Telegram Web Link
AHLEL MUSLIM
የልብ ጉዞ~abdu rumi : ሶስቱን በሮች ከቆላለፍን ቡኋላ በልቦናችን ላይ ፅልመት የሚያክለው "ኸዋጢር" ነው። ልብ ላይ ውል የሚል ሀሳብ። ይህ ሀሳብ ከሸይጣን ፣ ከነፍስያ ፣ አልያም ከመለክ ፣ ወይም ደግሞ ከአላህ ሱወ ዘንድ በኢልሀምነት የተላከ ይሆናል። በልባችን የሆነ ሀሳብ ውል ሲል በሶስት አይነት ሚዛን መልካም ወይም መጥፎነቱን መለየት ይቻለናል። አንደኛው በሸሪዐ ሚዛን እናየዋለን። ሀራም፣…
የልብ ጉዞ~
:
ሙሀመድ ኢብን ዋሲዕ ኢማናዊ ዕይታቸው ጥልቅ የነበረ ግለሰብ ናቸው። የልብ ሰራተኞች እጅጉን ማነሳቸውን ባስተዋሉ ጊዜ " እኛ የአላህ ነን ወደርሱም ተመላሾች ነን" በማለት ያለቅሱ ጀመር። ያለፉ ወንድሞቻቸውንም አስታውሰው " ወይ ጓደኞቼ! ጥለውኝ ሄዱ .." እያሉ ያነቡ ነበር። ቤተሰቦቻቸው ግራ ተጋብተው " አባ ዐብደላህ ሆይ! አላህ ይዘንልህ ቀን ሚፆሙና ለይል የሚሰግዱ በአላህም መንገድ የሚታገሉ ወጣቶች እያሉ?" በማለት ሊያፅኗኗቸው ሞከሩ። መልሳቸው ግን እንዲህ የሚል ነበር " በርግጥም አሉ። ዳሩ ግን ሁላችንም በራስ መኮፈስ በሽታ ተጠቅተናል።" በማለት ተናገሩ።
:
ምንም ያህል የተቀደሱ ተግባራቶችን ብንፈፅም የልብ ንፅህና ከሌለን ተግባራችን ውድቅ ነው።
ለይል ሶላት እየሰገደ ኡጅብና ኪብር ከተጠናወተው ሰው ይልቅ የወንጀለኛ ሰው የፀፀት እህህታ አሏህ ዘንድ ይበልጥ ዋጋ አለው።

ሀቢባችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም " አላህ ወደ ቁመናቹም ሆነ ወደ መልካቹ አይመለከት። ነገር ግን ወደ ልባቹና ስራችሁ ይመለከታል። " ብለውናል።
ሀዲሱ ሚያመላክተንም የቀልብ መስተካከል የመድህን በር መሆኑን ነው። 
የተቅዋ ልባስ እየረገበ ከላይ ላይ ለ'እዩልኝ' የምንሰራት ስራ : ስራው ምን የገዘፈ ቢሆን አላህ ዘንድ ያላት ዋጋ ግን ከብናኝም ያነሰ ነው።
አላህ ዘንድ ዋጋ ከማጣት በላይ ምን ክስረት አለ?

ሀቢባችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እጅግ ከሳሪ ስለሆኑ ሰዎች ሲናገሩ ;
አንደኛው በጂሀድ ላይ ነፍሱን የሰዋ ሰው ነው። ምን እንደሰራ ሲጠየቅ በደም ከተነከረ አካሉ ጋር ራሱን ለአላህ ብሎ እንደሰዎና ለአላህ ብሎ ሲዋጋ እንደነበር ይናዘዛል። ግና ዋሾ መሆኑ ይጋለጥበታል። ሲዋጋ የነበረው " ጀግና! ደፋር " እንዲባል እንደነበር ይነገረዋል። መሻቱን ዱንያ ላይ ጨርሶዋልና ልፋቱ ከንቱ መሆኑ ተነግሮት ወደ ጀሂም ይሳባል። ሁለተኛው ቁርዐንን ሲያስቀራ ፣ ኢልምን ሲያስተምር የነበረ ሰው ለጥያቄ ይቀርባል። ምን እንደሰራ ሲጠየቅ " ለአንተ ብዬ እውቀትን አውርሽያለሁ። ቁርዐንን አስተምሪያለሁ" እያለ ይሰራው የነበረውን ስራ ይናገራል። ነገር ግን ልቡ ውስጥ የተሸሸገ የይሉኝ በሽታ ነበርና ለቅጣት ይታጫል።
ምፅዋትን ሚያበዛም ሰው ለጥያቄ ሲቀርብ። ለአላህ ብሎ እንደሰጠ ቢናገርም የልቡ ምስጢር ይፋ ሚሆንበት ዕለት ነውና የሸሸገው ይጋለጥበታል። "ሰጪ ተብለህ እንድትባል ነበር የሰጠሀው!" ይባላል። በስራው ላይ ጥርት ያለ ኒያ ለአላህ ያልነበረ በመሆኑም ለቅጣት ይዳረጋል።
:
እርግጥ ነው መልካም ስራን መስራት ለራህመቱ እንድንታጭ ያደርገናል። ግና ስራችን ሚመዘነው በልባችን ዕሳቤ ነውና የልብ ንፅህና ከምንም በፊት አስፈላጊ ይሆናል።
__
👍3
ወዳጄ ሰሞኑ ሚያስጨንቅህ ነገር ከአላህ አቅም በልጦ ነዉ?? ትላንት እንቅልፍ የነሳህስ ቢሆን ለሱ ማይቻል ሆኖ ነዉ?? አብሽር ንገረዉ ከዛ ነገሮች ሁሉ ይስተካከላሉ
አላህም በነገሩ ላይ አሸናፊ ነዉ
በሉ የዱዐ ሰዐት ነዉ
👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍2
AHLEL MUSLIM
የልብ ጉዞ~ : ሙሀመድ ኢብን ዋሲዕ ኢማናዊ ዕይታቸው ጥልቅ የነበረ ግለሰብ ናቸው። የልብ ሰራተኞች እጅጉን ማነሳቸውን ባስተዋሉ ጊዜ " እኛ የአላህ ነን ወደርሱም ተመላሾች ነን" በማለት ያለቅሱ ጀመር። ያለፉ ወንድሞቻቸውንም አስታውሰው " ወይ ጓደኞቼ! ጥለውኝ ሄዱ .." እያሉ ያነቡ ነበር። ቤተሰቦቻቸው ግራ ተጋብተው " አባ ዐብደላህ ሆይ! አላህ ይዘንልህ ቀን ሚፆሙና ለይል የሚሰግዱ በአላህም መንገድ…
የልብ ጉዞ~

مزِّق القيدَ تَحرّر يا فتَى
كم ستَبقى مرهقًا حتّى متَى؟
-
جلال الدين الرومي

አንተ ሰው ነፃ ሁን ከእስርህ!
ለምን ያህል ጊዜ በእስር ትቆያለህ?

ጀላሉዲን አል-ሩሚይ!
:
አንዳንዴ ቆም ብሎ ማሰብ ይበጃል። ልብን ሰብሰብ አድርጎ በእርምጃ አጣጣላችን ኻቲማችንን ማሰቡ መልካም ነው። ምክንያቱም ሰው የሚሞተው በኖረበት ሁነት ላይ ነውና። በስሜትና በነፍስ ክጃሎት እስር ተጠፍንገን ባለንበት የሩህ ነፃነትን ማግኘት ማይቻል ነው።
የልብ ጭንቀት! ስክነት ማጣት. . .ጨለምላማ ነገርን ብቻ ማሰብ! ፍፁም የብቸኝነትና ራስን የመጥላት ስሜት ውስጥ የምንዘፈቀውም በነፍሳችን እስር ውስጥ ስንማቅቅ ነው።

ፍላጎቶቻችንን መግራትና ነፍስ ጌታዋ ባዘዛት ተግባራት  ላይ እንድትለምድና እንድትወድ ካደረገን ሰላማዊ ልብን እንታደላለን።

"ብርሀኑን ልቡ ላይ ያንጠለጠለ
ስለ አለም ጨለማ ግድ አይሰጠውም"
ይላሉ ጀላሉዲን አል~ሩሚይ

ልቡ ላይ የአላህን ፍቅር ያነገበ ሰው አለም ውጥንቅጡ ቢወጣ ሰላም ከርሱ ጉያ አትርቅም። በምንም አይነት ሀል ውስጥ ቢሆን ሰላም መረጋጋትና ተስፋ አይርቀውም። የልቡ ብርሀን ድቅድቅ መንገዶቹን እየከፋፈተለት በዱንያ ላይ ሰላማዊ ሀያትን ይታደላል። አኼራ ላይም ከሀድረተሏህ ደጀፍ ለመዝለቅ ከታጩት መሀል ይሆናል። እጅግ ታላቅ እድያ!!

የልብ ብርሀኑ የከሰመና ጥቁረት የወረሰው ሰው አለም በብርሀን ብታሸበርቅ እርሱ ዘንድ ያለው ግን ፅልመት ነው። ፈገግታ ለከውኑ ቢታደል ልቡ ላይ ሀዘን ድንኳን ቀልሶበታል። ዱንያ ላይ ያሉ ነገራቶች በጠቅላላ የልቡን ሰላም ማሰመለስ ይሳናቸዋል። እርካታ ያጣል። የመራራ ህይወትን ፅዋ ይጎነጫል።

ለልቡ ብርሀን ግንባሩን ከእግሩ ስር አኑሮ በሱጁዱ የልብ ጉዞውን ካላሰናዳ ወደ ሰላምና መድህን ደጃፍ ወደሚያሻግረው ድልድይ አይጠጋም።

" ከልብህ ላይ ጭንቀቶችህን ሁሉ ሊያሶግድልህ የሚችለው! የአላህ ሀይል ብቻ ነው "

ጀላሉዲን አል~ሩሚይ
_
👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍3
AHLEL MUSLIM
የልብ ጉዞ~ مزِّق القيدَ تَحرّر يا فتَى كم ستَبقى مرهقًا حتّى متَى؟ - جلال الدين الرومي አንተ ሰው ነፃ ሁን ከእስርህ! ለምን ያህል ጊዜ በእስር ትቆያለህ? ጀላሉዲን አል-ሩሚይ! : አንዳንዴ ቆም ብሎ ማሰብ ይበጃል። ልብን ሰብሰብ አድርጎ በእርምጃ አጣጣላችን ኻቲማችንን ማሰቡ መልካም ነው። ምክንያቱም ሰው የሚሞተው በኖረበት ሁነት ላይ ነውና። በስሜትና…
የልብ ጉዞ~አብዱ ሩሚ
:

" ልቡ ውስጥ የብናኝ ያህል ኩራት ያለበት ሰው ጀነት አይገባም" ሀቢበሏህ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም።

ልብ እንድትጥራራ ከበሽታዎቿ መታከም አለባት። ብዙ ጊዜ በመልካም ስራ ላይ የሚከሰትና ብዙ ማይስተዋል ከባድ በሽታ ነው። 'ኩራት'
ሰይዲ አቡ የዚድ አል ቡስጣሚይ " አንድ ሰው በማህበረሰቡ ውስጥ  'ከእኔ የባሰ መጥፎ ሰው አለ' ብሎ የሚያምን ከሆነ ኩራተኛ ነው።" በማለት የኩራት ድካውን ያሳዩናል።

ዳውድ አጥ-ጣዒ በአንድ ወቅት "አምባ ገነን መሪዎች ዘንድ በመግባት በመልካም ያዘዛቸውና ከክፉ የከለከላቸው ግለሰብ ምን ሊደርስበት ይችላል?" ተብለው ተጠየቁ
"ግርፋትን እፈራለታለሁ" ሲሉ መለሱ። "ግለሰቡ ይህንን መቋቋም ከቻለስ " ሲባሉ "በሰይፍ እንዳይቀላ እሰጋለታለሁ " አሉ። "ይህንንም ለመቀበል ከተዘጋጀስ "
ሲባሉ። እንግዲያውስ ብዙ ሰው ሊያመልጠው የማይችለውን አደገኛ በሽታን ተናገሩ " ድብቁን በሽታ እፈራለታለሁ ! ራስን የመኮፈስ በሽታ።" ሲሉ መለሱ

የመኮፈስ ስሜቱን የገደለ፣ እኩይ የነፍሱን ዝንባሌ ያከሰመና ልቡን ከአረሞቿ አጥርቶ የአላህና መልዕክተኛውን ፍቅር በልቦናው ላይ የተከለ ሰው ከአለም ውጥንቅትና ጥፋት ተቋርጦ ወደ ሰማያዊው ብርሀንና ሰላም የሚያደርሰውን እስትንፋስ ይምጋል። ስቃይና መከራ ከሞላት ጀሀነም ርቆ ወደ እዝነቱ ጉያ ይጠጋል።
ራሳችንን ከልብ በሽታዎች የጠራን ነን ብለን ማሰባችን መታከም እንዳንችል ያደርገናል። ነፍሳችንን አናጥራት።
ስለ እዩልኝ በሽታ አብዳህ ኢብን አቢ ሉባባህ የተሰኙ አቢድ እንዲህ ይላሉ
" ለይዩልኝ በሽታ ከማንም በላይ ቅርብ የሚሆነው በሽታው የለብኝም ብሎ የሚያስብ ግለሰብ ላይ ነው።"

ነፍስ በብዙ አይነት እኩይ ክጃሎቶች የተሞላች ናትና ከመሻቶቿ ሸሽታ ወደ አላህ ትዕዛዛትና ፍቅር ልትሰናዳ ይገባታል። ለዚህም ነፍሳችንን ማወቅ በሽታችንን ለመለየትና የልብ ህመማችንን ለማከም ይረዳናል።
👍4
የወራሪዋ እስራኤል ድሮን በፍልስጤማዊያን ላይ እሳት ማዝነቡን አጠናክሮ ቀጥሏል። ጋዛ ድብደባው በርትቶባታል። ህፃናት ከመሬቱ ተዘርረዋል። የዩኤን ሰራተኞች የጥቃቱ ሰለባ ሆነው ወድቀዋል።

ግብፅና ኳታር ከማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ ከኔትዛሪም አካፋይ ለቀው ወጥተዋል። ሰሜንና ደቡብ ጋዛን ለመክፈል የወራሪዋ ታንኮች መንገዱን ዘግተዋል።

የሃማስ ሁለት መሪዎችን ያሲር ሙሳ ሀርብ እና ሙሐመድ አል-ጀማሲን የወራሪዋ ጦር መግደሉን በይፋ አሳውቋል። በዚህ ጉዳይ ሐማስ እስካሁን የሰጠው ምንም መግለጫ የለም።

ከሐምሳ በላይ የወራሪዋ እስራኤል የጦር መኪኖች የሶርያን ድንበር ተሻግረው ገብተዋል። ቁነይጢራና ደርዓ ከተሞች ድረስ ዘልቀዋል። የአየር ጥቃቱም አልቆመም ከፍልስጤም እኩል ድብደባው ቀጥሏል።

የወራሪዋ እስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ካትዝ ዛሬ በሰጠው መግለጫ
  "ሁሉም እስረኞች ካልተፈቱና ሃማስ ጋዛን ለቆ ካልወጣ እስካሁን አይታችሁት የማታውቁትን ሃይል ይዘን ጋዛ እንገባለን። የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ምክር ተቀብላችሁ ታጋቾችን ፍቱ ሃማስንም አስወግዱ። ወደ ሌሎች አህጉራት መሰደድ ለምትፈልጉ መንገዶችን እናመቻቻለን። ሌላው ምርጫ ግን ፍጹም የሆነ ውድመትና ዕልቂት ብቻ ነው" በማለት ተናግሯል።

ይህ ጦርነት የመጨረሻው ፍልሚያ ጅማሮ እንጂ ሌላ አይደለም። ታላቁ ውጊያ ከመከሰቱ በፊት ለሕዝበ ሙስሊሙ የታሪክ ብዕርን አቀብሎ ከመዝገቡ የፈለጉትን እንዲያሰፍሩ እንካችሁ ብሏል። በክብር አሊያም በውርደት ገፆቻቸውን ያደምቁ ዘንድ ምርጫ ሰጥቷቸዋል።


                 Mahi Mahisho
😢5👍3
◕:مات وهو يقول
أمتي أمتي
إلا يستحق منا أن نصلي عليه
عليه افضل الصلاة والسلام
👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወላጆች

ከአሁኑ ለማስታወስ ያክል ነው
ሚጮሀውን መጫወቻ ከኢድ ሰላት በፊት ባትገዙ ለልጆቹም ለሰጋጁም አሪፍ ነው ቀልብ ውስጥ እንዳይገቡ እንደ አምና ስህተት እንዳይፈጠር ነው አደራ!
👍52
AHLEL MUSLIM pinned «ወላጆች ከአሁኑ ለማስታወስ ያክል ነው ሚጮሀውን መጫወቻ ከኢድ ሰላት በፊት ባትገዙ ለልጆቹም ለሰጋጁም አሪፍ ነው ቀልብ ውስጥ እንዳይገቡ እንደ አምና ስህተት እንዳይፈጠር ነው አደራ!»
Forwarded from Abdulkerim Muzeyen
2025/10/27 14:04:50
Back to Top
HTML Embed Code: