Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንደሐሳብ ብናወጋስ ! በቅርብ ቀን ይጠብቁ

#እንደሐሳብ
7👍3
Forwarded from 👳🏽ባለዕዳው
የዝምድና ገመዳችን መጠንከር ያለበት በቤተሰቦቻችን በጎ ፍቃድ ሳይሆን በኢስላም የተስፋ ቃል ነው ። ቤተሰቦቻችን የቆረጡትን ገመድ ይዘን መቋጠር እንጂ በበጠሱት ቦታ ቆመን መውደቅ የለብንም ።

ዝምድና ቀጥሉ🙌
👍73
የኩራት መገለጫዎች
***
ኢሕያእ ዑሉሚዲን መጽሐፍ
በኢማም አል-ገዛሊ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

* ኩራት በአንድ ሰው ሁኔታ ላይ ማለትም በፊቱ ሁኔታ፣ በእይታው፣ በአቀማመጡም ሆነ አደጋገፉ ላይ፣ በድምፁና በአነጋገሩ ቃና ላይ፣ በአረማመዱ በአቋቋሙና በአቀማመጡ፣ በእንቅስቃሴውና በእርጋታው፣ በድርጊቶቹ፣ በሌሎች የተለያዩ አኳኋኖቹ በንግግሮቹና በተግባራቱ ላይ ሁሉ ሊገለፅ ይችላል።

 *ከኩራተኞች መካከል ሰው እንዲነሳለት የሚወድ አለ። ዐሊ (ረ.ዐ.) እንዲህ ይላሉ፡- “ወደ እሳት ሰው መመልከት የፈለገ ሰው እሱ ተቀምጦ ሰዎች በዙሪያው የቆሙትን ሰው ይመልከት።” ብለዋል።

* ሲሄዱ በሰው መታጀብን መፈለግም የኩራት ምልክት ነው። ታላቁን ሶሐባ ዐብዱረሕማን ኢብኑ ዐውፍን ከአገልጋዮቹ መለየት አይቻልም ነበር ይባላል።

* እንዲዘይሩት መፈለግና ሌላን ለመዘየር አለመፍቀድም የኩራት መገለጫ ነው። ....

* ሌሎች ከሱ ቀርበው ሲቀመጡ መጠየፍም ኩራት ነው።

* በቤት ውስጥ ሥራ አለማገዝም ከኩራት ነው።

* የራስን ዕቃ ወስዶ ተሸክሞ ቤቱ አለማድረስም የትሁት ሰዎች መገለጫ አይደለም።
  ሠዕለባ ኢብኑ ማሊክ አልቁረዚ እንዲህ ይላሉ፡- አቢ ሁረይራ እስር እንጨት ተሸክሞ ከገበያ ሲመለስ አየሁት። እሱ ያኔ የመርዋን  ኸሊፋ ነበር።
7👍2
ኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል እንዲህ ይላሉ፦
" ገና በአሥር ዓመቴ ነው እናቴ ቁርኣን ያስሐፈዘችኝ። ለሱብሒ ሶላት ትቀሰቅሰኝ፣ ለከባድ የባግዳድ ብርድ ብላም የዉዱእ ዉሃ ታሞቅልኝ ነበር። መስጊዱ ከቤታችን እሩቅ ስለነበርና ጨለማዉም ስለሚያስፈራ ልብስ አልብሳኝ ሒጃቧን ለብሳ እና በደንብ ተሸፋፍና ወደ መስጊድ ትወስደኝ ነበር።" (አብኑል ቀይም እንዳወሩት።)
ብዙዎቹ የዓለማችን ትላልቅ ሰዎች በእናት እጅ ብቻ ያደጉ ናቸው
©️
👍101
ትናናሽ ኃጢአቶች ወደ ትላልቆቹ የሚያድጉበት ምክንያቶች
ምንጭ ፣ 'ወደ አላህ ሽሹ' መጽሐፍ

1-      በኃጢአት ላይ መዘውተር (ሙጭጭ ማለት) ፡-
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)  “ ከመዘውተር ጋር ትንሽ የሚባል ኃጢአት የለም። ከተውበት (ንስሃ) ጋር ደግሞ ትልቅ ኃጢአት የለም።”
2-      ኃጢአትን አሳንሶ መመልከት፡-  
ኢብን መስዑድ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡- “አማኝ ሰው ሃጢአቱን ልክ በራሱ ላይ ሊወድቅ እንደሚያንዣብብ ተራራ አድርጎ ይመለከተዋል። ዝንጉ (ሙናፊቅ) ሰው ግን ኃጢአቱን እጁን ቢያወናጭፍ ሊያባርራት እንደሚችል ዝንብ ነው የሚያየው።”(ቡኻሪና ሙስሊም)
 
አነስ ኢብን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡- “እናንተ እንደ ፀጉር አቅልላችሁ የምትመለከቱትን ኃጢአት በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጊዜ ከአውዳሚ ወንጀል እንቆጥረው ነበር።”        (ቡኻሪ ዘግበውታል)
 
ቢላል ኢብን ሰዕድ (አላህ ይዘንለትና) እንዲህ ይላል፡- “የኃጢአትህን ትንሽ መሆን አትመልከት የምታምጸውን ጌታ ታላቅነት ተመልከት።”
3-      በኃጢአት መደሰት፡-
አንድ ሰው “የእገሌን ክብር እንዴት እንዳዋረድኩትና ሃፍረት እስኪይዘው ድረስ ኃጢአቱን እየዘረዘርኩ እንዳሸማቀቅኩት አላየህምን? “ በማለት ሊናገር ይችላል። አንዱ ነጋዴ ደግሞ ለጓደኛው “ያንን ሰው እንዴት እንዳታለልኩትና እንደተጫወትኩበት አልሰማህምን?” በማለት ወንጀሉን ገድል አድርጎ ሊያወራ ይችላል። እነዚህን የመሠሉ አባባሎች ትንሹን ኃጢአት ወደ ትልቅ የሚቀይሩ ምሣሌዎች ናቸው።
4-     የአላህን ነውር የመሸፈን ፀጋ ችላ ማለት ፡-
 አላህ የአንድን ባሪያውን ኃጢአት በመሰተርና በቅጣቱ ባለመቸኮሉ መዘናጋት ታናናሽ ኃጢአቶችን ወደ ታላቅ ይቀይራቸዋል።
5-     የፈጸሙትን ኃጢአት በሌሎች ሰዎች ፊት ማውሳት፡-
አቡሁረይራ (ረ.ዐ.) የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፈዋል፡- “ከኡመቶቼ የፈጸሙትን ኃጢአት ይፋ የሚያደርጉ ሲቀሩ ሁሉም ምህረት ያገኛሉ። ሰውዬው በሌሊት የፈጸመውን ኃጢአት አላህ የሰተረው ሆኖ እያለ ሲነጋ “እገሌ ሆይ! እንዲህ ዓይነት ኃጢአት ትናንት ፈጸምኩ” በማለት ያወራል።”
6-    ኃጢአት የሚፈጽመው ሰው ሰዎች የሚመሩበት የዕውቀት ባለቤት ከሆነና የፈጸመው ኃጢአት ከታወቀ ወደ ታላቅ ኃጢአት ከፍ ይልበታል።
5👍1
ኢማም ሻፊዒ
****
ኢማም ሻፊዒ ረሒመሁላህ ለዚህ ዓለም እንደ ፀሐይ ናቸው የተባሉ ሊቅ ናቸው፡፡ የተወለዱት ፈለስጢን ምድር ገዛ ከተማ ነው፡፡ የቲም ሆነው ነው ያደጉት፡፡
ከአባታቸው ሞት በኋላ እናት ልጇን ማሳደግ ትልቁ ሥራዋ አደረገች፡፡ ሻፊዒን በልጅነታቸው በስለት መልክ በዕውቀት ፍለጋ ላይ አሰማራቻቸው፡፡ እርሣቸዉም ትልቁን ዕውቀትና ጥበብ ከእናታቸው እንዳገኙ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡
ኢማም ሻፊዒ ገና በወጣነትነታቸው ዒልሙን ሁሉ ሰበሰቡ፡፡ በ18 ዓመታቸው ፈትዋ መስጠት ጀመሩ፡፡

የኢማም ሻፊዒ ታሪካቸው ግዙፍ ነው፡፡ አላህ ዕውቀትንና ግንዛቤን ሠጥቷቸዋል፡፡ የዘመናቸው ልዩና ድንቅ ሰው መሆናቸዉን ሁሉም ይቀበላል፡፡ በሁሉም የዕውቀት ዘርፍ በሐዲሥ፣ በተፍሲር፣ በታሪክ፣ በፊቅህ፣ የበቃ ዕውቀት አላቸው፡፡

ኢብኑ ረሃወይህ እንዲህ ይላሉ- “እርሣቸው ሳላውቅ አንድ ቀን የሻፊዒ የዒልም መጅሊስ ላይ ታደምን፤ የሚናገሩት ሁሉ ከዚህ በፊት ሰምቼ የማላውቀው የተለየ ሆነብኝ፡፡ ስለ ፊቅሂ ሲያነሱ በዚህ ዙርያ ከርሣቸው በላይ ሊያውቅ የሚችል አንድም ሰው የለም እላለሁ፤ ስለ ሐዲሥም ስለ ተፍሲርም፣ ስለ ቋንቋም ስለ ታሪክም እንዲሁ፡፡ ወደ ኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል ዘወር አልኩና “ማነው ይህ ሰው! አላህ የዚህ ዓይነት ሰው የፈጠረ መሆኑን አላውቅም፣ በዐይኔም እስከዛሬ አላየሁም፡፡” አልኳቸው፡፡

ኢማሙ በርካታ መጽሐፎችን ፅፈዋል፣ አር-ሪሳላ እና አል-ኡም በዋናነት ይጠቀሱላቸዋል፡፡ የሰፊውን የጥልቁ ዕውቀት የፊቅህ መሠረታዊ መርሆች መሥራችም ናቸው፡፡

ሻፊዒ ስለ ወንድማማችነት ብዙ የሚጨነቁ ታጋሽና አስተዋይ እንደሆኑም ይነገርላቸዋል።
ዩኑስ ሱድፊ እንዲህ ይላል ፡- አንድ ቀን ከኢማም ሻፊዒ ጋር ተከራከርንና ሳንግባባ ተለያየን፤ የሆነ ቀን መንገድ ላይ አገኘኝና “የሙሳ አባት ሆይ በአንድ ጥያቄ ላይ መግባባት ቢያቅተን፤ ወንድማማችነታችን ማስቀጠል ያቅተናል ወይ፡፡” አለኝ፡፡

ኢማም ሻፊዒ ከ150-204 ዓ.ሂ ምድር ላይ 54 ዓመታትን ኖረዋል፡፡ አላህ ይዘንላቸው፡፡
👍63
ስለ አደብ ከተባሉት

፨ ልጆቹን በአደብ ያሳደገ በዕድሜው አመሻሽ ላይ ይረካባቸዋል።
፨ ከዕውቀት በፊት አደብን ተማሩ።
፨ ገንዘብ ካለው አደብ ያለው ይበልጣል።
፨ አደብ ከሌለ ማክበርም መከባበርም የለም።
፨ ከስንቅ በላጩ የአላህ ፍራቻ ሲሆን ከዉርስ ደግሞ ምርጡ አደብ ነው።
፨ አደብ የሌለው ሰው አውሬ ነው፤ ያገኘዉን ሁሉ ይናከሳል።
👍112
ነበር....


ህይወት የዓለማችን ትልቁ ትምህርት ቤት ናት፡፡ ዕድሜ የህይወት ትልቁ መምህር ነው፡፡ በዱኒያ ላይ ሁለት ቀን የኖረ ሰው አንድ ቀን ከኖረው በላይ ብዙ አይቷል፡፡ ረጅምና አጭር እድሜ በተሠጡ ሁለት ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ይብዛም ይነስ የተሠጠውን ነገር መጠቀሙ ላይ ነው፡፡ ረጅም እድሜ የተሠጣቸው ብዙ ሰዎች እድሜአቸውን ያለአንዳች ጥቅም ሲያባክኑ እናያለን፡፡ በተሠጣቸው ጥቂት የዱኒያ ላይ እድሜ የረጃጅሞቹን ያህልና ከዚያም በላይ የሚጠቀሙም እንዲሁ አለ፡፡ ያም ተባለ ይህ በምድር ላይ በህይወት እያለ ነገሮችን በጥልቀትና በማስተንተን ልቦና ያየ ሰው ካለፉትም ሆነ ካለበት ሁኔታዎችና ነገሮች ብዙ ብዙ መማር ይችላል፡፡

አንዳንዴ በህይወት ጉዞ መካከል ቆም ብለን የዚህችን ዓለም ሁኔታ በጥልቀት ብንቃኝ ጉድ እንሰኛለን፡፡ ከአባታችን አደም ዐለይህ ሰላም ጀምሮ በርካታ ፍጥረታት አልፈዋል …አልቀዋል፡፡ብዙዎች ወደዚህች ምድር መጥተው ተመልሰው ሒደዋል፡፡ ጥቂት ታሪክ የሚያወሳቸውና ትውልድ የሚቀባበላቸው ስሞች ብቻ ሲቀሩ ከመሬት በታች የዋለው አብዛኛው የሰው ዘር ስለመምጣቱም ሆነ ስለመፈጠሩ የማናውቀው በ‹ነበር› ብቻ ያለፈ ነው፡፡

ቅድመ አያቶቻችንም ሆኑ አያቶቻችን በአንድ ወቅት በዚህች ምድር ላይ ነበሩ ፤ ዛሬ ግን የሉም፡፡ ይህች ዓለም ከጊዜዎች በሆነ ጊዜ ላይ ዛሬ በሚዲያ ብዙ የሚባልላቸውን ፤ በአፈ ታሪክ በሠፊው የሚነገርላቸውን ግዙፍም ሆነ ድቃቃ ሰዎችን ተሸክማ ነበር፡፡ ያኔ ደረታቸውን ነፍተው ሲሔዱባት የነበሩ ሰዎች ዛሬ ውስጧ ሲገቡ የመሬት ውስጧም እንደ ላይዋ ይመቻቸው ይሆን ! … ምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ይሆን የሚገኙት ?

ከ'ልብ ላላሉ ልቦች' መጽሐፍ
በሙሐመድ ሰዒድ
3👍3
ለወላጅ መልካም መዋል ማለት ትርጉሙ በትክክል የገባው ይመስላል፡፡ ደክመው እቤት ከቀሩበት ጊዜ ጀምሮ ሀሳቡና ዉሎው ከአባቱ ጋር ሆኗል፡፡

ዛሬም ሊያዝናናቸው አስቦ ወጣ፡፡  ይዟቸው እራት ለመብላት ብሎ ወደ አንድ ቅንጡ ሆቴል ጎራ አለ፡፡ ፊትለፊቱ አስቀመጣቸው፣ ምግብ አዘዘና መጣላቸው፣ እንዲመገቡ ጋበዛቸው፣

አባቱ እጃቸው ይንቀጠቀጣል፣ ሲመገቡ ምግቡ ጠረጴዛው ላይ  ይወድቃል፣ ልብሳቸዉንም ያበላሻል፡፡ ልጅ ልጅነቱ ትዝ እያለው በሚያየው ነገር ይደሠታል፡፡

በምግብ ቤቱ ዉስጥ ያለ ሰው ሁሉ ወደነርሱ ይመለከታል፣
ልጅ ተረጋግቶ አባቱ በልቶ እስኪጨርስ ጠበቃቸው፣
በቃኝ ሲሉ እጃቸዉን ይዞ ወደ መታጠቢያ ቤት አመራ፡፡ እጃቸዉንና አፋቸዉን አጠበ፡፡ ልብሣቸዉንም ጠራረገ፡፡
ተመልሶ ጠረጴዛዉን አፀዳ፡፡ የምግቡን ሂሳብ ከፈለና ወጣ፡፡
ሲወጣ አንድ ሰው ተከተለው፡፡ የሽማግሌዉን ራስና ግንባር ሳመው፡፡
ወደ ልጁም “ አንተ የአባትህ የአስተዳደግ ዉጤት ስለሆንክ ነው እርሣቸዉን የሳምኩት፡፡ ግና የሆነ ነገር ትተህ የወጣህ አይመስልህምን?” አለው፡፡
“አረ ምንም አልተውኩም፡፡” አለው ልጅ፡፡
ሰዉዬዉም “አዎ ዕቃ አልተውክም ይሆናል፤ ነገርግን ለወላጆች መልካም በመሆን ዙርያ እዚህ ቤት ለተገኘው ሁሉ ትልቅ ትምህርት ትተህ ነው የወጣኸው፡፡” አለው፡፡
👍91
AHLEL MUSLIM
Photo
አንቶኒ ኤግለር ይባላል በጡረታ የተገለለ የአሜሪካ ልዩ ሀይል አባል የነበረ ነው ።

አንቶኒ ከልዩ ሀይሉ በጡረታ ከተገለለ በኋላ ዩጂ ሶሉሽን በሚባል የግል ሴኪውሪቲ ካምፓኒ በኩል በአሜሪካና እስራኤል በሚመራው Gaza Humanitarian Foundation (GHF) ውስጥ የሚሰሩ አሜሪካውያንን ደህንነት ለመጠበቅ ወደጋዛ ሄዶ ለብዙ ወራት የቆየ ነው ።

እና ሰሞኑን ተመልሶ ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ከBBC ጋር ቃለ መጠይቅ ባደረገበት ወቅት እንዲህ አለ
..
" ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት የአምስት አመት ልጅ ሲሆን ስሙ አሚር ይባላል ።
አሚር ወደዚህ የእርዳታ መስጫ ጣቢያ የመጣው 12 ኪ/ሜትር ተጉዞ ነበር ።
አንቶኒ ኤግለር በባዶ እግሩ ለሚሄደው በረሀብ የተጎሳቆለ ህጻን ትንሽ ሩዝ እና አንዳንድ ምግቦችን ሰጥቶት እንደጨረሰ
ትንሹ አሚር እጁን ዘርግቶለት እየጨበጠው አመሰግናለሁ አለው ።
በዚህ ወቅት በህጻኑ ሁኔታ ልቡ የተነካው አንቶኒ ኤግለር አሚር ወዳለበት በመጠጋት በርከክ ብሎ ስለ እናንተ ግድ የሚላቸው ፡ ስለ እናንተ የሚያስቡ ሰወች አሉ አለው ፡ አሚር በርህራሄ የሚያወራውን አሜሪካዊ ኮለኔል ጭንቅላት በትናንሽ አቧራማ እጆቹ ይዞ ጥርት ባለ እንግሊዝኛ አመሰግናለሁ ካለው በኋላ የተሰጠውን ምግብ ይዞ ሄደ ።

ከጥቂት ደቂቃ በኋላ የእስራኤል ጦር የእርዳታ ምግብ ሊወስዱ በመጡ የተራቡ ፍልስጤማውያን ላይ ተኩስ ከፈተ ።

በዚህ ተኩስ ብዙዎች በጥይት ተመቱ ፡ ከነዚህ መሀከልም ከደቂቃዎች በፊት በአቧራማ እጆቹ ጭንቅላቴን እየነካካ አመሰግናለሁ ያለኝ ትንሹ አሚር ይገኝበታል ።

አሚር በዚህ ተኩስ በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፋለች

ያየሁት ነገር ከምቋቋመው በላይ ሆነብኝ ፡ በዚህ ስፍራ በማየው አስፈሪ ነገር ምክንያት በስራ ላይ መቆየት የለብኝም በማለት ስራዬን ለቅቄ ወደ አሜሪካ ተመለስኩ ።

በጋዛ የዚህ አይነት እልቂት በየጊዜው ይከሰታል ፡ ይሄኔ የትንሹ አሚር ቤተሰብም በዚህ አይነት ሁኔታ ሞተው ምግብ ይዞ እንደሚመጣ አስባ የምትጠብቀው ትንሽ እህት ይኖረው ይሆናል
በማለት የእስራኤል ጦር ፡ በተራቡና ፡ አንዳችም ጦር መሳሪያ ባልታጠቁ ፍልስጤማውያን ላይ የሚፈጽመውን በጭካኔ የተሞላ አስፈሪና ዘግናኝ ድርጊት አጋልጧል ።

( ፎቶው አሚር ከመ7ደሉ ከደቂቃዎች በፊት በአንቶኒ ኤግለር የተነሳ ነው )
****
Wasihune Tesfaye
😭61
አቢ ሁረይራ (ረ.ዐ.) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ.)
"መንገድ ላይ ሰዉን ታስቸግር የነበረችን እንጨት በመቁረጡ ምክንያት ጀነት ዉስጥ የሚገላበጥ አንድ ሰውዬ አየሁ።" ብለዋል።

ከመንገድ ላይ አስቸጋሪን ነገር ማስወገድ ምጽዋት ነው
👍4
- አንድ ሰው ለኢማም አሽ-ሻፊዒ ዘንድ መጣና “አንድ ሙስሊም ከወላጆቹ ጋር ክርክር ይገጥማልን?” አላቸው፡፡
“በፍፁም! ሌላው ቀርቶ ከነርሱ የጫማ ክር ጋር እንኳን አይገጥምም” አሉት፡፡

- ወላጆቹ መሳሳታቸዉን ለማሳየት ብሎ ማስረጃ የሚያፈላልግ በነርሱ እንዳመፀ ነው የሚቆጠረው” ይላሉ አንድ ዓሊም፡፡

- ለወላጅ መልካም መዋል ማለት እነርሱ ካንተ ምንም ሳይፈልጉ የሚያስደስታቸዉን ሁሉ ማድረግ ነው ተብሏል፡፡

- ትልቅ መሆንህን የምታውቀው መቼ እንደሆነ ታውቃለህ? .. ወላጆችህን መፍራት ትተህ ለነርሱ መፍራት ስትጀምር፡፡

- የቲምነት ዓይነቱ ሁለት ነው፤ ትንሽ እና ትልቅ፡፡ ትንሹ ወላጆችህን በሞት ስታጣ ሲሆን ትልቁ የነርሱን ዱዓ ስታጣ ነው።

- ወላጆችህን ደጋግመህ በፍቅር ዐይን እያቸው፤ ትንሽ ሆነህ ልዑሌ ሲሉህ ነበር፤ አንተ ደግሞ ዛሬ ንጉሦቼ በላቸው፤

ተጠንቀቅ …
- ከሌሎች ጋር በትህትና እየኖርክ እነርሱን ከመገፈታተር
👍41
ጁሙዓ ቀን እና ነቢያዊ ፈለግ (ሶ.ዐ.ወ.)
1.         ጁሙዓ ቀንና ሌሊት በኔ (ሶ.ዐ.ወ.) ላይ ሶለዋት ማውረድ አብዙ ይደርሰኛል ብለዋል፣
2.         ሰዎች ለጁሙዓ ሶላት ማልደው እንዲወጡ አበረታተዋል፣
3.         ጁመዓ ቀን ገላን መታጠብ እንደሚገባ መክረዋል፣
4.         ለኹጥባ ወደ ሚንበር ሲወጡ ‹አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላህ ወበረካቱህ› ይላሉ፣
5.         ቆመው ኹጥባ ያደርጉ ነበር፣
6.         ኹጥባቸዉም ሁለት ነበር፣
7.         በኹጥባዎቹ መካከል መጠነኛ ዕረፍት ያደርጋሉ፣
8.         ኹጥባ በሚያደርጉበት ጊዜ ቀጭን ዱላ ይዘው ነው፤
9.         ኹጥባቸው ረጅምም አጭርም የሚባል አልነበረም፣
10.     ጥቁር ጥምጣም ለብሰው ኹጥባ ያደርጉ እንደነበር ተነግሯል፣
11.     የጁሙዓን ሶላት ፀሐይ ከመሃል ሰማይ ዘንበል ባለች ጊዜ ይሰግዱ ነበር፣
12.     ኹጥባ በሚያደርጉበት ጊዜ አላህን በማመስገንና በማወደስ ይጀምራሉ፣
13.     ኹጥባ በሚያደርጉበት ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ትኩረታቸዉም ይጨምራል፣
14.     ኹጥባ በሚያደርጉበት ጊዜ በሚንበሩ ላይ ከቁርኣን የ ‹ቃፍ›ን ምዕራፍ በማንበብ ይገስፁ ነበር፣
15.     ኹጥባ በሚያደርጉበት ወቅት ወደ መስጊድ የሚገባ ሰው ካለ ሁለት ፈጠን ያሉ ረከዓዎችን እንዲሰግድ ያዙት ነበር፣
16.     ቀድመው መስጊድ በገቡ ሰዎች ትከሻ ላይ መረማመድን ከልክለዋል፣
17.     የጁሙዓ ቀን አማኞች ባማረ ንጽህና ላይ እንዲገኙ፣ ነጭ ልብስ እንዲለብሱና ሽቶ እንዲቀቡ አዘዋል፣
18.     በጁሙዓ ሶላት ውስጥ በመጀመሪያው ረከዓ የ “ሰብቢሕ/አል-አዕላን” እና በሁለተኛው የ “አል-ጋሺያን” ምዕራፍ ያነቡ ነበር፡፡ ወይም በመጀመርያው የ‹አልጁሙዓ›ን ምዕራፍ በሁለተኛው ረከዓ የ ‹አል-ሙናፊቁን›ን ምዕራፍ ያነቡ ነበር፣
19.     ጁሙዓ ከሰገዱ በኋላ ሱና ያልሰገዱ እንደሆነ ወደ ቤታቸው ሲሄዱ ሁለት ረከዓ ቤታቸው ውስጥ ይሰግዱ ነበር፣
20.     ከጁሙዓ ሶላት በኋላ መስጊድ ውስጥ አራት ረከዓ ስገዱ ይሉ ነበር፣
21.     በጁሙዓ ቀን የአል-ከህፍን ምዕራፍ አንብቡ ብለዋል፣
22.     ሱብሒ ሶላት ላይ የ “አስ-ሰጅዳ”ንና የ “አል-ኢንሳን”ን ምዕራፍ ያነባሉ፣
23.     በጁሙዓ ቀን ወደ ኢማሙ ቀርቦ መቀመጥ እንደሚወደድ ተናግረዋል፣
24.     ኢማሙ ኹጥባ ሲያደርግ በፀጥታ ኹጥባዉን ማዳመጥ እንደሚገባ አሳስበዋል፣
25.     በጁሙዓ ቀን ዉስጥ ዱዓ ምላሽ የሚያገኝበት አንዲት ሰዓት እንዳለችና እሷንም እንድንጠባበቅ ጠቁመዋል፣

©️
2👍2
ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው ያሻውን ከሚከውን ፈጣሪው ኃይል ፊት ደካማነቱ ይሰማዋል፡፡ ጌታው የዩኒቨርሱ ፈጣሪ፣ መሪና አስተናባሪ ሲሆን እርሱ ግን ተፈጣሪ ተመሪና ስልጣን የለሽ ነው፡፡ ፈጣሪው ኃያል፣ የበላይና የሕይወት ምንጭ ሲሆን እርሱ ግን ፈሪና ደካማ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት አንድ ሺ አንድ ጐደሎ ባህሪያት የታጨቁበት የሰው ልጅ ፍፁምና የምሉዕ ባህርያት ባለሀብት የሆነው ፈጣሪው ድጋፍ ከምንም በላይ ያሻዋል፡፡
ከጌታው ጋር አስተማማኝ ቁርኝት መፍጠር የሰው ልጅ ዓይነተኛ አስፈልጐት ነው፡፡ ይህ ከተሳካለት ከፍርሃት ተነጥሎ፥ ከጭንቅ ተገላግሎ፥ በመለኮታዊ ጥበቃ ሥር የዋለች፥ በተድላ የሞቀች፥ በእውነተኛ እርካታ የደመቀች ሕይወትን መምራት ይቻለዋል፡፡ ታሪክ በአስደናቂነቱ ያሰፈረው የመጀመሪያው ቁርኣናዊ ትውልድ ላይም ሆነ አሁንም በእውነተኛ ሙስሊሞች ላይ የሚንፀባረቀው ማራኪ ሕይወት በስፋት እውን ሊሆን የሚችለው ግን በፈጣሪና በፍጡሩ መካከል ያለው የግንኙነት ሰንሰለት አስተማማኝ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ የኢማን ግንኙነት!፡፡ ስለሆነም በአላህና የዚህን ጥብቅ ትስስር ዝርዝር ሁኔታ ባስቀመጡልን ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ማመን ከምንም በላይ ያስፈልጋል፡፡

ምንጭ ፡ ከኢማን አድማስ መጽሐፍ
👍51
وَلَا تُصَعِّرْ خَدَّكَ لِلنَّاسِ
«ጉንጭህንም (በኩራት) ከሰዎች አታዙር፡፡

የህያ ኢብኑ ሙዒን እንዲህ ይላሉ።
እንደ አህመድ ኢብኑ ሀምበል ያለ ሰው አይቼ አላውቅም።
ለሀምሳ አመታት ተወዳጅተነዋል ግና እርሱ ዘንድ ካለው መልካምነትና በጎ ነገር አንድም ቀን እኛ ላይ ኮርቶብን አያውቅም።
" እኛ ሚስኪን ህዝቦች ነን" ይሉም ነበር።

ተናነስ!
እንድትኮራ የሚያደርግ ሀብት_ድህነት ነው!
የበላይነት እንዲሰማህ የሚያደርግ እውቀት_ጅህልና ነው!
ሌሎችን እንድትጨቁን የሚደርግ ጉልበት_ደካማነት ነው!

ክብር ፣ እውቀትና መብቃቃትን የሚተናነሱ ሰዎች ጋር ታገኛታለህ!
👍71
የመልካም ሥነምግባር ዋጋ🤗

አላህ (ሱ.ወ.)  ወዳጃቸዉን ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ.) ሲያወድሳቸውና በርሣቸው ላይ የዋለዉን ፀጋ ሲገልጽላቸው፡-
“አንተ በርግጥም በታላቅ ሥነ-ምግባር ላይ ነህ፡፡” ብሏቸዋል፡፡ ምርጥ ባህሪ ያስወድሳል፡፡

እናታችን ዓኢሻ (ረ.ዐ.) ሲናገሩ “የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ባህሪያቸው ቁርኣን ነው፡፡” ብለዋል፡፡
ቁርኣን አስተምሀሮው ሁሉ መልካም ነው፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) “የተላክሁት ምርጥ ሥነምግባራትን ላሟላ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ሥነምግባራት ያድጋለ፤ ይመጥቃሉም፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) በሌላ ሐዲሣቸው “በትንሳኤ ቀን በሚዛን ላይ ተደርገው እጅግ ከባድ ከሆኑት ነገሮች መካከል የአላህ ፍራቻ እና መልካም ሥነምግባር ነው፡፡” ብለዋል፡፡

በሌላም ሐዲሥ “የትም ብትሆን አላህን ፍራ፣ መጥፎ የሠራህ እንደሆነ በጥሩ አስከትል ታብሳታለችን፤ ከሰዎች ጋር በመልካም ሥነምግባር ተኗኗር፡፡” ብለዋል፡፡

ከአላህ መልዕክተኛ ዱዓዎች መካከል “ አላህ ሆይ ምርጥ ወደሆነው ሥነምግባር ምራኝ፤ ካንተ በላይ ወደ ምርጦቹ የሚመራ ማንም የለምና፤ መጥፎዎቹንም አስወግድልኝ፤ መጥፎዎቹን ካንተ በላይ የሚያስወግድ የለምና፡፡”
7👍2
የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 1
───────────
ኢብኑ_ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ዱንያ ውስጥ ካሉ ነገሮች አስደሳቹ አላህን ማወቅ ሲሆን አኺራ ውስጥ ካሉ ነገሮች አስደሳቹ ደግሞ አላህን መመልከት ነው ፤ ጥራት ይገባውና።»

📚 ۞ مجمـوع الفتـاوي【14/163】۞
12👍1
በእርግጥም አንተ የፈጅር ሰላት ሰግደህ
ዙህር ላይ ደግሞ አንተ ላይ ሊሰገድብህ ይችላልና
የ አላህን ትዛዝ ጠብቅ..

ንጋት ዱንያ ላይ ሆና
ምሽት ደግሞ አኺራ የሄደች
ስንት ነፍስ አለች..

መጨረሻችንን አላህ ያሳምርልን🤲
ሰባሁል ኸይር🌸
11👍1
2025/10/21 13:00:22
Back to Top
HTML Embed Code: