Telegram Web Link
Forwarded from Orthodox Tewahdo new
የኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ በጀርመን በርሊን መካሄድ ጀመረ ! 

መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]

በኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናትና በጀርመን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በሚል ዓላማ በጀርመን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው የኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ. ም በህንድ ማላንካራን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የመክፈቻ ጸሎት በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ተጀመረ።

እስከ መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ. ም በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ በውጭው ዓለም በተለይ በጀርመን ያሉ የኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት አባላት እናት ቤተ ክርስቲያናቸውን በመደገፍ ረገድ ያላቸውን ሚና አስመልክቶ የየራሳቸውን ተሞክሮ የሚያቀርቡበትና ውይይት የሚደረግበት ነው። በመኾኑም በጉባኤው የአምስት አኀት አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች የተገኙ ሲኾን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትን በመወከል ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተዋል። 

ጉባኤውን በጸሎት የከፈቱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ 3ኛ የህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የጉባኤውን አስፈላጊነት በማውሳት ፤ ለአዘጋጆቹ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በተመሳሳይም ከሮማ ካቶሊክ፣ ከምሥራቅ ኦርቶዶክስ፣ ከጀርመን ወንጌላዊት አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች በጉባኤው በመገኘት መልእክት አስተላልፈዋል።

©የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚድያ

✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Orthodox Tewahdo new
የምስራች ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ!

የግእዝ (የአብነት) ትምህርት በስልኮ መጣሎት።


ማንኛውም ምዕመን ውዳሴ ማርያምና መዝሙረ ዳዊትን መጸለይ እንደሚገባው ያውቃሉ ?

በተጨማሪም ገድላትን ለማንበብ ወይም ጸሎትዎን 
#በልሳነ_ግዕዝ ለማድረግ ከፈለጉ  የግድ #ንባብ መማር ያስፈልግዎታል።

ከሀገር ውጪ እየኖሩ ማንኛውንም
#የንባብ_ትምህርት፣ #ቅኔ  እንዲሁም #ቅዳሴ በቀላሉ መማር ከፈለጉ ያግኙን።

በጉባኤም ኾነ በግል ሰዓት ይዘን እናስተምራለን።

ስልክ +251934104451
Tg @lealem16


የምንሰጣቼው ትምህርቶች በጥቂቱ፦
፩) ንባብ ቤት

ሀ) የቃል ትምህርት በሙሉ (ከጸሎት ዘዘወትር እስከ መልክአ ኢየሱስ)

ለ) ምንባብ  (ወንጌለ ዮሐንስና መዝሙረ ዳዊት፣ በተጨማሪም ስንክሳርን ጨምሮ ገድላትና ድርሳናት እንዲሁም ሐዲስ ኪዳን ብሉይ ኪዳን ንባብ)

፪) ቅኔ ቤት
ቅኔ ነገራ፣ ቅኔ ዘረፋ፣ ግስ፣ አገባብ...

፫) ቅዳሴ ቤት
ግብረ ዲቁና፣ ፲፬ቱ ቅዳሴያት፣ ሰዓታት


ለበለጠ መረጃ፦
ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
@beteyared21
@beteyared21
@beteyared21
Forwarded from Orthodox Tewahdo new
"በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

📣 እንኳን
#ለዐቢይ_ጾም_ሰባተኛ_ሳምንት_ለኒቆዲሞስ #እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰ።


#የዚህ_ሳምንት_የኒቆዲሞስ_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "ሖረ ኀቤሁ #ዘስሙ_ኒቆዲሞስ ወይቤሎ #ለኢየሱስ_ረቢ_ንህነ_ነአምን ብከ ከመ እምኀበ #አብ_መጻእከ መራሔ ሕይወትነ ወሠራየ ኀጢአትነ ከመ #እምኀበ_አብ_መጻእከ ከመ ትኩን መምህረ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ አንሥአኒ በትንሣኤከ። ትርጉም፦ አስቀድሞ ሌሊት ወደ እርሱ ይሄድ የነበረ #ስሙ_ኒቆዲሞስ የሚባል መምህር ሆይ #ከአብ_አካል_ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ተወልደህ ወደዚህ ዓለም እንደ መጣህ ፈጽሞ እናምንብሃለን፤ የሕይወታችን መሪ ኀጢአታችንን ይቅር የምትል ነህ አለው"። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በጾመ_ድጓው_ላይ።

#ቅዱስ_ኒቆዲሞስ፦ ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የነበረው ሰው ነው፡፡ የአይሁድ አለቆች #አምላካችንኢየሱስ_ክርስቶስን "ምልክት አሳየን" እያሉ ይፈታተኑት ነበር፡፡ #ጌታችን ስለ ሞቱና ትንሣኤው በምሳሌ እያስረዳ ቢያስተምራቸውም እነርሱ ግን አልገባቸውም ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ #ጌታችን በተአምራቱ የታመሙትን ሲፈውስ "ሕጋችን ተሻረ" ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ዅሉ ተአምራትና ትምህርት የአይሁድ አለቆች #ክርስቶስን ለመክሰስ በሚፈልጉበት ወቅት ከአይሁድ አለቆች አንዱ ኒቆዲሞስ በቀን እንዳያደርገው አይሁድን ቢፈራ፣ አንድም ጊዜ ባያደርሰው እንደ ባልንጀሮቹ #ክርስቶስን ሳይቃወም በሌሊት ወደ #ጌታችን ዘንድ እየሔደ ወንጌልን ይማር ነበር፡፡

#አምላካችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በነፍስ የታመሙትን በቃሉ፣ በሥጋ የታመሙትን በተአምራቱ ሲፈውስ ኒቆዲሞስ ሰምቶ፣ ተመልክቶ በመምህርነቱ ሳይኮራ አለቅነቱን መመኪያ ሳያደርግ በልቦናው የተሳለውን እውነትን የመፈለግ ስሜት አንግቦ ከ #ጌታው፣ ከመምህሩ ከ #ክርስቶስ ዘንድ በሌሊት ይገሰግስ ነበር (ዮሐ. ፫፥፩)፡፡ ምስክርነቱንም እንዲህ ሲል መስጠት ጀመረ፤ "መምህር ልታስተምር ከ #እግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፡፡ #እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከኾነ በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል የለምና" (ዮሐ. ፱፥፳፬፤ ሐዋ. ፲፥፴፰)፡፡

ይህን ምስክርነቱን በሚሰጥበት ጊዜም ጎዶሎን የሚሞላ፤ አላዋቂነት በአዋቂነት የሚለውጥ፤ ከምድራዊ ዕውቀት ወደ ሰማያዊው ምሥጢር የሚያሸጋግር አምላክ "ዳግመኛ ያልተወለደ የ #እግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም"። በማለት የአይሁድ መምህር ለኾነው ኒቆዲሞስ ቢያስተምረው ምሥጢሩ አልተገለጠለትም ነበርና "ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?" በማለት ጥያቄ አቅርቧል (ዮሐ. ፫፥፮፤ ፩ኛጴጥ. ፩፥፳፫)፡፡ "እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከ #መንፈስ_ቅዱስ ያልተወለደ ወደ #እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስነውና"። (ኤፌ. ፭፥፳፮) በማለት #አምላካችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ ቢያስረዳውም ምሥጢሩ ከአቅሙ በላይ ስለ ኾነበት እንደምን ይቻላል? በማለት ጠይቋል፡፡

አበ ብዙኃን አብርሃም ከአምላኩ ሞገስን አግኝቶ የሰዶምና ገሞራ ጥፋት እንዳይደርስ ለመማለድ ከ #እግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር እንደ ነበረ፤ ኒቆዲሞስም አላዋቂነቱን አምኖ ያልገባውን ምሥጢር ከአምላኩ በጠየቀ ጊዜ #ኢየሱስ_ክርስቶስም፡- "አንተ የእስራኤል መምህራቸው ኾነህ ሳለ ይህን ነገር አታውቅምን? በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁ በሰማይ ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይየወጣ የለም … ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰውልጅ እንዲሁ ይሰቀላል፡፡ ያመነበት ዅሉ ለዘለዓለም ሕያው ኾኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፋ አይደለም ..." እያለ ሰው በመብል ምክንያት የአምላኩን ትእዛዝ አፍርሶ ከ #እግዚአብሔር ቢለይም የሰው ልጅ ያጣውን ልጅነት ለመመለስ፣ ስመ ክርስትናን፣ ሀብተ ወልድን ለመስጠት #ጌታችን መምጣቱን አስረዳው (ዮሐ. ፫፥፲፬)፡፡ ይህን የ #ክርስቶስን የማዳን ሥራና በሥጋ መገለጥም "ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዐመፃ በላዕሌየ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው፤ ልቤን ፈተንኸው፡፡ በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንከኝም፡፡ ምንም አላገኘህብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው" (መዝ. ፲፮፥፫) በማለት ቅዱስ ዳዊት ከኒቆዲሞስ ሕይወት ጋር በማዛመድ አመሥጥሮታል፡፡

በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምሥጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ቀድሞ በአደባባይ ሔዶ መማርን ይፈራ እንዳልነበረ ምሥጢሩ ሲገለጽለት ግን አይሁድ #ጌታችንን በሰቀሉት ዕለት ፍርኃት ርቆለት ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ፡፡ "ወአልቦ ፍርኃት ውስተ ተፋቅሮትነ፤ ፍጹም ፍቅር ፍርኃትን አውጥቶ ይጥላል" ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፯፥፶፰፤ ፩ኛዮሐ. ፬፥፲፰)፡፡

                                
#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

#ድምፀ_ተዋህዶ

✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Orthodox Tewahdo new
" #ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ..."
                                   
     #መዝ 8፣2
_

" የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።"
                                  
#ማቴ 21፣9

#ሆሣዕና_በአርያም
#ሆሣዕና_በአርያም
#ሆሣዕና_በአርያም

#ሆሳህና በአርያም ለወልደ ዳዊት

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

#ሰላምሽ_ዛሬ_ነው

ሰላምሽ ዛሬ ነው እየሩሳሌም
ወደአንች መጥቷልና አምላክ ዘላአለም/2/ 

ሆሣእና በአርያም እያሉ ዘመሩ 
ሕፃናት በኢየሩሳሌም 

አንቺ ቤተልሄም የዳዊት ከተማ
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2 /

ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት
መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒት /2 /

የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/2/

✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Orthodox Tewahdo new
" #ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ..."
                                   
     #መዝ 8፣2
_

" የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።"
                                  
#ማቴ 21፣9

#ሆሣዕና_በአርያም
#ሆሣዕና_በአርያም
#ሆሣዕና_በአርያም

#ሆሳህና በአርያም ለወልደ ዳዊት

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

#ሰላምሽ_ዛሬ_ነው

ሰላምሽ ዛሬ ነው እየሩሳሌም
ወደአንች መጥቷልና አምላክ ዘላአለም/2/ 

ሆሣእና በአርያም እያሉ ዘመሩ 
ሕፃናት በኢየሩሳሌም 

አንቺ ቤተልሄም የዳዊት ከተማ
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2 /

ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት
መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒት /2 /

የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/2/ 

✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Orthodox Tewahdo new
ማክሰኞ


የጥያቄ ቀን ይባላል፦
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

የትምህርት ቀን ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

✅ድምፀ ተዋህዶ
Forwarded from Orthodox Tewahdo new (Hab ዘ ልደታ)
​​​​​​በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸሙ ሥርዓቶች እንመልከት

1, ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።

2, ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።

በእነዚህም ሰዓታት የጌታችንን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።

3, ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም ይኸውም ቆሎ ዳቦ ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

4, አለመሳሳም :-
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ሾለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13  ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29

5. አክፍሎት :-
እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።

6, ጉልባን :-
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።

7, ጥብጠባ :-
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።

8, ቄጠማ :-
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።
Forwarded from Orthodox Tewahdo new
“ወእምግርማሁ ተሀውኩ ወኰኑ ከመ አብድንት እለ የአቅቡ መቃብረ [ እርሱን ከመፍራት የተነሣ መቃብሩን የሚጠብቁት ታወኩ እንደ በድንም ሆኑ] ” (ማቴ 28፥4)

🌿 ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤

                በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ 🌿

🌿 አሰሮ ለሰይጣን፤

                   አግዐዞ ለአዳም፤🌿

🌿ሠላም፤

                   እምይዕዜሰ፤ 🌿

🌿ኮነ፤

             ፍስሐ ወሠላም፡🌿



እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ !! ✝️🌿
Forwarded from Orthodox Tewahdo new
ብፁዕ አባታችን። ድንግል ማርያም ቤዛዊት አትባልም ብለው ድምዳሜ ሰጥተው ሲያስተምሩ ሰማሁ። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አይባልም ብለን ከምንደመድም እንዲህ ብንል አይሻልምን?

🥀እናታችን ድንግል ማርያምን ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም እንላታለን። ክርስቶስን ቤዛችን ስንለው በመስቀል ተሰቅሎ እኛን ስላዳነን ነው። ድንግል ማርያምን ቤዛዊት ስንላት ግን ቤዛኩሉ ክርስቶስን ስለወለደችልን ነው። ከእርሷ ተወልዶ ዓለምን አድኗልና ነው። ምክንያተ ድኂን ስለሆነች ነው። ልጇ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ ብሎ እንዳስተማረን እሱን ብርሃን እርሷን ደግሞ የብርሃን እናት እንላታለን። ልጇ አምላክ ስለሆነ እርሷ እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ትባላለች። አምላክን የወለደች የአምላክ እናት ማለት ነው። ቤዛዊት ናት ስንል በጸጋ እንደሆነ ልብ እናድርግ። ምናልባት በባሕርይው ቤዛ ሆኖ ያዳነን ክርስቶስ ብቻ ነው ለማለት ፈልገው ከሆነ መልካም ነው።

🥀ንስጥሮስን ክርስቶስ ላይ ያለው የምንታዌ (Dualism) እይታ ድንግል ማርያምን ወላዲተ ሰብእ ከማለት አደረሰው። ድንግል ማርያም የወለደችው ሰው የሆነ አምላክን አምላክ የሆነ ሰውን ነው እንጂ ዕሩቅ ብእሲ (ሰው ብቻን) አልወለደችም። ነገረ ክርስቶስን ከድንግል ማርያም በበለጠ የሚያውቀው ፍጡር የለም ። እርሷ ልጇን ይዛ ከሀገር ሀገር ተንከራታለች። በመስቀልም ጊዜ ከጽንዐ ፍቅሯ የተነሳ ከመስቀሉ ሼር አልቅሳለች። ድንግል ማርያምን እናከብራታለን፣ እናመሰግናታለን፣ እንሰግድላታለን። ነገር ግን ለእርሷ የምናቀርበው ስግደት እና ምስጋና የአክብሮት ስግደትና ምስጋና ነው እንጂ እንደ አምላክ የአምልኮ ስግደት አይደለም።  

🥀ድንግል ማርያም ዓለም ጣዖትን በማምለክ ጨለማ ውስጥ ሳለ ብርሃንን የወለደችልን እናታችን ናት። ድንግል ማርያም ዓለም ለሰይጣን በመገዛት ባርነት ውስጥ ሳለ በመስቀል ተሰቅሎ የእኛን ሞት ሞቶ ነጻነት የሚያጎናጽፍ ጌታን ወለደችልን። ዓለም ተርቦ ነበር። እሷ ግን የሕይወት እንጀራን ወለደችልን። ድንግል ማርያም የትሕትና እናት ናት። ምሥጢራዊም ናት።ማርያም ግን ይህንን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ነበር ተብሏል። እውነትን ይዛ ሳለ በሐሰተኞች ወደ ግብጽ እንድትሰደድ ሆነች።

የቤዛነትን ትርጉም ንገረን ላላችሁኝ እነሆ

ቤዛነት ምንድን ነው?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች በሰው ልጆች ምትክ ያደረገው ሥራ ቤዛነት ይባላል። ቤዛ በአገባቡ "ስለ" ነው። ምሥጢሩ ምትክነትን፣ መቤዠትን ይገልጻል። ቤዛ "ቤዘወ-አዳነ" ከሚለው ግሥ ሲወጣ መድኃኒት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። በሁለቱም ለክርስቶስ ቢነገር ያስኬዳል። መድኃኒታችንም ነውና። ቤዛ-ስለ በሚለው አገባብ ከተተረጎመ ስለእኛ በመስቀል ተሰቅሎ ማዳኑን ይነግረናል። ክርስቶስ ያደረገው ሥራ ሁሉ ስለእኛ ነው። በትርጓሜ በሐተታ በእንቲኣነ (ስለእኛ) እየተባለ የሚገለጸው እንደ ኃጥኣን ስቶ፣ እንደ ሰማዕታት ዕሴትን ሽቶ ያደረገው አለመሆኑን ለመግለጽ ነው።

ይህ ክርስቶስ ያደረገው የቤዛነት ሥራ የባሕርይ ሥራ ነው። ቅዱሳን ደግሞ አምላካቸው ክርስቶስን መስለው ስለሌላው ሰው ብለው የሚቀበሉት መከራ ቤዛነት ነው። ግን የጸጋ ቤዛነት ነው። "ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" የሚለው ቃል ሰዎችም በአቅማቸው አንዱ ለአንዱ ቤዛ መሆን እንዲችሉ የተነገረም ጭምር ነው። ግእዙ "አልቦ ዘየዐቢ ወይኄይስ እምዝ ፍቅር ከመ ብእሲ ዘይሜጡ ነፍሶ ቤዛ ነፍሰ ቢጹ" ይለዋል (ዮሐ.15፥13)። ቅዱሳን ክርስቶስን አብነት አድርገው ስለሌሎች ሰዎች ሲጸልዩ፣ ሲጾሙ፣ ሲሞቱ አይተናል። ጌታም የእነርሱን ፍቅር አይቶ ኃጥኣንን ሲምር በብዛት ተጽፏል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሐዲስ ኪዳን ላይ ስንገባ በሰፊው እንመለከተዋለን።

©በትረ ማርያም አበባው

#ድምፀ_ተዋህዶ
Forwarded from Orthodox Tewahdo new
ሰበር ዜና
ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶ የነበረው
የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው ታግዷል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሼር የሚሰሩ ኦርቶዶክሳውያን የሚዲያ ተቋማት በአንድ ማዕከል  እንዲያገለግሉ፣ የመረጃ ፍሰቱ ወጥነት ያለውና ተቋማዊ መሆን ይችል ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቶ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብረው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ ማከናወን የሚችሉበት ፈቃድ ከመምሪያው መሰጠቱ ይታወሳል።

ከእነዚህ የሚዲያ ተቋማት መካከልም የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን አንዱ ሆኖ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት "ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም።" በሚል ርእስ  የተላለፈው ትምህርትን ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያችን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን እንገልጻለን።

                ሚያዚያ ፲፭ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
                     አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ

          የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
                      ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

#ድምፀ_ተዋህዶ
#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ
Forwarded from Orthodox Tewahdo new (🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
      á‰Ľáá‹• አቡነ እንድርያስ      


▬▬▬▬▬▬   †    â–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Źâ–Ź

በእመቤታችን በቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ላይ ለተነገረው የጽርፈትና የስህተት ትምህርት የብፁዕነታቸው መልዕክት !


❝ ሳይማሩ ማስተማር ውድቀት ነው ! ❞

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Forwarded from Orthodox Tewahdo new (🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏)
ወደ ሀገር እንዲገቡ ተፈቀደ

ሲኖዶሱ መንግሥትን እንዲያናግሩ ፣ የወከላቸው የሲኖዶሱ አባላት ፣ ከመንግስት ጋር በተደረገው ስምምነት መሠረት  ሦስቱ  ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ( ዶ/ር )፣ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ (ዶ/ር) እና ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ  ፣ ወደ ሀገር እንዲገቡ የተፈቀደ ሲሆን ፣

ለሲኖዶሱ የስብሰባ ጥሪም እስከ ሰኞ ተጽፎ እንደሚደርሳቸው የመረጃ ምንጮቻችን አድርሰውናል ፣

ስለብፁዕ አቡነ ሉቃስ ግን ምን የተወሰነ ነገር አለመኖሩን እና እስካሁን በሲኖዶሱ ምዕልዓተ ጉባዔው ላይ እንዲሳተፉ ደብዳቤም እንዳልደረሳቸው የመረጃ ምንጮቻችን አድርሰውናል።

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Forwarded from Orthodox Tewahdo new (🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏)
"ገዳማት ወደ ቀደመ ክብራቸው እንዲመለሱ ገዳማውያኑ እና ሁላችንም ኃላፊነት አለብን!"፡-ብፁዕ አቡነ አብርሃም

ሥርዐተ መነኮሳት ለግብረ ትሩፋት በሚል መሪ ቃል የምክክር መርሐ ግብር ጠቅላይ ቤተ ክህነት የገዳማት መምሪያ አዘጋጅነት ለ3 ተከታታተይ ቀናት የሚቆይ መካሄድ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ በዛሬው ዕለት በጀመረው የምክክር በጉባኤው ከመላው ኢትዮጵያ የመጡ ገዳማውያን ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባሕርዳር እና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተዋል፡፡

ብፁዕነታቸው በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ወደ ቀደመ ክብራቸው እንዲመለሱ ገዳማውያኑ እንዲሁም ሁላችንም ኃላፊነት አለብን ያሉ ሲሆን ለእንግዶችም የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልክት አስተላልፈዋል፡፡

አክለውም ከዛሬ ጀምሮ በሚቀጥሉት ተከታታይ ቀናት  ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅሙ ሐሳቦች በገዳማውያኑ በኩል እንደሚነሳ ተስፋ አደርጋለው ሲሉ ተናግረዋል።

በተጀመረው ጉባኤ ላይ "ምንኩስና ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት አንጻር" በሚል ርእሰ ሊቃውንት በአባ ገብረ ኪዳን በመቅረብ ላይ ሲሆን በቀሪ ቀናት ውስጥ የተለያዩ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው የሚጠበቅ ይሆናል፡፡

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
✝እንኳን አደረሰነ!

☞ወርኀ ግንቦት ቡሩክ፤ አመ ፮፦

✝ርክበ ካህናት (በዓለ ጥብርያዶስ)
✝ተዝካረ በዓለ ልደታ ለእግዝእትነ ማርያም፥ ድንግል ወላዲተ አምላክ (እምነ ወትምክህተ ዘመድነ)
✝ወተዝካረ ሚጠታ ለድንግል (እምደብረ ቁስቋም)

✞ወበዓለ ቅዱሳን፦

✿መቃርዮስ ቀሲስ ጻድቅ ወክቡር (እስክንድርያዊ)
✿አሞን ጻድቅ ዘአበየ ሲመተ ጵጵስና (ወዘአጥረየ ግብረ ምንኩስና)
✿ይስሐቅ ሰማዕት (ዘሃገረ ዳፍራ)
✿በንደላዖን ሰማዕት (አቡሁ ለቅዱስ ኤስድሮስ)
✿ደናስዮስ ሰማዕት (ዘተከለለ በመጥባሕት)
✿ጴጥሮስ ጻድቅ (ዘወሎ)
✿ሰሎሜ ብጽዕት ወተሐራሚት (ዘደብረ ሊባኖስ)
✿ዲላጊ (ዳላዢ) ሰማዕት (ዘሃገረ እስና)
✿አርባዕ ደቂቃ (ሱርስ፥ ወኅርማን፥ ወያኑፋ፥ ወሰንጣንያ)
✿ኢያቄም ወሐና (ጻድቃን)

❖ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡


╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
➡️      @zkre_kdusan21⬅️                  
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/10/21 12:33:14
Back to Top
HTML Embed Code: