Telegram Web Link
🆔ICT_terms

♻️30 የ ICT ቴክኒካዊ ስያሜዎች

1. #ጥቁር_መዝገብ (Blacklist) - በገዳቢ የክልከላ ፖሊሰ የታገዱ ድረ ገጾች እና ሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶች ዝርዝር ነው።

2. #ብሉቱዝ (Bluetooth) -ገመድ አልባ ከሞባይል እና
ከባለመስመር ስልኮች በአጭር ርቀት ዳታ ለመላላክ የሚያስችል ገመድ የግንኙነት ደረጃ ነው። ቡሉቱዝ ዳታ ለመለዋወጥ አጭር ሞገዶችን ይጠቀማል

3. #ቡቲንግ (Booting) - ኮምፒውተርን ሥራ
ማስጀመር ወይም ማስነሳት ነው።

4. #አቫስት (Avast) - ጸረ ቫይረስ መሣሪያ

5. #መሠረታዊ _የግብአት/ውጤት ሲስተም ሶፍትዌር (Basic Input/Output System-BIOS) -የኮምፒውተር ሶፍትዌር የመጀመሪያው እና መሠረታዊው ደረጃ ነው። ባዮስ የኮምፒውተራችንን ሐርድዌር ደኅንነት ለማረጋገጥ የሚረዱ የተለያዩ አማራጮችን ይሰጠናል፤ ኮምፒውተራችን ሲከፈት በይለፍ ቃል ብቻ እንዲገባ ማድረግ ከእነዚህ አንዱ ነው።

6. #ሲክሊነር (CCleaner) - በነጻ የሚገኝ ሶፍትዌር ነው። በቅርብ በተጠቀምንባቸው ፕሮግራሞችና በዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲሰተም አማካኝነት በሐርድዌራችን ላይ የተተዉ ጊዜያዊ ፋይሎችን ዱካ የሚያሳዩ መረጃዎችን የሚያጸዳ ሶፍትዌር ነው።

7. #ሲዲ_በርነር (CD Burner) - በባዶ ሲዲዎች
ላይ መረጃ ለመጻፍ የሚችል የኮምፒውተር ድራይቭ ነው።
ዲቪዲ በርነር (DVD burners) በተመሳሳይ
መንገድ በባዶ ዲቪዲዎች ላይ ይጽፋል።
ሲዲ-አርደብሊው (CD-RW ) እና ዲቪዲ-አርደብሊው ድራይቮች (DVD-RW drives) ደግሞ በሲዲ/ ዲቪዲ ላይ የተጻፈውን አጥፍተው ከአንድ ጊዜ በላይ መልሰው
መጻፍ ይችላሉ።

8. #ሰርከምቬንሽን (Circumvention) - በኢንተርኔት አፈና የታገዱ ድረ ገጾችን እና
የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለማግኘት እገዳውን ማለፍ።

9. #ክሌም_ዊን (Clam Win) - ለዊንዶውስ የተሠራየኤፍኦኤስኤስ ጸረ ቫይረስ

10. #ኮቢያን_ባክአፕ (Cobian Backup) -
የኤፍኦኤስኤስ የመጠባበቂያ ማከማቻ መሣሪያ ነው።
የቅርብ ጊዜዎቹ የኮቢያን አይነቶች ምንጫቸው
የማይገለጽ ነገር ግን በነጻ የሚገኙ ናቸው፤
የቀድሞዎቹ ግን በኤፍኦኤስኤስ ብቻ የሚለቀቁ ነበሩ።

11. #ኮሞዶ_ፋየርዎል (Comodo Firewall) -
ምንጩ (ውስጣዊ መዋቅሩ) ለምርመራ ክፍት የሆነ፣በነጻ የሚገኝ የፋየርዎል መሣሪያ ነው።

12. #ኩኪ (Cookie) - የኢንተርኔት ማሰሻ
(browser) በኮምፒውተር ላይ የሚተዋቸው የጎበኘነውን ድረ ገጽ እና ተያያዥ መረጃዎችን መዝግቦ የሚይዝ አነስተኛ ፋይል ነው።

13. #ዲጂታል_ፊርማ (Digital signature) -
ኢንክሪፕሽንን በመጠቀም አንድ ፋይል ወይም መልእክት ከትክክለኛው ሰው የተላከ መሆኑን
የማረጋገጫ መንገድ

14. #የዶሜይን_ስም (Domain name) - በቃላት
የሚገለጽ የድረ ገጽ ወይም የኢንተርኔት አገልግሎት አድራሻ

15. #ኢንክሪፕሽን (Encryption) - የተራቀቀ ሒሳባዊ ስሌትን በመጠቀም ኢንክሪፕት (encrypt) ማድረግ፤ ትክከለኛው መረጃ ማለትም ያለው የይለፍ ቃል ወይም የኢንክሪፕሽን ቁልፍ (encryption key) ሰው ብቻ ኢንክሪፕት የተደረገውን መረጃ ዲክሪፕት ማድረግ/መክፈት (decrypted) እንዲችል የሚያደርግ

16. #ኢንጂሜይል (Enigmail) - የታንደርበርድ
የኢሜይል ፕሮግራም አጋዥ መሣሪያ (add-on) ነው፤ ተጠቃሚዎቹ ኢንክሪፕት የተደረገ ወይም
በዲጂታል ፊርማ የታተመ መልእክት ለመላክና ለመቀበል የሚያስችል

17. #ኢሬዘር/መደምሰሻ (Eraser) ከኮምፒውተር
ወይም ከሌሎች ተንቀሳቃሽ የመረጃ ማከማቻዎች ላይ የሚገኝ መረጃን በአስተማማኝ እና በዘላቂነት ከነጭራሹ ለማጥፋት (delete) የሚያከማይክሮሶፍት

18. #ፋየርፎክስ (Firefox) - የታወቀ የኤፍኦኤስኤስ ማሰሻ (FOSS Web browser) ነው፤ ከማይክሮሶፍት ማሰሻ “ከኢንተርኔት ኤክስፕሎረር” የተለየ አማራጭ ነው።

19. #ፋየርዎል (Firewall) - ኮምፒውተርን
አስተማማኝ ካልሆኑ የኢንተርኔት እና የቤት ውስጥ መረቦች ግንኙነት የሚጠብቅ መሣሪያ ነው።

20. #ነጻና_ቀመሩ የሚታይ ሶፍትዌር- ኤፍኦኤስኤስ
(Free and Open Source Software-FOSS) -
ያለክፍያ በነጻ የሚገኙ እንዲሁም ተጠቃሚዎች
የሶፍትዌሮቹን አሠራር እንዲመረምሩ፣ እንዲፈትሹ፣ እንዲያሻሽሉና ለሌሎች አሳልፈው እንዲሰጡ የሚፈቅዱ ሶፍትዌሮች ምድብ

21. #ፍሪዌር (Freeware) - በነጻ የሚገኙ፣ ነገር ግን ተጠቃሚዎች መሠረታዊ የፈጠራ አወቃቀሩን (sourcecode) እንዳያገኙ ሕጋዊና ቴክኒካዊ ክልከላዎችን የሚያደርጉ ሶፍትዌሮች

22. #ጂኤንዩ/ሊኑክስ (GNU/Linux) -
የኤፍኦኤስኤስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ነው፤
ለማይክሮሶፍት ዊንዶውስ አማራጭ ሲስተም ነው።

23. #ጂፒኤስ (Global Positioning System - GPያደረገ በስፔስ/ምህዋር ላይ መሠረት ያደረገ
በሳተላይት በመታገዝ ቦታንና ጊዜን ለመለየት የሚያስችል፤ በማንኛውም የአየር ሁኔታ፣
በየትኛውም የምድራችን ወይም በአቅራቢያዋ ባሉ ቦታዎች የሚሠራ፤ ከሞላ ጎደል በምንም ነገር የማያደናቀፍ ከሰማይ ከፍታ ለመመልከት የሚያስችል የሳተላይት መመልከቻ ነው።

24. #ሐከር/ሰባሪ (Hacker) በዚህ አገባቡ፣ ከርቀት ኮምፒውተራችንን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ወይም ስስ
መረጃዎቻችንን ለመስረቅ አይፒ የሚሞክር ወንጀለኛ
25.#የኢንተርኔት_ፕሮቶኮል_አድራሻ-(
አድራሻ) (Internet Protocol address -IP
address) - ማንኛውምሰጪ ኮምፒውተር ከኢንተርኔት ጋራ ሲገናኝ የሚሰጠው ልዩ መለያ

26. #ኢንተርኔት_አገልግሎት (አይኤስፒ)
(Internet Service Provider-ISP) - የኢንተርኔት ወይም ግንኙነት መስመር አገልግሎት የሚሰጥ ኩባንያ ወይም ድርጅት። የብዙ አገሮች መንግሥታት ኢንተርኔትን በጣም
ይቆጣጠራሉ፤ እነዚህን አገልግሎት ሰጪዎች (አይኤስፒ) በመጠቀምም የኢንተርኔት አሶሲዬሽን ክልከላ፣ ስለላ እና እገዳ ያደርጋሉ።

27. #ኢንፍራሬድ_ዳታ (Infrared Data
Association) (ኢርዳ/IrDAአልባ በአጭር ርቀት
የኢንፍራሬድ ስፔክተረም ጨረሮችን በመጠቀም
መረጃ/ዳታ ለመለዋወጥ የሚያስችል ገመድ አልባ የግንኙነት መንገድ ነው። በዘመናዊ መገልገያዎች ውስጥ ኢርዳ/IrDA በብሉቱዝ ተተክቷል።

28. #ጃቫ_አፕሊኬሽንስ (Java Applications)
(አፕልትስ/Applets) በብዙ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ላይ የሚሠሩ አነስተኛ ፕሮግራሞች ናቸው። ብዙውን ጊዜ በድረ ገጾች ውስጥ የተሻሻሉ አገልግሎቶችን (functionalities) ለመስጠት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

29. #ኪይሎገር (Keylogger) - ለስለላ ተግባር
የሚውል የስፓይዌር አይነት ነው፤ በኮምፒውተሩ
የመተየቢያ keyboard ላይ የተጫንናቸውን ቁልፎች/ፊደሎች በሙሉ መዝግቦ ለሦስተኛ ወገን ይልካል። ኪይሎገሮች የኢሜይሎችን እና የይለፍ ቃሎችን ለመስረቅ በብዛት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

30. #ኪፓስ (KeePass) - የአስተማማኝ የይለፍ ቃል ማከማቻ (database) ፍሪዌር ነው።

🔱 @addis_ken
🔱 @addis_ken_group
🔱 Fb : https://www.facebook.com/AddisTech1/
🔱 our entertainment youtube channel 😂👉https://youtube.com/channel/UCJhkdfYsC2Fj3B36V4nmSRw
ሰላም የ #ADDIS'ቴክ ቤተሰቦች

ምን ያስደስቶታል? 🤔
እስቲ አንድ የመዝናኛ channel ላስተዋውቃችሁ!
#ET_TOK ይሰኛል።
ቲክቶክን በዩቲዩብ ማስጠቀም የሚችል ቻናል ነው😁
አዝናኝ የቲክቶክ ቪዲዮችን ለማየት ቲክቶክ አፕ ኖራችሁ አልኖራችሁ አደለም ወሳኙ ነገር ፤ ET_TOK'ን subscribe ማረጋቹ ነው😁

በየሳምንቱ የተመረጡ አዝናኝ የቲክቶክ ቪዲዮዎች የለቀቃሉ።

ከቲክቶክ ቪዲዮች በተጨማሪም የተለያዩ normal interview'ዎችን ወደ አስቂኝ ቪዲዮ በመቀየር ሌሎች አዝናኝ video'ዎች አየተሰሩ በየሳምንቱ ይለቀቃሉ።

Subscribe ያድርጉ ፣ ለወዳጅ ዘመዶም ያጋሩ...channel'ኡን ለማግኘት ከስር ያለውን link ይጠቀሙ👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCJhkdfYsC2Fj3B36V4nmSRw

🎩
😁
👕👍subscribe!😁
👖

#ET_TOK
#ETHIOPIANS_TIK_TOK

#MAKE_YOUR_DAY_WITH_ET_TOK ✌️

🔱 @addis_ken
🔱 @addis_ken_group
🔱 Fb : https://www.facebook.com/AddisTech1/
In this day one of the greatest programming language was introduce by the Dutch programmer Guido van Rossum
HBD PYHTON🥳🤣

🔱 @addis_ken
🔱 @addis_ken_group
🔱 Fb : https://www.facebook.com/AddisTech1/
the evolution of the memory card🤣🤣🤣

🔱 @addis_ken
🔱 @addis_ken_group
🔱 Fb : https://www.facebook.com/AddisTech1/
የአድዋ ጦርነት የመጀመርያው ኢታሎ-ኢትዮጵያ ጦርነት ወሳኝ ውጊያ ነበር ፡፡ የኢትዮጵያ ጦር የጣሊያን ወራሪ ኃይልን እሁድ 1 ማርች 1896(እ.ኤ.አ) በአድዋ ከተማ አቅራቢያ አሸነፈ ፡፡ ወሳኙ ድል የጣሊያን መንግሥት በአፍሪካ ቀንድ የቅኝ ግዛትዋን ለማስፋት ዘመቻውን አከሽፈ ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ የአውሮፓ ኃይሎች ከበርሊን ጉባኤ በኋላ መላውን አፍሪካን ቀርፀው ነበር ፡፡ አሁንም ነፃነታቸውን ያስጠበቁት ኢትዮጵያ ፣ ላይቤሪያ እና የዴርሽ መንግስት ብቻ ናቸው ፡፡ አድዋ ከአርባ ዓመታት በኋላ እስከ ሁለተኛው ኢታሎ-ኢትዮጵያ ጦርነት ድረስ አድዋ የፓን አፍሪካኒዝም ቀዳሚ ታዋቂ ምልክት ሆና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አረጋግጣለች ፡፡
how to type on keyboard

🔱 @addis_ken
🔱 @addis_ken_group
🔱 Fb : https://www.facebook.com/AddisTech1/
where can we use python????🧐

major on one of those framework
🔱 @addis_ken
🔱 @addis_ken_group
🔱 Fb : https://www.facebook.com/AddisTech1/
#Addis #Tech #learn
Want To Master Your English at Home in 30 Days? 🔥 Take a 🚀1-Minute Quiz🚀 and Get Your Perfect English Study Plan ⭐️
😍 Try Now and Enjoy Everyday Progress😍
👉👉👉 TRY IT👈👈👈
🔱 @addis_ken
🔱 @addis_ken_group
🔱 Fb : https://www.facebook.com/AddisTech1/
SHARE AND SUPPORT US FOR MORE
🆔Gmail_የሚሰጣቸው_ጥቅሞች

#Gmail ማለት ጎግል ከሚሰጣቸው ከ 50 በላይ አገልግሎቶች አንዱ የመልእክት ወይም የኢሜል መለዋወጫ አገልግሎት ነው፡፡

#Gmail ኢሜል በምትላላኩበት ግዜ ብዙ አማራጮችን ይሰጣል፡፡ በተለይ አፕዴት ካደረጋችሁት፡፡

♻️Gmail ከሚሰጣቸው የተለያዩ ጠቀሜታዎች መካከል የተወሰኑትን ላንሳላችሁ፦

❇️1ኛ፦ #Google_Smart_Compose_Feature
አንዳንዴ ኢሜል እየፃፋችሁ ቀጥሎ የምትፅፉትን ዓ/ነገር ወይም ሃሳብ ሲጠፋባችሁ ጎግል ይረዳችሃል፡፡

Google Smart Compose Feature የሚል አገልግሎት እዛወ ጂሜል ላይ ታገኛላችሁ፡፡ ይህ አገልግሎት ዓ/ነገር ሲጠፋባችሁ ወይም ሃሳብ ሲጠፋባችሁ "እንዲህ ማለት ፈልገህ ነው " እያለ ቀጥሎ ሊመጣ የሚችለውን ዓ/ነገር ገምቶ ይሞላላችኃል፡፡

❇️2ኛ፦ #Schedule_emails_to_be_sent_at_a_later_date

ይሄ አገልግሎት ደሞ ለምሳሌ ከ 3 ቀናት በኃላ መላክ ያለባችሁ ኢሜል ካለና ነገር ግን በዛ ቀን ኢሜል ለመላክ የማይመቻቸሁ ከሆነ ለምሳሌ ሰርግ ቢኖርባችሁ ወይም ሌላ ነገር ቢኖርባችሁ ኢሜሉን ዛሬ ትፅፉትና ከሶስት ቀን በኃላ ለምሳሌ፡ቀኑ ሀሙስ በ12 ሰዓት ኢሜሉ ኢንዲላክ ስኬጁል ወይም ቀጠሮ ማስያዝ ይቻላል፡፡

❇️3ኛ፦ ጂሜል ኢንተርኔት በማታገኙበት ጊዜ ወይም ኦፍ ላይን ስትሆኑም ጂሜልን መጠቀም ትችላላችሁ።

❇️4ኛ፦ #Confidential_Mode: -

ይህ በጣም ጠቃሚ የጂሜል አገልግሎት ነው፡፡
ለምሳሌ፡- የቢዝነስ ፕሮፖዛል፣ወይም የፊልም ድርሰት፣ወይም በአጠቃላይ ሚስጥራዊ መረጃዎች በኢሜል ልትልኩ ስትሉ ትሰጋላችሁ። ምክንያቱም የምትሉክት ሚስጥራዎ መረጃ የላካችሁለት ሰው ቢወስድብኝስ፣ወይም ፕሪንት አድርጎ ቢጠቀምበትስ፣ወይም ዶክመቱን ማየት ለሌለበት ሰው ቢሰጥብኝብስ..ወዘተ የሚል ስጋት ይኖራችኃል፡፡

ነገር ግን ጂሜል ላይ Confidential Mode ኦን ካረጋችሁ ሚስጥራዊ መረጃ የላካችሁለት ሰው ዶክምንቱን ፕሪንት ማድረግ አይችልም፤ ኮፒ ማድረግ አይችልም፣ወደሌላ ሰው ኢሜል አድራሻም ፎርዋርድ ማድረግ አይችልም፡፡

❇️5ኛ፦የጎግል አካውንት ወይም የጂሜል አካውንት ስትከፍቱ ጎግል 15 GB Space ይሰጣችኃል፡፡

ምንማለት ነው፦ስልካችሁ ላይ የምትፈልጓቸው ፎቶዎች፤ቪዲዮዎች፤ዶክመንቶች ይኖራሉ፡፡እነዚህንና የመሳሰሉ ጠቃሚ ዶክምንቶችን የምታስቀምጡበት 15 GB የሚሆን መጋዘን ይሰጣችኃል፡፡ በነፃ እዚህ ማስቀመጥ ትችላላችሁ፡፡፤ ሰዎች ስልኬ ጠፋ…እኔ ስልኩ ይቅርብኝ ግን ስልኩ ውስጥ ያሉ ዶክመንቶች መጥፋታቸው ነው የሚያናድደኝ ይላሉ፡፡ ካሁን በኃላ ጂሜል አካውንት ከከፈታችሁ ከዚያ ዶክመንቶቻችሁን ወደ ጂሜል ሲንክ ማድረግ ነው፡፡ጂሜል አካውንት ካላችሁ ስልካችሁ ሲሰረቅ ሌላ ስልክ ስትገዙ ጂሜላችሁን ከፍታችሁ ሁሉም ዶክመንቶቻችሁን ማግኘት ትችላላችሁ።

ሌላው ሰዎች ስልክ ሲጠፋባቸው ስልካቸው ላይ ያሉት ኮንታክቶች አብሮ ይጠፋሉ፡፡ እና ብዙ ሰው ይቸገራል ።፡ ስልካችሁ ቢጠፋም ጂሜል አካውንት ካላችሁ እያንዳንዱ ኮንታክቶቻችሁ ጂሜል ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

ሁላችሁም የ Gmail አካውንት ዛሬውኑ ማውጣት አለባችሁ፡፡

🔱 @addis_ken
🔱 @addis_ken_group
🔱 Fb : https://www.facebook.com/AddisTech1/
🔱 our entertainment youtube channel 😂👉https://youtube.com/channel/UCJhkdfYsC2Fj3B36V4nmSRw
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Dev:
"It was working Yesterday"🙆‍♂️🙆‍♂️
🤣🤣

🔱 @addis_ken
🔱 @addis_ken_group
🔱 Fb : https://www.facebook.com/AddisTech1/
🔱 our entertainment youtube channel 😂👉https://youtube.com/channel/UCJhkdfYsC2Fj3B36V4nmSRw
2025/07/07 10:29:06
Back to Top
HTML Embed Code: