Telegram Web Link
#የሰይዲ_ኸድር_ቅዳሜ

የአውሊያ ሙርሰሉ የሁሉ ጓደኛ:
የኢልምና ኢማን የሀብት መገኛ:
ሰይዲና ኸድር የምድሩ ሹመኛ:
ባለ ሀይባ ናቸው ንጉስ ፈረሰኛ:
ጀሊሉ አጠጥቷቸው የህይወትን ውሀ:
በዱንያም አኺራ አወጣቸው ነጃና ፈለሀ:
ጠብቀናል አንቱን አመታት በሙሉ:
ከኢልምና ሀብት ሰጥተው እንዲያሞሉ:
መቼም አዛኝ ኖት ለምስኪን ለደሀ:
እኛንም ዘንድሮ አውጡን ፈለሀ:
ሰላትና ሰላም በኸድር ኢማሙ:
በሚወዱት ሁሉ በሚጠሩት ስሙ።

*አላሁመ ሷሊ አላ ሰይዲና ኸድር!

@abduftsemier
@abduftsemier
#ተሰናዳሁና

ሀሳቤ: ምኞቴ: ፍቅሬ: ህይወቴ አንቱ ኖት ያረሱለላህ በቻልኩት ሁሉ ልቤን ለርሷ ከፈትኩ ናፈቁኝ: አሰኙኝ: ፃፍኩኝ: ገጠምኩኝ: አለቀስኩኝ: አዜምኩኝ ግን ይበርዳል ስል ባሰብኝ ቅጥ አሳጣኝ አንቱን ብቻ አስባለሁኝ እንቅልፍ አጣሁኝ ለሊቱን ወዳንቱ ነጓድኩኝ መራቧትን ድንጋይ ማሰረዎትን ስሰማ አቃተኝ ትንሽም ቢገባኝ ብዬ ዘውትር ፆምኩኝ ግን ጨመረ እንጂ አልቀነሰም ከእንግዲህስ በቃ በናፍቆት አልባዝንም ብዬ ሻንጣዬን አዘጋጀሁ ልሄድ ተሰናዳሁ "ሀቢቢ መጣሁኝ የሄደው ቀልቤ አሁን በጀሰዴ" ስል ስንኝ ቆጠርኩ ግን መሄድ አቃተኝ ገናነህ ተባልኩኝ ሳይሳካ ቀረ ሻንጣዬም ከነገ ዛሬ እያለ እንደተዘጋጀ አለ። በአንደበቴ ብቻ ሳይሆን ሀያቴን ሙሉ በአንቱ መንገድ ለመሄድ ተሰናድቻለሁ ፍቀዱልኝ ሰይዲ ከሀድራችሁ አስገቡኝ ከወዳጆቻችሁ አድርጉኝ።

<የንፋሱ_ፖስታ>

አላሁመ ሷሊ በዘይኔ ሙሀመድ:
በከውኑ ሞገስ ላይ ዳኢመል አበድ:
ተሰናዳሁና ወዳንቱ ላቀና ጓዜን አዘጋጀው:
ልቤ እንደሄደ ጀሰዴም አንቱን ፈልጎ ነው:
ቀን ከሌት አይልም ሙሀባው ሲነሳ:
ብቸኝነት አይወድ ልብን የሚያሰሳ:
አንቱ የኸልቁ አይነታ ውሰዱኝ አንዳፍታ:
ህመሜ ይሻርልኝ ላድርስሎት ሰላምታ።

ሀሳቤም ውጥኔ እቅዴም ህይወቴ:
አንቱ ኖት ሀበቢ የኔ ማንነቴ:
ባንቱ ነው የላቅኩት ባንቱ ነው ምከብረው:
ባንቱ ነው ያለሁት ላንቱ ነው ምኖረው:
ወንጀሌ ነው እንጂ እርሷማ ቅርቤ ኖት:
ለኔ ብለው አይደል ናፍቀው ያለቀሱት:
እንደው ይሄን ሳስብማ ያንገበግበኛል:
ምሆነው ጠፍቷኝ ቅጡን ያሳጣኛል:
ሰለዋት እያልኩኝ በእጅግ እጓዛለው:
አንቱን በማወደስ ደስታን አገኛለው:
ጌትዬ እንዳለው በዚክር ነውና ልብ የሚረጋው።

ደግሞ ከወረቀት ብዕር አነሳለሁ:
የናፍቆት ደብዳቤ ስሜት እከትባለሁ:
ፍቅሬን መደሰቴን ሀዘኔን አሳፍራለሁ:
እባክሁ ሰይዲ ጥሩኝ እሎታለሁ:
ከመጨረሻው ላይ ሰለዋት አሰፍራለሁ:
ከቤት እወጣና ዱኣ አደርጋለሁ:
ጌትዬ ይሄንን መዲና ውሰድልኝ:
እንደ ጀት እበርረህ ከቁባው ጣልልኝ:
ከዛም እልካለሁ የናፍቆት ደብዳቤ በንፋሱ ፖስታ:
አድርሰህው ይሆን ያንን ሁሉ ፖስታ?
እንደው ሙሀባ እንጂ እርሷማ ሁሌም ይሰሙናል:
ፖስታም አያስፈልግ ሰለዋት ያደርሰናል:
ፍቅራችንን በዚህ ብንገልፅስ ብለናል።

አንድ ነው ምኞቴ አንድ ነው አምሮቴ:
ላንቱ እያደገደጉ መኖር ነው ሀያቴ:
ካንቱ ጋር መሆን ነው የሰርክ ፍላጎቴ:
ጥሩኝ ሰይዲ ከዛ ከሀድራችሁ ከአረንጓዴው ቁባ:
እኔም በአደቡ ልዘለቅና ልግባ:
ነፍሴም ቤተሰቤ ያለኝ የሚኖረኝ ይሁን ላንቱ ይገባ።

*አላህ መዲናዬ ጋር ይውሰደን! የመዲናዋስ?

@abduftsemier
@abduftsemier
#ሰው_ነበሩ

አንድ ተማሪ (ደረሳ) ሼሁን "የነጀማሉዲን አንይ እና የዳንዮችን (የሁለቱ ዳንይን ፣ አወሉን እና ሳኒውን ማለቱ ነው) የህይወት ታሪክ፣ ስለ ከራማቸው ፣ስለ ቸርነታቸው፣ እና ስለ ብዙ ነገራቸው የማትነግሩን ለምንድን ነው?" ሲል ደረሳው መምህሩን ጠየቃቸው።

ሸህየውም ፣ እማልነግራቹሁ!" ሰው ይመስላቹሃል ብየ ነው! በማለት መልስ ሰጡ።
ደረሳውም፣ አልገባውም ። ተደናግሮ ዝም አለ ።
ደረሳውም ወደ ሌላ የኢልም መንደር (ሐሪማ)
ለዝያራ በሄደበት ወቅት ለሸሁ እንዲህ አላቸው፣
ሸሆቹ፣ ለምንድን ነው የዳኖችን እና የአንይን የህይወት ታሪክ የማትነግሩን? ሲል ጠየቃቸው ። "ሸሁም ሰው ይመስሏቹሃል ብየ ነው አሉት። "ዳንይና አንይ እንደኛው ሰው አልነበሩም እንዴ? ሲል በግርምት ጠየቃቸው ደረሳው።
ሸህ ምን ቢሉት ጡሩ ነው……
"ከነሱ ሌላ ሰው የት አለና? እኛ ሰው ነን እንዴ? ሰው ማለት እነሱ ናቸው ። ብለው መለሱለት ""
ሼሄን ጠየቅኳቸው ስለ አካቢሮቹ ከራማ ሁሉም ሰው ያወራል ስለ ኢባዳቸውና ስራቸው ግን አይወራም ምክንያቱ ምንድነው? "ከከራማቸው በላይ የሚሰሩት ኢባዳና ስራ ነው ለአቅል ሚከብደው። ተናጋሪው ስለማይሰራው አፍሮ ዝም ይላል ከመናገር ይቆጠባል።"

*አሁን ላይ ሱፊ ነኝ የሚለው እንደ ቀደምቶቹ የሀቂቃ ሱፊ ቢሆን ኖሮ ይሄ አለም ላይ ያለው ጣጣ ባልነበር። ይህው ሱፊ ነኝ ባይ ሁላ በሚያጠፈው ጥፋት ደግሞ አለም ሁሉ ይቀጣል።

@abduftsemier
@abduftsemier
#እውነተኛ_ፍቅር

መልከመልካም የሆነ ወጣት ልጅ በውበቷ አቻ ካልተገኘላት ቆንጆ ሴት ጋር ትዳር ይፈፅማል። ከቆይታ ቡሀላ በድንገት ሚስቱ በቆዳ በሽታ ትያዛለች ቀስ በቀስም የሚያምረው ውበቷ ሁሉ ረገፈ። በዚሁ አጋጣሚ ባሏ በአደጋ የአይን ብርሀኑን ያጣል። ነገር ግን የትዳር ህይወታቸው ላይ ምንም ችግር ሳይገጥም ቀጠለ አይነስውሩ ባል ሚስቱ እንደሁልጊዜው ቆንጆ መሆኖን እንጂ ውበቷ ማጥፋቱን አያውቀም። በጣም የሚዋደዱ ቢሆንም የማይቀረው ሞት መጣና ሚስቱን ወሰዳት። ባልየው ሀዘኑን ነቋቋም ስላልቻለ ከተማውን ለቆ መውጣት ፈለገ። በዚህ ጊዜ አንድ ሰው ከሆላ ነካ አደረገውና "አሁን እንዴት ብቻህን ትራመዳለህ? በፊት ሚስትህ ነበረች መንገድ የምትመራህ።"
ይሄ ሀዘንተኛ እንዲህ ሲል መለሰለት <እኔ አይነስውር አይደለሁም ባለቤቴ በቆዳ በሽታ የነበራት ውበት ሲረግፍ እኔ እንዳየሁ ብታውቅ ኖሮ ከበሽታዋ በላይ ትጎዳ ነበር። ቢያንስ እኔ እንደማላየት ስታውቅ ትፅናናለች። ውበቷን ብቻ አይደለም የወደድኩት ሁሉነገሮን ነበር ያፈቀርኩት ለዛም ነው አይነስውር እንደሆንኩ ያስመሰልኩት ለርሷ ደስታ ስል።

("ውበት እያደር ይረግፋል ልብና ነፍስ ግን ዘላለማዊ ናቸው። ሰውን ከላይ ሳይሆን ከልብህ ውደድ")
*አፍቃሪ ሁሌም የተወዳጁን ደስታ ያስቀድማል።
*ሱፍይነት በንግግር አይደለም የሚታየው በተግባር ነው። ልቡ የተዘጋ ሁሉ ሱፍይ መሆን አይችልም። በቅድሚያ ልብህን ክፈት።

@abduftsemier
@abduftsemier
#የነቀሽበንዲያ_ኡስማኖግሉ ሼኽ የሆኑት ሰይድ ሀሰን ኢፈንዲ(ቀ.ሲ) በትናንትናው እለት ወደ ማይቀረው ሀገር ተሻግረዋል። ዝርያቸው ከኦቶማን መንግስት መስራቹ ሱልጣን ኡስማን (ቤይ) ይመዘዛል። በዛሬውም እለት የቱርኩ አሚርና የኢስላሙ አለም ተስፋ የሆኑት ረጀብ ጠይብ ኤርዶሀን በተገኙበት ተሸኝተዋል።
#ፋቲሀ
#የሀብትና_ፀጋ_ባለቤት!

በአንድ ዘመን ኡሙ ጃእፋር ከምትባል ባለፀጋ እንስት አጠገብ የሚኖሩ ሁለት ደሀ ሰዎች ነበሩ። አንደኛው "አላህ ሆይ አንተ ዘንድ ካለ ሀብትህ ለግሰኝ?" ሲል ሌላኛው ደግሞ "አላህ ሆይ ከኡሙ ጃእፋር ዘንድ ካለ ሀብት ስጠኝ" ሲሉ ዘውትር ዱኣ ያደርጋሉ። ኡሙ ጃእፋርም የነዚህን ሰዎች ዱኣ ትሰማ ነበርና። ከአላህ ሀብት ለሚጠይቀውሰው ሁለት የወርቅ ሳንቲም ከእሷ ሀብትን ለሚጠየቀው ደግሞ በተጠበሰ ዶሮ ውስጥ አድርጋ አስር የወርቅ ሳንቲሞችን ትሰጠው ነበር። ዶሮ የተሰጠውም ሰው ውስጡ ያሉትን ሳንቲሞች አያውቅም ነበር እናም ለጓደኛው በሁለት የወርቅ ሳንቲም ይሸጥለት ነበር። በዚህ መልኩ አስር ቀናቶች አለፉ በቀጣዩም ቀን
ኡሙ ጃእፋር በኩራት ተሞልታ ከእሷ ሀብት ለሚጠይቀው ሰው እንዲህ አለችው "ችሮታችን ሀብታም አላደረገህምን?" ሰውዬውም ግራ ተጋብቷ የምን ችሮታ አላት። እሷም በኩራት "በአስር ቀን ውስጥ መቶ የወርቅ ሳንቲም ማግኘትህ ነዋ።" ስትል መለሰችለት። ሰውዬውም በጭራሽ እኔ ምንም ሳንቲም አላገኘሁም በየቀኑ የማገኘው አንድ የተጠበሰ ዶሮ ነው እሱንም ለጓደኛዬ እሸጥለት ነበር። ኡሙ ጃእፋርም ተገርማና አዝና እያለቀሰች አላህን ምህረት መጠየቅ ጀመረች እንዲህም አለች "ይህ ሰው ከእኔ ዘንድ ካለ ሀብት ጠየቀ አላህም እጁ ውስጥ የገባን ሀብት ነጠቀው: ሌላኛው ደግሞ ከአላህ የሆነን ችሮታ ጠየቀ አላህም አላሳፈረውም ሁሉን ነገር አሞላለት። ለካ ሀብትንም ሆነ ፀጋ የሚሰጠው አላህ ነው።"

@abduftsemier
@abduftsemier
#ትልቆች

የትልቅ ሰው ወዳጅ እሱም ትልቅ ነውና:
ስማቸውን ላንሳ የሀበሾቹን ገናና:
ከአንይ ጀምሮ እስከ አብሬትዩ:
የሁሉም መነሻ ሸይኹል ቃዲሪዩ:
የሁሉም አለቃ ኻተመ ነብዩ:
የሀበሻ ሳዳቶች ለአቅል የራቁ:
ለዲናቸው ሲሉ ቀንሌት ተዋደቁ:
የዲኑን አዝመራ ማየት እንደናፈቁ:
የአውሊያው ኩራት ሲፋቸው ዳንዩ:
አወሉም ሳኒ ወሳሊሱ ከሁሉ የተለዩ:
ሸይኾቼ ወርቆቼ ጌታው የቁባ አባ:
አሁን ጠራሆት አህለን ወመርሀባ:
የጦሪቃን ኩታ የተባሉ ጀባ:
የኔ ተወዳጁ ሰይድ አበራሙዝ:
ይናገር ነበረ ከለውሀል መህፉዝ:
ሰይዲ ሰነዲ ሼኼ የኔ መላ:
ትናንትም ዛሬ ነገ ገባሁ ካንቱ ጥላ:
ምስኪኑ አሽከሮ አብዱ ይሎታል ሺሊላ:
ዛሬ ይግባ በሉት ሰይዲ ቡደላ:
ንግስናችሁ ይጨምር ሳይቀንስ በሙላ:
ሰላሙ ይብዛለት የጠራችሁ ሁላ:
በአባታችሁም አሊ ከረሙላ:
በሙሀመድ አሚን በኡመቱም ጥላ:
ከአደም ጀምሮ በሚመጡ እስከ ቂያም:
ባሉት ደጋግ ሁሉ ይውረድ ኮርማ ኮርማ።

*አላሁመ ሷሊ አላ ሀቢቢና ሙሀመድ ወአላ ጀሚኢል አስሀባ ወል አውሊያ!

@abduftsemier
@abduftsemier
@YEFKIR_MENGED pls JOIN & SHARE
#ዲናዊ_ፍቅር

አንቺኳ ለኔ ረመዳን ፆም ነሽ:
እጅጉን የጓጓሁ እስከማፈጥርብሽ:
ስሁርም አፍጥር አንቺን ነው ማስብሽ:
ፀሀይ ትውጣ ትግባ የማውቅ ነው ሳይሽ:
ተራዊህ ተሀጁድ ስሰግድ አነጋለሁ ስልሽ:
ለደቂቃ የቆምኩ አይመስለኝ ሳስብሽ:
አልዋሽም ውዴዋ የኔ ኢድ አንቺው ነሽ:
ፊጥር አድርጌ ፆሜ የሚያበቃብሽ:
ምቀኛ ይቃጠል ትንሿ ኢድ ሸዋሌ ነሽ:
ዳግም ዝምድናን የምቀጥልብሽ:
የኔ ምርጥ ልዩ ጁመኣም አንቺ ነሽ:
ለማንም ሳይረታ ልቤ ሰገደልሽ:
አድሀ ኡድሂያ አረፋዬ ነሽ:
በፍቅር በመውደድ መስዋእት ሆንኩልሽ:
አልፎም ተርፎ ለኔኳ መውሊዴ ነሽ:
ዳግም የተወለድኩ በሀያሉ ፍቅርሽ:
ሰላቴም አዝካሬ እወቂ አንቺ ነሽ:
በቀን ሀምሳ ጊዜ የምከንፍ በትዝታሽ:
የመኖር አርካኔ ሲፋዬ አንቺው ነሽ:
ለዚህ ነው በጀውላ የምመላለስ ቤትሽ:
ተርጊብ በያን ይጣፍጣል ከአፍሽ:
ለዚሁ አይደለ እድሜዬን በሙሉ ኹሩጅ የወጣሁልሽ:
እንደ ራይውንድ ኒዛም ሚከፈል አይምሰልሽ:
ከማንም ከምንም አጥብቄ ምወድሽ:
እንደ ኡስጣዚያ ለገንዘብ አይምሰልሽ:
ፍቅሬ ቢደኣ አይደለም ከሚሉት ዶላላ:
መውደዴ አይሎል ከናር በላይ እየፈላ:
እኔ ባንቺ ጉዳይ ከሳዳት ከማል ብሻለሁ:
ኢናሊላህ እያልኩ በቀን አስር ጊዜ አወድስሻለሁ:
ምንም ቢለው ቅር በነሙአዝ ድቤ አስደበድባለሁ:
ከነአሚን ጎራም ነሺዳ አስብላለሁ:
እንጉርጉሮ አልቀረኝ ምርኩዝ አቁሜለሁ:
ቅጡን ልንገርሽ መዝሀቤ አንቺ ነሽ!!!

*ጊዚያዊ ፍቅር ለአይን አፍቃሪ ነው: በነፍስ በልቡ ለሚወድ መለያየት የለም።
MY ሩሚ

@abduftsemier
@abduftsemier
#ያለ_ፍቅር_ሁሉ_ከንቱ_ነው!

ጀነት ልዩ ሀገር ያደረጋት ወንዙ: ፎቁ: ወርቁ: ወሀ: ማሩ: ወተቱ: አይደለም የአላህ ፍቅር የተሞላባት መሆኖ ነው ያለዛ ከጀሀነም በምን ተለየ? ጀሀነም አስፈሪ ያደረጋት እሳቶ ወይ አስፈሪ ነገራት በውስጦ መኖሩ አይደለም የአላህ ቁጣ እንጂ ፍቅር በውስጦ አለመኖሩ ነው። የአላህ ፍቅር ባይኖር ጀነት ጀሀነም ናት: ጀሀነም የአላህ ፍቅር ቢኖርበት ከማንም ማትወዳደር ሀገር በሆነች ነበር። ተርቲብ ሺ ብትጠብቅ ወንድም እያማህ ክፉ እያወራህ ሙሀባ ከሌላ ችግር ነው። ሙሀባ ከነበረበት የቀዲሚቹ ዘመን የተወጣ አንድ ቀን ከአሁኑ የንትርክ አራት ወር ይልቃል። ከየትኛውም ሀድራ ብትሽከረከር ብታርድ ብትሰድቅ ሙሀባ ከሌላ ትርፍ አልባ ነው። መናናቅ ካለበት ስፍራ ጥሬ እየቆረጥክ ሀድራ ከምትል: ቆሎ በልተህ በሙሀባ የተቀመጥከው ሀድራ ይበጃል። ኡስታዝ ብትሆን ሼኽ በጥቅም እየተቦጫጨቅክ እርዳታ እያነከትክ ዳኢ ነኝ ብለህ በመድረክ ሀዲስ ብትዶሰኩር ሙሀባ ከሌለ ሁሉም አንድ ነው።
<ዲን የመጣው በፍቅር ነው: ከፍ የሚለው በፍቅር ነው: ዝቅም የሚለውም ፍቅር ሲጠፋ ነው።>

@abduftsemier
@abduftsemier
#የሴቶች_ሳምንት

ኢንሻአላህ በዚህ ሳምንት የሀገራችንና የውጭ ሴት ወሊዬችን እናወሳለን።
#ዘቡራ

የአንድ ትልቅ ዓሊም እናት ናቸው ፡፡ የዓሊሙን ስም በኋላ ላይ እነግራችኋለሁ ፡፡ ‹‹ካልተዘመረላቸው ›› የዕውቀት ጀግኖች መካከልም ናቸው ፡፡ ስለርሳቸዉ ጥቂት ነጥቦችን እናንሳ :- ሲበዛ ቆንጆ ነበሩ ይባላል ፡፡ በዚያ ላይ ሊቅ (ዐሊም) ፡፡ አንድ ቀን ወንዝ ወርደው ልብስ በማጠብ ላይ እያሉ ሁለት ወጣት ደረሶች (የቆሎ ተማሪዎች እንደማለት) ወንዙን ሲያቋርጡ በጎን መልከት አደረጓቸውና በውበታቸው ተደመሙ፡፡ እናም እርሳቸው እንዳይሰሟቸው ከቁርአን ገለጻ ተውሰው በዐረብኛ ‹‹ወዘየናሀ ሊናዚሪን›› (ለተመልካች ውብ አደረግናት) አሉ ፡፡ ይህ የቁርአን አንቀጽ የተነገረው የሰማይን (የአድማሱን) ውበት ለመግለጽ ቢሆንም ወጣቶቹ የዘቡራን ቁንጅና ለመግለጽ በተውሶ ተጠቀሙበት ፡፡ ይህ ዓይነቱ ገለጻን የመዋስ ድርጊት በዐረብኛ የስዋሰውና የስነጽሁፍ ትምህርት ‹‹ሰሪቃ›› ይባላል ፡፡ ሁለቱ ደረሶች ‹‹በላጋ›› የተሰኘውን የዕውቀት ዘርፍ እንደተማሩ ገለጻቸው ያስታውቃል ፡፡ ወጣቷ ዘቡራ የዋዛ አልነበሩምና ቀበል አድርገው ‹‹ወሀፊዝናሀ ሚን ኩሊ ሸይጣኒን ረጅም›› (ከተረገመው ሰይጣን ሁሉ ጠበቅናት) የሚለውን ቀጣይ የቁርአን መልዕክት አነበቡ ፡፡ ‹‹ምንም ቁንጅናየ ቢስባችሁም ሰይጣን እንዳያሳስታችሁ ፡፡ እኔ በአምላኬ ከሰይጣን የተጠበቅኩ ነኝ›› ማለታቸው ነው ፡፡ ደረሶቹ ተራ የገጠር ኮረዳ አድርገው ያሰቧት እንስት የነርሱን የረቀቀ ቅኔ መረዳቷ አስደነገጣቸውና ከአካባቢው በፍጥነት ሸሹ፡፡
ዘቡራ  "ኢህያእ ዑሉሙ ዲን" የተሰኘውን የኢማም አቡሀሚድ አልገዛሊ ባለ 4 ጥራዝ ኪታብ (መጽሀፍ) በቃላቸው (በሂፍዝ) ያውቁት ነበር ይባላል ፡፡ በዚህ ድርጊት ይህን ኪታብ በቃል ካጠኑ የዓለማችን ትልልቅ ሊቃውንት (ዑለሞች) ተርታ ተሰልፈዋል ፡፡ "ኢህያእ ዑሉሙዲን" በዕውቅ ዑለሞች በብዛት ከመተሀፈዙ የተነሳ "ካደል ኢህያኡ አንየኩነ ቁርአና" /" 'ኢህያእ' ቁርአን ሊሆን ትንሽ ቀረው"/ ተብሎለታል ፡፡
ዘቡራ የዐረብኛ ጽሑፍ (ኸጥ) ልዩ ችሎታ ነበራቸው ፡፡ የሃይማኖት መጻሕፍት (ኪታቦች) እንደልብ በማይገኙበትና ማተሚያ ማሽን ባልነበረበት በጥንቱ ዘመን ኪታቦችን በብራና ላይ የሚጽፉ እንደዘቡራ ዓይነት ጸሐፍት በዕውቀት ቅብብሎሹ ሂደት ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል፡፡
እመት ዘቡራ ሸኽ ኢብራሂም ያሲን ከተባሉ ትልቅ ዐሊም ጋር በጋብቻ ተጣመሩ ፡፡ እነዚህ ጥንዶች ልጅ የመውለድ ነገር ለዓመታት ዘገየባቸው ፡፡ ሸኽ ኢብራሂም "ልጅ አላህ አልሰጠንም ፤ ስለዚህ ችግሩ ከኔም ይሁን ካንቺ ተለያይተን ዕድላችንን በየፊናችን እንሞክር" የሚል ጥያቄ ደጋግመው ያነሱ ነበር፡፡ አንድ ቀን ዘቡራ የሰጡት መልስ ይገርማል ፡፡ "ከርስዎ ጋር መሆንን የምመርጠው ለሌሊት ሶላት ስል እንጅ ሌላ ባል የማግኘት ዕድል የሌለኝ ሆኖ አይደለም ፡፡" ሸኽ ኢብራሂም የሌሊት ሶላት ያበዛሉ ፡፡ ዘቡራም አብረው ሲሰግዱ ያድራሉ ፡፡ ይህ መልስ የሸኽ ኢብራሂምን ልብ ነካ፡፡ ተንሰቅስቀው አለቀሱ ፡፡ ከዚያ ቀን በኋላ የመለያየት ሀሳቡን እርግፍ አድርገው ተውት ፡፡ ከዚያ ይልቅ የማይሳነው አምላክ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ዱዐ ማድረጉን ተያያዙት ፡፡ አንድ ቀን ሸኽ ኢብራሂም ዱዐ ለማስደረግ ባልንጀሮቻቸውን ሰበሰቡ፡፡ ዱዐው ተጀመረ ፡፡
ከመሀከል አንደኛው ፡- "አላህ ዘጠኝ ልጅ ይስጣችሁ" በማለት ሲመርቁ እመት ዘቡራ ሰሙና "ዘጠኝ ልጆች አርግዤ ስወልድና ሳሳድግ የሌሊት ሶላቴ በብዛት ይስተጓጎላል ፡፡ ይህን ኪሳራ ደግሞ አልችለውም ፡፡ ከዚያ ይልቅ የዘጠኝ ሰው አቅም ያለው አንድ ልጅ ይሰጠኝ ዘንድ ዱዐ አድርጉልኝ"  በማለት ተናገሩ ፡፡ የዱዐው አቅጣጫ ወደዚህ ዞረ፡፡ ጥቂት ቆይቶ ዘቡራ አረገዙ ፡፡ ወንድ ልጅም ወለዱ ፡፡ ስሙንም "ሰይድ" አሉት ፡፡ ልጁ አደገ ፡፡ በዕውቀትም በስሜትም ጎለበተ ፡፡ ከሀገራችን ታላላቅ ሊቃውንትና ባለቅኔዎች መሀከልም ሆነ፡፡ "የመድህ ንጉሥ" ተሰኘም ፡፡ ሸኽ ሰይድ ኢብራሂም ፣ በቅጽል ስማቸው "የጫሌ ሸኽ"፡፡ 
ዘቡራ ከሸኽ ጫሌ በኋላ ሌላ ልጅ አልወለዱም ፡፡ የሚወዱትን የሌሊት ሶላት ሳያስተጓጉሉ በደስታ ኖሩ ፡፡ ሸኽ ጫሌ የሁለት ታላላቅ ዐሊሞች ልጅ ቢሆኑም እናታቸዉን ይበልጥ ያደንቁ ነበር፡፡ ለዚህ ይመስላል ሲፎክሩ "የዘቡራ ልጅ" ይሉ የነበረው ፡፡ ረህመቱላሂ ዐለይሃ ፡፡
የብዕሩ ንጉስ ሰይዲ ሀሰን ታጁ

@abduftsemier
@abduftsemier
#የፍቅር_ሰማእቷ

የአደም ልጅ ሁሉ በተኙበት ቅፅበት አንዲት ከጌታዋ ጋር ምታወራ አንዲት ሴት ቤት ሌባ ገብቶ ወዲህ ወዲያ ይላል እሷ ሶላት ላይ ነች ሌባውም ቤቱን ሲያስስ ቆይቶ ከአንድ የውሃ ማንቆርቆሪየ ውጭ ባለማግኘቱ ባዶ እጁን ሊወጣ ሲል እንስቷ ሶላቷን ጨርሳ ቀና አለች "ለመዝረፍ መጥተህ ከሆነ እባክህን ባዶ እጅህን እንዳትወጣ" አለችው "ምንም እኳ የለም ቤትሽ ውስጥ" በማለት በግርምት መለሰላት "አንተ ምስኪን ሂድ እስቲ ውዱዕ አድርግና እዚያች ክፍል ሁለት ረከዐ ስገድ ባዶ እጅህን አትወጣም" አለችው እጆንም ወደላይ ዘርግታ "አላህ ሆይ ይሄ ሰው እኔ ዘንድ መጥቶ ምንም አላገኘም ከአንተ እንዲቆም ልኬዋለሁና ከፀጋህ ለግሰው" አለች
ሌባውም ውዱዑን አድርጎ ሶላት ጀምሯል ሁለት ረከዐ ሰግዶ ደስ ብሎት ሲደጋግም ፈጅር ደረሰ "እሺ ለሊቱ እንዴት ነበር?" ብላ ጠየቀችው "ጌታዬ ፊት ምህረትን ሽቼ ተዋርጄ ሰገድኩ ምህረቱን ለግሶ ሃሳቤን ሞላልኝ" ብሎ ከቤቷ ወጣ ዳግም ወደ ሰማይ እጇን ዘረጋች "አላህ ሆይ ይህ ሰው ውስን ሰአታትን ከፊትህ ቢቆም ተቀበልከው እኔ ካወቅኩህ ሰአት አንስቶ ፊትህ ከመቆም ቦዝኜ አላውቅም ታድያ ተቀብለኸኝ ይሁን?" ስትል ጌታዋን ጠየቀች ከጀርባዋ ድምፅ ሰማች "አንቺ ራቢአ ስላንቺ ስንል ተቀብለነዋል ባንቺው ሰበብም አስጠግተነዋል"

*ይህች ሴት ራቢአተል አደዊያ ናት ለጌታዋ ፍቅር ነፍሷን የሰዋች ሴት የውዴታ መስዋእት!
[The library of great sufi poet]
@abduftsemier
@abduftsemier
@YEFKIR_MENGED pls JOIN & SHARE
Live stream started
Live stream finished (3 minutes)
#የካይሮዋ_ቅድስት

ሙሉ ስሟ ሰይዳ ነፊሳ ቢንት አሚረልሙእሚን ሀሰን አንዋር ኢብን ዘይድ አብላጅ ኢብን ሀሰን አሊ ኢብን አቢ ጣሊብ ሲሆን የታላቁ ነብይ ሙሀመድ ዘር ስትሆን ውልደቷ በመካ ከተማ በ762(እ.አ.አ) አካባቢ ነበር ።

የነብያችን መሐመድ ዘር የሆነውን ጃእፋር ሳዲቅ ልጅ ኢስሀቅ አል-ሙእታሚንን አገባች። አብራውም ከሂጃዝ ወደ ግብፅ ተሰደደች። 'ቃሲም' የሚባል ወንድ ልጅ እና ኡሙ ኩልሱም' የምትባል ሁለት ልጆች አፈሩ። 
የሀይማኖት አስተማሪ የነበረች ሲሆን ተማሪዎቿ ከሩቅ ቦታዎች ድረስ ይመጡ ነበሩ ከነሱም መካከል የሻፊዒያ መዝሀብ መስራች የነበሩት ኢማሙ ሻፊዒ ይገኙበታል ።  ኢብኑ ከሲር በአል -ቢዲያህ ላይ ስለእሷ የሚከተለውን ተናግረዋል።
ባለጸጋ ሴት ነበረች, ለሰዎች በተለይም ሽባ ለሆኑ, በጠና ህመም ላለባቸው እና ለሌሎች በሽተኞች ሁሉ ብዙ እንክብካቤን ታደርግ ነበር። ቅን እና ብዙ በጎ ምግባር ያላት ነበረች።
-  ኢብኑ ከሲር [2]

ኢማሙ አል ሻፊዒ እንደ ኢማም አቡ ሀኒፋ የኢማም ጃዕፈር ተማሪ የነበረው የሌላው ታላቅ የሱኒ ፊቂህ ኢማም ማሊክ ኢብኑ አነስ ተማሪ እንደነበሩ ተዘግቧል።  ሻፊዒ ወደ ካይሮ ከመጡ በኋላ ከሰይዳ ነፊሳ ዘንድ ሀዲሶችን ያጠኑ ነበር። በቤቷ ውስጥ አዘውትሮ እንግዳ ሲሆኑ በመስጂዷ ውስጥ ትምህርቶቿን ያዳምጡ ነበር፣ እናም ታሪክ ጸሐፊዎች እንደዘገቡት፣ ከሷ ዱዓዋን (በረከትን) ፈልገው ነበር። 
ኢማሙ ሻፊኢ ህመም ሲሰማቸው ዱኣ እንዲያረጉላት ደረሳቸውን ወደ ሰይዳ ጋር ይልኩ ነበር ደረሳቸው ከመመለሱ በፊት ከህመማቸው ይሽረየ ነበር። እና በኋላም አጀላቸው ሲቃረብ ጊዜ ሰይዳ ነፊሳ የቀብር ጸሎትን (ሶላት አል-ጀናዛን ) እንድትሰግድባቸው ዘንድ ኑዛዜ ፃፉ። አላህ በርሷ ሰበብ ምህረትን ይለግሰኝ ዘንድ።" ኢማሙ ከሞቱ በኋላ አስከሬናቸው ወደ ቤቷ ተወሰደ እና የጀናዛ ሰላት ሰገደች። በዘመኑ "ያለ ታዋቂነት፣ ዝና፣ እና በሕዝብ ዘንድ ያለ ክብር" እንደሷ ሊሆን አይችልም ተብሏል።

የሰይዳ እህት ልጅ የሆኑት ዘይነብ አክስቷ በሶስት ቀን አንድ ጊዜ ትበላ እንደምትበላ ገልፃለች። ዘይነብ ከእለታት ባንዱ ቀን አክስቴ ባዶ መሶብ ውስጥ ትንሽ ነገር ለመብላት በፈለገች ጊዜ እጇን ወደ ውስጥ ስታስገባ ከአላህ ዘንድ የተላከ ነገር አገኘች። ስትል ገልፃለች። ዘይነብ አክስቷን “ራስሽን መንከባከብ አለብሽ” ሰትል ጠየቀቻት። " ወደጌታዬ ሳልደርስ እንዴት እራሴን መጠበቅ አለብኝ? ከፊት ለፊቴ ብዙ መሰናክሎች አሉ ከተሳካላቸው በስተቀር ማንም የማይሻገራቸው ስትል መለሰች።"

በህይወት ዘመኗ ሆነ ከሞት በኋላ ከ150 በላይ ከራማ ለነፊሳሳ ተሰጥተዋል። ካይሮ ውስጥ ከተቀመጠች በኋላ ሙስሊም ያልሆኑት ጎረቤቷቿ ሽባ የሆነች ልጅ ነበራቸው። አንድ ቀን እናቷ ገበያ ስትሄድ ይህች ልጅ ወደ ሰይዳ ቤት አመራች። ሰይዳ ነፊሳ ከሶላት በፊት ውዱ ስታደርግ አንዳንድ የውሃ ጠብታዎች ልጅቷን ነክተው ይህች ሽባ ልጅ መንቀሳቀስ ጀመረች። ሲቲ ነፊሳ ሰላት መስገድ ስተጀምር ልጅቷ ተነስታ ከገበያ ወደ ምትመጣው እናቷ ሮጠች፤ በዚያው ቅጽበት እናት በጣም ተደሰተች። ከዚያ ተአምር በኋላ መላው ቤተሰብ እና ሌሎች ጎረቤቶች እስልምናን ተቀበሉ። 
ከሞተች በኋላ አንዳንድ ሌቦች መስጂዷ ገብተው አስራ ስድስት የብር መብራቶችን ወሰዱ። ወዲያው ማምለጥ ቢፈልጉም የገቡበትን በሮች ማግኘት አልቻሉም። በጓዳ ውስጥ እንዳሉ ተይዘው ነበር። 

ሰዎች በረከቷን ሊፈልጉ ከሩቅም ከቅርብም እስኪመጡ ድረስ ምግባሯ ዝነኛ ነበር። ከግብፅ ለመውጣት መወሰኗን የአህለል-በይትን ("የመሐመድ ቤተሰብ ") በረከቶች ለመሻት በመጡት ብዙ ሰዎች ምክንያት የኢባዳ ጊዜዋን ተሻማባት። ነገር ግን የግብፅ አስተዳዳሪ አሲር ኢብኑል-ሃከም እና ህዝቡ ከግብፅ እንዳትወጣ ያቀረቡት ልመና እንድትቀር አሳምኗታል። በቀጥታም ሆነ በጸሎት እርዳታ ለሚሹ ሰዎች ስላደረገችው ተአምር፣ ማየት የተሳነውን ሕፃን ማዳን፣ አባይ እንደታሰበው አንድ ዓመት ውሃው በቀነሰ ጊዜ እንዲበዛ ስለማድረጓ፣ መርከብ እንዳይሰምጥ መከልከሏ፣ የመሳሰሉ ከራማዎች ተዘርዝረዋል።  ህይወቷን ያሳለፈችው ቤተሰቧን ለመደገፍ ሱፍ ስትፈትል፣ እስረኛን በሀገር ገዥ ዘንድ በነበራት ክብር በምልጃዋ ነፃ በማውጣት እና ሰዎችን በችግራቸው ውስጥ በማገዝ ነው። 
ሰይዳህ ናፊሳህ፣ ሰይዳህ ሩቂያህ እና ሰይዳህ ዘይነብ ቢንት አሊ በተለምዶ  የካይሮ ቅዱሳን ተደርገው ይወሰዳሉ። 

*ሂማ ያ ሰይዳ ነፊሳ!
*አጊሱና ያ አህለል በይት!

@abduftsemier
@abduftsemier
Live stream started
Live stream finished (6 minutes)
2025/07/01 16:43:51
Back to Top
HTML Embed Code: