This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሆላንድ ዋና ከተማ አምስተርዳም የፍልስጤምን ነፃነት ለመጠየቅ የወጣው ከ250,000 በላይ የሚሆን የሕዝብ ማዕበል በዚህ መልኩ በድሮን ተቀርጿል። ቪዲዮውን መጀመሪያ ላይ ሳየው የቲማቲም ማሳ ወይም ክምር የሀላባ ዛላ በርበሬ መስሎኝ ነበር።
🍅🍅🍅 🌶️🌶️🌶️


http://www.tg-me.com/abuafnanmoh
👍365🔥2
48👍8
Mohammed Ahmed Official
Photo
ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ነበር። ከኮምቦልቻ ወደ አዲስ አበባ ስጓዝ፣ ጽድት ባለች ሚኒባስ ጋቢና ውስጥ ተቀምጬ ነበር። ፎንተኒና አካባቢ ስንደርስ ከጎኔ ከተቀመጠው ተሳፋሪ ጋሪ ሞቅ ያለ ትውውቅ አደረግን። እሱ አብነት አካባቢ ተውልዶ ያደገ የአዲስ አበባ ነዋሪ ነው። በወቅቱ ኮምቦልቻ የመጣው የታመሙትን የባለቤቱን አባት ሊጠይቅ ነበር።

​ከዚያን ዕለት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ አልፎ አልፎ እንደዋወላለን። መርካቶ ውስጥ በጣም ጥሩ ሥራና ገቢ የነበረው ታታሪ ወንድም ነበር። ከተቸገሩ ሰዎች ጎን ለመቆም እጁን ቶሎ የሚዘረጋ ደግና ቸር ሰውም ነበር። በብዙዎች ህይወት ውስጥ የበጎነት አሻራ ጥሎ ያለፈ ሰው።

​ዛሬ ጠዋት ግን ባልተለመደ ሁኔታ ስልክ ደወለልኝ። በህይወቴ ይጠይቀኛል ብዬ የማላስበውን ጥያቄ በከፍተኛ ጭንቀት አነሳ። ❝ሙሐመድዬ፣ ለልጆቼ ስል መኖር እፈልጋለሁ። በተለይ አሁን ላይ ለመኖር ጓጓሁ። ነፍሴን ለመቀጠል የሚያግዘኝ መድኃኒት መግዣ እጅ አጠረኝ። ትላንት ብዙ ነገሮችን የማደርግ ሰው፣ ይህን ስጠይቅህ ግራ እንደምታጋባ እረዳለሁ ❞ አለኝ። በእርግጥም የሁኔታው ክብደትና ንፅፅር ግራ አጋባኝ።

በህመም አልጋ ላይ የወደቁ ሰዎችን ታክመው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ምክንያት የነበረው ወንድም፣ ዛሬ ላይ በከፋ የሳንባ ደም መርጋት (Pulmonary Embolism - PE) ህመም ተይዞ አልጋ ላይ ወድቋል። ከታች በምስሉ ላይ የሚታየውን፣ አደገኛ የደም መርጋት ለማከም እና ለመከላከል የሚያገለግል ፀረ-የደም መርጋት (ደም ማቅጠኛ) መድሃኒት ለመግዛት አቅም አጥቷል።

የህክምናው ወጪ እና አስፈላጊው ገንዘብ ስሌት

​የህክምናውን ሂደት ለመቀጠል አስቸኳይ የመድኃኒት ግዢ ያስፈልጋል። ​እያንዳንዱ እሽግ መድሃኒት 14 ፍሬ ይይዛል። ​የአንድ እሽግ ዋጋ 3,955 ብር ነው። ​ወንድማችን በቀን 2 ፍሬ መውሰድ አለበት። ይህም ማለት በየሳምንቱ አንድ እሽግ ያልቃል። ​ቢያንስ ለ 3 ወር (90 ቀናት) ህይወቱን ለማዳን የሚያስፈልገው አጠቃላይ ወጪ 47,460 ብር ነው።

ይህ ወጪ ለእሱ የህይወት እና ሞት ጥያቄ ነው። በችግር ውስጥ ለነበሩት ሁሉ እጁን የዘረጋውን ይህን ወንድማችንን ለመርዳት የሁላችንም ፈጣን ምላሽ ያስፈልጋል። ሁላችንም በአቅማችን የምንችለውን በማድረግ ህይወቱን እናድን! ወንድማችንን ለመደገፍ ፈቃደኛ የሆናችሁ በሙሉ፣
ከስር በተቀመጠው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር የአቅማችሁን ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ።

SHAMEDIN AHIMED MOHAMMED
CBE 1000288221107
Mobile :-
+251909692144

ሙሉ የህክምና ማስረጃዎቹንም በውስጥ መስመር ላቀብላችሁ እችላለሁ።

http://www.tg-me.com/abuafnanmoh
😭94
የሰው ልጅ ከሶስት ዓመት በላይ በተለያዩ ጊዜያት በምናቀርበው የድጋፍ ጥሪ ሁሉ ያለማቋረጥ ሁለት ሺህ ብር (2,000 ብር) እንዴት ሊሰጥ ይችላል? ይህ ለአእምሮ የሚከብድ እውነታ ነው። ​ይህች በጎ አድራጊ እህት ከእኔ ጋር በፌስቡክ ጓደኛ የሆነችው ሚያዝያ 9 ቀን 2014 ዓ.ል ነው። ከሰላምታ በኋላ በቀጥታ የጀመረችው ድጋፍ የሚያስፈልገው ልጅ ወደተቀመጠበት የባንክ ሂሳብ 2,000 ብር በማስገባት ነበር። ​የሚያሳዝነው ፣ እርዳታ የተደረገለት ወንድማችን ህንድ አገር ድረስ ሄዶ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ቢያደርግም፣ ህመሙ የጠና በመሆኑ ብዙም ሳይቆይ ወደማይቀረው ዓለም ተሻግሯል። (አላህ ይማረው)

​ይህች እህት አሁን ደግሞ፣ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ለመድኃኒት መግዣ ድጋፍ ለሚያስፈልገው ወንድም ባቀረብኩት ጥሪ ለመሳተፍ በውስጥ መስመር ብቅ አለች።
​«አሰላሙ አለይኩም! ማሜዋ፣ ሁለት ሺህ ብር አለኝ። አንዷን (አንድ ሺህ ብር ማለቷ ነው) ለአሁን መድኃኒት ለሚያስፈልገው ልጅ እናድርጋት አካውንት ቁጥር ስጠኝ» አለችኝ።

​ለመጀመሪያ ጊዜ ከ2,000 ብር በታች ድጋፍ ማድረጓን ስላስተዋልኩ፣ "ስለ ሁኔታዋ" ማሰብ ጀምሬ ነበር። እሷም ተረዳችኝ መሰለኝ «ማሜ፣ ደመወዝ እስከሚገባልኝ ድረስ ነው። ትንሽ ቢቆይ እንጂ ቀሪውንም በሚቀጥለው የድጋፍ ጥሪ አስገባለሁ» አለችኝ።

አላህ ማንነታቸውን የሰው ልጆች የማያውቋቸው በርካታ ደጋግ ባሮች የሉትምን ???? ወላሂ ይህችን ልጅ እኔም አላውቃትም !!!


http://www.tg-me.com/abuafnanmoh
24👍5😭3
የመጀመሪያ ዙር የዑምራ ጉዞ ምዝገባ ተጠናቋል!

​አውላ የጉዞ ወኪል፣ በተከበሩት ሸይኽ ያሲን ጀማል እና ተወዳጁ ዳዒ ዐብዱረሕማን ሙሐመድ መሪነት ከጥቅምት 5 እስከ ጥቅምት 16 /2018 ዓ.ል ወደ ሁለቱ ቅዱሳን ስፍራዎች (መካና መዲና) የሚያደርገውን የመጀመሪያ ዙር ዑምራ ጉዞ ምዝገባ በስኬት አጠናቋል።

​የጉዞ ወኪላችንን ሲመርጡ፣ የቤተሰባችን አንድ አካል መሆንዎን ያስታውሱ። በተለይም ወላጆቻችሁን እንደ ወላጆቻችን የመንከባከብ ኃላፊነት እና ግዴታ በትከሻችን ላይ መውደቁን በጽኑ እናምናለን።

​ለሚቀጥለው ዙር ምዝገባ ዝግጁ ይሁኑ!

​ለቀጣይ ዙር የጉዞ ልባችሁ የተነሳሳችሁ ምዕመናን፣ ወይንም ስለ ቀጣዩ ጉዞ መረጃ ለማግኘት የምትፈልጉ፣ በሚከተሉት አድራሻዎች እና ስልክ ቁጥሮች ልታገኙን ትችላላችሁ፦

📞 + 251943989999
+ 251911955887
+ 251921555158

ቴሌግራም እና ዋትስአፕ
👉 @afhasmen
👉 +251921555158

ቤተል ፊውቸር ሞል ሶስተኛ ፎቅ - ቢሮ ቁጥር 305
6👍4
ትላንት ለወንድማችን ሻመዲን አሕመድ ቢያንስ ለሦስት ወራት የሚያስፈልገውን መድኃኒት ለመግዛት 47,460 ብር ጠይቀናችሁ ነበር። እናንተ ባለ ቅን ልቦች ግን በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 137,647 ብር ወደ አካውንቱ በማስገባት የተስፋው ሰንሰለት እንዳይቋረጥ ምክንያት ሆናችሁ። በዚህ ድጋፍ፣ ወንድማችን ከሚጠበቀው ጊዜ በላይ ሕክምናውን እንዲቀጥል የሚያስችል ትልቅ አቅም ተፈጥሯል። ​በተጨማሪም፣ እህታችን Alif Cut ከቱርክ የመጣ፣ 39,550 ብር ግምት ያለው፣ ተመሳሳይ የሆነ 10 እሽግ መድኃኒት ለወንድማችን ለመስጠት ቃል በገባችው መሰረት መድሃኒቱ በእጁ እንዲደርስ አድርጋለች። ይህ የዓይነት እርዳታ የገንዘብ ድጋፉን ይበልጥ አጠናክሮታል። የድጋፍ እንቅስቃሴውን በዚሁ ቋጭተናል።

ለተደረገው ሁሉ አላህ ምንዳችሁን ይክፈላችሁ። የልባችሁን መሻት ሁሉ ይሙላላችሁ። ከጠበቃችሁት በላይ ሀሴትን በሚያጎናጽፍ ጸጋ ይካሳችሁ። በደስታና በስኬት የታጀበ፣ በሰፊ ሪዝቅ የተከበበ፣ በጤና እና ዘላቂ ዕድሜ የተዋበ፣ ከችግር የራቀ፣ በልጆች ፈገግታ የደመቀ፣ በወላጆች ዱዓ የተመረቀ፣ እንደ ጫካ ማር የጣፈጠ ሐያት ይስጣችሁ። በመጪው ዓለም ደግሞ የዘላለማዊ ድሎት ከተማ የሆነችውን ጀነት ከሚወርሱት የአላህ ባለሟሎች ተርታ ያሰልፋችሁ።

http://www.tg-me.com/abuafnanmoh
36😭2👍1
Mohammed Ahmed Official
Video
የዛሬው ገጠመኝ

​ዛሬ ከአንድ የከባድ መኪና ሾፌር ዘንድ ከጂቡቲ ለዘመድ የተላከልኝን እቃ ለመቀበል አዲስ አበባ ውኃ ልማት ማርያም ሰፈር ወደሚገኝ የመኪና ጋራዥ መሄድ ነበረብኝ። ከዋናው አስፋልት መንገድ ወደ ውስጥ ለመግባት ረዥም የጠጠር መንገድ በባጃጅ ማቆራረጥ ግድ ይላል።

​በመጨረሻም ሾፌሩን አገኘሁት። የመጣው ዕቃ ክብደት ያለው ከመሆኑም በላይ፣ ቦታው ለራይድ ተሽከርካሪዎች አመቺ ስላልሆነ ሾፌሮች ወደ ውስጥ መግባት አይፈልጉም። በዚህ ጊዜ ሾፌሩ፦ «አንተ ወደ መሪ አካባቢ የምትሄድ ከሆነ እስከ ኮዬ ፈጬ ድረስ አብረን እንሂድና ከዚያ በኋላ ራይድ ይዘህ ትሄዳለህ» አለኝ።

​በከባድ መኪናው ላይ ተሳፍሬ የጠጠሩን መንገድ እያቆራረጥን ስንጓዝ፣ በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ሁለት የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጽ/ቤት ሰራተኞች አይኔ ውስጥ ገቡ። የሚያደርጉት በጎ ተግባር ልቤን ነካው።

​ሁኔታው እንዲህ ነበር፡- ይዞኝ የሚሄደው ሾፌር የቤቱን ቁልፍ ረስቶ ኖሯል። ከጋራዡ መካኒኮች አንዱ ቁልፉን መርሳቱን ደውሎ ነገረው። በባጃጅ ይዞለት እስኪመጣ መንገድ ላይ መጠበቅ ጀመርን። በዚህ መሃል የምትመለከቱት ምስኪን ሰውዬ ከኋላው ካለ ጎድጓዳ ስፍራ በእጁ ከያዘው ጆንያ ጋር ወደቀ። ስፍራውም በቆሻሻ የተሞላ ነበር። ​

ሁለቱ ደንብ አስከባሪዎች የወደቀውን ሰውዬ ገጽታ ተመልክተው ምንም ሳይጠየፉ ከገባበት ጉድጓድ ተሸክመው ሲያወጡት በገዛ ዓይኔ ተመለከትኩ። ምንም እንኳን ይህን ቅጽበት በካሜራዬ ማስቀረት ባልችልም ቀሪውን ትዕይንት በዚህ መልኩ ለማስቀረት ዕድል አገኘሁ።

​እኔ ከባድ መኪናው ውስጥ ሆኜ በሰፊው የፊት መስታወት አሻግሬ ትዕይንቱን እቀርጽ ጀመር። ማንም ሰው አይመለከተኝም ነበር። ደንብ አስከባሪዎቹ ለራሳቸው የገዙትን አንድ ኪሎ ግራም ሙዝ ከፌስታል ውስጥ አውጥተው እየላጡ ምስኪኑ ሰው እንዲመገብ አደረጉ። ​በአቅራቢያቸው የሚሸጥ እንጀራ ተሸክሞ የሚያልፍ አንድ ወጣት ሲያዩ፣ እንጀራ ሊገዙት ሲጠይቁት «አላስከፍላችሁም» ብሎ አንድ እንጀራ አጥፎ ሰጣቸው። ከጎኔ ተቀምጦ የነበረው ሾፌርም «ቆይ አንዴ ውኃ ልስጠው» ብሎ ወርዶ ውኃ አጠጣው።

​ቀረጻውን ከጨረስኩ በኋላ ሞባይሌን ኪሴ ውስጥ ከተትኩና ከከባድ መኪናው ላይ ወረድኩ። ከዚያም ከደንብ አስከባሪዎቹ ጋር ተዋወቅሁ። ወንዱ ተስፋሁን ሳሙኤል ኢንፎሮ ሲባል ሴቷ ደግሞ ሌንሳ ከቤ ዋቅጂራ ትባላለች። የነበረውን ሁኔታም በዝርዝር አስረዱኝ።

​የቀረጽኩትን ቪዲዮ ባላሳያቸውም የመልካም ተግባራቸውን ቀረጻ እንደያዝኩ ስነግራቸው በመጠኑ ገርሟቸው ተመለከቱኝ። ይህ ተግባራቸው በተመሳሳይ ሙያ ላይ ለተሰማሩ ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መልካምነት በመሆኑ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ለህዝብ እንዲደርስ ፈቃዳቸውን ጠይቄ ለእናንተ እንዲህ አጋርቻችኋለሁ።

ተጨማሪ
🍀🍀🍀

👉 ሾፌሩ ቁልፉን ጋራዥ ውስጥ ባይጥለው ኖሮ ይህን ትዕይንት ማየት አንችልም ነበር
👉 መንገዱ አስፓልት ቢሆን ኖሮ እቃውን ከቦታው በራይድ ይዤ ስለምሄድ ትዕይንቱ ያመልጠን ነበር
👉 ደንብ አስከባሪዎቹ ቪዲዮውን ለማስተላለፍ ፈቃድ ባይሰጡኝ ኖሮ ይህን ትዕይንት ማየት አትችሉም ነበር

http://www.tg-me.com/abuafnanmoh
25👍4
ጋዜጠኛ አነስ አሸሪፍ ሰማዕትነትን ከተቀዳጀ በኋላ የቅርብ ወዳጁና የሥራ ባልደረባው ሷሊሕ አል ጀዕፈራዊ ሐዘኑ በረታበት። ይኸው አሁን ደግሞ ከሐዘኑ ሳያገግም፣ በጥቂት ወራት ልዩነት በተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ሕይወቱ አልፋለች። ሁለቱ የጋዛ ድምጾች በተከታታይ ሰማዕትነትን ተጎናጽፈዋል።

​አነስ በዚያኛው ዓለም የተጎናጸፈውን ጸጋ የልብ ወዳጁ ሷሊሕ አል ጀዕፈራዊም እንዲደርሰው የተመኘ ይመስል በአጭር ጊዜ ውስጥ ተከትሎት ሄደ።

​አላህ የተመቸ አገር ያድርግላችሁ


http://www.tg-me.com/abuafnanmoh
😭14
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትላንት በጋዛ ምድር ላይ የነበሩት አነስ እና ሷሊሕ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የሰው ልጅ ሊቋቋመው ከሚችለው በላይ የሆነውን ታላቅ ፈተናና ሥቃይ በጽናት ተወጥተው ፣ ይህችን ጊዜያዊ ዱንያ ለቀሩት ነዋሪዎቿ ትተው ወደ ዘላለማዊው ዓለም ተሰናብተዋል።

አብረው በመስዋዕትነት እስከወደቁበት የመጨረሻ ደቂቃ ድረስ፣ እውነትን ፍለጋ ያደረጉት ጉዞ ከጋዜጠኝነት በላይ ጀግንነት ነበር። ዛሬ በሞት ቢነጠሉም፣ የሙያ ትሩፋታቸውና ጀግንነታቸው ለዘላለም ይኖራል።

http://www.tg-me.com/abuafnanmoh
😭181👍1
😭20👍2
ዛሬ ከዐስር ሶላት በኋላ የደረሰኝ መልእክት እጅግ ልብ የሚነካ ነው። ይህ መልእክት ትልቅ ደስታንና ጥልቅ ሐዘንን የሚፈጥር ልዩ ስሜት በውስጡ ይዟል። መልእክቱ ለብዙዎች ተስፋ የሚሰጥ፣ ተስፋ የማንቆርጥበት ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እንዳለን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ስለዚህ፣ በሕይወታችን የጎደለንን ሁሉ እንዲሞላ “ያ አላህ!” በማለት እንድንለምነውና እንድንጨቀጭቀው አቅም ይሆነን ዘንድ ይህን መልዕክት የባለቤቱን ፈቃድ በመጠየቅ አጋራኋችሁ።

​እህታችን ለዓመታት በጉጉት ስትጠብቀው የነበረውን ጸጋ አላህ በድንገት ሲወፍቃት፣ በሌላ በኩል ደግሞ የልብ ጓደኛዋን ወደዘላለማዊው ዓለም ሲወስዳት፣ የእርሱ አሠራር ምን ያህል ረቂቅና ጥበብ የተሞላበት እንደሆነ በግልጽ ያሳያል።

​የእህታችን መልእክት:

​አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ ማሜ! ​እንዴት ነህ? ሁሉ ሰላም ነው? ዐፊያ፣ ኢማንና ዒባዳ እንዴት ናቸው? ​አልሐምዱሊላህ! ባለፈው ዱዓ አድርግልኝ ብዬህ ነበር።
​አልሐምዱሊላህ! አላህ ምን ይሳነዋልና! “አትወልጅም” ተብዬ ብዙ እንባ አፍስሼ ነበር። አልሐምዱሊላህ ፣ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ አላህ ሴት ልጅን ወፈቀኝ። አሳቀፈኝ! አልሐምዱሊላሂ ረቢል ዐለሚን!

"​ነገር ግን"... ይህንን ታላቅ ደስታ ባገኘሁበት ቅጽበት፣ የምወዳት ጓደኛዬን ጀናዛ ለማጠብ አልታደልኩም። እሷ ዱንያን ለቃ በሄደችበት ወቅት፣ እኔም ወደዚች ዱንያ አንዲት ሴት ልጅ አመጣሁ። ጓደኛዬን ማጣት ከባድ ነው። ሐዘንና ደስታዬ በእኩል መጠን ሆነብኝ። ወላኪን (​ቢሆንም) አልሐምዱሊላህ! ጓደኛዬንም አላህ ጀነተል ፊርደውስን ይወፍቃት። ​በዱዓህ አስበኝ ወንድሜ!

እህታችንን አላህ የድሎት ከተማ የሆነችውን ጀነት ከሚወርሱት ባለሟሎቹ ተርታ ያሰልፋት - አሚን።

http://www.tg-me.com/abuafnanmoh
👍1610😭6
እውነተኛ ረሃብ የሚመነጨው ከነፍስ እንጂ ከሆድ አይደለም።

እውነተኛ ጥጋብም የሚገኘው በዓይን ውስጥ እንጂ በሆድ ሙላት አይደለም።

​ነፍሱ የተራበችና ዓይኑ ባዶ የሆነ ሰው፣ ምድሪቱን በሙሉ ቢወርስ እንኳን አይጠግብም። ዘወትር የሰዎችን እጅ ከመመልከት ወደኋላ አይልም። ሁልጊዜም በሌሎች ንብረት ላይ በስስት ያፈጣል እንጂ የውስጥ እረፍት አያገኝም።

​በተቃራኒው፣ ነፍሱ የጠገበችና ዓይኑ የሞላለት ሰው በጥልቅ እርካታና ልግስና እንደተሞላ ታገኘዋለህ። እንዲህ ያለው ሰው የሌላውን ሰው ጉርሻ አይመለከትም። አላህ ለሌሎች በዋለው ጸጋም አይቀናም።

​ይልቁንስ፣ እሱ ራሱ የአላህን እገዛ ከማንም በላይ ቢሻም፣ ከልቡ ለሰዎች ሁሉ መልካሙን ነገር ከአላህ ይለምናል። ይህ ሰው የጥጋቡ ምንጭ ሀብት ሳይሆን ልበ ንጹህነትና በፈጣሪ መደሰት እንደሆነ ያውቃል።

د. أدهم شرقاوي


http://www.tg-me.com/abuafnanmoh
12👍3
Mohammed Ahmed Official
Video
ነዒማ ሕመድ የተባለች እህት በፌስቡክ የውስጥ መልዕክት ላከችልኝ። እንዲህ ይላል፡ «አባቴ ከእናንተ ጋር ዑምራ እንዲያደርግ እፈልጋለሁ። አባቴ ልጆች ሳለን ጀምሮ መካና መዲናን በቴሌቪዥን መስኮት ሲመለከት፣ 'አላህ ሆይ! እነዚህን ቦታዎች ሳልጎበኝ ወዳንተ እንዳትወስደኝ' እያለ እንባ ይተናነቀው ነበር።» ... እኔም ከእርሳቸው ጋር መሄድ ለእኛ ታላቅ ደስታ እንደሆነ ገለጽኩላት።

አባቷ ጋሽ አሕመድ ኢማም ዑምራ ለማድረግ ይህ የመጀመሪያቸው በመሆኑ በእሷ ውስጥ ከፍተኛ ጉጉት አድሯል። በመሆኑም አልፎ አልፎ «ሙሐመድ፣ እባክህን አደራ! በመካ እና መዲና ቆይታችሁ የአባቴን ደስታ በፎቶም ሆነ በቪዲዮ እንድታጋራኝ፤ የዘመናት ምኞቱ ተሳክቶ ለማየት በጣም ጓጉቻለሁ» የሚል ጥያቄ ታነሳብኝ ነበር። እኔም «አባትሽን እንደ ወላጅ አባታችን የምንመለከት በመሆኑና ጉዞውንም እንደ ቤተሰብ ጉዞ የምንቆጥረው ስለሆነ፣ የተጣለብን አደራ ትልቅ መሆኑን ተረድተናል» ብዬ መለስኩላት።

የዚያ ሁሉ ውጣ ውረድ ፍጻሜ እነሆ ደረሰና፣ ትላንት በቢላሉል ሐበሺይ አዳራሽ ውስጥ፣ አውላ የጉዞ ወኪል ለመጀመሪያ ጊዜ ለዑምራ ተጓዦች የሚሆን የስልጠናና የሽኝት ፕሮግራም ማከናወን ቻለ። የልጅቱ አባት ጋሽ አሕመድ ኢማም ከወንድ ልጃቸው ሰልማን አሕመድ ጋር በቦታው ተገኝተው ነበር። አባትና ልጅ ከመድረኩ በሚተላለፈው መልዕክት እጅጉን ተማርከዋል። ምንም እንኳን ልጃቸው በአካል አዲስ አበባ ቢሆንም፣ ሃሳቡ ግን መካና መዲና ደርሶ ነበር። ልጁ አባቱን የሚሸኝ እንጂ፣ ከአባቱ ጋር ዑምራ የሚጓዝ አልነበረም።


​በመጨረሻም፣ ተጓዦቹ በፕሮግራሙ ላይ የተሰማቸውን ስሜት እንዲሁም ሊጠናከር የሚገባውን ጉዳይ እንዲገልጹልን ለእያንዳንዳቸው አስተያየታቸውን የመስጠት እድል ሰጠናቸው። ጋሽ አሕመድ ኢማም እና ልጃቸው ሰልማን አሕመድ ከፊት ለፊት ተቀምጠው ስለነበር፣ አጋጣሚውን ተጠቅመን አስተያየቱን ለሰልማን ሰጠነው። ሰልማን በልቡ የያዘውን ስሜት መቆጣጠር ተስኖት እንባውን በጉንጮቹ ላይ ለቀቀው። በዙሪያው የነበሩት ተጓዦች አንገታቸውን አቀረቀሩ። በፕሮግራሙ አዳራሽ ውስጥ ጸጥታ ነገሰ። የተወሰኑት ተጓዦች የሰልማን ስሜት ተሰምቷቸው ከወንበሮቻቸው እየተነሱ ወጡ። እኛም የዚያን ስሜት መቆጣጠር ተስኖን፣ ተጓዦችም ሌላ ምንም ማለት ሲያቅታቸው፣ በሰልማን እንባ ብቻ ፕሮግራሙን በድንገት አብቃን።

​አባቱን ለመሸኘት የመጣው ሰልማን እንባው እንዲህ ከፈሰሰ ጋሽ አሕመድ ኢማምስ ምን ያህል ውስጣዊ ደስታ ተሰምቷቸው ይሆን የሚል ጥያቄ በውስጣችን አደረ።

http://www.tg-me.com/abuafnanmoh
😭5👍4
Mohammed Ahmed Official
ነዒማ ሕመድ የተባለች እህት በፌስቡክ የውስጥ መልዕክት ላከችልኝ። እንዲህ ይላል፡ «አባቴ ከእናንተ ጋር ዑምራ እንዲያደርግ እፈልጋለሁ። አባቴ ልጆች ሳለን ጀምሮ መካና መዲናን በቴሌቪዥን መስኮት ሲመለከት፣ 'አላህ ሆይ! እነዚህን ቦታዎች ሳልጎበኝ ወዳንተ እንዳትወስደኝ' እያለ እንባ ይተናነቀው ነበር።» ... እኔም ከእርሳቸው ጋር መሄድ ለእኛ ታላቅ ደስታ እንደሆነ ገለጽኩላት። አባቷ ጋሽ አሕመድ ኢማም…
​ይህን ቪዲዮ እንድለቀው ጥያቄውን በእህቱ በነዒማ አሕመድ በኩል ለሰልማን እና ለአባቱ አቀረብኩላቸው። መጀመሪያ ላይ ሰልማን ያንገራገረ ቢሆንም፣ በመጨረሻ ለእህቱ እንዲህ ሲል መለሰላት፦

«ኢንሻአላህ፣ ይልቀቀው። ለረሱል (ﷺ) ማልቀስ ሲያንስባቸው ነው። እንኳን ለእሳቸው የሠው ልጅ እኮ ለወንድ ወይም ለሴት ያለቅሳል። ወላሂ በጣም ልቤ ተነክቶ ነበር።»
4😭3
የምትመለከቱት ወጣት ማሕሙድ አቡ ፉል ይባላል፤ የ28 ዓመት ወጣት ነው። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 በእስ*ራኤል የቦምብ ጥቃት ሳቢያ አንዱ እግሩ ተቆርጧል። ይሁንና፣ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ በእስ*ራኤል ጦር ከከማል አድዋን ሆስፒታል ታፍኖ ተወስዶ ታስሯል። በእስር ላይ በነበረበት ወቅትም በብረት መሣሪያዎችና በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ንዝረት አማካይነት ከባድ ስቃይ ደርሶበታል። በዚህ አሰቃቂ ድርጊት ምክንያትም፣ ለሁለት ሰዓታት ከቆየበት ኮማ እንደነቃ፣ የዓይኑን ብርሃን ሙሉ በሙሉ አጥቷል። በአጠቃላይ ስምንት ወራትን በእስር ቤት ውስጥ በስቃይ ካሳለፈ በኋላ ከትናንት በስቲያ ቢለቀቅም፣ ለዓይኖቹ የሚሆን አስቸኳይ የሕክምና ዕርዳታ ማግኘት አልቻለም። በመሆኑም፣ የዓይኑን ብርሃን መልሶ ለማግኘት ሲል በውጭ አገር ሕክምና እንዲያገኝ መላውን ዓለም እየተማጸነ ነው።

​ማሕሙድ አቡ ፉል ከእስር ከተፈታ በኋላ "ቢያንስ በአንድ ዓይኔ ቤተሰቦቼን ማየት ብችል" የሚል ጥልቅ ምኞት ነበረው። ነገር ግን እግሩን፣ ዓይኖቹንና ቤቱን ሙሉ በሙሉ አጥቷል። የበርካታ የጋዛ ነዋሪዎች ዕጣ ፈንታ እንደሆነው ሁሉ፣ እርሱም በአሁኑ ወቅት የሚኖረውና የሚተኛው በጊዜያዊ መጠለያ ድንኳን ውስጥ ነው።

ጋዜጠኛ ኡሳማ አል ካሕሉት ከጋዛ እንደጻፈው

Ramallah News - رام الله الإخباري
😭334
2025/10/20 09:14:08
Back to Top
HTML Embed Code: