#ታላቅ_መውሊድ_በቀጨኔ
ጥቅምት 11 ከመድሀኒአለም ቤ/ን ጀርባ በሚገኘው በ04 ወረዳ ወጣት ማዕከል አዳራሽ!!
ሁላችሁም ተጠርታችሆል መገኘት ብቻ!! ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ!

ያንቆለጳጳስናት የተቀኘንላት:
ግጥም ገጥመን የደረስንላት:
የመዲናዋ ብለን የሰይመናት:
ሙገሳ የቸርናት የተፈተንባት:
ከራስ በላይ ቦታ የሰጠናት:
በአፋችን የቀረው የመሐላችን ቃል:
ከልባችን ኪዳን ላይኖር ይሰረዛል።
መጅኑኑ የተማረከው በውበት በሀብት በስሜት አልነበረም። ይልቁንስ ሁሉንም ነገር ሰብስቦ በያዘው ፍቅር ነበር። ላንተ ከምትወደው ሰው በላይ ሀብታም ከምታፈቅረው የበለጠ ቆንጆ የለም። ያ ከጎደለህ የምትወደውን ሰው ክፍተት ድክመት ብቻ የምታይ ከሆነ ፍቅርህን ፈትሸው: ምክንያቱም አፍቃሪ ጓዶሎውን ሞልቷ መጥፎውን አሳምሮ ነውና ሚመለከተው ብቻ ተውት...... ፍቅር ጉድ ነው።
@abduftsemier

#ለዛሬ_አትኖርም
ብዙ ሰዎች ዛሬን ኑር እንጂ ስለ ነገ ወደፊት አትጨነቅ ሲሉ ይሰማል። ይሄ ለኔ የሞኞች ንግግር ብቻ ነው። ምክንያቱም በመሰረቱ የሰው ልጅ ዱንያ ላይ ሰርቶ ለነገ አኺራ እንዲኖር ነው የታዘዘው። ሚኖረው እኳ ለዛሬ አይደለም ለነገ ነው። ዛሬማ ዱንያ ጠፊ ነች በጥሩ እንጂ በሌላ መባከን የለባትም ስለዚህ ዛሬ ምትለፋው ነገህ እንዲያምር ነው። ስራም ስትሰራ ነገ እሞታለው ስለዚህ ዛሬ በልቼ ልጠጣ ያለኝን ልጨርስ ማለት የለብህም። (ስትሰሩ እሞታለው ብላችሁ እያሰባችሁ አይሁን) ሰዐወ። ዛሬ ምትለፋው ለዛሬ ለመብላት ለመጠጣት ለመልበስ ለማማር ብቻ አይደለም ነገህንም ለማሳመር ነው። ስለዚህ ዛሬ ያለህው አላህን ለማመስገን ነው። ሁሌም ተገንዘብ የምትኖረው ለነገ ነው።
ዛሬ ለመስራት ነገ ለመኖር!!
ሀሳብ ማጋራት ይቻላል...
@abdudtsemier
@absuftsemier

#አለመተዋወቅ ......
ታላቁ ሼኽ አሊምና የአረብኛ ስነፅሁፍ ሊቅ ዓሊይ አን-ጠንጣዊ አንዴ የስነፅሁፍ ኮርስ ለመስጠት ወደ ኢራቅ ይሄዳሉ። በንጋታው የባግዳድን መንገዶች ለመጎብኘት ብዙ ተጉዘው ከነ ላባቸው ወደ ዩኒቨርስቲው ገቡ።
አንድ አስተማሪ"ዛሬ ታላቁ አሊምና የስነፅሁፍ ሰው ዓሊይ-ጠንጣዊ የሚመጡበት ቀን ስለሆነ ደስ ሊላቹ ይገባል።"እያለ እያስተዋወቃቸው እሳቸው ወደ ክፍል ሲገቡ ተገጣጠሙ።
አስተማሪውም ተናዶ "አንተ አህያ የሆንክ ተማሪ የት ሄደህ ነው ያረፈድከው" በማለት ጮህባቸው። እሳቸውም ይቅርታ ጠየቁ ከዛም አስተማሪው ለመሆኑ ማን ነው ስምህ አላቸው። ዓሊይ አን-ጠንጣዊ ሲሉት፣ ሰውየው ራሱን መቆጣጠር አልቻለም። እግራቸው ላይ ተደፍቶ ይቅርታ ጠየቀ። እሳቸው ምንም ችግር እንደሌለው ነግረው እንዲህ መከሩት...... "እውቀትህ መተናነስን ካላስተማረህ መሀይምነት ይሆንብሀል። ምንም ብትተልቅ ራስህን ለትንሹም ለትልቁም ሁሌም ዝቅ አድርግ።"
*አዋቂ ራሱን ስላሳነሰ እና ዝቅ ስላደረገ መሀይም ነው ብለህ አታስብ የበለጠ አክብረው እንጂ።

የአማን መስጂድ ወጣት ጀመዐ! በመስጂዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቅ መውሊድ እያዘጋጁ ይገኛል ለማገዝ አጅር ለመቆደስ የፈለገ inbox ከች ይበል @ABDU_EMRE ለመውሊድ የወጣ እውቀት ጉልበት ገንዘብ በዱንያም በአኺራም መከታ ነው። ሚወደሱበት አሽረፈል ኸልቅ ናቸውና።
@abduftsemier
@abduftsemier
@abduftsemier
@abduftsemier
#የልብን_ማን_ያውቃል?
"እነዚህ እንቅልፋሞች! ተኝተው ከሚያንኮራፉ፣ ተነስተው አይሰግዱም!" ኢብን ረጀብ ካፋቸው አመለጣቸው ይሄን የሰሙ አባት ቆጣ ብለው "ልጄ ሆይ ይሄ ቃል ከአፍህ ከሚወጣ ዘላለሙን ለይል ባትነሳ ይሻልህ ነበርኮ!" በማለት ገለፁ።
መጠጡን እየቸለሰ ሁሌም እየመጣ የሚገረፈውን ሰሃባ ታሪክ አልሰማህም በአንዱ ቀን መቶ ሲገረፍ ሶሃቦቹ "ምን አይነት ማያፍር ፍጥረት ነው!" በማለት አንጓጠጡት፣ አዛኙ ነብይም እየተንደረደሩ ፊታቸው ቀልቶና ተለውጦ መጡ፣ እንዲህም መሰከሩለት "ተዎት! እሱኮ አላህንና መልክተኛውን ይወዳል!"
*በነገራችን ላይ ኢብሊስም ሙእሚን ነበር ያንተም መጨረሻ አይታወቅምና ብዙ አትመፃደቅ።

#ምን_ነክቶኝ_ይሆን?
እንጃ ምን እንደሆንኩ ሰሞኑን ጀምሮ
ይሻላል ብዬ እንጂ ማመስገን ከመኖር አማሮ
እንጃ ግን ሰሞኑን ልቤ በጣም ሰግቷል
የሆነ አዲስ ነገር ዙሪያዬ ተፈጥሯል
ግን አሁንም አለው በሰልፍ እኖራለው
በቃ በቃ ዝም ብዬ ዝም ብዬ እኖራለው
ጥቅም ይሰጣል ወይ በሰልፍ መኖሬ
ግን አሁንም አለው
ዝም ብዬ እኖራለው
ደሞ ደሞ በዚ በላይ
ምን አንደሆንኩ እንኳን ችግሬን አላውቀው
ግን አሁንም አለው ዝም በዬ እኖራለው
ብቻ......
የሰራሁት ፍርስ የያዝኩትን ብትን
የረገጥኩት ክድት ያሰብኩት ብትንትን
እራሴን መሆን ግን አቅቶኛል አሁን
ምን ነክቶኝ ይሆን ምን ተፈጥሮስ ይሆን
ግን ብቻ ግን ደሞ እባክህ ኢላሂ
ውስጤን ሰላም አርገው
እጆቼን ዘርግቼ አንገቴን አቅንቼ
አልኩት ብቻ ሰላም አርገው
ጌትዬ መለሰ: -
እንደዚ የሆንከው ሰሞኑን ምን ነካህ
ተስፋ የቆረጥከው መሬት አቀርቀርህ
ቀና በል ወደኔ ምንድን ነው የፈለከው
በርግጥ አውቀዋልው ምን እንደገጠምህ
ግን አስኪ አሳየኝ እምነትህ የት አለ?
*ምን ተብሎ ይመለሳል ራስ መፈተሽ ነው ኢማናችን የታል?
*ዙል ጀላሊ ወልኢክራም(የክብርና የልግስና ጌታ) ፈተናውን ያለፈ ችግርን የተቋቋመ ክብርና ልግስናን ያገኛል። ለምን ፈተና ችግር አስፈለገ? እውነተኛ ባሪያውን ለይቷ ለማወቅ በችግር ጊዜ ተስፋ ሳይቆርጥ አላህ ካለ ያኔ በእሳት የተፈተና ወርቅ ሰው ጋር ውድ እንደሆነው ይሄም ሰውዬ አላህ ጋር ውድ ይሆናል።

#ካላሰቡት_የሚረዝቅ!
ሰይዲና አሊ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በጣም ለጋስ ነበሩ። ሲሰጡ ገደብ የላቸውም ነበር። አንድ ቀን ሚስቱና ልጆቹ በረሃብ ሲያለቅሱ አገኛቸው።ለሁለት ቀን ምንም አልበሉም ነበር ሰይዲና ፋጢማ (ረዐ) እናቷ ስድስት ሳንቲም ነበራት። ኸዲጃ (ረዐ) ለቀብርዋ እያጠራቀመች የነበረ ሳንቲም ነው።
ለሰይዲና አሊ (ረዐ) ሰጠቻቸውና ከገበያ ምግብ እንዲያመጣላቸው ጠየቀችው። ዓልይ (ረዐ) ወደ ገበያው ሲገቡ አንድ አይሁዳዊ አንድን ሙስሊም በጉሮሮ ይዞ እንደሚገድለው እየዛተ ነበር። ሙስሊሙ ከአይሁዳዊው የተበደረውን እዳ አልከፈለም ሙስሊሙ ብዙ ልጆች ነበሩት ማን ይንከባከባቸው? ሙስሊሙ የተበደረው ገንዘብ 6 ሳንቲም ነበር። ዓልይ (ረዐ) ለአይሁዳዊው ሰጡት፡ ሙስሊሙም ከዕዳ ነፃ መሆኑ ደስተኛ አደረገው፡ አይሁዱም ገንዘቡ ስለተመለሰለት ደስተኛ ነበር፡ ያልተደሰተው ዓልይ (ረዐ) ብቻ ነው። ለልጆቹ ምግብ የሚገዛበት ምንም ገንዘብ አልነበረውም።ወደ ቤት ሄዶ ለሰይዲና ፋጢማ (ረዐ) ነገራት። እሷም "ምንም አይደል ጥሩ አድርገሀል ልጆቹን አስተኝቻቸዋለሁ" አለችው። ሰይዲና አሊ (ረዐ) የበለጠ አዘኑ። "ሰይዲና ፋጢማ (ረዐ) በጣም ጥሩ ትሁት ሴት ነች" ሲል አሰበ። ማንኛውም ሚስት ብትሆን በጣም ትናደድ ነበር"። ሰይዲ አሊ ረዐ በጣም በሚያዝኑበት ወይም በተራቡ ቁጥር ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፊት መሄድ ልማዳቸው ነበር። ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቤት በሚወስደው መንገድ ላይ ዓልይ (ረዐ) አንድ በደዊን (ገጠሬ) ሰው የሰባ ግመል በገመድ ሲጎትት አዩ። ይህ ግመል በጣም አመጸኛ ነው” አሉ አሊይ፡ “ምን ትሰጠኛለህ ይህን ብሰጥህ?” አለው ገጠሬው። ሰይዲና አሊ (ረ.ዐ) በማግስቱ ለገጠሬው አንድ መቶ ሳንቲም እንደሚከፍለው ነገረው። ገጠሬውም ተስማምቷ ሰጣቸው ሰይድና አሊ (ረ.ዐ) ግመሉን ወስደው ትንሽ መንገድ እንደሄዱ ሌላ ገጠሬ አገኙና ግመሉን በሦስት መቶ ሳንቲሞችን ልግዛህ አላቸው። ሰይዲና አሊ(ረ.ዐ) ግመሉን ሸጠው የመጀመሪያውን የገጠሬውን መቶ ሳንቲም ከፈሉት። ከዚያም ለቤተሰቡ ምግብ ከገበያ ገዛ። ልጆቹ በጣም ተደስተው ነበር።
ሰይዲና አሊ (ረዐ) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለማግኘት ሄዱ ነብዩም ታሪኩን ትነግረኝ ወይስ ልንገርህ? አሉ ሰይዲና አሊ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እርሷ ይናገሩ ያረሱለላህ (ሰ.ዐ.ወ)። ከዚያም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- “የመጀመሪያው ገጠሬ ግመሉን የሸጠልህ ጅብሪል (ዐ.ሰ) ሲሆን ሁለተኛው ግመሉን የገዛው ሚካኢል (ዐ.ሰ) ነው። ግመሉ ከጀነት መንጋ ነበር:: የሙስሊሙን ባለዕዳ ነፃ ለማውጣት በሰጠህው ስድስት ሳንቲሞች አላህ ሃምሳ እጥፍ አድርጎ እንደከፈለው ነገሩት። በትንሳኤ ቀን ምን አይነት ስጦታዎች፣ ምን አይነት ሽልማቶች እንደሚሰጡ አታውቅም።"
*አላህ ካላሰብከው ቦታ መረዘቅ የሚችል: የወንድምህን ሀጃ ስትሞላ ላንተ ሀጃ እርሱ የሚበቃልህ ጌታ ነው።

#እድለኛው_ዑማ
አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ ሰው ሁሉ ሰላቱን "አህመድ" በሚል ስያሜ እንዲሰግዱ አዘዘ። ማለትም:
ቂያም ከአሊፍ (ا) ፊደል ጋር: ሩኩዕ (ከወገብ ማጎንበስ) ሀ (ح) ፊደል ጋር: ስጁድ (መውደቅ) ሚም (م) ፊደል ጋር: በእግሮቹ መቀመጥ ዳል (د) ፊደል ጋር ይመሳሰላል።
አላህ ነብዩን በብዙ መንገድ ነው ያላቃቸው። ኢማሙ ሱዩጢ እንዲህ ይላሉ መላኢኮች ለነብዩላህ አደም ከሰገዱላቸው በላይ ሰለዋት ይበልጣል። ምክንያቱም: 1ኛ) ለአደም የሰገዱት መላይኮች ናቸው: ሰለዋት ግን አላህ ጀምሯ ነው ያዘዘው። 2ኛ) ለአደም የሰገዱት አንድ ጊዜ ነው: ሰለዋት ግን አላህ የሚያወርደው የማይቋርጥ ዘላለማዊ ነው።
*አልሀምዱሊላህ ዑመት አድርጎ ላከበረን።
*አላሁመ ሷሊ አላ ሀቢቢና ሙሀመድ!

#ሰላተል_ኩሱፍ የጨረቃ ግርዶሽ ሰላት
በዚህ ወቅት ሁለት ረከዐ ይሰገዳል። አንደኛው - ሁለት ረክዐ እንደማንኛውም ረክዐተይን ሰላት ። ኡሰሊ ሱነተ ሰላተል ኩሱፍ ብሎ መስገድ ይቻላል።
ሁለተኛው - በሁለት ቂያምና በሁለት ሩኩዕ ይሰገዳል ።
- ነይቶ በተክቢር ወደ ሰላት ይገባል። መክፈቻ ዱዐውን ይላል
- ፋቲሀና ሱራ ይቀራል ( ረጅም ሱራ ቢሆን ይመረጣል )
- ሩኩዕ ይወርዳል
- ከሩኩዕ ይነሳል፤ ረበና ለከል ሀምድ ብሎ ዱዐውን ይላል
- ከዛ ድጋሚ ፋቲሀና ሱራ ይቀራል ( ከመጀመርያው ሱራ አነስ ያለ ቢሆን ይመረጣል )
- ሩኩዕ ይወርዳል
- ከሩኩዕ ይነሳል
- ረበና ለከል ሀምድ ብሎ የኢዕቲዳል ዱዐ ይላል
- ሱጁድ ይወርዳል ፤ ይነሳል፤ ሁለተኛ ሱጁድ ያደርጋል
- ከዛ ተነስቶ ሁለተኛውንም ረክዐ በእንደዚህ አይነት ይጨርሳል።

“رباهُ
وجهت وجهي نحو بابكَ راجياً
والحالُ لا يخفى وأنت عظيمُ”
اللهم صلي وسلم وبارك عليه ❤️📿
"አምላኬ ሆይ በተስፋ ፊቴን ወደ ደጅህ አዞርኩ...."
የአላህ እዝነትንና ሰላም በሙሀመድ ላይ ይሁን።
*በሀጃ አሚና አዲል የተዘጋጀውን የነብዩላህ አደም (ዐሰ) ያልተሰሙ ታሪኮችን ተርጉመን ስለጨርሰን ከነገ ጀምሮ እናቀርባለን።

#አባታችን_አደም 1⃣
ይህ ዘገባ ከካአብ አል-አክበር አቡ ኢስሃቅ የተላለፈ ነው.
ካብ የአይሁድ ሊቃውንት ነበርና በብፁህ ነብዩ ሰዐወ ዘመን በየመን አገር ይኖር ነበር። በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ዘመን የእውነተኛ እምነትን ክብር አልተቀበለም ፣ ግን ከዚያ በኋላ በአቡበክር አስ-ሲዲቅ ኸሊፋ ወይም በሌሎች ዘገባዎች መሠረት ፣ በዑመር ጊዜ እስልምናን ተቀብሏል። የተከበሩ የነብዩ ሰሀቦች ባስተላለፉት ሀዲሥ ላይም ተጠቅሷል።
ከነዚህ ሶሓቦች መካከል አንዱ ሰሂፍ ብን ዑመር አል-አንሷሪ ከአባቱ አምር እንደ ሰማው ይናገራል፡-
ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) በህይወት በነበሩበት ጊዜ ከካዕብ ጋር ተዋወቅሁ እና በብዙ ጉባኤያት እገኘው ነበር።
የቅዱስ ነቢይ ማኅበር, እና ገና እሱን ሳያገኛቸው, እርሱ በእርግጥ የነቢያት ማኅተም መሆኑን አረጋግጧል; በማለት በተደጋጋሚ ይገልፃል።
አንድ ቀን ይህ የቅዱስ ነቢይ የመጨረሻ አመት እንደሚሆን ነግሮናል እና እሱ በሰዓቱ መሄድ ፈልጎ ነበር። ዝግጅቱን አፋጠነ እና ጉዞውን ጀመረ።ነገር ግን በዛች ሌሊት በተደጋጋሚ ሲገባ እና ሲወጣ ታየ፣ የሌሊቱን ሰማይ ትኩር ብሎ እያየ አለቀሰ።
ጎህ ሲቀድም አናግሬው፡- “ አቡ ይስሃቅ፣ ምን ነካህ? ሰማዩን እያየህ እያለቀስክ ነው? ምንድን የተደበቀ ነገር አለን? ወደ እኔ ዞሮ እንዲህ ሲል መለሰ፡- “በዚህች ሌሊት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በመዲና አል-ሙነወራ ወደ ቀጣዩ አለም ተሻግረው ነበር።
ወደ ቀጣዩ. ሰማያትን ተመለከትኩ እና እሱን ለመቀበል የሰማይ ደጆች ተከፍተው አየሁ፣ እና ሁሉም መልአክ በዝግጅቱ ላይ ቆመው በምስጋና እና በክብር መምጣቱን ሲያከብሩ አየሁ።
በምድርም ሁሉ ላይ የተባረከ አካላቸው ከሚቀበርበት ስፍራ የተሻለ ስፍራ የለም; በዚህ ዓለም ውስጥ ካሉት ስፍራዎች ሁሉ የሚመረጥ ነው።
በተናገረው ነገር በጣም ደነገጥኩ ወደ መዲናም እንደደረስን ነብዩ ሰዐወ ከዚህች አለም ወደ ዘላለምነት የተጓዙት በዚያች ለሊት ነበር። ነገር ግን አቡበክር ሲዲቅን አላገኘሁም ከሳቸው ሞት ቡሀላ ኸሊፋውን ዑመር ረዐ ለማየት በሄድኩ ጊዜ አገኘሁትና ሰላምታ ሰጠሁት ተመለከተኝና አወቀኝና በክብርም ተቀበለኝ። ከዚያም ለኸሊፋውና ለተሰበሰቡት ከካብ አክበር የታዘብኩትን ሁሉ ነገርኳቸው።
ጠንቋይ መሆን አለበት እያሉ በቦታው የነበሩት ተደነቁ። በወርቃማ መቆለፊያ የታሸገ ነጭ እንቁ የሚመስል ትንሽ ሳጥን ከፈተ በአረንጓዴ ሀር እጥፎች ውስጥ የታጠፈ ነገር አወጣ። ይህ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? በማለት ጠየቁ አናውቅም ሲሉ መለሱ። እርሱም "በኦሪት (ተውራት)ና ኢንጅል (ብሉይና ሐዲሳት) መፃሀፍት የተጠቀለለ ሲሆን በውስጡም የነብዩ መምጣት ምልክቶች ሁሉን ቻይ በሆነው አላህ የተቀመጡበት ነው።
ከዚያም አላሁ አክበር ሲሉ ሰሀባው ሁላ ጮኸ አቡ ይስሀቅ ሆይ! አልሀምዱሊላህ አላህ ይዘንልህ! የፍጥረት መጀመሪያ ነብዩ ሲፈጠሩ ንገረን! ሲሉ ተማፀኑ።
እንዲህ ሲል ተናገረ: አላህ ከአደም ልጆች ሁሉ የላቀውን ሊፈጥር ባሰበ ጊዜ ታማኝ የሆነውን መልአክ ጅብሪልን በምድር ካሉ ንፁህና የላቀ ቦታ በቂ የሆነ ሸክላ አፈር እንዲያመጣ አዘዘው። ጅብሪል የታላቁ የሰማይ ጉባኤ ከፍተኛ አዛዥ ወደ ምድር ወርዶ አሁን የነብዩ (ሰዐወ) አካል ከተቀበረበት ቦታ የተሻለ ቦታ ስለማይኖር ከዛ አፈሩን ወሰደ። ከዚያን አላህ ይህንን ሸክላ አፈር ከጀነት ከሚፈሰው የተስኒም ወንዝ ቀላቀለው ከነጭ እንቁ የሚመስል ሆነ። በመቀጠልም እንቁው ወደ ተለያዩ የጀነት ወንዞች ጅረቷች ተቀላቀለ አስደናቂ ነገርም ሆነ። ከዚያን ለሰባቱ ሰማይና ምድር ንጣፎች ተገለጠ በዝናም በምስጋና በሰማይና በምድር ከሚኖሩ ሁሉ በመለኮታዊ ተቀባይነትና ከፍተኛ ክብርን እንዳገኘ ተገለፀ።
አደም ከተፈጠረ ቡሀላ ይህ ብርሀን በግንባሩ ላይ ተቀመጠ እናም የሚወርድ ወንዝ ድምፅ ከእርሱ ተሰማ። አደም ጌታውን ጠየቀ "ጌታዬ ሆይ ምስጋና ይገባህ ይህ በግምባሬ ላይ ያለው ድምፅ ምንድነው? አላህም: "የነብያት ማህተም ብርሀን የሰይዲና ሙሀመድ ሰዐወ የምስጋናና የማወደስ ድምፅ ነው! ይህን ብርሀን ከፍ አድርገህ ያዝ ለዘር እንደሚተላለፍ እወቅ። ስለዚህ ንፁህና ጨዋ ሴቶችን ብቻ ለሚስቶቻቸው እንዲወስዱና የዚያ ብርሀን ባለቤት ወደ አለም እስኪመጣ ድረስ ከስንፍና ከንቱ ምግባር እንዲቆጠቡ እዘዛቸው። አደምም ይህን ሊፈፅም ተሳለ እና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሙሀመድ ብርሀን በተባረከ ግንባሩ ላይ በራ። በመጀመሪያ አደም በተፈጠረ ጊዜ ብርሀኑ በጀርባው ላይ እንደተቀመጠ ይነገራል። አደም በሄደበት ሁሉ መላእክት ይከተሉትና ሲቆም ከሆላው ቆመው ይህን የሚያበራ ብርሀን እያመሰገኑና እያከበሩ ነበር። በመጨረሻ አደም "ጌታዬ ሆይ ለምንድነው መላእክት ሁል ጊዜ በጀርባዬ ሚሰባሰቡት በጀርባዬ ያለው ምንድነው? ሲል ጠየቀ። አላህም : አደም ሆይ ጀርባህ ላይ የሙሀመድን ብርሀን አኑሬያለው መላእክቱም ለእርሱ ክብር ይሰጣሉ። አደም እንዲህ አለ : ጌታዬ ሆይ መላእክት ከሆላዬ እንዳይሆኑ ይህን የተባረከ ብርሀን ከፊት ለፊቴ አኑር።
ጌታም ይህን ውለታ ሰጠው በግንባሩ ላይ አደረገለት። አሁን መላእክቱ ከፊት ለፊቱ ይቆሙ ነበር። አደም መላእክቱ ለዚህ ብርሀን ያላቸውን ታላቅ ፍቅርና ትጋት ተረድቷ በመጨረሻ እንዲህ ተማፀነ: ጌታዬ ሆይ እልፍ አእላፍት መላእክቶች ያለ ማቋረጥ የሚሰግዱበትን ይህን አስደናቂ ብርሀን እኔም እንዳየው እድል አትሰጠኝምን? ሲል ጠየቀ
ጌታ ፀሎቱን ሰምቶ ለአደም ልመና መልስ የሙሀመድን ብርሀን በቀኝ እጁ አመልካች ጣት ላይ አደረገ። (የሸሀዳ ጣት ይባላል) አደምም ይችን ጣት "ሳጃህ" ብሎ ጠራት። በመቀጠልም የዚያን ድንቅ ብርሀን ባለቤት ሰለዋት በማውረድ ከነብያት ሁሉ የላቀና ፍፁም በሆኑት የሙሀመድ ሰዐወ ብርሀን ማወደስ ጀመሩ።
አደምና ሀዋ በጀነት በመለኮታዊ ትእዛዝ በተባረሩ ጊዜ የጀነት ልብሳቸው ተገፎ እርቃናቸውን ተደርገው እንዲያፍሩ ተደረጉ። እራሳቸውን ከመላእክቶች ለመደበቅ ከጀነት ዛፎች ጀርባ ለመደበቅ ሞከሩ። ነገር ግን ዛፎቹ እምቢ አሏቸው። ከዑድ (እሬት) ዛፍ በቀር። ሁሉን ቻይ የሆነውም አላህ ይህን ዛፍ ሁሉም እምቢ ብለው ሳለ ለምን አደምና ሀዋን እንደደበቀ ጠየቀው። የኡድ (እሬት) ዛፍ እንዲህ ሲል መለሰ። "አቤቱ መሀሪው ጌታዬ ሆይ የአንተን ተወዳጁ ሙሀመድን ሰዐወ ብርሀን በግንባሩ አስቀምጠሀል ፍጥረታት ሁሉ ብርሀኑን ሲመለከቱ እንዲያመሰግኑ አዘሀቸዋል። አደም ይህን ብርሀን ይዞ ወደኔ መጣ መጠጊያን ለመነኝ። ለዚህ የተቀደሰ ብርሀን ስል እንዴት ልከልክለው እምቢ ልል ነውር ተሰማኝ እና ወደ ጥላዬ ተቀበልኩት።"
ይቀጥላል...

#አባታችን_አደም 2⃣
ሁሉን ቻይ የሆነው አላህም እንዲህ ሲል መለሰ።
" የኡድ ዛፍ (እሬት) ሆይ! የወዳጄን ብርሃን እንዲሁ ስላከበርክ ከሌሎች ዛፎች ይልበጥ በባሪያዎቼ ዘንድ ከፍ እንድትል አደርግሃለሁ፤ ቅጠሎችህንም ነጭ አድርጌአለሁ። ነገር ግን ያለእኔ ፈቃድ ስላደረግከው የፈለጋችሁትን ሽቶ አመድ እንዳትቃጠል ማድረግ አትችልም።
አደምና ሃዋ ራቁታቸውን በቆሙ ጊዜ ሰውነታቸውን መሸፈኛ ቅጠል ከጀነት ዛፎች ለመኑ። ሁሉም ፍቃደኛ አልሆኑም ነበር። ተስፋ ቆርጠው ወደ በለስ እስኪደርሱ ድረስ። ይህ ዛፍ አዘነላቸውና የሚሸፍኑበትን ቅጠል ሰጣቸው። ቅጠሉን ከወሰዱ ቡሀላ ግን ምንም ጥቅም አልነበረውም ቅጠሉ ደረቀ። በዚህ ጊዜ ይበልጥ ማልቀስ ጀመሩ። ከዛ አንድ ድምፅ ሰሙ " አላህ መጎናፀፊያውን ያወለቀው ማንም ሊለብስ ስልጣን እንደሌለው አወቁ በጌታው የተተወ አገልጋይ ከየትኛውም አቅጣጫ እርዳታ ማግኘት አይችልም።" ይህን ሲሰሙ አደም የሁሉ ነገር ምንጭ ወደሆነው አላህ ተመለሰና ሀፍረተ ገላቸውን መሸፈኛ እንዲሰጣቸው ለመነ። ዳግመኛም ወደ በለሱ መጡ በፈቃዱም አደም ዛፉን አንቀጠቀጡ ሶስት ቅጠሎች ወደቁ። በእነዚህም አደም ራሱን ሸፈነ። ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ ዛፉን አናወጠው 5 ቅጠሎች ወደቁ በእነዚህ ሀዋ ራሷን ሸፈነች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የወንዶች ጀናዛ ለቀብር በ3 ያልተሰፋ ጨርቅ መጠቅለል የተለመደ ሲሆን ሴቶች ግን በ5 ቁርጥራጭ በጨርቅ ትጠቀለላች።
አላህም "በለስ ሆይ አደምን ከቅጠለህ ስጦታ ሰጠህው?" አለው። ዛፉም "ጌታዬ ሆይ አልከለከልከውም ነበር ስለዚህ ቅጠሎቼን ሰጠሆቸው" ሲል መለሰ። አላህም "ለአደም ቁጣዬ በእርሱ ላይ በሆነ ጊዜ እንደራራህለት ሰዎች እንዳይወጡብህ እንጨትህንም በከንቱ እንዳይጠቀሙ ከውስጥህ ባዶ አደርጌሀለሁ ለማገዶም አትቃጠልም። በምድር ላይ የሚጠፍጥ አደርግሀለሁ የሚያጣምምህ ህያው እንስሳ የለም።"
የአለማት ጌታ ለአደም ከጀነት ወርዶ በምድር ላይ እንዲሰፍር መለኮታዊ ትእዛዙን ባዘዘ ጊዜ አደም በጭንቀት አላህን የነብያት ማህተም የተከበረችውን የሙሀመድን ነፍስ እንድታማልድ ዘንድ ጠራትና ብዙ አለቀሰ። "ጌታዬ የፈጠረኝና በዚህች ጀነት ውስጥ ያስቀመጠኝ ከዚህ የተድላ ማደሪያ ሊያስወግደኝና በታችኛው አለም ምድር ላይ እንድኖር ያደረገኝ ሚስጥሩ ምንድነው? ሲል ጮኸ
ሁሉን ቻይ የሆነው አላህም: አደም ሆይ በግርማዬና በኃይሌ በምድር ላይ የእኔ ተወካይ እንድትሆን ፈጠርኩህ። መጀመሪያ በነዚህ የጀነት አትክልቶች እንድትኖር ያደረኩህ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን አንተና ዘሮችህ ሁሉ ወደዚህች የደስታ ግዛት እውነተኛ የትውልድ ሀገራችሁ እንድትመለከቱ ነው። ልቦቻችሁን ወደ እርሷ በናፍቆትና በፍላጎት እንዲያዞሩ በአንድነቴም እንዲያምኑ የነቢያቶቼንና የመልእክተኞቼንን መልእክት እንዲያረጋግጡ በቃላቸውና ስራቸውም ለትእዛዜ ምላሽ እንዲሰጡ የትውልድ አገራቸውን ጀነት ለመመለስ እንዲተጉ ነው።
"የትውልድ ሀገርን መውደድ የኢማን አካል ነው።" ሰዐወ
የሰው ልጅ መነሻ የሆነውን ጀነትን ሲያመለክት ይህ ሀዲስ የዚህ ሚስጥር ምልክትና ማሳያ ነው። አደም የአላህን ቃል በሰማ ጊዜ ጀነትን ተወ።
አደም ዐሰ ወደ ሳራንዲብ ተራራ (ሲሪላንካ) ወረደ ሀዋ ወደ ምድር በጅዳ መጣች። ሸይጣንም ተባረረ ግን የት እንዳረፈ የተለያዩ መረጃዎች አሉ። አንዳንዶች በበስራ ሌሎች ሌላ ቦታ: ከፊሉ ደግሞ የትኛውም ቦታ አልወረደም ይላሉ። አደምና ሀዋ ከኢብሊስ ጋር በተባረሩ ጊዜ። ኢብሊስ "አደምና ሀዋን ከጀነት ማስወጣት ችያለሁ።" ምድር ላይ ምን ጥፋት ላድርስበት? ሲል አሰበ። ስለዚህ ነገር በምድር ላይ የሚኖሩትን አራዊት ሁሉ ሰብስቦ የአደም መምጣት ዘሮቹ መላውን የምድር አራዊት ሁሉ እያደነ እንዲጠፋ እንደሚያደርግ ነገራቸው። "አለቅን ምን እናድርግ?" ብለው ጮኹ። ሰይጣንም "ይህን አድርጉ አደም በሚወርድበት ስፍራ ተሰብሰቡ በመጣም ጊዜ ሁላችሁም አጥቁትና ሰባብሩት የዘላለም ፍፃሜው ይሆናል" በማለት ተናገረ። ኢብሊስ ሁሉንም እንስሳት በአደም ላይ አሳመፀ። አደም በምድር ላይ እግሩን በረገጠ ጊዜ ተሰብስበው ለማጥቃት እየተዘጋጁ አገኛቸው። አደም በዚህ አቀባበል ግራ ተጋባ ምን ማድረግ እንዳለበት አላወቀም። መልአኩ ጅብሪል ከቅፅበት ባነሰ ጊዜ ወደ አደም መጥቶ እንዲህ አለው። "አደም ሆይ የጌታችን ድንቅና ታላቅነት ሀይል ትመሰክር ዘንድ እጅህን ዘርግተህ የውሻውን ራስ ምታ።" አደም እንደታዘዘው አደረገ ውሻ መጀመሪያ አደምን ለማጥቃት መጣ አደምም መታው በእንስሳቱ ላይ ወደቀባቸውና ተበታተኑ። ከዚያ ቀን ጀምሮ ውሻው የሌሎች አዳኞች አውሬዎች ሁሉ ጠላት ሆነ።
አደም ዐለይሂ ሰላም ረጅም አመታትን በምድር ያለማቋረጥ እያለቀሰ አላህ እንዲምረው ሲለምን አሳለፈ። በመጨረሻም ከባለቤቱ ሀዋ ጋር እንዲያገናኘው ወደ አላህ ፀለየ። ከዚያም ዱኣው ተቀባይነት አገኘ። የአደም ዱኣው እንዲህ ነበር ይላሉ ሰይዱና አሊ ረዐ።
"ላ ኢላሀ ኢላ አንተ ሱብሀነከ ረቢ አሚልቱ ሱአን ወዘለምቱ ነፍሲ ወአነተ አርሀሙ ራሂሚን።"
(ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም: ክብር ላንተ ይሁን ጌታዬ ሆይ በድያለሁ: ነፍሴንም በድልኩ: አንተም ከአዛኚች የበለጠ አዛኝ ነህ።)
*ሀጢያቱ የውቅያኖስ አረፋ ቢያህል ወይም አንደ በረሃ አሸዋ ቢበዛ ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ በዚህ ዱኣ የለመነውን ይቅር ይላል።
አደም ይቅርታ ተደረገለትና ከጀነት ውስጥ የተሰራውን ቤት ከሰማይ አውረደለት በይተል መእሙር ሰማያዊ ቤት ይባላል። ሁለት በሮች ነበሩት አንደኛው በምስራቅ ሌላው በምእራብ ዛሬ ካእባ መካ ላይ በቆመበት ቦታ ተቀምጦል። ከዚያም አደም ይህንን ሰማያዊ ቤት እንዲዞር በራእይ ታዞ ነበርና ሀጅና የሰእይን ስርአት በመልአኩ ጅብሪል ተምሮል። ጠዋፍና ሰእይን ካጠናቀቀ ቡሀላ ከሀዋ ጋር ለመገናኘት ወደ አራፋት ተራራ (መተዋወቂያ: አረፍተኒ አረፍቱኪ አወቅሽኝ አወከኝ የተባባሉባት ቦታ ነበረች) ተወሰደ። አደምና ሀዋ የበረታ ናፍቆታቸውን ተወጡ። መልአኩም የሚፈልጉትን ጠየቃቸው። "እኛ የጌታችንን ምህረት እንጂ አንፈልግም።" ብለው መለሱ ይህ ቦታ ሙና (ተስፋ: ምኞት) ይባላል።

ስለ "Halal Jobs" ሰምተዋል?
ይህ ፕላትፎርም የተከፈተው ሐላል የሆኑ የስራ ማስታወቂያዎችን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ለማድረስ ሲሆን፥
አዲስ ስራ ለሚፈልጉ፣ ስራ መቀየር ላሰቡና እንዲሁም ቀጣሪዎች የስራ ማስታወቂያቸውን በነፃ እንዲለቁበት በማሰብ የተዘጋጀ ፕላትፎርም ነው!።
ይወዳጁን! ይከታተሉን! ወዳጅዎንም ይጋብዙ! ያተርፉበታል!
እርስዎም ለወዳጅዎ በማጋራት የአላማችን ተካፋይ ይሁኑ።
ቻናል👉 www.tg-me.com/HalalJobsEth

አላህ በሱረቱ ቲን ላይ እንዲህ ይላል:
لقد خلقنا الإنسان في أحسن تقويم
"እኛ ሰውን በመልካሙ ሀውልት ፈጠርነው።"
<ምርጥ ሀውልት> ለሚለው ምላሽ አካላዊ መዋቀር: በህክምና ሳይንስ እውቀት በማዛመድ አንድ ሚስጥራዊ ምልከታ ቀርቧል። ይህውም የሰው አካል (አደም) ሐውልት ሙሐመድ(محمد) የሚለውን አረብኛ ስም ይወክላል። አላህ የሱን አደም ከሌሎች ሁሉ የበላይ አደረገው። ስለዚህ የሰው ልጅ በመላው አፅናፈ ሰማይ ውስጥ ከፍተኛ ፍጡር ሆነና የአካሉ አወቃቀር በቅዱስ ቁርአን ውስጥ በተጠቀሰው ምርጥ ምስል ተፈጠረ። እንደ እውነቱ ከሆነ የሰው አካል በእንዲህ አይነት መዋቀር መፈጠር የአላህን ለነቢዩ ሙሀመድ ሰዐወ ያለውን ወሰን የለሽ ፍቅር ያሳያል። ይህን በተመለከተ በቅዱስ ቁርአን ውስጥ ደጋፊ የሆኑ አንቀፆች ተብራርተዋል።
*ሱብሀንአላህ እጅ እግርህን ሁሉን አስተንትን።

#የሚስት_ፈገግታ!
*አንዲት ሴት ለባሏ ፈገግ ብላ ከሆነ አላህ ጀነት በር እንዲከፈትላት ያዛል። ለእርሷ, ከዚህ በፊት ተዘጋጅቶ የማያውቅ ቤተ መንግስት ያዘጋጃል። ከዚህ በፊት ያልተበረከተ በረከትን ይለግሳታል!
*አሏህ ለምን እንዲህ አይነት ፀጋዎችን ይለግሳል?
<ምክንያቱም አንዲት ሚስት ባሏን በፈገግታ ስትቀበል ቀኑን ሙሉ የሚደርስበትን ችግርና ድካም ከትከሻው ታራግፍለታለች። በመካከላቸው ፍቅርን ይጨምራል።>
*ፍቅር የቤተሰብ ህይወትን ለመቀጠል ምክንያት ነው።
*ፍቅር ከሌለ ቤተሰብ ይለያያል።
*ስለዚህ አላህ ፈገግ ያሉ ፊቶችን ይወዳል። ቀላል ነገር ነው, ግን በጣም አስፈላጊ።
*የፈገግታ ሚስጥር ብዙ ነው። ሁሉ ቢያቅትህ ፈገግ በል ከሁሉ ይልቃልና።
*አላህ በባልና ሚስት መካከል ወይም በሙእሚን መካከል ጥላቻን ፈጽሞ አይወድም*።

<ይችን የቁስ አለም አልፈልጋትም:
ይህን የሞት አለም አልፈልግም:
ጀነትን አይደለም ምፈልገው:
ከውሰርን አይደለም ፍላጎቴ:
እኔ የምፈልገው አንተን (አላህ) ብቻ ነው።>
<ጌታዬ እንደ ኢስማኢል አንገቴን ላንተ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ።>
#አሺቅ_ዩኑስ
@abduftsmeier
@abduftsemier
ይህን የሞት አለም አልፈልግም:
ጀነትን አይደለም ምፈልገው:
ከውሰርን አይደለም ፍላጎቴ:
እኔ የምፈልገው አንተን (አላህ) ብቻ ነው።>
<ጌታዬ እንደ ኢስማኢል አንገቴን ላንተ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ።>
#አሺቅ_ዩኑስ
@abduftsmeier
@abduftsemier