Telegram Web Link
የሟችና_አልቃሽ አስገራሚ ገፅታ

አንድ ቀን አላህን በጣም የሚገዛ ሰው ወደ ሞት እየተቃረበ መጣ በዙሪያው ያሉ ቤተሰቦቹ ማልቀስ ጀመሩ...ከዛም ይህ ሊሞት የተቃረበ ሰው ለቤተሰቦቹ "ቁጭ አድርጉኝ " አላቸው ደግፈው አስቀመጡት ..ከዛም ወደ አባቱ ዞረና ለምን ታለቅሳለህ ብሎ ጠየቀው

:- አባቱም አንተን ማጣቴ ከአንተ በኋላ ብቸኛ መሆኔ ነው የሚያስለቅሰኝ ብሎ መለሰ ..

ለእናቱም ዞረና እናቴ ለምንድነው የምታለቅሺው አላት
:- እናትየውም "የልጅ ማጣት መሪር ሀዘን ነው የሚያስለቅሰኝ " አለችው ..

ለሚስቱ ዞረና ባለቤቴ ምንድነው የሚያስለቅስሽ አላት
:-እሷም " የአንተን መልካም ነገር ስለማጣ ፤ወደሌላ ስለምከጅል ሸክም ስለምሆን ነው አለችው

ለልጆቹም ዞረና ምንድነው የሚያስለቅሳችሁ አላቸው
:-እነሱም " ካሁን በኋላ ወደ የቲምነት ወደ ውርደትና ደጋፊ ወደማጣት ስለምንጓዝ አሉት....

ይህን ሁሉ ከሰማ በኋላ በጣም አለቀሰ ቤተሰቦቹም ለምን ታለቅሳለህ አሉት እሱም ሁላችሁም ለኔ ብላችሁ ሳይሆን ለራሳችሁ ጥቅም ነው የምታለቅሱት ከናንተ ውስጥ ...ለጉዞዬ መርዘም ለስንቄ ማነስ የሚያለቅስልኝ የለም??....ከናንተ ውስጥ ከዚህ በኋላ መኝታዬ ለብቻዬ አፈር ለመሆኑ የሚያለቅስልኝ የለም ?? ከናንተ ውስጥ ከዚህ በኋላ ስለሚጠብቀኝ አስደንጋጭ ጥያቄዎች የሚያለቅስልኝ ሰው የለም ?? ከናንተ ውስጥ የአለማት ጌታ ፊት መቆሜን አስታውሶ የሚያለቅስልኝ የለም.አለና በፊቱ ወደቀ ቢያንቀሳቅሱትም ህይወቱ አልፋ ነበር።

በዚች አለም ሰትኖር አላህን ለማስደሰት እንጂ ሰዎችን ለማስደሰት አትኑር። በሞትክ ጊዜ ሰዎች ሰለሚያጡት ነገር እንጂ ሰላአንተ ሰለሚገጥምህ ነገሮች አሰበው አይጨነቁም።
9👍2
2025/10/18 16:05:59
Back to Top
HTML Embed Code: