Telegram Web Link
Channel photo updated
ከኮሮና ወዲህ ቺክ ጠብሶ የማያዉቀዉን ጀለሴን አግኝቼዉ አዲስ አመት እኮ ገባ የዘንድሮ እቅድህን በደንብ አወጣህ አልኩት? (ባይ ዘ ዌይ ሁሉንም ሰዉ እቅድህ ምንድነዉ አይባልም እቅዱን እሱና እግዜር ካወቁት ይበቃል። እኛ ቀስ ብለን እያየን እንሄዳለን የሰዉ ህይወት ዉስጥ ገብቶ የመፈትፈት ሱስ ይብቃችሁ)

"አዋ በደንብ! ግን ከኔ እቅድ በተጨማሪ ዘንድሮ ረዥም፣ ቀይ፣ ግብዳ ዲምፕላም ቂጥ ያላት ቸከስ ሰጥቶ ህይወቴን እንዲያረሰርሰዉ ነዉ ፈጣሪዬን የለመንኩት" አለኝ 😁😂

"ግን ብትመጣ ተዘጋጅተሃል አንተ?" አልኩት 😁

"አዋ ለዚያውም ከኮሮና ጀምሮ ራሴ ላይ ስሰራ ነዉ የቆየሁት" አለኝ

"በለዉ! ጎርፍ በጎርፍ ልታደርጋት ነዋ" 😜😁

"ምን ማለት ነዉ ደግሞ?" አለኝ

"ኧይ ያዉ ይቅናህ ማለቴ ነዉ" 😂😁

አዲስ ዓመት ሲመጣ ከሚታቀዱ ነገሮች አንዱ ትዳር ነዉ። ዘንድሮ ለማግባት ያቀዳችሁ ፈጣሪ በእቅዳችሁ ላይ ይጨመርበት። ያሰባችሁት ይሳካ። ልሰብሰብ ያለን እናበረታታለን 😁

በጎ እቅዳችሁ በሙሉ ይስመርላችሁ!!
2017 የመልካም ዜና ዓመት ይሁንላችሁ!!
🙏11👍3😁2
እንኳን ለ1499ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል !!
👍3
አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ

ነፍስ ይማር!!
💔12👍1
The best mezmur Meskel A...
El shaddai Tube
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!!

ፈጣሪ ህይወታችሁን ይባርክላችሁ!!
4
ማለት እንዴት ሰዉ ፊቱን በላይፍ ቦይ ይታጠባል?


አጃክስና ኦሞ ምን አደረጉ?
😁14👍1
ዝንቅ መዝናኛ
https://youtu.be/edosDhGYzMk
ያበደ የዘጠናዎቹ ኮከቦች mix

የቤት መፈራረስ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የአዲስ ዓመት ክረምት፣ የቀወሰ መንግስት፣ የማያጠግብ ደመወዝ፣ ግራ የገባዉ ወጣትነትና ነጋዴ መስሪያ ቤቶች በበዙባት ከተማ ሆነን ይህቺን አዲስ የዩትዩብ ዲጄ ቅንብር ጋብዝኳችሁ።

አይዟችሁ ያልፋል!!
6🔥1
Channel photo updated
በቸልሲ እና አርሰናል መካከል በዛሬው እለት በሚካሄደው ተጠባቂ የለንደን ደርቢ ማን ያሸንፋል? #PremierLeague #Arsenal #Chelsea
anonymous poll

አርሰናል – 28
👍👍👍👍👍👍👍 48%

ቼልሲ – 19
👍👍👍👍👍 33%

አቻ – 11
👍👍👍 19%

👥 58 people voted so far. Poll closed.
1
The final form of ሆ ኢዝ ሪሊጅየስ person ይላል የተከበረዉ የጣሊያን ህዝብ 😁😂

እስቲ አቻ ፍቺውን በሀገርኛ አባባል የሚሞክር 😁😂
😁2👍1🤔1
የሆነ ቪድዮ እያየሁ ነበረ

ያማረላት መስሏት ወንድ ልጅ ብሉቱዝ ነዉ በቅርቡ ያገኘዉን ኮኔክት ያደርጋል ሴት ልጅ ዋይፋይ ናት ጠንካራዉን አይታ ኮኔክት ታደርጋለች አለች እሷ

እሱ ደግሞ ቀበል አድርጎ አዎ ሴት ልጅ ዋይፋይ ናት አስሩም ኮኔክት የሚያደርጋት አዎ ወንድ ልጅ ብሉቱዝ ነዉ አንዱን ኮኔክት ለማድረግ መጀመሪያ የያዘዉን መልቀቅ ያለበት አለ ነገር አሳመርኩ ብሎ

ግን እኔ የምለዉ እሱኮ ድሮ ድሮ ነዉ አሁን ለዋይፋይም ኮኔክት የሚያደርገዉን መጠን መገደቢያ ሴትንግ አለዉ። ብሉቱዝም ዘመናዊ ስልኮች ላይ በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ ዲቫይስ ላይ ኮኔክት ማድረግ ይችላል።

ስለዚህ ሁሉም የምርጫ ጉዳይ እንጂ ብልግና በፆታ አይደለም። እዉነቱ ሲገለጥ ሁለቱም ፆታ ባለጌ ነዉ ተፋፍሮ ነዉ እንጂ። አጉል አትመፃደቁ!!
😁12👍6
ነጭቶ ነጭቶ ሲጠግብ ከቤተሰብ ላስተዋዉቅሽ ሲላትኮ በቃ እሷ የጠበቀችዉ ሌላ ነዉ 😁😂

ጀለስ የሁለት ልጆቹንና ሚስቱን ፎቶ አልበም ይዞ ከች አላለም? 😁😂 ቱ! ጌታዬ ለባለትዳር ወንዶች የሰጠኸዉን ኮንፊደንስ ግማሹን ለኛ ስጠን 😂😄

ሴት ቶሎ ቶሎ የምጠብሰዉ ሴት ለመጥበስ እንዲመቸኘ ነዉ ያለኝ ጀለሴ ምን ማለት ፈልጎ እንደነበረ አልገባኝም ነበረ 😁 አሁን ግልጥልጥ አለልኝ
😁5👏2🙏1🫡1
ሴት ልጅ ምን አይነት ወንድ ይመችሻል ስትላት የምትነግርህ ባሏ ወይም ጓደኛዋ የሆነ ሰዉ እንዲሆንላት የምትፈልገዉን እንጂ የምትመሰጥበትን ነገር አይደለም። ኤክሶቿን ብታይ አንዱም እሷ ያለችዉን መስፈርት አያሟሉም። 😁 ግን በፍቅር ክንፍ ብላላቸዋለች። ስለዚህ ሴት ልጅ መጥበስ ከፈለክ ሴት አታማክር። ብትችል እንደዉም ማንንም አታማክር የፈለከዉን ልብህ የፈቀደዉን ሁሉ እያደረግክ ራስህን ሁን። ማማከር የግድ ካለብህ ግን ወንድ አማክር። ከጠበስካት በኃላ ግን ከተመቸችህና ልታጣት ካልፈለክ የዛኔ አማክራት የምትልህንም ስማ!!
👍122
አንዳንድ ሰዎች ምስቅልቅል ካለ ሕይወታቸው እንድታድናቸዉ ነዉ የሚፈልጉት። ስለዚህ ወደ ማጥ ዉስጥ ይጋብዙሃል። ብራዘር እኔ የበጎ አድራጎት ድርጅት አይደለሁ... ምን አድርገዉ ፈጣሪ እዚህ ምስቅልቅል ዉስጥ ገብተዉ እንዲዳክሩ እንደተዋቸዉ አላዉቅም። ስለዚህ ስራቸዉ ያዉጣቸዉ ብለህ ሰበብ ፈጥረህ ዞር ማለት ነዉ 😎😎

ማንም የማንም ባለዕዳ አይደለም!
እያኗኗርን ሳይሆን እየኖርን እንሙት!
መልካም ዕለተ-ዕሮብ!!
9👎6👍4
ጅላሶች እንዲሁ ደዉላችሁ ለረዥም ደቂቃ ልታወሩት የምትችሉትን የኔ የምትሉትን ሰዉ ማግኘት መታደል ነዉ። ለማዉራት ያህልማ ከማንም ጋር ይወራል። አንዳንድ ጊዜ ግን ለረዥም ደቂቃ ወይ ሰዓታትም ይሆናል አዉርታችሁ ስታበቁ ያ ሰዉ የናንተ ካልሆነ ባዶነት እንዲሁም ድጋሚ ድብርት ዉስጥ ትገባላችሁ። ነፍሳችሁ ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ያሏት ይመስል ጭንቀት ዉስጥ ትዘፈቃለች። የኔ ከምትሉት ጋር ሰዉ ግን ሰላምታ ብቻውን ቀናችሁን ያሳምራል። ፍቅር ስለ ህይወት ያለንን ጨለም ያለ ዕይታ በብርሃን ይሞላዋል። የኔ የምትሉትን ሰዉ አጥብቃችሁ ያዙ። ተቀባይ ብቻ ሳትሆኑ ሰጪም ሁኑ። ብዙዎች የኔ የሚሉትን ሰዉ ያጡት በተቀባይ ስሜት ብቻ ራሳቸዉን እየፈተሹ ጉድለት ሲቆጥሩ ነዉ። ከመቀበል ደግሞ መስጠት የእዉነተኛ ደስታ ምንጭ ነዉ። ሰጪ ያድርጋችሁ!! ቀናችሁ ይለምልም!!

መልካም እሁድ!!
12👍2
ሰዉ ክፉ ነዉ። ሰዉ ብቻ ሳይሆን አንተም አንቺም እኔም ክፉ ነን። ሰዉ ሲባል ሌላዉን ብቻ ይመስለናል። በክፉ ሰዎች መኃል ሆነን ግን ክፋትህን አምላክ ሳይቆጥርብህ የምትወዳትን የምትወድህን ቺክ አምላክ ሲሰጥህ አመስግን፤ የምር ደስ ይበልህ። መልካም ወንድ ሁንላት። በፍቅር ክነፉ። ስለሰዉ ስለሰዉ ቀድጄ ልልበሰዉ በሉ። ግን እንደ ወንድ ዓላማህን አትርሳ። ስራህን አትጣል።

ሐሙስ
የቀን ቅዱስ!
ሰናይ የስራና የፍቅር ቀን ይሁንላችሁ!!
19👍2
ችግሩ ወንድ ልጅ ቸከሱ የምታደርጋቸዉ ነገሮች ከሱ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የምታደርግ ይመስለዋል። ሴት ደግሞ ወንድ ልጅ የሚያደርጋቸው ነገሮች ለመጨረሻ ጊዜ ከሷ ጋር ብቻ የሚያደርግ ይመስላታል።


ሁለቱም ይህ እዉነት እንዳልሆነ ያወቁ ዕለት ግን እሱ «አታላይ ነች ይቺ ልጅ አታላይ ነች . . . » እያለ ሲዘፍን እሷ ደግሞ «ከኔ ምን አተህ ነዉ . . .» የሚለዉን ትዘፍናለች
😂😁😁😂

ለማንኛውም ቅዳሜ ነዉ ቀኑ!
ደስ ብሏችሁ ዋሉልኝ!
😁14🔥121
ሰዉ የሚለዉ ሲያጣ ከኮርና የተላኩ ልክስክስ ጎሎች እያለም ራሱን ያፅናናል
😁9👍1
2025/10/21 23:35:41
Back to Top
HTML Embed Code: