Telegram Web Link
#ከሰይዲ_ማዕድ

ሰይድ ሚቅባስ ወጣት ሳሉ የመንግስት ሥራ ጀምረው ነበር። ሥራው ግን የአዕምሮ እረፍት አልሰጣቸውም። ይሄ ሥራ ከነቢ መንገድ ጋር አብሮ ባይሄድስ ብለው ይሰጉ ነበር። አንድ ቀን ስጋታቸው ባስ አለና ጉድ እንዳልሆን በሚል ጭንቀት ሲያለቅሱ ዋሉ። የዛን እለት ማታ ታድያ እንቅልፍ ሸለብ እንዳደረጋቸው በህልማቸው እንዲህ ሆነ። አንድ ሰውዬ ይመጣና "ረሱል ይፈልጉሃል!" ይላቸዋል። በፍጥነት ብድግ ብለው "መርሐባ መርሐባ የት ናቸው?" ሲሉ ወደ አንድ ክፍል አመላከታቸው። እየተጣደፉ ሲገቡ ክፍሉ ባዶ ነበር። ሌላ ክፍል ከፍተው ሲገቡ አንድ ሰው ወንበር ላይ ተቀምጦ አዩ። ያ ሰው ሰይድ አቡበክር ሲዲቅ ረ.ዓ ናቸው። ወለላው ነቢ ደግሞ በተፈጠሩበት፣ በተወለዱበት መልክ አልጋ ላይ አረፍ ብለዋል። ውዱን ሰው በተኸለቁበት መልክ ማየታቸው ሆዳቸውን ቢያማታው እያለቀሱ በእንብርክክ፣ በዳዴ፣ በእንፉቅቅ ወደ አልጋው ይንደረደሩ ጀመር። ሊደርሱ ትንሽ ሲቀራቸው የኔ ነቢ አፈፍ አደረጓቸውና "ያንተ ጀነት’ኮ ከእኔና ከአቡበክር ጋር ነው!" አሏቸው። ሲነቁ ህልም ነው። ሲነጋ ለባለቤታቸው ወስያ መስጠት እንደሚፈልጉ ይነግሯቸዋል። ምክንያቱን ሲጠይቋቸውም "በቃ እኔ ልሞት ነው!" ብለው ከህልሙ የተረዱ የመሰላቸውን ፍቺ ይነግሯቸዋል። ያንን ቀን ከነቢና ከአቡበክር ጎን እንደሚሆኑ ከዛ ማር አንደበት የሰሙትን ብስራት እያሰቡ ሲስቁ፣ ወዲህ ደግሞ ከአባታቸው መለየትን እያስታወሱ ሲያለቅሱ ዋሉ። በሁኔታቸው የተደናገጡትና የእሜቴ አዒሻ ሞክሼ የሆኑት ባለቤታቸው ዱዓ ብለው በግ አስመጡ። ሁነኛ ሰውም አስጠሩ። ሰይድ ሙሒቡ መጡና ምን እንደተፈጠረ ጠየቋቸው። ይሄኔ እናት አዒሻ ሰይዲ ህልም ማየታቸውንና እሞታለሁ ብለው ማሰባቸውን ነግረው ዱዓ እንዲያደርጉላቸው ጠየቋቸው። ሰይድ ሙሒቡ "ህልሙን ልስማው" ብለው አጥብቀው ያዟቸው። ሰይድ ሙሒቡ ህልሙን ሲሰሙ ሳቁ። "ታድያ የዚህ መናም ፍቺ’ኮ እርስዎ እንዳሰቡት የሞት አይደለም። የመንግስት ሥራ ቀጥተኛውን መንገድ ያስተኛል ብለው ሲሰጉ ስለነበር ቀንዎ ሲደርስ ኺታምዎ የሚሆነው ከነርሱ ጋር መሆኑን ነግረው አይስጉ እያሉዎ፣ እያባሸሩዎ ነው።" አሏቸው። ደስታ ሆነ። ለዱዓ የታሰበው በግ ለሹኩር ታረደ። ለካ የዋሻውን እግረኛ ሲዲቁል አክበርን "አትዘን አላህ ከ’ኛ ጋር ነው" እንዳሏቸው አብሽር አንተ ከ’ኛ ጋር ነህ ብለው ቀድመው እያባሸሯቸው ኖሯል። ለነገሩ ጌትዬውስ በወለላው ቃሉ "ላኸውፉን ዓለይሂም ወላሁም የህዘኑን!" ያለው እነሱን አይደል? በሁለቱም ዓለም ፍርሃት የለባቸው፣ ጭንቅ አያገኛቸው!
ሰይደቲ_አቲቃ

አሏሁመ ሶሊ አላ ሰይዲና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም💚💚💚
@abduftsemier
@abduftsemier
#ጥበቃ

ታዋቂው የሀዲስ ዘጋቢ እና የሰሃባ ተማሪ (ረዲየሏሁ ዐንሁም) ሙሐመድ ቢን ሲሪን (ረሂመሁላህ) በአንድ ወቅት ከሰዎች ጋር እየተጓዙ ሳለ መሸባቸውና በወንዝ ዳርቻ ላይ ለማደር ወሰኑ። ማደሪያ ሲያዘጋጁ የአካባቢው ሰዎች ወደ እነርሱ ቀርበው እንዲጅ አሏቸው “ከዚህ ቦታ ሂዱ እዚህ ለማረፍ የሚሞክር ሁሉ ይዘረፋል። ይህንን ሲሰሙ ቡድኑ በሙሉ ዕቃውን ጠቅልለው ወደ ሌላ ቦታ ሄዱ - ከመሐመድ ቢን ሲሪን (ረሂመሁላህ) በስተቀር። እሳቸው ባነበቡት የጥበቃ አያት በሚሰጠው ደህንነት በመተማመን ብቻቸውን ምንም ሳይፈሩ ቀሩ።

ከዚያም ሙሐመድ ቢን ሲሪን (ረሂመሁላህ) የተከሰቱትን ክስተቶች እንዲህ ብለዋል:- “ወንበዴዎቹን ሳይ ገና አልተኛሁም። የተመዘዘ ሰይፍ ይዘው ነበር። ከሰላሳ ጊዜ በላይ ሊቀርቡኝ ቢሞክሩም መቅረብ አልቻሉም። ደህናና ሰላማዊ ሆኜ እስከ ጠዋት ድረስ በደንብ ተኛሁ። ሲነጋ እቃዬን ሰብስቤ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ስጓዝ ከዘራፊዎቹ አንዱ ግዙፍ የሆመ ቀስት ተሸክሞ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ቁጥቋጦ ውስጥ አጋጠመኝ። ጠራኝና “አንተ ሰው ነህ ወይስ ጂን?” ሲል ጠየቀኝ። "ሰው - ከአደም (ዐለይሂ ሰላም) ዘሮች" ስል መለስኩለት። ይህን ሲሰማ ደነገጠ፡- “ግን ሚስጥርህ ምንድን ነው? ከ70 ጊዜ በላይ ልናገኝህ ብንሞክርም በብረት ግንብ ተዘጋግተናል። እኔም መለስኩለት፡- “ምስጢሩ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ከነብይ (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) የነገሩኝ ሐዲስ ነው፡- “በሌሊት ሰላሳ ሶስት የቁርኣን አንቀፅ ያነበበ ከሰው ሸር ፤ ከአዳኝ አውሬ፤ በቤተሰቡና በሀብቱ ከሚደርስ አደጋ ይጠበቃል እስከ ማለዳ ድረስ ፍጹም ደኅንነት እና ምቾት ይኖረዋል።” ሐዲሱን ዘግቤ ስጨርስ ውስጡ በጣም ተነካ ከፈረሱ ላይ ወርዶ ቀስቱን ሰበረ። "በአላህ ተአላ ስም ዳግም ወደ ዘረፋ ህይወት እንደማይመለስ ቃል ገባ።"

በሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሱት አንቀጾች፡-
1. ሱረቱ በቀራህ (ቁጥር 1-5፣ 255-257፣ እና 284-286)
2. ሱረቱ አዕራፍ (ቁጥር 54-56)
3. ሱረቱ በኑ ኢስራኢል (ቁጥር 110-111)
4. ሱረቱ ሳፋት (ቁጥር 1-11)
5. ሱረቱ ረህማን (ቁጥር 33-35)
6. ሱረቱ ሐሽር (ቁጥር 21-24)
7. ሱረቱ ጂን (ቁጥር 3-4)

@abduftsemier
@abduftsemier
#የረቢዕ_ሽታ

ውዳችን ላይ የለይል ሰላት ፈርድ ነበር፣ ለሊቱን እግራቸው እስኪሰነጠቅ ይቆማሉ፣ ሲደክማቸው አንድ እግራቸውን ከፍ ያደርጋሉ፣ ድጋሚ ሲደክማቸው አንዱን አሳርፈው፣ ሌላውን ያነሱና ይቀጥላሉ። ይህን የሚመለከተው አላህ በቁርአኑ እንዲህ አላቸው ...

"ጧ . ሓ ....
ቁርአንን ባንተ ላይ አንድትቸገር አላወረድንም።" ጧሃ÷1
ከዛም ከለሊቱ ትንሽ ማረፍ ጀመሩ!
ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይኢ!

❤️አህለን ወሳህላ ያ ሙሸሪፈ ረቢዒ❤️

@abduftsemier
@abduftsemier
#ረቢዑል_ኑር

'ወማ አርሰናልካ ኢላ ራህመታን ሊል-አለሚን (ቁርኣን 21፡107)፣ "(ሙሐመድ ሆይ) ለዓለማት እዝነት አድርገን እንጂ አላክንህም።" ነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለዓለማት እዝነት ላካቸው።

“የመውሊድ ወር የቅዱስነታችን ወር ነው። ይህ የተቀደሰ በረካ የተሞላ ወር ኢንሻአላህ የመልካምነት መጠቀሚያ ይሆናል። ዘንድሮ ትንሽ ከብዶ አልፏል። ባለፈው አመት ይህን ያህል ጭቆና አልነበረም። ጭቆና በበዛ ቁጥር። ከዚህ በተቃራኒ ግን አላህ አዛ ወጀላ የነብያችንን ﷺ ወር የእዝነትና የበረካ ወር አድርጓታል።

ስለዚህ በዚህ ወር ሰለዋት ባደረግን ቁጥር በነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ “ሰለዋት ባደረግክ ቁጥር ‹ወአለይኩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም› በማለት ይመልሳሉ። አስር፣ አምስት፣ መቶ ወይም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ሰለዋት ቢያደርግ አላህ አዛ ወጀላ ለሁሉም ምላሽ እንዲሰጡ አስችሏቸዋል።

ነብያችንን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሚያከብር አላህ ያከብረዋል። ነብያችንን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን የማያከብር ሰው የቅንጣትን ዋጋ የለውም፤ አላህ ﷻ ይጠብቀን። አላህ ﷻ ይህን የተቀደሰ ወር በረካ የተሞላ ያድርግልን፤ የተጨቆኑትንም ያድናቸው። አሚን!

@abduftsemier
@abduftsemier
#ማመን

በአንድ ወቅት ግመሉን ይዞ ከገበያ ወደ ቤቱ የሚመለስ አንድ ሰው ነበር፤ ጥሩ ቀን በማሳለፉ፣ በመንገድ ላይ መስጂድ ሲመለከት ለአላህ ምስጋናውን ለማቅረብ ወሰነ።
ግመሉን ውጭ ላይ ትቶ የሶላቱን ምንጣፍ ይዞ ገባ፤ ለሰአታት አላህን በማመስገን እየፀለየ እና ወደፊት ጥሩ ሙስሊም እንደሚሆን፣ ድሆችን እንደሚረዳ እና የማህበረሰቡ ምሰሶ እንደሚሆን ቃል ሲገባ ቆይቶ፤ ሲወጣ ሰማዩ ጨልሞ ነበር፤ ውጪ ላይ የተዋትን ግመል ወዲህና ወዲያ እያለ ሲፈልግ አጣት!
ወዲያው ሰውዬው በሀይለኛው ተናደደና እጁን ወደ ሰማይ እየጠቆመ: -
"አላህ ሆይ! ይህን እንዴት ልታደርገኝ ቻልክ? ሙሉ በሙሉ በአንተ ታምኜ ሳለሁ ግመሌ ለምን ጠፋ?”
የሚያልፍ ሱፊ ደረሳ ሰውዬውን ሲጮህ ሰምቶ ለራሱ ሳቀ።
"ስማ ወዳጄ አላህን እመን ግን ግመልህን እሰር!"

ሞኝ ከፍ ሲል ትልቅነት ይመስለዋል፤
አወዳደቁ መክፋቱን መች ይረዳዋል፤
እኛም እንታረቅ ከሰይደል ውጁድ፤
በረቢዐል አወል በሀድራው እንመድድ፤
ጊዜው ለኛ ይሁን ዑመቱን እንካድም፤
አንቱን የጠየቀ እምቢ አይባልም፤
ያሰብነው ኒያ ተቅዋ ተጨምሮ፤
ሁሉም ይፈረጅ ሰይዲ ዘንድሮ!

*አላህ ታማኝ ነው፤ ግን ታምነህ ከልብህ የሰጠህውን ነው።
*አላሁሙ ሷሊ አላ ሀቢቡሏህ፤ ወአላ ኡመቲ ረሱሊላህ!

@abduftsemier
@abduftsemier
#የጀነት_በር .....

አንድ ሴት ነበረች ወንድ ልጇን ዘውትር በሰዎች ፊት ትደበድበው ነበር.. ልጁ ግን ለምን ተመታሁ ብሎ አያለቅስም ምንም ቃል አይናገርም ለማምለጥም አይሞክርም ነበር....  ከአመታት ቡሀላ ልጁ ወጣት ሆነ እና አሁንም በየቀኑ እናቱ በሰዎች ፊት ትመታዋለች ግን አሁንም አይቃወምም ነበር ...  እናቱም እያረጀች መጣች እናም አንድ ቀን መታችው ሰውዬውም ፂሙ እስኪረጥብ ድረስ አለቀሰ... እናቱ ከእርሱ ስትርቅም አንድ ሰው መጣና እስከዛሬ ስትመታህ ምንም ብለህ አልቅሰህም አታቅም ዛሬ ለምን አለቀስክ? ሲል ጠየቀው..
ሰውየውም እያለቀሰ እንዲህ አለ : እንዴት አላለቅስም? እናቴ እየደከመች ነው የጀነት በር ሊዘጋ እኳ ነው!!

  *አላህ ሆይ የእናቶቻችንን ሀያት አርዝምልን፤ የታመሙትን ፈውስልን፤ የሞቱትን ፊርደውስ ወፍቅልን!
#መገን_ረቢዕ
   
@abduftsemier
@abduftsemier
#የአላህ_ፍራቻ

ሰውነቱ በጣም ልዩ የሆነ ሚስክ ሽቶ ጠረን የሚወጣው ሰው ነበር። አንድ ወዳጁ አንድ ቀን እንዲህ ሲል ጠየቀው፡- “ሁልጊዜ በአንተ ላይ የሚሸተው ይህ አስደናቂ መዓዛ ምንድን ነው? ደጋግመህ ስትጠቀም ለሚስክ ሽቶ ብዙ ገንዘብ እያወጣህ መሆን አለበት?” ሰውየውም “በአላህ እምላለሁ! ሚስክን ገዝቼ አላውቅም አረ ተቀብቼውም አላውቅ!” ጓደኛውም በመገረም “ታዲያ መዓዛህ ከየት የመጣ ነው?” ሲል ጠየቀው። ጥያቄውን ለመመለስ ፍላጎት ስላልነበረው “ለምን ትጠይቀኛለህ?” አለው። ጓደኛው “በምትነግረኝ ነገር አላህ ተዓላ በሆነ መንገድ እንድጠቀም እንደሚፈቅድልኝ ተስፋ አደርጋለሁ” ሲል ገለጸ። በጓደኛው ንግግር በመገፋፋት፤ በመጨረሻም የሚከተለውን ነገረው። "በወጣትነቴ በጣም ቆንጆ ልጅ ነበርኩ። አባቴ ነጋዴ ነበር እና ጊዜዬን እሱን በማገዝ አሳልፋለሁ። አንድ ቀን አንዲት አሮጊት ሴት ወደ ሱቅ መጥታ ጨርቅ ገዛች፤ ገንዘቡን የምትከፍልበት ገንዘብ ስላልያዘች አባቴን አብሮ ቤቷ ሄዷ ብር የሚቀበል ሰው እንዲያዘጋጅ ነገረችው። አባቴ አብሪያት እንድሄድ ነገረኝና አንድ ትልቅ ቤተ መንግሥት ፊት እስክንቆም ድረስ ተከተልኳት። አሮጊቷ ወደ ሚገርም ግቢ አስገቡኝ፤ ስገባ እይታዬ ወደ አንዲት ቆንጆ ወጣት ልጅ ሆነ ከሐር ትራስ ላይ ከፍ ባለ ወንበር ላይ ተቀምጣለች። ባየችኝ ቅጽበት፣ በውበቴ ደነገጠች እና አብሪያት እንድቀመጥ ጠየቀች። እኔም እምቢ አልኩኝ፤ የእኔ እምቢተኝነት ወደ እኔ እንድትወርድ አነሳሳት። ከዚያም በፍቅር ስሜት እየጎተተች ወደ ራሷ እንድቀርብ ታረገኝ ጀመር። በእውነተኛ ችግር ውስጥ ነበርኩ። ከእቅፏ ለማምለጥ መጸዳጃ ቤት መጠቀም እችል እንደሆነ ጠየቅኋት። ትዕግሥት ብታጣም ወደ መጸዳጃ ቤት መራችኝ፤ መጸዳጃ ቤት ከገባሁ ቡሀላ በሰውነቴ፣ በልብሴ እና በፊቴ ላይ ቆሻሻ ቀባሁ። ከመጸዳጃ ቤት ስወጣ በጉጉት የምትጠብቀው ልጅ የመልከ መልካም ወጣት ሳይሆን በሰው ቆሻሻ የተሸፈነ ሰው እይታ እና ሽታ ተቀበለች! የፍላጎቷ ነበልባል፣ በአንድ ጊዜ፣ ጠፋ እና ለአገልጋዮቿ በፍርሃት እና በመጸየፍ ጮኸች፣ “ይህ እብድ ነው! ወደ ውጪ ጣሉት!” አለች፤ ያለምንም ችግር ወደ ውጪ ወጣሁ በአጋጣሚ ከእኔ ጋር አንድ ዲርሃም ነበረኝ። ስሄድ ሳሙና ገዛሁ እና ወደ ወንዙ ወርጄ ሰውነቴን እና ልብሴን ከቆሻሻ ከአጸዳሁ ቡሀላ ወደ አባቴ ተመለስኩ ግን ስለተፈጠረው ነገር አንድም ቃል አልተናገርኩም። በዚያ ሌሊት አንድ ጥሩ መዓዛ ያለው መልከ መልካም ሰው ወደ እኔ የመጣበትን ሕልም አየሁ። ማን እንደሆነ ጠየቅኩት እሱም ጅብሪል (ዐለይሂ ሰላም) ነው ሲል መለሰልኝ። እንዲህም አለኝ፡- “አላህ ተአላ ጀናን እንዳበስርህና ሽቶዋን እንዳረግብህ ላከኝ በኃጢአት ላለመውድቅ ባደረግከው ድርጊት አላህ ተደስቷል። ከዚያም እጆቹ በፊቴ፣ ሰውነቴና ልብሴ ላይ አልፎ ሄደ። በማግስቱ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ፣ እስከ ዛሬ ድረስ ከሰውነቴ ውስጥ ለዘላለም የሚሸተውን ጥሩ መዓዛ አገኘሁ።"

(አት-ተርጊብ ወተረሂብ ሊል ያፊኢ ገጽ-165)

@abduftsemier
@abduftsemier
#እንኳን_አደረሳችሁ!

<እንዴትና በምን ልገልፀው እንደምችል የሚቸግረኝ እለት ነው "መውሊድ"። ... ከበዓላት (ዒዶች) ተርታ ማድረግ ማሳነስ ሆኖ የሚሰማኝ የላቀ ቀን ነው። ... ልክ ነው: "መውሊድ በአል አይደለም"... ይልቁንም የአመቱን ቀናት ሁሉ ወደ ኢድነት(በአልነት) የቀየረ የማይተመን ድንቅ ስጦታ እንጂ። ልዩ ፍቅርና እዝነት የዘነበበት ልዩ ቀን!!!>

  አላሁመ ሷሊ ወሰሊም አላ ሀቢቢና ወሰይዲና ሙሐመድ!!

   #ሸይኽ_ጀሚል_ይርጋ (ብዕሩሏህ)

@abduftsemier
@abduftsemier
"እንደ ሃይማኖት ያለንበት ደረጃ የማንም አይሁድ መጫወቻ የውርጋጥ አፍ መክፈቻ ሁነናል፤ ሶሪያ፣ ኢራቅ፣ የመን፣ ፍልስጤም.. ወዘተ እየሆነ ያለው ይሄው ነው። በቁጥር አንሰን አይደለም ግን ታላቁ ነብይ ሰዐወ እንዳሉት "የባህር ላይ አረፋ ሆነናል.."። መስጂድ ገብቼ ኢማኔን ላድስ ስትል የእገሌ ግሩፕ እያሉ ግራ ያጋቡሀል፤ ኹሩጅ ስትል የእነንትና ጀመዓ እያሉ ይወሰውሱሀል። ሌላው እንደ ሀገር ያለንበት አዘቅት እጅግ የከፋ ነው፤ ነገ የአላህ ነው እንጂ ነገን የሚያጨልም በሚመሰል መልኩ ነው እየተሰራ ያለው። ከዚህ ሁሉ መውጣት የሚቻለው እራስህን በመገንባትና ለቁርዐን፣ ለአዝካር ጊዜ መስጠት ይገባል.. የሆኖ ሆኖ ብሩህ የሆነውን ቀን አላህ ያሳየን።"
አላሁመ ሷሊ አላ ሀቢቢከል ሙስጠፋ!

@abduftsemier
@abduftsemier
ሀበሻ መርከዝ የ6 ወር ሹራ ባመረ መልኩ ተጠናቋል። አልሀምዱሊላህ!! ሀቅ ከፍ ብሎ ባጢል ሚንኳታኳትበት ዘመን ቅርብ ነው። ኢንሻአላህ!!

@abduftsemier
@abduftsemier
<ሀበሻ ገብቶ እንደ ሙፍቲ ያሉ ታላላቅ የሀበሻ ዑለሞችን ያልተገናኝና የንጉስ ነጃሺን ዶሪህ ሳይዘይር የተመለሰ ምነኛ ከሰረ ድንቄም የአለም አሚር።>

@abduftsemier
@abduftsemier
#ኢስቲኻራ

አንድ ሰው በተወሰነ ጉዳይ ላይ ከአላህ ﷻ መመሪያ ለመጠየቅ ከፈለገ ሰላተል-ኢስቲኻራን በሚከተለው መልኩ መስገድ ይችላል።

1. ከኢሻ ሰላት በኋላ እና ከመተኛታችን በፊት።
2. መመሪያ ለመፈለግ በማሰብ ሁለት ረከዓዎችን መስገድ (ኒያህ ለኢስቲኻራ)።
በእያንዳንዱ ረከዓ ሱረቱል ፋቲሀን ካነበቡ በኋላ ሱረቱ አል-ኢኽላስን 3 ጊዜ ማንበብ።
3. ሶላትን ከጨረስክ በኋላ ጭንቅላትህ ወደ ሰሜንና ፊትህ ወደ ቂብላ አዙረህ ተኛ።
4. ዚክር፦ "النور الظاهر الباسط"
እንቅልፍ እስኪወስዱ ድረስ ያለማቋረጥ፦
"አኑር ዛሂሩል ባሲጥ"
5. ኢንሻአላህ ﷻ የጥያቄህ መልስ በህልምህ ውስጥ ይታያል።

ከሰይዲና ሼክ አብዱልቃዲር ጂላኒ አል-ባግዳዲ የተተረከ የኢስቲኻራ አሰራር ሌሎች ዘዴዎችም አሉ ነገርግን በረጅም ጽሁፎች ምክንያት ሁሉንም ነገር ከመጥቀስ እቆጠባለሁ።
ይህ የኢስቲኻራ አሰራር መንገድ አላህ ﷻ በታቀደው ጉዳይ ላይ ግልፅነትን እና መመሪያን ለመጠየቅ የታሰበ ሲሆን ይህም የተሻለውን ተግባር እንደሚገልፅ በመተማመን ነው።

@abduftsemier
@abduftsemier
#የተባረከችዋ_ሌሊት 

አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ  ውድ Abdu Ft Hasu ቤተሰቦች ስላለንባት የሻዕባን 15 ሌሊት ትሩፋቶች ጥቂት እንተዋወስ በሚል  ተከታዩን ጽሁፍ ወደናንተ ለማድረስ ወደድኩ!

🍃ሻዕባን 15  የጌታችን በረካዎች ከሚፈሱባቸው የተመረጡ ቀናቶች መሀከል የምትመደብ  ቀኗ ደምቆ  የሌሊቷ  ዱዐ ሰምሮ የምታልፍ  ኢላሂይ ስጦታ ናት።

   🌱ሰይዲና አቡ ኡማማህ በዝገቡት ሐዲስ ረሱላችን(ሶላት እና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን)  ተከታዩን ብለዋል፡
             •• ዱዐ(ጸሎት)  ምላሽ የማያጣባቸው 5 ሌሊቶች አሉ። እነርሱም  የረጀብ የመጀመሪያዋ ሌሊት፡ ^የሻዕባን 15ተኛ ሌሊት ፡በሐሙስ እና ጁመዐ መሀከል ያለችዋ ሌሊት፡ የኢድ አል ፊጥር ሌሊት እና   የኢድ አል አድሃ (የዙል ሂጃ 10ኛ ሌሊት ናቸው)።
                  📓ይህንን ሐዲስ  ኢማም ኢብን አሳኪር  ታሪኽ አል ዲሚሽቅ በተሰኘው ገናና ኪታባቸው ላይ በሰነዳቸው አስፍረውታል።

         🍃 በሻዕባን 15 ዙሪያ የመጡ በርካታ ሰሂህ፡ሃሰን እና ደኢፍ(ደካማ) ደረጃ የሚሰጣቸው ሐዲሶች  መጥተዋል፡እነዚህን ሐዲሶች እንዴት ማስተናገድ እንዳለብን ኋላ ላይ የምናየው ይሆናል፡በአሏህ ፍቃድ።

🌴የሻዕባን 15 ሌሊትን እንዴት እንቀበላት?
         🍃ኡዱአችንን አሟልተን ካደረግን በኋላ  ተሂየተል ዉዱእ እንስገድ፡ቀጥለንም   በምንሰግደው የሱና ሶላት ላይ   ከፋቲሃ ምዕራፍ በኋላ  አየተል ኩርሲይን አንዴ  ፡ሱራህ አል ኢኽላስን 3ቴ እናንብብ።

      🍃 በተጨማሪም  ከመግሪብ ሶላት በኋላ 4ጥንድ ጥንድ ሶላቶችን(8ረከዐ)  እንስገድ፡በነዚህ ስግደቶች ላይ  በእያንዳንዱ ረከዐ  አየተል ኩርሲይን አንዴ   ሱራህ አል ኢኽላስን 15ግዜ እንቅራ።

  🌴ከማለዳው የጸሃይ መውጪያ ንጋት በፊት ምን እንቅራ?
         ^IslamWay^ በተባለው የኢስላማዊ ጥናቶች መወያያ  ምህዳር ላይ እንዳየሁት   ፡የሻዕባን 15ሌሊት ተጠናቆ  ብርሃን ከመፈንጠቋ በፊት ተከታዩን ዚክር    ያነበበ ሰው   ~አሏህ የ40 አመት ወንጀሉን ይሰርይለታል፡ 40 ውብ ሁረል አይኖችም እርሱን በመጠባበቅ  ይሞሸራሉ~      ተዝካሩ ቀጣዩን ይመስላል
🍃3 ግዜ በረሱላችን ላይ ሶለዋትን ካወረድን በኋላ  ቀጣዩን አጭር ዚክር እንበል
           لا حول ولا قوت إلا بالله العلي العظيم
ሃይልም ሆነ ብልሃት  የለም  ከፍ ባለውና ታላቅነቱ ወደር  በሌለው ጌታችን አሏህ ቢሆን እንጂ

ይህንን ዚክር 40 ግዜ ደጋግመን ከቀራን በኋላ   ተጨማሪ 3 ሶለዋቶችን  ማውረድ እንዳንዘነጋ፡በአሏህ ፍቃድ  ሃጃችን መቋጫውን ያገኛል።

     🌴ረሱላችን ስለዚህች ሌሊት  ከተናገሯቸው ትሩፋቶች መካከል
    ••አሏህ  በሻዕባን 15 ላይ  የተለየ ክብር እና እዝነትን ሾሟል፡    በዚህች ሌሊት ላይ  አሏህ   ከበኒ ከልብ  ጎሳ በጎች ጸጉር የበረከቱ ኡማዎቼን  ይቅር ይላል••
     ልብ በሉ * በኑከልብ የተባሉት ጎሳዎች በርካታ  በጎች የነበሯቸው የዐረብ ከበርቴዎች ናቸው፡ታዲያ በዚህች ሌሊት  ከነዚህ   ሜዳ  ኮረብታውን ከሞሉ በጎችም አልፎ በጸግራቸው ልክ  ምህረት የሚወርድልን ከሆነ   መዘናጋትን ለምን እንመርጣለን?

     🌴 የሞቱ ሰዎች ነፍስ(አርዋሁል አምዋት) እና የዚህች ሌሊት ቁርኝነት፡
          ••በዚህች የተባረከች ሌሊት ላይ የሞተ ሰው ነፍስ   በህይወት ወዳሉ ሰዎች መኖሪያ ሄዳ እንድትዘይር  ፍቃድ ይሰጣታል ፡ይህች የአማኝ ነፍስ ወደ ህያዋኖቹ መንደር ከዘለቀች በኋላ እንዲህ ትላለች።
         °እናንት በህይወት ያላችሁ ሰዎች! እናንተ  የኛን ሓብት ወረሳችሁ፡በልጆቻችንም ተጠቃቀማችሁ ! አደራችሁን   ለኛ የምትሰጡትን አጅር(የምንቀራላቸው ቁርዐን^የምንጾምላቸው ጾም እና ሶደቃ መሰል ተግባራቶች)    አታቋርጡብን ! እኛ ሞተናልና  መዝገባችን ተዘግቷል   የናንተ መዝገብ ግን አዲስ ስራዎችን ትቀበላለች።••

       💡ጥቆማ-በዚህች ሌሊት   ለሞቱብን መሻይኾች ፡እናትና አባቶቻችን፡ወንድምና እህቶቻችን    ሶለዋት እያወረድን  የቻልነውን ቁርዐን ከቀራንላቸው   ነፍሶቻቸው  ተደስተው ወደመጡበት የነፍስ ዐለም ይመለሳሉ።

     🌴በሻዕባን 15 ሌሊት   ቀደመን የሞቱ አማኞችን ቀብር መዘየር እና ለእነርሱ ምህረትን መለመን
   ታላቁ የሐዲስ ሊቅ  ኢማም አል በይሐቂይ በሰነዳቸው በዘገቡት ሐዲስ    እናታችን አኢሻእ  ስለ ረሱላችን እንዲህ ትላለች
               🍃 •• በአንድ የሻዕባን 15 ሌሊት ላይ ረሱላችንን አጣኋቸውና  እርሳቸውን ፍለጋ ከቤት ወጣሁ። በመዲና የአማኞች መካነ መቃብር  (በቂእ) ላይም አገኘኋቸው። ለሙታን አማኞች ይቅርታ እና ምህረትን እየጠየቁ ነበር።

  🌴በሻዐባን 15 ላይ መጾም
     ኢብን ሂባን የተባሉት እውቅ የሐዲስ ምሁር  እንደዘገቡት  ረሱላችን የሻዕባን 15 ሌሊትን አስመልክተው ተከታዩን ተናግረዋል
    ••የሻዕባን 15 ሌሊትን የተጣዳችሁ ግዜ ሌሊቱን(በአምልኮ) ከእንቅልፍ ራቁ፡ ቀጣዩንም ቀን ፁሙ።
      ኢማም አል በይሐቂይ በዘገቡት ተጨማሪ ሐዲስ ላይም ሰይዲና አባሁረይራህ  ረሱላችን በኹጥባቸው ላይ  ተከታዩን ሐዲስ እንዳስተላለፉ  አስተምረዋል።
••ሰዎች ሆይ  የሻዕባንን ወር በመጾም ሰውነታችሁን አቅልሉ`አጥሩ።በዚህም ምክንያት  የረመዷን ወር ጾም  ቀለል ይልላችኋል።

             የሻዕባንን 3ቀናቶች የጾመ ሰው  ያለፈ ወንጀሉ ሁሉ ይማርለታል••
      📓ሙሀዲስ ኢብን ማጃህ  በሱነናቸው  ሐዲስ ቁጥር 1388   ላይ እንዳሰፈሩት   ሰይዲና ኢማም ዐሊይ (ከረመሏሁ ወጀሀህ)   ካለፈው ተመሳሳይ የሆነ ሐዲስ  ከተጨማሪ ሃሳብ ጋር ዘግበዋል
           ••ጌታችን አሏህ  በዚህች ሌሊት ላይ የእዝነት መላዕክቶቹን ወደምድር ያወርዳል፡እንዲህም ይላል
   °ምህረትን የሚፈልግ  ሰው ይኖራልን? በመሀሪነቴ የምምረው ፡   ከኔ ረድኤት ሪዝቅን የሚፈልግ ሰው ይኖራልን?   ከችሮታዬ የማጠቃቅመው?••
           አንዳንድ ወንድሞቻችን (የሰለፊይ አስተሳሰብ ተከታዮች)   በዚህች ሌሊት ላይ የሚወርደው አሏህ እራሱ  በዛቱ ነው እንደሚሉ  ይታወቃል፡ ይህ  እሳቤ  በበርካታ የአህለሱና ወልጀመዐ ሊቃውንቶች ዘንድ የተወገዘ  እና  ለጌታችን አሏህ  ክብር የማይመጥን እይታ ነው።

           መላዕክት ወደምድር ሳይወርዱ በራህመት የመሸፈን ችሎታ የላቸውምና ወደ ምድር በአካላቸው ይወርዳሉ፡ ጌታችን አሏህ ግን  ይወርዳል ይወጣል   ይመጣል ይሄዳል ፡ የማይባል  አንድንም የፍጡር ባህሪ ያልተላበሰ  ለሰው ልጅ አእምሮ ያልተገለጸ   የምሉዕ ባህሪ ባለቤት ጌታ ነው!  ስለዚህ  ራህመቱን ለኛ ለመስጠት  ወደ የትኛውም ቦታ መምጣት አያስፈልገውም ! ከጅምሩም  ጌታችን ቦታን ይፍጠር እንጂ ቦታ እርሱን አትገልጸውም!

      🍃 ወደ ዋናው ርዕሳችን ስንመለስ፡    የሻዕባን 13 ፥14  እና 15ተኛ ቀናቶችን  የምንችል ሰዎች  መጾም ይኖርብናል።  *ብርሃናማ ሌሊቶችን ጹሙ የሚለው ሐዲስን ይህንን ሃሳብ ያግዛል*

🌴የዚህችን ሌሊት እዝነት የሚከለከሉት ሰዎች እነማን ይሆኑ?

@abduftsemier
@abduftsemier
#ረመዳን ከሪም
ለተወዳጁ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስና ለመላው ሙስሊም ያማረ የደመቀ ረመዳን ይሁንልን!
"እውነት ከሰባት ምድር በታች ቢቀብሩት መዝለቁ አይቀርም፤ ሀሰትን ከሰባት ሰማይ በላይ ቢሰቅሉት መውረዱ አይታበይም።"
*ይህ ንግግር የታላቁ ሸየኹል አላማ ሰይዲ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ ነው፤ በዘመናችን የምናየውም የውሸትን ከፍ ብሎ መሰቀል ቢሆንም፡ አልሀምዱሊላህ እያደር እውነት እራሷን እየገለጠች ነው።

@abduftsemier
@abduftsemier
ከ20ኛው ክፍለ ጊዜ ወዲህ አለምና ሙስሊሙ እኚህን የመሰለ ፍትሀዊ መሪ አይቶ ሰምቶም አያውቅም!! የበዳዬች ዱላ የጭቁኖች ከለላ የመሪዎች ቁንጮ። ለኔ ኸሊፋዬ!! አያቶላህ ሰይድ አሊ ኻሚናኢ!!

@abduftsemier
@abduftsemier
ቁርኣን ላለመቅራታችን ምንም ምክንያት የለንም‼️

በዱንያ ላይ እያለን ሌሎች ነገሮችን
ማንበብ ችለን የአላህ ቃል(ቁርኣንን)
ጊዜ ሰጥተን ባለመማራችን እና
ባለመቅራታችን አላህ ዘንድ ምክንያታችን ምን ይሆን⁉️

🎙🎙 ታላቅ ብስራት ለቁርአን እውቀት ፈላጊዎች በሙሉ !!

📖 አል-ነጃሺ ኦንላይን የቁርአን ንባብ ማዕከል ⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
     በስራ ፣ በጊዜ ፣ በቦታ ምክንያት ቁርኣን አለመቅራትዎ አሳስቦታል?

ጊዜና ቦታ ሳይገድብዎ ባሉበት ሆነው በሚመችዎ ሰዓት ኦንላይን ማስቀራት ጀምረናል።
አል-ነጃሺ የቁርኣን ማዕከል 
ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ልምድ ባላቸው የቁርኣን ሃፊዞች

ቁርአንን ባሉበት ቦታ ሆነው በተመቾት ሰአት የእጅ ስልኮን ብቻ በመጠቀም ይማሩ። በየትኛውም የእድሜ እና የቂርአት ደረጃ ላይ ቢሆኑም ይስተናገዳሉ።

     ⚡️  ቃኢደቱ ኑራኒያ ለጀማሪዎች
    
     ⚡️ ነዘር ከመሰረታዊ ተጅዊድ ጋር
    
     ⚡️ የተሟላ የተጅዊድ ትምህርት
   
     ⚡️  የቁርዐን ሂፍዝ  ከሙራጀዐ ጋር።

  𒊹︎︎︎ የቁርዐን ትምህርት አሰጣጥ ሁኔታ
አንድ ተማሪ ከተመዘገበ በኋላ የተመደበለት ኡስታዝጋ
☞︎︎︎ በዙም አፕልኬሽን
☞︎︎︎ በቴሌ ግራም
☞︎︎︎ በዋትስ አፕ
☞︎︎︎ በኢሞ እንዲሁም
☞︎︎︎ በተጨማሪ መንገዶች የሚሰጥ ይሆናል።
  𒊹︎︎︎ የቁርአን ቂረአት የሚሰጥበት ጊዜ
☞︎︎︎ በሳምንት 5 ቀን   
☞︎︎︎ በሳምንት 3 ቀን 
☞︎︎︎ በቀን ለ 30 ደቂቃ ለአንድ ተማሪ
☞︎︎︎  ተማሪው በሚመቸው ሰአት
ልብ ይበሉ ማዕከላችን በአላህ ፍቃድ በአጭር ግዜ ብቻ ቁርኣንን ማንበብ እንዲችሉ ያደርጋል
📋 ለመመዝገብ እነዚህን መንገዶች ይጠቀሙ
  ☞︎︎︎ @Besam21
2025/06/28 00:46:38
Back to Top
HTML Embed Code: