Telegram Web Link
<የሴት ልጅን እንባ በጣም ተጠንቀቅ: ፈጣሪ እንባዋን ይቆጥራልና። ሴት ልጅ የበታች እንድትሆን ከእግሩ አጥንት አይደለም ወይም የበላይ እንድትሆን ከጭንቅላቱ አይደለም ያስገኛት: ከጎን አጥንት የፈጠራት እኩል እንድትሆን ከእቅፉ ስር እንድትጠበቅ ነው።>

@abduftsemier
@abduftsemier
#የሰይጣን_ቅሬታ

አንድ ቀን ሰይጣን ለነብዩ ሙሳ አሰ እንዲህ አላቸው: አደም ስህተት ሰራ ነገር ግን ይቅር አለው። ለእኔ ግን ይቅር አላለኝም። ጌታህ በዳይ ነው አላቸው።
ሙሳም ጡር ተራራ ሄደ። አላህም ሙሳ ምን አሰብክ አላቸው "ጌታዬ ሆይ እንደምታውቀው አደምና ሰይጣን አጥፍተዋል አንተ ግን አደምን ይቅር አልከው ሰይጣንን ለምን?

አላህም: ሙሳ ሆይ በጣም ቀላል ነው። ስትመለስ ሰይጣንን ስታገኘው ጌታዬ መሀሪ ነው። በለው አደም የት እንደተቀበረ ያውቃል ወደ ቀብሩ ይሂድና አንድ ጊዜ ለአደም ይስገድ ሁሉንም ወንጀልና ጥፋት እምርለታለሁ።
ሙሳም ይህን ሲነግሩት ሰይጣን እንዲህ አለ: በህይወት እያለ ያልሰገድኩለት አሁን ለሞተ አጥንቱ ልሰግድለት ይፈልጋልን?

*አላህ ማንንም ለመማር ዝግጁ ነው: እስከተመለሱ ድረስ። ሁሌም በአላህ ተስፋና ምህረት ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ ሁን። ሰይጣን እንኳን የቂያማ ቀን አላህ ይምረኝ ይሆናል። ብሎ ተስፋ ያደርጋል።

@abduftsemier
@abduftsemier
#የይቅርታ_ስጦታ

ሶሪያ ውስጥ አንድ ምስኪን የታክሲ ሹፌር ነበር። ህክምና የሚያጠናን ተማሪ በስህተት ገጭቷ ለሞት ዳረገው። ሸይኽ ሙሀመድ አይዋድና ሌሎች ዑለሞች ዳኛ ወደ ሆነው ወደ ሞች አባት ሄደው የታክሲ ሹፌሩ ልጅህን በስህተት ገሎል ይቅር በለው የደም ካሳም አቀረቡለት። አባትየውም በሚገርም ሁኔታ እንዲህ አለ... <ይቅር ብየዋለሁ ከእሱ ገንዘብ አልፈልግም ነገ እራሴ እስር ቤት ሄጄ አስፈታዋለሁ ሼህ አይዋድ ሆይ እርሷ ቤቴ መጥተው አፍረው እንዲሄዱ አልፈቅድም!> በንጋታው የታክሲ ሹፌሩም በይቅርታ ተፈታ።

ከአመታት ቡሀላ ይህ አባት ፓላራይዝ ሆኑ። ቤተሰባቸውም የመጨረሻ ጉብኝታቸውን ወደ መካ ወሰዷቸው። በእንጨት ተደግፈው ጠዋፍ እያደረጉ እንዲህ አሉ: ሼህ አይዋድ ልጄን የገደለውን ሰው ይቅር በለው ብሎ ወደ እኔ መጣ: እኔም አፍረህ ከቤቴ አንድትወጣ አልፈቅድልህም አልኩት። "ጌታዬ ሆይ ዛሬ ቤትህ ድረስ ፓላራይዝ ሆኜ መጥቼ እንዳታሳዝነኝ እጠይቅሀለሁ!" ይሄን ዱኣ ሳይጨርሱ አላህ አፊያ (ጤና) መለሰላቸው። ጠዋፉንም በእግራቸው እየተራመዱ አጠናቀቁ። በዚያ ቦታ የነበሩ ሁሉ በእንባ ታጠቡ።

*የበደለህን ይቅር በል: አላህ አያሳፍርህም።
*የእዝነቱ ነብይ ሰዐወ ተበድለው ይቅርታን: ተሰድበው እዝነትን ያስቀድሙ ነበር።

@abduftsemier
@abduftsemier
<አላህ ለምትወደው ሰው ያፈሰስካትን እያንዳንዷን እንባ ያውቃል። ልብህ በትካዜና ሀዘን የሰመጠችበትን ጊዜ ያውቃል። ምንም ጥርጥር የለውም ከሚንቆረቆሩት ከንፈሮችህ የወጡትን ሁሉ ቃላት አላህ ሰምቷል። ለአፍታም ተስፋ አትቁረጥ: እስከሚያስፈልግህ ድረስ ወደ እርሱ አልቅስ: የሀዘን እንባህን ወደ ፍፁም ደስታ የሚቀይርልህ እርሱ ብቻ ነውና።>

*አላሁመ ሷሊ ወሰሊም አላ ሰይዲና ሙሀመድ!

@abduftsemier
@abduftsemier
ኢብራሂም ኢብኑ አድሀም በመካ ካሉ በአንዱ ተራራ ላይ ሆነው እያስተማሩ እንዲህ አሉ: "የአላህ ወሊያ የሆነ ተራራን ውደም ቢል ይፈርሳል።"
በዚህ ጊዜ የቆሙበት ተራራ ከስሩ መንቀሳቀስ ጀመረ: ተራራውንም በእግራቸው መቱና እንዲህ አሉት: "ለተማሪዎቼ ምሳሌ ለመስጠት ነበር ዝም በል!"
[ከራማት አል-አውሊያ: አቡ ሙሀመድ አል-ኸላል: 43]

*አላህ ላይ የሀቂቅ የቂን ካለህ ሁሉ ይታዘዝሀል: ምክንያቱም የሁሉም ጌታ እሱ ነው።

@abduftsemier
@abduftsemier
#የኢስላም_ክብር

ቁድስ (አቅሷ :እየሩሳሌም) በሙስሊሞች ድል ስትደረግ አንድ ቄስ ለአሚረል ሙእሚኒን ዑመር ኢብኑ ኸጣብ እንዲህ አላቸው: "አንተ የሙስሊሞች መሪ ነህ እዚህ ስትገባ ግመል መንዳትህ አይመጥንም የቱርክ ፈረስ ብትገልብና ሌላ ውድ ልብስ ብትለብስ በሮማውያን ዘንድ የበለጠ ክብር ይኖርሀል።" ዑመርም እንዲህ ሲሉ መለሱ: እውነት አሳፋሪ ህዝቦች ነበርን አላህ በኢስላም አከበረን። አላህ እያከበረን ሳለ የሌሎችን ክብር ብንፈልግ እንዋረዳለን።"
*ኢብኑ ከሲር "አል ቢዳያ ወል ሂዳያ"

@abduftsemier
@abduftsemier
@YEFKIR_MENGED
#የሜላት_አፍቃሪ ዘውትር 3:30
በአብዱ ኤምሬ
#እናት_የታላቅነት_ሚስጥር!

ኢማሙ ሻፊኢይ አባታቸው ሲያርፉ ህፃን ልጅ ስለነበሩ እናታቸው ከጋዛ ወደ መካ ተጉዛ ነበር። ይህም የዲኑ ምሁር ለመሆን ይበልጥ እድል ሰጣቸው። በከባድ ድህነት ውስጥ ቢኖሩም በ7 አመታቸው ቁርዐንን ሀፈዙ: በ10 አመታቸው ከ2000 በላይ ሀዲሶች ሸመደዱ፣ በወጣትነታቸው በአለም ላይ ካሉ ታላላቅ አሊሞች ተርታ ተሰለፉ። እናታቸው ይህን ሁሉ ድህነትና ረሀብ አሳልፋ ብቻዋን ያሳደገቻቸው ልጇን የዚህ የሙሀመድ ሰዐወ እምነት አገልጋይ እንዲሆንላት ብቻ በመሻት ነበር።

ኢማሙ ሻፊዒይ የመን በሄዱ ጊዜ የሀገሪቱ ነዋሪዎች ለአመታት የሚያቆያቸውን ድልብ ሀብት በስጦታ አበረከቱላቸው። ነገር ግን ሁሉንም በሰደቃ ሰጡት። ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ያደረጉትን ሁሉ ለእናታቸው ነገሯት እሷም "ወላሂ አንድ ድርሀም ይዘህ ብትመጣ ኖሮ መቼም ቤቴ እንድትገባ አልፈቅድልህም ነበር!"። ኢማሙ ሻፊኢይ ሲታመሙ ወደ ነብዩ ሰዐወ የልጅ ልጅ ወደሆነችው እመቤት ነፊሳህ ዘንድ ተማሪያቸውን 'ዱኣ አድርጊልኝ' ሲሉ መልእክት ይሰዳሉ። ተማሪያቸው መልእክቱን አድርሶ ሳይመለስ ኢማሙ ሙሉ ለሙሉ ይድኑ ነበር።

*"አላህ ለቁርዐን ታላቅነትና፣ ለሱና ብርሀን: ለዑለማ፣ አውሊያእና ለኡማው ቅንነት ሲል የጋዛ ወንድሞቻችንን አላህ ይዘንላቸው ፍትህን ያንግስላቸው።"

@abduftsemier
@abduftsemier
#የዲን_ብርሀኖች!

አቡ ዱጃናህ ረዐ ዘውትር ሱቢህ ሰላት ከነብዩ ሰዐወ ጀርባ ይሰግዱ ነበር። ነገር ግን ሶላት ከጨረሱ ቡሀላ ቶሎ ከመስጂድ ይወጣሉ። አንድ ቀን ነብዩ ሰዐወ አስቆሙትና አቡ ዱጃና ሆይ ከአላህ ምንም አትፈልግምን? አሉት። "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ እፈልጋለሁ: ያለ አላህማ መኖር አልችልም ለአይን ጥቅሽ ያህልም ጊዜ ቢሆን።"

ነቢዩም ሰዐወ ታዲያ ለምን ከሶላት ቡሃላ ከኛ ጋር ቆይተህ ከአላህ የሚያስፈልግህን አትጠይቅም?
አቡ ዱጃናም: 'የኔ ነብይ የቴምር ዛፍ ያለው የአይሁድ ጎረቤት አለኝ ቅርንጫፎቹ በኔ ግቢ ውስጥ ናቸው። ለሊት ንፋስ ሲነፍስ ፍሬዎቹ በግቢዬ ላይ ይወድቃሉ። ከመስጂድ የምወጣው ሄጄ ቴምሩን ሰብስቤ ለባለቤቱ ለመመለስ ነው ልጆቼ ከእንቅልፍ ሳይነቁ። ከተነሱ ርቧቸው ይበሉታልና።'
እንደውም የኔ ነብይ ሰዐወ "አንድ ቀን ከልጄ አንዱ ሲበላ አይቼው ጣቴን ከጉሮሮው አስገብቼ ሳይውጠው አወጣሁት።" ልጄ በሚያለቅስ ጊዜም እንዲህ አልኩት "አታፍርም ሌባ ሆንህ አላህ ፊት ስትቆም?"
አቡበከር ረዐ አቡዱጃና ያለውን ሲሰሙ ወደ አይሁዱ ቤት ሄደው የቴምሩን ዛፍ ገዝተው ለአቡ ዱጃና ልጆች ሰጧቸው። አይሁዱም ነገሩን ሲሰማ በመደነቅ በፍጥነት ልጆቹንና ቤተሰቡን ሰብስቦ ወደ ነብዩ ሰዐወ በመሄድ ወደ እስልምና መግባታቸውን ይፋ አደረጉ።

*ኢስላም በጥበብ፣ በፍትህ፣ በርትህና በፍቅር የተስፋፋ እንጂ በአሉባልታ የመጣ አይደለም።

@abduftsemier
@abduftsemier
#እድለኛው_ዑማ

ነብዩ ሰዐወ ሶላት ላይ ቆመው ሳለ፣ ስለ ከሀዲያን ቅጣት የሚገልፀው አንቀፅ በደረሱ ጊዜ: የእኛ ነገር አስታወስው እጆቻቸውን አነሱ። ሰሀባው ሁሉ ስለ ራሱ ተጨንቋ ማልቀስ ጀመረ። ነብዩም ኡመቴ! ኡመቴ! እያሉ የተባረከው ጢማቸው እስኪርስ ድረስ አለቀሱ። አላህም ጅብሪልን መልዕክት ሰዶ ላከው። ጅብሪልም ለነብዩ ሰዐወ የእንባቸውን ምክንያት ጠየቃቸው፣ እሳቸውም የኡመታቸው መቀጣት ስጋት ገብቷቸው መሆኑን ነገሩት። ጅብሪልም እንዲህ አለ: "አላህ እንዳሳውቅህ ነግሮኛል በኡመቶችህ ጉዳይ አትጨነቅ ያስደስትሀልና መቼም አያሳፍርህም ጀነትን ይሰጣቸዋል።

*ሳያዩ ያፈቀሩንን ነብይ አንዲቷን ጠብታ አንባቸውን እንዴት እንከፍላለን?😭
*አላሁመ ሷሊ ወሰሊም ወባሪክ አላ ሰይዲና ሙሀመድ!

@abduftsemier
@abduftsemier
Forwarded from Smart bot 🤖
#የሜላት_አፍቃሪ ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የፍቅር ታሪክ አሁኑኑ ያንብቡት!
ፀሀፊ አብዱ ኤምሬ
#ሰይዲን_በህልሜ!

ኢማሙ ነወዊ አዝካር በሚለው ኪታባቸው ላይ ረሱልን በመናም ማየት የፈለገ ጁሙኣ ለይል ላይ ሁለት ረከዐ ሰግዶ በእያንዳንዱ ረከዐ 5ጊዜ አያተል ኩርሲይን ይቅራ ሰላቱን ከጨረሰ ቡሃላ 1000× በነብዩ ላይ ሰለዋት ያውርድ በአላህ ፍቃድ ረሱልን (ሰዐወ) መኝታ ላይ እንዳለ ይመለከታቸዋል።

*አላሁ ሷሊ ወሰሊም አላ ሰይዲና ሙሀመድ* ወአላ አሊሂ ወሷህቢሂ ወሰለም!

@abduftsemier
@abduftsemier
#አንድ_ከግማሽ_ሙሪድ!

በኦቶማን መንግስት ዘመን አንድ ሼህ ነበሩ። አንዳንድ ወረኞች ወደ ሀገሩ ገዢ ሱልጣኑ ጋር ሄደው "ሱልጣን ሆይ ይህ ሸይኽ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሙሪድ (ተከታይ) አሉት። ከፈለገ ሙሉ ግዛቱን ሊወስድብህ ይችላል።"

ሱልጣኑ ሼሁን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው: ስለ አንተ የሚናገሩት ነገር እውነት ነው? ሸይኹም እንዲህ አሉ: "ሱልጣን ሆይ እውነት አይደለም እኔ አንድ ከግማሽ ሙሪድ ብቻ ነው ያለኝ። " ሱልጣኑም እናያለን ብሎ ሁሉንም የሸይኹ ሙሪዶች ነን ያሉትን በአንድ ሜዳ እንዲሰባሰቡ ነገረ። በማግስቱ ሜዳው ሞልቷ ነበር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኙ:

ሱልጣኑም እንዲህ አለ: ተመልከት ይህ ሁሉ ያንተ ተከታይ ነኝ እያለ ነው።
ሼሁም "እንዲህ አይደለም አንድ ተኩል ብቻ ሙሪድ ነው ያለኝ አሉ።"
ሱልጣኑም ለታዳሚያን ጮክ ብሎ ይሄ "ሼሀችሁ ወንጀል ሰርቷል እኔ ደግሞ በምትኩ አስር ሙታን ካልሞቱለት እገድለዋለሁ።" አንዱ ሰውዬ ቀርቦ እኔ ለሼይኼ እሞታለሁ! ሲል በድንኳኑ ወሰዱት በድንኳኑ ውስጥ ጥቂት በጎች ነበሩ። ከነዛ አንዱን በግ ቆረጡትና ከድንኳን ደም መውጣት ጀመረ። ሁሉም ህዝብ ከድንኳኑ የሚወጣውን ደም አዩ ሁሉም በድንጋጤ ፀጥ አሉ።
ሱልጣኑም : ቀጣይ ለሸይኹ ሚሞት ማነው አለ? ማንም ወደ ፊት አልመጣም። አንዲት ሴት ብቻ ቀርባ እኔ ለሸይኼ እሞታለሁ! አለች። ዳግመኛ ድንኳኑ ወሰዷትና ሌላ በግ ቆረጡ ከድንኳኑም ደም ሲወጣ ባዩ ጊዜ ሁሉም ሰዎች እግሬ አውጪኝ ብለው ሸሹ። ሸይኹም "ሱልጣን ሆይ አያችሁ አንድ ከግማሽ ሙሪድ ብቻ ነው ያለኝ።" ሱልጣኑም: ወንዱ አንድ ሙሪድህ ሴቷ ግማሽ ሙሪድህ ማለት ነው? ሸይኹም እንዲህ አሉ: "በተቃራኒው ነው። ሰውየው ከመወሰዱ በፊት እንደሚሞት በእርግጠኝነት አላወቀም። እናማ ግማሽ ሙሪድ ነው። ሴቲቱ ግን በፊቷ ያለውን ሞት እያየች ዝግጁ ሆነች ስለዚህ ሙሉ ሙሪዴ ነች።"

@abduftsemier
@abduftsemier
#በተቃራኒ

አንድ ቀን እናታችን አኢሻ ረዐ በጣም ደስተኛ ሆና ወደ አባቷ ሰይዲና አቡበከር ረዐ ቤት አመራች። አቡበከርም ሲያዩት ምንድነው እንዲህ ያስደሳሽ የአብራኬ ክፋይ? ሲሉ ጠየቋት። እሷም የኔ ነብይ ሰዐወ እንዲህ ሲል ሰማሆቸው: "ሁለት የተጣሉ ሰዎች ያስታረቀ አላህ ጀነትን ቃል ገባለት።" እኔም በጣም ተደሰትኩ። አቡበከር ረዐ ግን በተቃራኒው ማልቀስ ጀመሩ። አባቴ ለምን አትደሳም ጀነት እኳ ነው ለምን ታለቅሳለህ? ውዷ ልጄ ሆይ አንቺ በቀጥታ እኔ ደግሞ በተቃራኒ ነው ያየሁት "ሁለት ሰው ያስታረቀ ጀነት ከተሰጠው: ሁለት ሰው ያጣላስ ቅጣቱ ምን ይሆን? እኔ በዚህ ምላሴ ሰዎችን አጣልቼ እንዳይሆን ፈራሁ።

*ለስንቱ መጣላት ሰበብ ሆነን ይሆናል። በንግግራችን በተግባራችን። ስንቱን ለማጋጨትስ አስበን ነበር? አላህ መሀሪ ነውና ከክፉ ጠብቋ ከራህመቱ አቅርቦ ይማረን።

@abduftsemier
@abduftsemier
cros inbox @ABDU_EMRE
#ደረሳው_ሌባ

በአንድ ውድቅት ለሊት ቤታቸው ሌባ ይገባል። እየሰገዱ ስለነበር ሶላታቸውን ጨረሰው ሲዞሩና፣ ሌባው የሰረቀውን ገንዘብ ይዞ ሲወጣ ተገጣጠሙ እንዲህ አሉት .... "ልጄ ሆይ እሱ የአደራ ገንዘብ ነው። እባክህ የኔ ገንዘብ እዛ ጋር አለልህ እሱን ውሰድ አሉት።" ሌባውም ደንግጦና እየተገረመ የተባለውን ገንዘብ ይዞ ሄደ። በቀጣይ ሌባውን ስላዩት ቤቱ ሊዘይሩት ሄዱ ። ወደ ቤቱ ገብተው ቁጭ ካሉ ቡሀላ እንዲህ አሉት ... ልጄ ሆይ! ለአላህ ብለህ ይቅር በለን። ጥፋቱ የኛ ነው እንዲህ እንደቸገረህ አላወቅንም ነበር። እኛ ነን ብራችንን አስቀምጠን አንተን እንድትቸገር ያደረግንህ። በማለት ለስጦታ የያዙት ብር ሲሰጡት ሌባው ተንሰቅስቆ አለቀሰ ወደ አላህም ተውበት አደረገ፣ የሼኹም ቀንደኛ ተማሪ እና ኻዳሚ ሆነ።
አላህ እንደዚህ አይነትም ባሮች አሉት።
#ሼህ_አህመድ_አሽ_ሻሚ

@abduftsemier
@abduftsemier
#የወጣቶቹ_ሀዘን

ኢማሙ አሊይ እመቤት ፋጢማን ሊቀብሩ በሄዱ ጊዜ እንዲህ አሉ። "ይህ የመጨረሻው ሰአት ነው ሀሰንና ሁሴን ሆይ እናታችሁን ተሰናበቱ ይህ የመለያያ ጊዜ ነው በሰማይ እስክናገኘት ድረስ።" ሀሰንና ሁሴን ከዛ ወደ እናታቸው ቀርበው እንዲህ ሲሉ ተናገሩ...

"እናታችን ሆይ አያታችንን ረሱሉላህ ስታገኚ ሰላምታችንን ላኪላቸው ከርሷ ቡሀላ የልጅ ልጆቻችሁ በዱንያ አለም ወላጅ አልባ ሆነዋል በያቸው..."

ሁለቱ ወጣት መኳንንቶች እናታቸውን ለመጨረሻ ጊዜ ሲሰናበቱ ኢማም ዐሊ ከእርሷ እስኪያነሳቸው ድረስ በስቃይ አለቀሱ። አሊም እንዲህ አሉ: ከሰማይ አንድ ድምፅ ሰማሁ: "ያ አበል ሐሰን ከእርሷ ላይ ወጣቶቹን አንሳቸው የሰማይ መላእክት እንባ አብዝተዋልና!"
ቢሃር አል አንዋር

@abduftsemier
@abduftsemier
#የፋቲሀ_ሲር(ሚስጥራት)

ይህ ሱራ 7 አንቀፆች አሉት መኪይ እና መዳኒ ተብሏል። በመካም በመዲናም የወረደ። በመጅሙዑል በያን ላይ እንደተከተበው ይህን ሱራ የቀራ ከቁርዐን 2/3 የመቅራት አጅር ያገኛል ።
ከረሱል ሰዐወ ባልደረቦች አንዱ ይህን ሱራ በአንድ ወቅት አነበበ። ነብዩም ሰዐወ እንዲህ አሉ : ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለው ይሄን የሚመስል ወህይ በተውራት (ቶራህ): ኢንጂል(መፅሀፍ ቅዱስ): ዘቡር (መዝሙረ ዳዊት) በየትኛውም አይገኝም፣ በቅዱስ ቁርአን ውስጥ ሲቀር።
ረሱል ሰዐወ በአንድ ወቅት ጃቢር ኢብኑ አብደላህ አንሳሪ እንዲህ ሲሉ ጠየቁት: <በሙሉ ቁርአኑ ላይ ሌላ አምሳያ የሌላትን ሱራ ላስተምርህ?> ጃቢርም: አባቴና እናቴ ቤዛ ይሁንሎ አስተምሩኝ። ስለ ሱረቱል ፋቲሃ አስተማሩተ። ከዚያም ነብዩ ሰዐወ ጃቢር ሆይ ስለ ፋቲሀ አንድ ነገር ልንገርህ? ጃቢርም "ወላጆቼ ቤዛ ይሁንሎ ይንገሩኝ" ሲል መለሰ። ነብዩም ሰዐወ: 'ሱረቱል ፋቲሀ ከሞት በስተቀር ለሁሉም ህመም ፈውስ ነው።'

ኢማም አቡ ዐብዲላህ ጃፋር ሲዲቅ ረዐ እንዲህ ብለዋል: በሱረቱል ፋቲሀ የማይድን ሰው ምንም ፈውስ የለውም። በሌላ ዘገባ: በየትኛውም ሰውነት ክፍሉ ላይ ይህን ሱራ 70 ጊዜ ቢቀራ ህመሙ እንዲሚወገድ ገልፀዋል። በርግጥም የዚህ ሱራ አቅም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ በሬሳ ላይ 70 ጊዜ ቢቀራ ያ ሰውነት መንቀሳቀስ ቢጀምር ሊገርም አይገባም።

ሱረቱል ፋቲሀ ለስጋዊና ለመንፈሳዊ ህመም ፈውስ ነው። ያለዚች ሱራ የዘውትር ሰላት እንኳን ሙሉ አይሆንም። በርግጥም ትልቅ ሀብት ነው ከአላህ ዘንድ የተቸረንና አንድም የቀድሞ ነብይ ያልተሰጠው። ይህ ሱራ "ኡሙል ኪታብ"ና "ሰብዑል መሳኒ" በመባል ይታወቃል።

@abduftsemier
@abduftsemier
Live stream started
Live stream finished (3 minutes)
2025/07/01 09:12:24
Back to Top
HTML Embed Code: