Telegram Web Link
ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጠው ቢላል ማይክሮ ፋይናንስ የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ ከፈተ!

(ሀሩን ሚድያ ነሀሴ 4/2016፤አዲስ አበባ)
.
ቡዙ ውጣውረዶችን ያለፈው ሙሉ ለሙሉ ሸሪአውን መሰረት ያደረገ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎት የሚሰጠው ቢላል ማክሮፋይናንስ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ ቅርንጫፉን "ኢህሳን አጠና ተራ" በሚል ስያሜ የምርቃትና የማስጀመሪያ መርሀግብር አካሂድዋል።
.
ዝቅተኛ ገቢ ያለው ሙስሊም ማህበረሰብ በወለድ ምክንያት ከማይክሮ ፋይናንስ ተገሎ እንደቆየ የተገለፀ ሲሆን ቢላል ማይክሮ ፋይናንስ ለሴቶችና ወጣቶች በከተማና በገጠር ያለውን ሙስሊም ማህበረሰብ ሸሪዓውን የጠበቀ የፋይናንስ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
.
በዛሬው ዝግጅት ላይ ቢላል ማይክሮ ፋይናንስ እውን እንዲሆን አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
.
¤ሀሩን ሚድያም በዝግጅቱ ላይ ተገኝቶ ያጠናቀረውን የቪዲዮ ዘገባ በቅርቡ ወደናንተ ያደርሳል!

©ሀሩን ሚድያ
ቀን 12/12/2016
       የአፋልጉኝ ማስታወቂያ
 ተፈላጊዎች፥-  1ኛ)አቶ ሰይድ ሀሰን ሙሄ ወይም አማረ ገብሬ
               2ኛ) ቃል ኪዳን አማረ ገብሬ
የትውልድ ቦታ፥- ወሎ ሀይቅ ልዩ ስሙ 012 ቀበሌ ጎበያ
አድራሻ ፥-አድስ አበባ ኮተቤ አካባቢ
 ፈላጊዎች
1)  አቶ መሀመድ ሀሰን ወንድም
2) ወ/ሮ ፋጤ አሊ እህት
3) አቶ አሊ መሀመድ የወንድም ልጅ
4) አቶ አደም መሀመድ የወንድም ልጅ
            አድራሻ፡- ኮምቦልቻ
ተፈላጊ አጎታችን አቶ ሰይድ ሀሰን ሙሄ ሲሆን ከትውልድ ቦታው ወሎ ሀይቅ ልዩ ስሙ 012 ቀበሌ ጎበያ ከወጣ በኋላ ስሙን ቀይሮ አማረ ገብሬ ተብሎ ነው የሚጠራው አጎታችን አቶ ሰይድ ሀሰን ( አማረ ገብሬ በ1965 አም ጀምሮ ከትውልድ ቦታው ለስራ ብሎ ወደ አድስ አበባ እንደሄድ ሰምተናል።ነገር ግን የዛሬ 30 አመት አካባቢ ለቤተሰብ በላከው ደብዳቤ አድስ አበባ ኮተቤ አካባቢ እንደሚኖር ቃል ኪዳን አበራ የምትባል ልጅ መውለዱን ያሳወቀን ቢሆንም እስካሁን ስልኩንም ሆነ አድራሻውን ማግኜት አልቻልንም ።
አቶ አማረ ገብሬን(ሰይድ ሀሰን ሙሄ) ን ወይም ልጁን ቃልኪዳን አማረ  የምታውቋቸው ካላችሁ 0911084205 ስልክ ደውላችሁ ብትነግሩን ወርታውን እንከፍላለን፡፡
ፈላጊ ቤተሰቦቹ
ልጄን አድኑልኝ !

#Ethiopia | በፈጣሪ ስም እለምናችኃለሁ ልጄን አድኑልኝ !!!

ልጄ ሪናድ ሠይድ ትባላላች። የ13 ዓመት ልጅ ናት። ባጋጠማት የልብ ችግር እንደ ጓደኞቿ ወጥታ ለመማርም ሆነ እንደልጅ ለመቧርቅ አልቻለችም። በአልጋ ላይ ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል እስካአሁን በጳውሎስና በጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ህክምና በትከታታለም ከህመሟ ልትድንልኝ አልቻለችም።

በአሁኑ ሠዓት በአስቸኳይ ወደዉጪ ሀገር ሄዳ መታከም እንዳለባት የሀኪሞች ቦርድ ወስኗል። ለዚህም ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ህክምናው እንደሚፈጅ ተነግሮኛል።

እባካችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን ድረሱልኝ ልጄን ከሞት ታደጉልኝ

ወላጅ አባቷ ሠይድ ኑሩ አብዱልቃድር

አካውንት ቁጥር ንግድ ባንክ 1000002846636

አዋሽ ባንክ
01425897443200

ስልክ ቍጥር
0911174518
ወይም
0777 85 45 18

ድረሱ
“በትንሳዔ ዕለት የስራ መዝገቡ አስደስቶት መመልከትን የወደደ እስቲግፋር ማድረግ ያብዛ።”

ረሱል (‎ﷺ)
“ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።”

ረሱል (ﷺ)
ከራስህና ከቤተሰብህ ጀምር…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

“አላህ ለአንዳችሁ መልካምን ነገር (ገንዘብን) ከዋለላችሁ መጠቀሙን ከራሱና ከቤተሰቡ ይጀምር።”

ሙስሊም ዘግበውታል: 1822
“ከወንድሙ ክብር በርቀት (በሌለበት) የተከላከለ ሰው በአላህ ላይ ከእሳት ነፃ ሊያወጣው ሐቅ አለ።”

ረሱል (ﷺ)
🛑 እስከሚነጋ ወይም እስከሚመሽ ድረስ በ70 ሺ መልዐክ ዱዐ እንዲደረግልህ ትፈልጋለህ?

ዐልይ ኢብን አቢ ጧሊብ(ረዐ) "የአላህ መልእክተኛን(ሰዐወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አሉ:–

🛑 "አንድ ሙስሊም ጠዋት ላይ የታመመን ሙስሊም አይጠይቅም በሱ ላይ እስከሚመሽ ድረስ 70 ሺ መልአክ ሶለዋት የሚያወርድበት ቢሆን እንጂ። በማታ ከጠየቀውም እስከሚነጋ ድረስ ሰባ ሺ መልአክ ሶላት ቢያወርድበት እንጂ።"

🛑ቴሌግራም ቻናል T.me/ahmedin99
“ሌሊት መስገድን አስቦ ወደ ፍራሹ የሄደ ከዚያም እስከ ንጋት ዓይኑ ያሸነፈችው ያሰበውን አላህ ይፅፍለታል፤ እንቅልፉም ከጌታው ዘንድ ሶደቃ ይሆንለታል”

ረሱል ﷺ

(ነሳኢ 1787ና ኢብኑ ማጀህ 1344)
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿ما مِن يَومٍ يُصْبِحُ العِبادُ فِيهِ، إلّا مَلَكانِ يَنْزِلانِ، فيَقولُ أحَدُهُما: اللَّهُمَّ أعْطِ مُنْفِقًا خَلَفًا، ويقولُ الآخَرُ: اللَّهُمَّ أعْطِ مُمْسِكًا تَلَفًا﴾

“በሁሉም ቀናት ላይ ባሮች ባነጉ ቁጥር ሁለት መላአክቶች ወደ ምድር ይወርዳሉ። አንደኛው ይላል፦ ‘አላህ ሆይ! ለሰጪው ስጠው (ተካለት)’ ሌላኛው ደግሞ፦ ‘አላህ ሆይ! ሰሳችን (ቋጣሪን) ማጥፋትን ስጠው’ ይላል።”

📕ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 1442
2025/07/05 20:05:58
Back to Top
HTML Embed Code: