Telegram Web Link
ወላሂ ቀብር ውስጥ ሆነህ ታመሰግነኛለህ!
🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢

በትንሹ ለ100 ሺህ ዓመታት ቀብርህ ውስጥ ምን ትሰራለህ? ከደጋጎቹ አንዱ ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣሉ። "በርግጥ ለደጋጎች ካልሆነ በቀር ቀብር አስፈሪ ነው። ዱንያንና ውስጧን እጅግ የምጠላ ስሆን አሁን እድሜዬ 54 ነው። በትንሹ ቀብሬ ውስጥ ለ100 ሺ ዓመታት ምንድን ነው የምሰራው? ስል አሰብኩ።

እናም እንደሚከተለው መስራት ጀመርኩ ። እኔ እንደሆነ እሞታለሁ፣ የሚጠብቀኝም ሙሉ በሙሉ ጨለማና ባዶ የሆነ ቀብር ነው። እናም ይህ ቀብር ጌጣጌጥ ይሻል፣ የማደርጋትን እያንዳንዷን ኢስቲግፋርና አዝካር ብቸኝነቴን ያጫውተኝ ዘንድ ወደ ቀብሬ ቀድሞ እንዲጠብቀኝ እየላኩት ነው ብዬ ማሰብ ጀመርኩ። እውነቴን ነው አልቀለድኩም፣ የቀብሬን ለሕድ በሺዎች በሚቆጠሩ ተስቢሖች ማጌጡን ተያያዝኩት።

እዚህ ሳለሁ በትንሹ 300 ጊዜ ቁርአንን ቀርቼ አኸትመዋለሁ፣ እያንዳንዷን የሰላት ረከዐ ለቀብር ሒሳብ አካውንት ላይ ጥሪት አድርጌ አስባታለሁ፣ ሁሉም ጥሎኝ ወደ ቤቱ ይመለሳል፣ ምናልባት ብቻዬን ሚሊዮን ዓመታትን እዛ ነኝ። ቀብሬ የግድ ጨፌ፣ ብርሃናማ እና የምርም ጀነት መሆን ይኖርበታል።

እናም ከእያንዳንዷ መልካም ተግባር፣ ከዚክርና ቁርአኔ፣ ከሰደቃና ተሸሁዴ በነርሱ ተከብቤ አብረን ስንስቅና ስንጫወት በእዝነ ህሊናዬ አስባለሁ። በዚህ ጨዋታ መሃል በረሱሉ (ሰዐወ) የተደረገ ሶለዋት ጨዋታውን ሲካፈል አስባለሁ። ከሕይወት በኋላ ሌላ ሕይወት....

ምድር ላይ ሳለሁ ከሃሜትና ነገር ማዋሰድ፣ ለአላህ ተብሎ ካልተሰራ ስራዬ ውጤት ማለትም ከጭንቀት፣ ከቅጣትና ከጨለማና ቅጣት አይሻለኝም?!

ከዛሬ ጀምሮ ለናንተ ያለኝ ምክር ይላሉ ይህ ደግ ሰው

ቀብራችሁን ባንክ አድርጉትና ሁሌም ከመልካም ስራዎች ጣል እያደረጋችሁበት ሙሉት። በዒባዳዎች ላይ ጠንክሩ። ወላሂ ቀብር ውስጥ ሆነህ ታመሰግነኛለህ፣ ከዱንያ ይልቅ ለወዲያኛው ዓለም ተጠበብ።

አሁንማ ቤተሰብ መሃል ሆነህ ያሻህን ትለብሳለህ፣ ትመገባለህ እንዲሁም ደስ ብሎህ እንቅልፍህንም ትተኛለህ። ሁሉም ፍላጎቶቻችን ተሟልተው እንኳ ተጨባጫችንን እናማርራለን። ይህ ምቾት ማጣት እስቲ ከምድር ሆድ ውስጥ ቢሆን ብለህ አስበው?!

ስለዚህ እያንዳንዷን ተስቢሕ በትኩረት አድርግ፣ መልካም አጫዋችና አቀማማጬ ትሆኝልኝ ዘንድ ቀብር ቀድመሽ ጠብቂኝ በላት።"

[ሐሳቡ (አላህ ይዘንላቸውና)የዶክተር ሙስጠፋ ማሕሙድ ነው።]

©️ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን
📌 ለወንድምህ ዱዐ አድርግለት

“ወንድም ለወንድሙ በሌለበት የሚያደርገው ዱዓ አይመለስም። (ተቀባይነት አለው)።”

ረሱል (ﷺ)
“ከፆም፣ ከሰላት፣ ከሰደቃ በላጭና ደረጃው ከፍ ያለውን ተግባር አልነግራችሁምን? እንዴታ! ይንገሩን አሉ ሶሃቦች፦ ‘በሰዎች መካካል ማስታረቅ’ ነው አሉ።”

ረሱል (ﷺ)
“ሰዎች ቢያዩብህ የምትጠላውን ነገር ብቻህን ስትሆን አትስራው።”

ነቢዩ (ﷺ)
“አትቆጣ ጀነት ይኖርሃል።”

ረሱል (ﷺ)
Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል
Photo
‹‹አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ! የግፍ አገዛዝ አይበቃህም ወይ?››
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

📌 የዛሬ 50 አመት በ1966 ዓል ልክ በዚህ ሳምንት እንዲህ ሆነ!
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ክፍል አንድ

በእምነቱ ምክንያት መገፋቱ ሙስሊሙን አብግኖታል። የስውርና የግልጽ ሴራ ተጠቂነቱ ከንክኖታል። በገዛ አገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠሩ የእግር እሳት ሆኖበታል። ኢትዮጵያ ለሙስሊሙ ከክፉ ከእንጀራ እናት በላይ ከፋችበት። ‹‹አገር የጋራ ሃይማኖት የግል›› በሚል የሽንገላ ቃላት ሊያሞኙት እየሞከሩ በተግባር ግን የሃይማኖት ነጻነት መነፈጉ አብግኖታል። ከትምህርት አራቁት። ሙስሊም በመሆኑ ብቻ በአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ድርብ ጭቆና ቀመሰ። አንድነቱን በማሳጣት እርስ በርስ እየተጠራጠረ እንዲኖር መደረጉ ቆጭቶታል።

የዘመናት ብሶትና ቁጭት ለመብቱ ሊታገል ሙስሊሙን ግድ አሉት። ከትግል ሥልቶቹ አንዱ ሕዝባዊና ሰላማዊ ሰልፍ ነበር። ቁጣውንና ብሶቱን በማሰማት የመብት ጥያቄውን ሊገፋበት ወሰነ፤ ይህም በዕለተ ቅዳሜ ሚያዚያ 12 ቀን 1966 ዓ.ል በመዲናችን አዲስ አበባ በዓይነቱና በስፋቱ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር።

ትዕይንተ-ሕዝቡ በኢትዮጵያም ሆነ በሙስሊሙ ታሪክ ጉልህ ሥፍራ ነበረው። ግና ተዘነጋ። በሰላማዊ መንገድ ለሚታገሉት ፈር ቀዳጅ ሆኖ ሳለ ቸል ተባለ። በሰልፉ ሙስሊሙ ብሶቱንና ቁጭቱን ገልጾ መብቱን ለማስከበር ነቅሎ ወጣ። መብቱንም መንግሥት ያረጋግጥለት ዘንድ አስገደደ። ‹‹የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ነውና የግድ ልናውቀው ይገባል›› በሚል ታሪኩ ሰፋ ባለ መልኩ እንደሚከተለው ቀርቧል። የሰልፉ አቀነባባሪዎች እነማን ነበሩ? ለምን እና እንዴት ሊደረግ ቻለ? የወጣቱና የሙስሊሙ ተማሪ ሚና ምን ነበር? መነቃቃቱስ እንዴት ሊመጣ ቻለ? የሙስሊሙ ጥያቄዎችስ ምን ነበሩ?

የወጣቶች ክበብ እና የዒድ ፓርቲ
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

‹‹እስላሞች ተጨቁነዋል እየተባለ በኢትዮጵያ ብጥብጥ እንዲነሳ ብዙ ጊዜ በመገናኛ ብዙሃን ወቀሳ ይነገራል፡፡›› (ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ)

በአፄው ዘመን የመማር ዕድል ያገኙ ጥቂት ሙስሊም ተማሪዎች በአዲስ አበባ ከ 1950ዎቹ ጀምሮ ‹‹የዒድ ፓርቲ›› በሚል በዒድ ቀን ይገናኙ ነበር። በዚያው ዝግጅት ላይ ስለ ኢስላም የሚያስተምራቸው ግለሰብ እየፈለጉ፣ እየተማማሩና እየተዝናኑ ዒድን ያከብሩ ጀመር። በጥቂት ሙስሊሞች የተጀመረው ይህ ሂደት ቀስ በቀስ ስለሙስሊሙ ተጨባጭ ሁኔታ እና መብት ወደመወያየት ገባ። የእርስ በርስ ግንዛቤያቸውን ማዳበሪያ መድረክ ሆኖ ቀጠለ። ይህ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ (የዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) የተጀመረው የተማሪዎች የግንኙነት መድረክ ቀስ እያለ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ቀልብ ሳበ።

ዐብዱ መስዑድና ሙሐመድ ሐሰን ከመድኃኒዓለም ትምህርት ቤት፣ ሙሐመድ ዩሱፍ ከልዑል መኮንን ት/ቤት እና አበጋዝና ዐብዶ በሽር ከተግባረ-ዕድ ትምህርት ቤት በጋራ በመሆን በ1964 ዓ.ል ‹‹የሙስሊም ወጣቶች ክበብ››ን አቋቋሙ። ብዙም ሳይቆይ የክበቡን ዓላማ የተረዱ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ከተለያዩ ት/ቤቶች ወደ ክበቡ በአባልነት ተቀላቀሉ። ክበቡም ከዒድ ፓርቲ ልምድ በመቅሰም በሙስሊም በዓል ቀናት ሙስሊሙ ተማሪ የሚገናኝበትንና የሚማማርበትን መድረክ ማዘጋጀቱን ተያያዘው።

ከበዓል ቀናት ውጪም መገናኘትና መማማር እንዳለባቸው ተመካከሩ። ቋሚ የሚማሩበትንና ስለሙስሊሙ በደል፣ ስለመንግሥት ግልጽና ስውር ጸረ-ኢስላም ተግባራት፣ እንዲሁም የሙስሊሙ መብት የሚከበርበትን ቋሚ መንገድና አጠቃላይ መፍትሄ የሚገኝበትን ዘዴ ሊማከሩ ግድ ሆነ። ለመገናኘት የሚሆናቸው ስፍራ ሲታሰብ አንዋር መስጂድ ምቹ ሆኖ ታያቸው። የአንዋር መስጂድ አስተዳዳሪ የነበሩትን ሐጂ ዐብዱረሕማን ሸሪፍን ጠየቁ። እሳቸውም ወጣቶችን የሚያቀርቡ ነበሩና የመስጅዱን ቅጥር ግቢ ፈቀዱላቸው።

ተማሪዎች በዚያ መገናኘት ጀመሩ። ሥፍራዋም ለክበቡ አባላት የስብሰባና የቤተ-መጽሐፍት አገልግሎትን መስጠት ጀመረች። የስፖርት፣ የሥነ-ጽሑፍ፣ የሴቶች፣ የደዕዋና መሰል ንዑስ ኮሚቴዎችን አዋቀሩ። በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ቁጥር ያለው ሙስሊም ወጣት አንዋርን አጥለቀለቀ። በኢስላማዊውም ሆነ በዓለማዊው ትምህርት እውቀት ያላቸውን ግለሰቦች በየሳምንቱ መጋበዙን ተያያዙት።

ሸኽ ሐሚድ ዩሱፍ፣ ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ እና ሸኽ ሰይድ ሙሐመድ ሷዲቅ ዲናዊ ትምህርቶችን ለወጣቶች ያስተምሩ ጀመር። ሸኽ ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ ከዲናዊ ትምህርት ጎን ለጎን ስለመብታቸውና ስለሙስሊሙ ጭቆና ወጣቶቹን ማስገንዘቡን ተያያዙት። አባቢያ አባጆቢር ስለ ሕግ ሲያስተምሩ ጋዜጠኛ ሐጂ በሽር ዳዉድና ሙሐመድ ኢድሪስ የተለያዩ አርእስቶችን እየመረጡ ወጣቱን ያነቃቁ ጀመር። ሐጂ ዐብዱልከሪም ኑር ሑሴን እና ሐጂ ዑመር ሑሴንም የየራሳቸው ፕሮግራሞች ነበሯቸው።

በሂደት የወጣት ክበቡ ከአንዋር መስጂድ ወጣ እያለ መድረክ ለመፍጠር ሙከራ አደረገ። አባቶች ግን ሥጋት ነበራቸው። ምክንያቱም እነሱ ‹‹የሰላም ማኅበር›› በሚል ሥያሜ አቋቁመውት የነበረው ድርጅታቸው በኃይለ ሥላሴ ደህንነቶች በሐሰት ተወንጅሎ መዘጋቱ ይቆጫቸው ነበርና ነው። የወጣት ክበቡ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ‹የዒድ ፓርቲ› አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር በመተባበር አዳራሽ እየተከራየ ፕሮግራም በጋራ ማዘጋጀት ጀመሩ። መሰል የወጣት ክበቦች (ስብስቦች) በየአካባቢው ብቅ ብቅ አሉ። የወጣቱም ንቃተ-ሕሊና እየዳበረ ሄደ።

የሕግ ባለሞያና ጠበቃ የነበሩት አባቢያ አባ ጆቢር (የጅማው አባጂፋር የልጅ ልጅ ልጅ ናቸው) በየቲያትር ቤቱ በሚዘጋጀው መድረክ በግልጽ ስለ ሙስሊሙ መብት መቀስቀሱን ተያያዙት። በዚህ ጊዜም ከደህንነት አባላት ዛቻና ማስፈራሪያ ይደርስባቸው ነበር። የሙስሊሙ መብት መጣሱ እጅግ ይቆጫቸው ነበርና የደህንነትን ዛቻና ማስፈራሪያ ከቁብ አልቆጠሩትም። በደህንነት አባላት እንዳይታፈኑ በመሥጋት ወጣቱ እያጀባቸው ቤት ድረስ ይሸኛቸው ነበር። በ1964 ዓ.ል በሲኒማ ራስ በተዘጋጀው መድረክ ‹‹የእስልምና ማኅበራዊ ግዴታዎች ምንድናቸው?›› በሚል ርዕስ ንግግር አድርገዋል። ‹‹ኢስላም ሕግም፣ ንግድም፣ ፖለቲካም፣ ባህልም፣ ሥልጣንም፣ ማኅበራዊ ኑሮም፣ ሳይንስም፣ ሁሉንም ነው። አንዱን ነገር ብቻ ነጥለን የምንመራበት ሳይሆን ሁለንተናዊ ነው›› ሲሉ አስተምረዋል። ወጣቱ ስለ መብቱና እምነቱ፣ ስለ ሕልውናው እና አገሩ ይጨነቅ ዘንድ፣ እንዲሁም ለሙስሊሞች መብት መከበር መታገል እንዳለበት ጥሪ አድርገዋል። ሌሎችም በተለያዩ አርእስቶች ሥር የየራሳቸውን ትምህርት ሰጥተዋል።

በ1965 የዒድ ፓርቲና የወጣቶች ክበብ በጋራ በመሆን የአገር ፍቅር አዳራሽን ተከራይተው የትምህርት መድረክ አዘጋጁ። በመሰል መድረኮች ንቃተ-ሕሊናው የዳበረው ወጣት ስለሙስሊሙ መብት መጣስና አጠቃላይ ጭቆና ይማከር ያዘ። ዑለሞችንም ያማክር ቀጠለ።በመስጂድ መገናኘትና መወያየትን አዘወተረ። የመድኃኒዓለም፣ ተግባረ ዕድ፣ ኮሜርስ ት/ቤት እና የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በይበልጥ ብርቱና ንቁ ተሳታፊ ነበሩ።

ይቀጥላል……..
“አምስቱ ሰላቶች፣ ከጁምዓ እስከ ጁምዓ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው ያሉትን ኃጢአቶች ያብሳሉ ታላላቅ ወንጀሎችን ሲቀር፡፡”


ረሱል (ﷺ)
ታላቁ አሊም ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን በጠና መታመማቸው ተገለፀ!
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን ፣በመዲና ዩንቨርስቲ በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁና በወሎ ከሚሴ እንዲሁም በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በዳአዋ በርካቶችን በማስተማር እና በሀገር ሽማግሌነት ትልቅ ተሰሚነት ያላቸው ታላቅ አሊም ናቸው።
...
ሼህ አብድልለጢፍ ሸረፈዲን በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ጦርነት ወቅት ህዝቡን በማሰተባበር ለተቸገሩ ወገኖች መሰረታዊ ቁሳቁሶችን በማቅረብ ህዝቡን በጦርነት ውስጥ ሲታደጉ የቆዩ ቢሆንም ለሁለት አመታት በአዋሽ አርባ እና በከሚሴ እስር ቤት ታስረው እንደነበር ይታወሳል።
...
እስር ቤት ውስጥ በነበሩ ሰአት ህመሙ የጀመራቸው ሲሆን ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሀገረ በቱርክዬ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን፣አሁን ላይ የህክምና ወጪው ከቤተሰብ አቅም በላይ በመሆኑ በአሊሞች እና የሀገር ሽማግሌዎች የተዊቀረ ኮሚቴ በተከፈተ አካውንት ድጋፍ እንድታደረግላቸው ጥሪ ቀርቧል።
...
ድጋፍ ለማድረግ፦
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የአካውንት :-1000392652788
የአካውንት ስም፦የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮምዩኒቲ ሰፖርት
አካውንቱን የሚከታተሉ ኮሚቴዎች
ሸኽ ጡሃ ሸኽ መሀመድ
ሸኽ ሁሴን ሀሰን ሱሩር
ሸኽ አህመድ አሊ ሃሰን
...
“ሌሊት መስገድን አስቦ ወደ ፍራሹ የሄደ ከዚያም እስከ ንጋት ዓይኑ ያሸነፈችው ያሰበውን አላህ ይፅፍለታል፤ እንቅልፉም ከጌታው ዘንድ ሶደቃ ይሆንለታል”

ረሱል ﷺ

(ነሳኢ 1787ና ኢብኑ ማጀህ 1344)
2025/07/07 22:01:59
Back to Top
HTML Embed Code: