጓደኛ!" 😎

"ምንንንን?" 😡😡

"ማለቴ ገርልፍሬንድ" 😃

"እኮ ዛሬ August 1 አለም አቀፍ የገርል ፍሬንዶች ቀን ነዉ!"

"በቃ በጭስ ያበደ ቡና ከቸኮሌት ጋር እጋብዝሻለሁ 😁"

"አፈር!!"

"ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ ነዋ"

"ስንት ሰዓት ነዉ ስራ የምትጨርሰዉ?"

"ከሰዓት free ነኝ"

"እሺ እመጣለሁ በቃ"

"እወድሻለሁ"

"እኔም"

"ቸዉ"

"ቸዉ!"

ሐሙስ የቀን ቅዱስ!
መለስተኛ የፍቅር ቀን!
ደስታ ከህይወታችሁ አይራቅ!
Channel photo updated
አጠገባችሁ ያለዉን ሰዉ አትጥበሱና Online እየሻፈዳችሁ ኑሩ 😁😂

ነገ የፍቅር ቀንን አስመልክቶ የምፅፈዉ ረጅም ፅሑፍ ርዕስ ነዉ። ኦሎምፒካችን እንደሆነ ተሸብሯል። እሺ ምን ማድረግ ይሻላል? ማልቀስ ይሻላል? 😂😁
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቀኑ እሁድ ነዉ የፍቅር ቀን እንዲሁም የእረፍት ቀን!

እረፍታችሁን የምታደምቁበት ምርጥ ኢትዮጵያን የሚመስል ኢትዮጵያዊ ፊልም ልጋብዛችሁ

"Running against the wind /የንፋሱ ፍልሚያ/"

ይመቻችሁ!
እሁድ የፍቅር ቀን፣
በፍቅር ዋሉ።
በጠዋት ጩጬዉ ቀኔን አበላሽቶት ነበረ ለትንሽ አመለጥኩት "ሸረሪት ግን የሴቷም የወንዱም ስም እንዴት ሊሆን ይችላል?" ብሎን ያልተደወለ ስልክ ሄሎ ሄሎ እያልኩ ወጣሁ።

ይሄ ፈላስፋ ጩጬ ቅዳሜዬን ሊበላብኝ 😳
ቅዳሜ ናት ፏ ብላችሁ ዋሉልኝ!
Channel photo updated
2025/06/28 05:33:26
Back to Top
HTML Embed Code: