Telegram Web Link
Our journey with Let's Know Our Country Club began with laughter, culture, connection, and pride. From warm welcomes to vibrant conversations, the opening ceremony was more than just an event—it was the first page in a story we're writing together. Here's to unity, learning, and celebrating the beauty of our country.

be a member today and lets know our country together:
https://www.tg-me.com/+n7bTyG-8lfZhMDQ0
👏7👍1
Just 2 days to go until Culture Day — and we’ve got exciting news!

You can order your very own cultural outfit and be part of the vibrant celebration in style!

Whether it’s bold patterns, rich colors, or traditional elegance — we’ve got you covered.

To place your order, call: +251979199343
Let your culture shine, your roots speak, and your outfit tell a story.

If you have any question don't hesitate to ask [departments committee]

#CultureDay #3DaysLeft #WearYourHeritage #CelebrateInStyle
የዩኒቨርሲቲያችን የተማሪዎች ኅብረት ሥራ አስፈጻሚዎች እና የክፍል ተወካዮች በመቄዶንያ የአረጋውያንና ሕሙማን መርጃ ማዕከል ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል ።
በማዕከሉ ተማሪዎችን ተቀብለው ንግግር ያደረጉት የመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማዕከል ምክትል ፕሬዚዳንት ወጣት ራጁ እንደ ግቢ እየተደረጉ ያሉት የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻዎች ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጀምሮ ያሉት ቀና ትብብሮችንም ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች አርዓያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ወላጅ ከሚልክላቸው ላይ አንሥተው ከሚሰጡት የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም የሥጋ ሜኑን በሌላ ምግብ ማስቀየሩ መልካም እንደሆነ ጠቅሰው ከዚያ በዘለለ ግን ተማሪዎች ማታ ላይ በሰይፉ ሾው እና በመቄዶንያ ዩቲዩብ ቻናሎች የሚተላለፈውን የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ እንዲከታተሉ እንዲሁም ቻናሎቹን ላይክ ፣ ሼር እና ሰብስክራይብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል ።

በጉዞው ላይ የተሳተፉ ተማሪዎችም ቦታውን በአካል በማየታቸው እና የሚሠራውን የበጎ አድራጎት ሥራ እንዲሁም የተጀመሩ ፕሮጄክቶችን ካዩ በኋላ ለማዕከሉ አቅማቸው በፈቀደው ሁሉ ከቤተሰብ ፣ ጓደኛ እንዲሁም ከክፍል ተማሪዎች በማስተባበር የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻውን እንደሚቀላቀሉ ተናግረዋል ።

ሚያዝያ 01/ 2017ዓ/ም
👍15
📣 Culture Day Celebration Alert! 🎉
Get ready to experience the colors, sounds, and vibes of our rich and diverse heritage!

🗓 Date: Friday, April 11, 2025 G.C.
🕠 Time: Starting from 5:30 PM (Local Time)
📍 Location: In front of Block 10

What’s Happening?
Vibrant Photoshoot Sessions – Dress in your traditional best!
🎧 Electrifying Musical Performance with DJ – Dance into the moment!

Don't miss this epic evening filled with tradition, rhythm, and fun. Let’s celebrate culture the way it deserves to be – loud, proud, and unforgettable!

Help us build the ultimate Culture Day Playlist 🎧

Drop your favorite bangers, cultural hits, or party anthems:
👉LINK👈

Come slay for the camera & vibe to the beat!
Everyone’s invited!
Let’s make Culture Day unforgettable — together!
👍2
https://www.youtube.com/@seifufantahun

https://www.youtube.com/@Mekedonia

ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው !


#በጎነት
#ቸርነት
#ለጋስነት
#በጎ_አድራጎት
#መረዳዳት
#የወደቁትን_ማንሣት
#ሰብአዊነት

እንደ ግቢ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና ሕሙማን መርጃ ማእከል የሚደረገውን የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ይቀላቀሉ ። እኛ እንደ ቀላል የምናያት ነገር ተሰባስባ ትልቅ ቀዳዳን ትሞላለች እና ለመስጠት አናቅማማ ።
ቢያንስ 3000 ተማሪ 100 ብር ቢለግስኳ 300,000 ብር ድጋፍ ማድረግ እንችል ይሆናል ።

እንደሚታወቀው ካፌ ተጠቃሚ ተማሪዎች የሦስት ሳምንት ዜርፎር በሌላ ምግብ እንዲቀየር እና ገቢው ለመቄዶንያ እንዲሆን ፈርመዋል ።

ነን ካፌ የሆናችሁ ደግሞ በዛሬው ዕለት የነን ካፌ ክፍያ ተፈጽሞላችኋል እናም ካላችሁ ቢያንስ 100 ብር ብትልኩ ትልቅ ድጋፍ ነው ። ከ 2700 በላይ ነን ካፌ ተማሪ ስላለን ኹሉም እጁን መዘርጋት ከቻለ 270,000 ብር ከዚህ ብቻ ማግኘት ይቻላል ።


CBE : 1000684467968 (Yosetena and Kidus and Naomiy)

እስካሁን ከ 40,000 ብር በላይ ተሰባስቧል ።

የምትረዱት በገንዘብ ብቻ ሳይሆን ቻናሎቻቸውን ሰብስክራይብ ፣ ላይክ እና ሼር በማድረግ እንዲሁም ፕሮግራሙን በቀጥ በመከታተልም ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረግ ትችላላችሁ ።

=>
https://www.youtube.com/@seifufantahun

=>
https://www.youtube.com/@Mekedonia
ስክሪንሹት
@aastu_supo ይላኩልን ለምታደርጉት አስተዋጽኦ በአረጋውያኑ ስም እጅግ አድርገን እናመሰግናለን ።
👍16
💡ለ2017 ተመራቂ ተማሪዎች

📣 የዚህ ዓመት ተመራቂ ተማሪዎች ረቡዕ፣ ሚያዝያ 8/2017 ዓ.ም ለሚካሄደው የ4ተኛ ዓመት Engineering እና 3ተኛ ዓመት Applied Science ዲፓርትመንት ተማሪዎች  internship orientation (ገለጻ) ለመስጠት ፈቃደኛ የሆናችሁ ይህንን ፎርም እድትሞሉ እናሳስባለን።

👉👉👉👉 ፎርም 👈👈👈👈👈

ተሳታፊ ለምትሆኑ የእውቅና ሰርተፊኬት የምንሰጥ ይሆናል።

📌የሚፈለገው ተማሪ ትንሽ ስለሆነ ቀድማችሁ ለምትሞሉ ቅድሚያ ይሰጣል።

ለተጨማሪ መረጃ : 0910631120 መደወል ትችላላችሁ።

🖇 LinkedIn
📨 Telegram

🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓
                Career Club
💼💼💼💼💼💼💼💼💼💼💼💼
👍42
#የኢትዮጵያልጆች👏

ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና የሁዋዌ " ቴክፎርጉድ ግሎባል " ውድድርን #አንደኛ በመሆን አሸነፉ።

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሁዋዌ ሲድስ ፎር  ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ ግሎባል ውድድርን አንደኛ በመሆን አሸንፈዋል።

ውድድሩ ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የቆየ ሲሆን በቻይና ቤጂንግ እና ሼንዘን የሚገኙ የቴክኖሎጂ ማዕከሎችን ጉብኝትና የተግባር ስልጠናዎችን ካካተተው ዝግጅት ጋር የተካሄደ ነው።

በስድስት ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን ተማሪዎቹን ፦
➡️ ከአዲስ አበባ፣
➡️ ከሐረማያ፣
➡️ ከጅማ፣
➡️ ከወልቂጤ 
➡️ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (AASTU) ዩኒቨርስቲዎች ነው ያሰባሰበው።

ቡድኑ በውድድሩ ከሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካ፤ አርጀንቲና አየርላንድ፣ ማላዊ፣ ቬትናም፣ አረብ ኤምሬትስና ሌሎችን ጨምሮ ከዓለም ዙሪያ ከተውጣጡ 12 ልዩ ቡድኖች ጋር ተወዳድሯል።

የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ግሎባል አምባሳደር የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ አሲያ ከሊፋም በዝግጅቱ በእንግድነት ተገኝታለች።

ተማሪዎቹ በምን ፕሮጀክት አሸነፉ ?

ተማሪዎቹ የእንስሳትን ህመሞች አስቀድሞ ለመለየት በተዘጋጀውና በአርተፊሻል አስተውሎት (AI) በጎለበተው ኤርሊ ቬት (EarlyVet) በተሰኘው ፕሮጀክታቸው ነው የተወዳደሩት። በዚህም ትኩረት ለመሳብ ችለዋል።

ይህ የፈጠራ ፕሮጀክት ከተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) በተለይም ግብ 2 " ዜሮ ርሃብ " እና ግብ 15 " ህይወት በምድር " ከሚለው ጋር የተጣጣመ መሆኑና በግብርና እና በእንስሳት ጤና ላይ ያሉ ወሳኝ ተግዳሮቶችን ይፈታል ተብሎ እንደሚታመን በውድድሩ ተብራርቷል።

የሁዋዌ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሚስተር ሊሚንግ ዬ ምን አሉ ?

ዳይሬክቱ ፥ በቡድኑ ስኬት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው " ድሉ የኢትዮጵያውያን ወጣቶች ልዩ ችሎታ እና ፈጠራ የታየበት ነው " ብለዋል።

መጪው ትውልድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመጣው የቴክኖሎጂ ገጽታ ውስጥ እንዲበለጽግ በሚያስፈልገውን ድጋፍ እና እድሎች ማመቻቸቱን ለማስቀጠል ሁዋዌ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ቡድኑ ለዓለም አቀፋዊ ውድድር እድል ያገኘው  በግንቦት 2016 ዓ.ም በኤሳውራ ሞሮኮ በተካሄደው የክፍለ አህጉራዊ የቴክፎርጉድ (Tech4Good) ውድድር ወቅት ከ17 የአፍሪካ ሀገራት ከተውጣጡ 28 ቡድኖች ጋር ተወዳድሮ አንደኛ በመውጣቱ ነው።

መረጃው ከሁዋዌ ኢትዮጵያ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
35👍12👏8
2025/07/09 18:19:17
Back to Top
HTML Embed Code: