🛑 ተራዊህ በመስገድ ከሚገኙ ጥቅሞች
📌 ቀኑን በጾም ሌሊቱን በሰላት በማሳለፋችን ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች እንመደባለን
📌 ቁርኣን በብዛት በማድመጣችን የአላህን እዝነት እናገኛለን
📌ተራዊሕ ብዙ ሩኩዕና ሱጁድ ስላለበት ሰፊ የዱዓና የዚክር እድል እናገኛለን
📌ከወንጀል ርቀን ጊዜያችንን በመልካም ስራ እናሳልፋለን
📌ዒባዳ ላይ ትዕግስትን እንማራለን
📌ሰላተል-ለይል እንለማመዳለን
📌በተደጋጋሚ ከኢማሙና ማእሙሞች ጋር "አሚን" በማለታችን ወንጀላችን ይማራል
📌 መስጂድ ስንሄድና ስንመለስ በእርምጃችን ልክ ወንጀሎች ተራግፈው መልካም ስራዎች ይጻፉልናል
📌 ሰላት እየጠበቀን በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች መላኢካዎች ምህረት ይጠይቁልናል
📌 የሙስሊሞችን ጀማዓ በማብዛት ሸይጣንና አጋዦችን እናስቆጫለን
📌 ከመልካም ሰዎች ጋር በመቀላቀላችን መልካም ስራዎቻችን ወደ ሰማይ እንዲወጡና ተቀባይነት እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል
📌 ከአልባሌ ነገሮች ለመራቅ ለወጣቱ መልካም አርዓያ እንሆናለን
📌 ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉም ነገር ቀላልና የሚቻል መሆኑን በተጨባጭ እናይበታለን
📌 ቁርኣንን በብዛት በመስማት የአላህን እዝነት እናገኛለን እንዲሁም ብዙ በመስማት ትክክለኛውን የቁርኣን አቀራርም እንማራለን
📌 በቁኑት ዱዓ ወቅት ብዙ እኛ ያላሰብናቸውና መግለጽ የማንችላቸው ነገሮች ዱዓ ተደርጎ "አሚን" በማለታችን ትርፋማ እንሆናለን
📌 ከኢማሙ ጋር እስከሰላቱ ፍጻሜ ድረስ አብረን እየሰገድን ከቆየን ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ ያደረን ሰው እጅር /ምንዳ እንሸምታለን
📌 የቂያማ ቀን መቆምን ያቀልልናል፥ዱኒያ ላይ ለጌታው ብሎ ረጅም ሰዓት የቆመ የቂያማ ቀን መቆም አይከብደውም
📌 ሰግደን ስንመለስ የውስጥ ደስታና እፎይታና ሌሎችንም የዲንም የዱኒያ በርካታ ጥቅሞችን እናገኛልንና ተራዊህን ሳንሰለች እንስገድ።
አላህ ያግራልን

Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል
Video
የዛሬ 13 ዓመት ነበር ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሲበሰር የባምዛ አካባቢ ነዋሪዎች ቄያቸውን ለልማት ቀዳሚ ሆነው ሀገር ትልማ ፣ ትደግ ሁላችንም በጋራ ከፍ እንበል በማለት ያለምንም ካሳ ለመነሳት ፈቀዱ።
ያ ሲሆን በመንግስት በኩል አስፈላጊውን መሠረታዊ ልማት ለማሟላት ቃል ተገባ ፣ መንገድ ፣ ሆስፒታል ፣ ጤና ጣቢያ ፣ ት/ቤት ፣ ውሃ እና ቤተ እምነቶችን ለመገንባት መንግስት ለህዝቡ ቃል ገባ ቃሉን ተከትሎ
- ቤተ ክርስቲያን ተሰራ
- ትምህርት ቤት ተሰራ
- ሆስፒታል ተሰራ
- መንገድ ተጀመረ
- ውሃው ጅምር ላይ ሆነ
መስጅዱ ግን የለም ፣ አልተሰራም ለዚህም እንጠይቃለን መስጂዱ የታለ ? አው በተገባው ቃል መሠረት በቂ ያልሆነ አሸዋና ጠጠር አውርደው ደብዛቸው ጠፍቷል።
ለዓመታት ልጆቹን እያከፈሩበትና ፣ የስነ ልቦና ተጠቂ ሆኖ ዲኑን ለመጠበቅ ድንበር ተሻግሮ ሱዳን በመግባት ልጆችን በማስተማር እምነቱን ጠብቆ ለማቆየት እየተጋ ይገኛል ።
የአካባቢው ማህበረሰብ ይህ ግን እስከ መቼ ብለው ይጠየቃሉ የአካባቢው አመራሮች ? መስጅዱን ሆን
ተብሎ በሚያስብል ደረጃ የአካባቢው ማህበረሰብ በልማት ተነሺው ሙስሊሙ ሆኖ ሳለ እስከ አሁን ድረስ ለዓመታት መስጅዱ አልተሰራለትም፣ ይህን ተከትሎ አካባቢው የአክፍሮት ሀይላት መናኸሪያ ሆኗል። ይህን መቀየርና መለወጥ አንድና አንድ ነው ተቋም መገንባት በመሆኑ ለዚህም ባምዛ አራህማን መስጅድን ማዕከልን እውን ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ በመደረግ ላይ ይገኛል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የፊታችን ጁምዓ የረመዳን የመጀመሪያ ጁምዓ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ መስጅዶችና አለም አቀፍ ማህበረሰብ በሶሻል ሚዲያዎች በሚደረገው የሰደቀቱል ጃሪያ ባምዛ አራህማን መስጅድን እውን ለማድረግ በሚደረገው
ዘመቻ ላይ ተሳታፊ በመሆን ኢስላማዊ ግዴታውን እንዲወጣ የቤንሻጉል ጉምዝ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት እና የባምዛ አራህማን መስጅድ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ይጠይቃሉ።
“የአላህን ቤት (መስጅድ) የገነባ ፣ አላህ በጀነት ለሱ ቤት ይገነባለታል።“ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
የአካውንት ስም:- ባምዛ አራህማን መሰጅድ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 1000661869953
ሂጅራ ባንክ:- 1000039130001
አዋሽ ባንክ:- 01425156535600
ኦሮሚያ ሕብረት ስራ:- 1013800153709
ዘምዘም ባንክ:- 0051190110301
አቢሲንያ ባንክ:- 219545827
ዳሽን ባንክ:- 2966782305111

ለባለሃብቱ!
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
ለገቢዎች ባለስልጣን መስሪያ ቤት የምትከፍለውን ግብር እያሰብክ ከዘካ እንዳትዘናጋ። ዘካ ለደካሞች የሚሰጥ ሐቅ እንጂ ለሹማምንት የሚሰጥ ግብር ወይም ጉቦ አይደለም። አኺል ከሪም! ገንዘቡን የሰጠህ አላህ ነው። እንጂ ካንተ የበለጠ የሚለፉ ድሃዎች በዙሪያህ አሉኮ። በእውቀቴ አገኘሁት እንዳትል ካንተ የበለጠ የተማሩ ድሃዎች ሞልተዋልኮ። ጥለኸው ለምትሄደው ገንዘብ ብለህ በራስህ ላይ አትሳሳ። እውነተኛው ያንተ ገንዘብ ማለት ለአኺራህ ያሻገርከው ነው። ዐብዱላህ ብኑ ሺኺር - ረዲየሏሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላሉ፦
"ነብያችን ﷺ ዘንድ መጣሁኝ። {በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ} የሚለውን እየቀሩ ነው። ቀጥለው እንዲህ አሉ፦
'የአደም ልጅ 'ገንዘቤ ገንዘቤ!' ይላል። የአደም ልጅ ሆይ! በልተህ ከጨረስከው፣ ለብሰህ ካሳለቅከው፣ ሶደቃ ሰጥተህ አጅሩን ካሻገርከው ውጭ ገንዘብ አለህ'ንዴ?' " [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2958]
እወቅ! የምታወጣው ካጠቃላይ ገንዘብህ 2.5 ከመቶ ብቻ ነው። መቶ ብር ያለው ሰው ሁለት ብር ከሃምሳ ሳንቲም ቢያወጣ ብዙ ነው ወይ? ምስሉ ላይ በጣት የተጠቆመችዋን ተመልከት። ካጠቃላይ ሃብትህ ይቺን ታክል ለዘመዶችህ፣ ለጎረቤቶችህ፣ ለምታውቃቸው ምስኪኖች ብታወጣ ብዙ ነውን? በአኺራ እጥፍ ድርብ ምንዳ እንደሚጠብቅህ የቂን የለህም ወይ?
ደግሞም እወቅ! ወላሂ ሶደቃ ሃብትን አይቀንስም። ይልቁንም ይበልጥ በረካ እንዲኖረው ነው የሚያደርግልህ። አላህ ትእዛዙን ለመፈፀም ያግራልህ።
©️Ibnu Munewor

““Halkan jum'aatiifi guyyaa jum'aa anarratti salawaata buusuu baay'isaa.”
Ergamaa Rabbii ﷺ
Ergamaa Rabbii ﷺ
ዛሬ ጁምዐ በመላው አዲስ አበባ በሚገኙ መስጅዶች ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ባምዛ መስጂድ ግንባታ ገንዘብ ስለሚሰበሰብ ሁላችንም አሻራችንን እናኑር።
የባንክ አካውንቶች ለምትፈልጉ 👇
የአካውንት ስም:- ባምዛ አራህማን መሰጅድ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 1000661869953
ሂጅራ ባንክ:- 1000039130001
አዋሽ ባንክ:- 01425156535600
ኦሮሚያ ሕብረት ስራ:- 1013800153709
ዘምዘም ባንክ:- 0051190110301
አቢሲንያ ባንክ:- 219545827
ዳሽን ባንክ:- 2966782305111
የባንክ አካውንቶች ለምትፈልጉ 👇
የአካውንት ስም:- ባምዛ አራህማን መሰጅድ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 1000661869953
ሂጅራ ባንክ:- 1000039130001
አዋሽ ባንክ:- 01425156535600
ኦሮሚያ ሕብረት ስራ:- 1013800153709
ዘምዘም ባንክ:- 0051190110301
አቢሲንያ ባንክ:- 219545827
ዳሽን ባንክ:- 2966782305111
“በትንሳዔ ዕለት የስራ መዝገቡ አስደስቶት መመልከትን የወደደ እስቲግፋር ማድረግ ያብዛ።”
ረሱል (ﷺ)
ረሱል (ﷺ)
Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል
Photo
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በጥላቻ ንግግር ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ኢትዮጵያ ብዝሃ ሀይማኖት የሆነች ሀገር እንደ መሆኗ የተለያየ እምነት ተከታዬች ለዘመናት ተፈቃቅደውና ተከባብረው ኖረውባታል። እየኖሩባትም ይገኛሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተለይም የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ይህንን በጎ እሴት በመሸርሸር ውዝግብና ግጭት ለመፍጠር የሚሰሩ አካላት እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡
በተለይም የእስልምናን መልካም እሴቶች እና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር በመዳፈር ህዝበ ሙስሊሙን የሚያስቆጡ የጥላቻ ንግግሮች በስፋት እየተሰራጩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተረድቷል።
ጠቅላይ ም/ቤቱ እነዚህ አካላት ከዛሬ ነገ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ከጥፋታቸው ይታረማሉ በሚል ቀና እሳቤ ጉዳዩን በትዕግስት ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ጠቅላይ ም/ቤቱ ችግሩን ከዚህ በላይ በትዕግስት መመልከት ውጤቱ የከፋ በመሆኑ የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር የሚነኩ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ከየትኛው አይነት ተግባር ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል፡፡ የጥላቻ ንግግር በየትኛውም ወገን ቢሰነዘር ጠቅላይ ም/ቤቱ በጽኑ እንደሚያወግዝና ተጠያቂነት እንዲሰፍን እንደሚሰራም ማወቅ ይገባል፡፡
በመሆኑም በተደጋጋሚ ተከስቶ በቸልታ እየታለፈ ያለው የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብርየሚነካ የጥላቻ ንግግር ያደረጉ ግለሰቦች አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የፍትህ፣ የፀጥታና የደህንነት አካላት የህግ ተጠያቂነትን ለማምጣትና መሰል ጥፋቶች እንዳይደገሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ ም/ቤቱ ያሳስባል።
በመሆኑም፡-
1. የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጉዳዩ ከዚህ በላይ ከመክረሩ በፊት የጋራ አቋም በመያዝ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲወስን።
2. ይህ በአደባባይ የተላለፈ የጥላቻ ንግግርና ሀይማኖታዊ ትንኮሳ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈጠረውን ህመም በአግባቡ በመረዳት የሚመለከታቸው የፀጥታና የህግ አካላት ተጨማሪ ጥፋት ከመከተሉ በፊት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ፤
3. የሰሞኑ የጥላቻ ንግግር ምንጩ የተራ ግለሰብ ቢመስልም ከጀርባ የአጀንዳና የሃሳብ ተጋሪዎች ያሉት በመሆኑ ህዝባዊ ቁጣ ከመቀስቀሱ በፊት የሀገርና የህዝብ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ከጠቅላይ ም/ቤቱ ጋር በመቆም ትንኮሳውን እንዲያወግዙ፤ እንዲሁም
4. ወቅቱ በሙስሊሞች እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች የፆም ወቅት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት ከሀይማኖትና ከኢትዮጵያዊነት እሴት ያፈነገጡ የጥላቻ ንግግሮች የሚገሰፁበትና የሚታረሙበት የፅሞና ወቅት እንዲሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ጠቅላይ ም/ቤቱ የእስልምና አንኳር እሴቶችን በተለይም የፈጣሪያችንን አሏህ፣ የነቢያትን፣ የመለኮታዊ መፃህፍትንና የደጋግ ተከታዮችን ክብር የሚያጎድፉ ማንኛውም አይነት የጥላቻ ትንኮሳና ድርጊት በህግ አግባብ እንዲታረሙ ተቋማዊ ኃላፊነቱን የሚወጣም ይሆናል፡፡
ለእውነተኛ ሰላምና አብሮነት የሚቆረቆሩ አካላት ሁሉ ድርጊቱን እንዲያወግዙና ለፍትህ እንዲሰሩም ጠቅላይ ም/ቤቱ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

“አንዳችሁ አላመነም ‘እምነቱ ሙሉ አይሆንም’ እኔ እሱ ዘንድ ከልጆቹ ከወላጆቹ ከሰዎች በጠቅላላ ይበልጥ ተወዳጅ እስክሆን ድረስ።”
ረሱል (ﷺ)
ረሱል (ﷺ)
በወቅታዊው በማኅበራዊ ሚዲያ እየተካሄደ ያለውን ሃይማኖትን ሽፋን ስላደረገው ክብረ-ነክ፣ የትንኮሳ፣ የጥላቻና ጸብ ቀስቃሽ ዘመቻዎችን አስመልክቶ
በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተሠጠ መግለጫ
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
“የሃይማኖት ንጽጽር - በከፍተኛ የሃይማኖት ሊቃውንቶች መካከል በሕግ፣ በሥርዓት እና በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚመራ በዶግማዊ ጉዳዮች ላይ የሚደረግ የሰከነ ውይይት ነው፤ በአማኞች መካከል የሚደረግ ሥርዓት የለሽ እና አንዱ ሌላውን የሚያውገዝ፣ የሚያጠልሸ እና ክብረ-ነክ መሆን ወንጅል ነው፤” ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የማኅበራዊ ሚዲያውን እድገትና ተደራሽነት መስፋትን ተከትሎ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ አጀንዳዎች ላይ በአወንታዊነት እና በአሉታዊነት የሚፈረጅ ይዘት ያላቸው ሥራዎች ተሠርተው አየር ላይ ሲውሉ እናያለን፤
አንዳንዶች ደግሞ የራሳቸውን የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ በመክፈት የተለያዩ ግለሰቦችን ወደመድረካቸው በመጋበዝ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በደጋፊነት እና በነቃፊነት ላይ ተሰልፈው የጦፈ ክርክር ሲደርጉም እንመለከታለን፡፡
ዘርፉና የመገናኛ መድረኩ የራሱ የሆነ የአጠቃቀም መመሪያ ያለውና በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ የሚጠበቅ ቢሆንም አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች መድረኩን ከዓላማው ውጪ ለሆነና ለግልና ቡድናዊ ፍላጎታቸው መጠቀሚያ በማድረግ በተለያዩ ሃይማኖት/እምነት ተከታዮች መካከል መተማመኑ እና መከባበሩን የሚሸረሽሩ ይዘቶችን፣ ክብረ ነካዊ በሆነ አቀራረብ ግልፅ ጥላቻን የመስበኩ ልምምድ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ ይገኛል፡፡
ይህ ዓይነቱ አቀራረብና ልምምድ አልፎ አልፎ በአንዳንድ የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ በመደበኛ የአምልኮ መርሀ ግብር ላይ በፊት ለፊት መድረኮች ሲቀርብ አይተናል፡፡ ልምምዱና አቀራረቡ ከወዲሁ ሊታረምና በሕግና ሥርዓት ሊከናውን እንደሚገበው ጉባኤያችን በጽኑ ያምናል፡፡ ከዚህ አንፃር ከሰሞኑ የሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች የተቀደሰ የጾም፣ የጸሎትና በከፍተኛ ደረጃ የመንፈሳዊ እነፃ ላይ በሚገኙበት ጊዜ ከመንፈሳዊነትና ከሃይማኖቶች መሠረታዊ ዕሴት ጋር የሚቃረን ተግባር በማኅበራዊ ሚዲው በስፋት እየተሠራጨ ይገኛል፡፡
በተለይም አንዳንድ የኦርቶዶክስ ክርስትና አማኝ ነን የሚሉ ግለሰቦች፣ የእስልምና ሃይማኖት ነቢይ በሆኑት በነቢዩ መሐመድ (የአላህ እዝነትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና) ላይ ድፍረት የተሞላበት ክብረ ነክና ጽያፍ ንግግር ሲያደርጉ ታየረተዋል፡፡ ይህም ሙስሊሙን ወገን ብቻ ሳይሆን ሰላም ወዳዱን ወገን ሁሉ አሳዝኗል፡፡
ጉባኤችንም ይህ ዓይነቱ ኢ-ሥነምግባራዊ እና ሕገ ወጥ ተግባር የትኛውንም የሃይማኖት ተቋም የማይወክል፣ ይልቁንም የሚወገዝ ተግባር መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኝ ነን የሚሉ ወንድሞችና እህቶች የግለሰቡን ሕገ-ወጥ ተግባር ተቋማዊ ለማድረግ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያጤኑና ግለሰብንና ተቋምን እንዲለዩ እንመክራለን፡፡
በአንፃሩ አንዳንድ ሙስሊም ነን የሚሉ ግለሰቦች ተደፈርን በሚል ስሜት የክርስትና አስተምህሮንና የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር የሚነቅፍና የሚያጠለሽ፣ መላውን ክርስቲያን በሚያዋርድ መልኩ ምላሽ ሲሠጡ እና ድርጊቱን በፈፀመው ግለሰብ ላይ የደቦ ፍርድ ሲያስተላልፉ ይታያሉ፡፡
ይህም ሕገ-ወጥነትን ከማስፋፋት ባለፈ ጥፋትን በሌላ ጥፋት ማረም ፈጽሞ የማይቻል መሆኑን ተገንዝበው ከድርጊታቸው በመታረም የሕግ የበላይነትን እንዲስቀድሙ ጉባኤያችን በአጽንኦት ይመክራል፡፡ በየትኛውም አካል የተፈፀሙትና የሚፈፀሙት ይህን መሠል ሕገ-ወጥ ተግባራት በሁሉም ሃይማኖቶች አስተምህሮ ተቀባይነት
የሌላቸው ብቻ ሳይሆን የሚወገዙ ተግባራት መሆናቸውን ጉባኤያችን እያስገነዘበ ድርጊቱ በወንጀል የሚስጠይቅ ስለመሆኑም ለማስታወስ ይወዳል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሀ ሀይማኖት መገኛና መኖሪያ ከመሆኗ አንፃር የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የትኛውንም ዓይነት የሃይማኖት ተቋማትን፣ አስተምህሯቸውንና መገለጫዎቻቸውን የሚያንቋሽሹና የሚያዋርዱ ንግግሮችንም ሆነ ተግባራትን በጽኑ ያወግዛል። እንዲህ ያሉት ክብረ-ነክ የሆኑ ተግባራትና አስተያየቶች ሁሉ ድርጊቱ ለተፈፀመባቸው እምነት ተከታዮችን በእጅጉ የሚያስቆጡ ብቻ ሳይሆኑ መላ ኢትዮጵያዊያንን በእጅጉ የሚያስቆጡ ናቸው፡፡ የመከባበርና የአብሮነት እሴቱን በመሸርሸር በሀገራችን የሰላምና የሰላማዊ ማህበረሰብ ግንባታ ሂደቱንና ጥረቱን እንዳይያሳካ ያደርጋሉ፡፡
ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አንዱ የሌላውን እምነት ለመስደብ ወይም ለማዋረድ በፍፁም ጥቅም ላይ መዋል የለበትም። የእምነት ነፃነት እና የማምለክ መብት ለሁሉም ማህበረሰቦች የተጠበቀ ሲሆን ይህ መብት የሌሎች አማኞችን መብት በመጋፋና ስሜት በመንካት ለጠብ ማነሳሽነት ሲውል በዝምታ ሊታለፍ አይገባውም፡፡
ይህንን ከባድ ጥፋት በዘላቂነት እንዲታረም የሚመለከታቸው አካላት አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሰረት ይህንንና ተመሳሳይ ተግባር በፈፀሙና በሚፈጽሙ አካላት ላይ አፋጣኝ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን። ለእንደዚህ አይነት ወንጀሎች ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ለወደፊቱ የሃይማኖትን ስም ማጥፋት ለመከላከልና የሁሉም እምነት ተከታዮች ክብርን ለመጠበቅና
ለማስጠበቅ በእጅጉ ይረዳል።
በተጨማሪም የሃይማኖት መሪዎች፣ የሃይማኖት ምሁራን እና መላ ሕብረተሰቡ በሃይማኖቶች መካከል መከባበር፣ መግባባትና መረዳዳት ይበልጥ ሊያጠናክሩ በሚያስችሉ የጋራና የተመረጡ አጀንዳዎች ላይ በሕግ፣ በሥርዓትና በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚመሩና ግልጽ ዓላማና ግብ የተቀመጠላቸው ውይይቶችና ምክክሮች በተጠናከረ መልኩ በማከናውን በሃይማኖቶች መካከል ትብብራቸውንና አጋርነታቸውን እንደ ሚያጠናክሩ ይጠበቃል፡፡
በቅርቡ ጉባኤያችን ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በመዳሰስና በመተንተን ሀገራዊ ዓውዱንና ተግዳሮቶች ታሳቢ በማድረግ፣ እንዲሁም ተቋሙ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል የመተዳደሪያ ደንቡን አሻሽሏል፡፡ የተሻሻለው ደንብም በተቋማት መካከል አለመከባበርን፣ አለመቻቻልን የሚሰብኩ፣ ጥላቻን የሚቀሰቅሱና ግጭትን የሚያባብሱ ተንኳሽና ክብረ-ነክ ንግግሮችንና ተግባራትን የሚፈፅሙ ግለሰቦችና ቡድኖች በራሳቸው ተቋም ተጠያቂ የሚያደርግ ሥርዓት እንዲኖር የሚያደርግ ድንጋጌ በደንቡ ላይ እንዲካተት ተደርጓል፡፡
የችግሩ ስፋትና ጥልቀት እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞም ችግሮን በዘላቂነት ለመፍታትም ከአባል የሃይማኖት ተቋማት የሚወከሉ የሕግና አግባብነት ያላቸው ባለሙያዎች የሚካተቱበት የተከላካይ ግብር-ኃይል አደረጃጀት በጊዜያዊነትና በቋሚነት በማደራጀት የቅደመ መከላከል ሥራዎች ለመስራት ተዘጋጅቷል፡፡
ግብር-ኃይሉም ችግሮችንና የችግር አዝማሚያዎችን በማሰባሰብ፣ በመተንተንና የመፍትሔ ሀሳቦችን በመስጠት ሙያዊ እገዛ በማድረግ ሕግና ሕጋዊነትን የማስጠበቅ ሥራ በመስራት የሀገር ሰላምንና የሃይማኖት ተቋማትን ክብርና ልዕልና የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ይወጣል፡፡
የሁለቱም እምነት ተከታዮች እና አማኞች በማኅበራዊ ሚዲያው ባለው አሉታዊ ዘመቻና በተፈጠረው ወቅታዊ ችግር ሳይረበሹ የጾም፣ ጸሎትና የንስሀና ተግባሮቻቸው ላይ እንዲያተኩሩ ጉባኤያችን ይመክራል፡፡
የሕግ አስከባሪ አካሉም፣ በአማኞች መካከል ያለው ሰላምና መከባበር የሚያውኩ፣ ሕገ-ወጥ ግለሰቦችና ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲታረሙ በማድረግ ሕግና ሥርዓት የማስጠበቅ የተለመደ ሕጋዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጉባኤያችን ጥሪውን ያቀርባል፡:

በመጨረሻም ሁላችንም የሃይማኖት ተቋሞቻችንንና የአስተምህሯችንን ክብር፣ ልዕልናና ቅድስና እንጠበቅ በማለት ጉባኤያችን የአደራ መልዕክቱንና ጥሪውን ያቀርባል፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ - ለሰላም፣ ለመተባበር እና ለአብሮነት
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ
መጋቢት 2 ቀን 2017
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

“ummata kiyyarraa anaaf jaalala cimaa kan qaban ka ana boodaan dhufantu jira. Tokkoon isaanii maatii isaatii fi qabeenya isaa naaf wareegama godhee na arguu jaalata.”
Ergamaa Rabbii (ﷺ)
Ergamaa Rabbii (ﷺ)
የውዱ ነብያችንን (ﷺ) ክብር የተዳፈረው ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ጠቅላይ ምክር ቤቱ በትኩረት እየሰራ ነው።
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ውዱ ነብያችን (ﷺ) ሲነኩ ከልባችን የምንታመም ቢሆንም ችግሩን የምነፈታው ግን በህጋዊ አግባብ ነው ብለዋል።
ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ አክለውም ግለሰቡ ለጊዜው ተደብቆ ቢሰወርም ተይዞ ለህግ እንዲቀርብ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተቀናጀ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ግለሰብንና ተቋምን ለይቶ የሚረዳ በመሆኑ የተፈፀመው ትንኮሳ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር ያለን መልካም ግንኙነት አይሻክረውም ነው ያሉት።
የሀይማኖት ተቋማት ግለሰቡ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በቅርበት ሊሰሩ ይገባል ያሉት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም የመንግስት የፀጥታና የደህነት አካላት ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
ተመሳሳይ ድርጊቶች ከተፈፀሙ ፈፅሞ አንታገስም ያሉት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ህዝበ ሙስሊሙ ግለሰቡ በህግ እንዲጠየቅ አስፈላጊው ስራ እየተሰራ መሆኑም በመገንዘብ ውጤቱን በትዕግስት እንዲጠብቅም አደራ ብለዋል።

“በኔ ላይ አንድን ሰለዋት ያወረደ አላህ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል። አስር ሀጢያቱን ይሰርዝለታል። ደረጃውን በአስር ከፍ ያደርግለታል።”
ረሱል (ﷺ)
ረሱል (ﷺ)
አቻነት ፍለጋ የ16 ዓመት ጉዞ
❇❇❇❇❇❇❇❇❇
በአሕመዲን ጀበል
🕜🕝🕝🕝🕝
ይህችን አምስት ገጽ አንብቦ መጨረስ ካቃተህማ ጉድ ነው!
መልክቱ ለሁሉም እንዲደርስ በሁሉም መንገድ ያሰራጩ።
❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌
ሰሞኑን አጀንዳ የሆነው ሙስሊሞችን በማስቆጣት ቀድሞ የታቀደ በሚመስል መልኩ የሆነ ዓላማን ለማሳካት የአላህን መልዕክተኛ (ሰዐወ) በማህበራዊ ሚዲያ የማንቋሸሽ፥ የማነወር እና የማዋረድ ተግባር ሁሉንም ሙስሊሞችን አስቆጥቷል። የድርጊቱ ፈጻሚ ግለሰብም በአስቸኳይ ለሕግ ቀርቦ ተገቢውን ቅጥት ማግኘት ይገባዋል።
በፕሮፓጋንዳ፥ በፖለቲካና በስነ-ልቦና ጦርነት ስልቶች ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በመቆጣጠር የራስን ወገን ወንጀል ለመደበቅ፥ ሌላውን ተከሳሽ አድርጎ ለማቅረብ፥ ተጠቂ በደሉን እንዳያቀርብ ለማፈን፥ አልያም የምላሹን መጠንና የሙቀት ደረጃን ለመለካት ሲባል ሁለት የማይገናኙ ወይም የማይዛመዱ ነገሮችን አሳሳች በሆነ መልኩ ትይዩ አድርጎ አመሳስሎ ለማቅረብ የተለየያዩ ስልቶችና ጥረቶች ይተገበራሉ።
በሰሞኑ የአላህ መልዕክተኛ (ሰዐወ) ክብረ ነክ ስድብ፥ የጥላቻ ንግግርና ማንቋሸሽ ጉዳይ ላይ አንዳንድ ግለሰቦች፥ አክቲቪስቶችና ሚዲያዎች ጉዳዩ ላይ የተከተሏቸውን ስልቶች፥ ጉዳዩን የዳሰሱበትን መንገድና ተያያዥ ነገሮችን ከፕሮፓጋንዳ፥ ከስነልቦና ጦርነትና ከፖለቲካ ስትራቴጂ አንጻር ያስተዋለ ሰው የተገበሯቸውን በርካታ ስልቶች በቀላሉ ይረዳል። በማስከተል የሚከተሉትን ጥቂት ቁልፍ ስልቶቻቸውን እንመልከት።
1/ የሐሰት አቻነት መፍጠር (False Equivalence)
🚼🚼🚼🚼🚼🚼🚼🚼🚼🚼🚼🚼🚼🚼🚼
ይህ ስልት ታዋቂ ግለሰቦች፥ አክቲቪስቶችና ሚዲያዎች በሰሞኑ እንደታየው የነቢዩ ሙሐመድን (ሰዐወ) ክብር ነክ በሆነ ሁኔታ መሰደብን ከሃይማኖት ንጽጽር ጋር አቻ አድርጎ በማቅረብ ሁኔታ የታየ ነው። በዚህ ሂደት “ነቢዩ ሙሐመድን መስደብ የሃይማኖት ንጽጽር ነው” የሚል አቻነት የመፍጠር ጥረት ተደርጓል። ይህን ያደረጉበት ዓላማም በሃይማኖት ንጽጽር እና በጥላቻ ንግግር፥ በስድብና በሹፈት መካካል ያለው ልዩነት እንዲደበዝዝ በማድረግ የግለሰቡ ተግባር በኖርማልነት እንዲታይ ለማድረግ ነው።
በተጨማሪም አንዳንድ ወገኖች ደግሞ ከዚሁ የሐሰት አቻነት ፈጠራ ጋር በተያያዘ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንደታየው ከጥላቻ ንግግር ባለቤትና ተሳዳቢው ግለሰብ ጋር አብረው እንደሆኑ በመግለጽና ቤተ እምነታቸው እንደ መጅሊስ መግለጫ እንዲያወጣ ጥሪ ያደረጉ ሲሆን ከፊሎቹ ደግሞ “የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እኛንም እነሱንም በእኩል ዓይን ማየት ሲገባውና ዋና ጸሐፊው ቀሲስ ታጋይ የእኛን ሃይማኖት እየተከተለ ስለምን በእኛ ላይ መግለጫ ያወጣል?” በማለት የግለሰቡን እምነት ጥያቄ ዉስጥ ለመክተት ሲታትሩ አይተናል።
2/ ታሪክን ዋቢ በማድረግ ትክክለኛነትን ማሳየት (Historical Justification)
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅
ይህ ስልት ከዚህ ከአሁኑ የነቢዩ (ሰዐወ) ክብረ ነክ ስድብ ጋር የማይገናኙ የተለያዩ ታሪካዊ ማስረጃዎችን በመለቃቀም ታሪክን አጣቅሶ የአሁን ነውረኛ ድርጊትን ትክክለኛነት ለማሳየት መሞከር ነው። “ክርስቶስ ማነው?” መጽሐፍና ሌሎችም ከዚህ የተነሳ ነው ለዋቢነት ተፈላልገው ዳግም መቅረብ የያዙት። ነቢዩ ሙሐመድን (ሰዐወ) መስደብ፥ ማንቋሸሽና ማነወርን ዓላማ ያደረገውን የጥላቻ ንግግር ሁሉም ሃይማኖቶች ከሚተገብሩት የሃይማኖት ንጽጽር (comparative religion) መካከል የሙስሊሞችን ብቻ ነጥሎ ከስድቡ ጋር በአቻነት እንዲታይ የሚያደርግ የሚዲያ ቅኝት ተጠቅመዋል። የሃይማኖት ንጽጽር የሚደረገው እውነትን ለማወቅ በሚደረግ ማስረጃን መሠረት ያደረገ ጨዋ ትንታኔ መሆኑን እያወቁ ሆነ ብለው ከግላዊ ጥላቻ፥ ስድብና ሹፈት ጋር አመሳስለው ለማቅረብ ጥረዋል።
3/ የሞራል እኩሌታ መፍጠር (Moral Equivalence)
🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀
የግለሰቡን ክብረ ነክ ድርጊት አንዳንድ በድርጊቱ የተናደዱ ሙስሊሞች ስሜታዊ ሆነው ከሚሰጡት ግብረ መልስ ጋር በማነጻጸር ግለሰቡን ለመጉዳት የዛቱ ጥቂት ሙስሊሞችን ድርጊት በማጉላት “ሰላማችን አደጋ ውስጥ ወድቋል” የሚሉ አቀራረብ ያላቸውን መልዕክቶችን አሠራጭተዋል። እጅግ አደገኛ የሆነውን የጥላቻ ንግግርን፥ ስድብን እና ማንቋሸሽን ከሃይማኖት ንጽጽር ጋር አመሳስለው በማቅረብ የሃይማኖት ንጽጽርን ልክ እንደ ጥላቻ ንግግር ቆጥረዋል። የዚህ ሂደት አስኳል “እናንተ እገሌ የተናገረውን እንደ ጥላቻ፥ ስድብና ማንቋሸሽ ከቆጠራችሁ እኛም የእናንተ ድርጊት ተመሳሳይ ነው የሚል እንድምታ እንፈጥራለን” የሚል ነው። መቋጫውም “ያ ጥፋት ከሆነ ይህም ጥፋት ነው” የሚል ግንዛቤ መፍጠር ነው።
4/ ቅኝቱን በመቆጣጠር ድርጊቱ በተናጠል እንዳይወገዝ መከላከል (Controlling the Discourse to Avoid Isolation)
📥📥📥📥📥📥📥📥📥📥📥📥📥📥📥📥
ይህ ስልት በገለጽነው መልኩም ሆነ በማንኛውም መንገድ ለወንጀሉ አቻ የሚመስል ነገር በመፍጠር በሚዲያ፥ በሕብረተሰቡ ዘንድ፥ በአጀንዳነት ብሎም በውግዘት ጉዳዩ ለብቻው እንዳይወገዝ መታገል ነው። ይህም እውን እንዲሆን የህብረተሰቡን ስሜት፥ እምነትና ስስ ጎኑን ነካክቶ በዚያ መስመር ውስጥ እንዲፈስ በማድረግ ሀሳቡን በስሜት እንዲገልጽ በማድረግ በመሰል ጉዳዮች ላይ ባለድርሻ የሆኑት የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፥ የመንግስት አካላት፥ ሚዲያዎችና ሌሎች አካላት የእነሱን ትርክት ተቀብለው ጥፋተኛውን ግለሰብ፣ ወይም ደጋፊዎቹን በተናጠል ከመተቸት እንዲርቁ በማድረግ በሁሉም መንገድ መታገል ነው። ይህ ሲሆን የሙስሊምና የክርስትና ሃይማኖት አባቶች በጋራ ወጥተው “ጥፋተኞች ሁላችንም ዘንድ አሉ” የሚል አቀራረብ ያለው ትርክትን እንዲቀበሉ ጫና ይፈጥርላቸዋል። መንግስትም በዚህ ትርክት ጫና ዉስጥ ገብቶ በሚዲያዎቹ በኩልም ሆነ በባለስልጣናቱ በኩል ደረጃው ምንም ይሁን ምን ጉዳዩ ሁለቱንም ወገን እንደሚመለከት የሚያንጸባርቅ ቅኝት ያለው ዘገባ ወይም ንግግር ወደማድረግ ይዘነበላል።
5/ ተበዳይን ማዞር (Victim Reversal)
↖️↖️↖️↖️↖️↖️↗️↗️↘️↘️↖️↗️
ይህ ስልት ተጠቂ የሆኑትን አካላት መልሶ አጥቂ አስመስሎ ማቅረብ ነው። ለምሳሌ በሕግ አግባብ ቅጣቱን ማግኘት የሚገባውን ወንጀለኛ ተግባር ችላ በማለት በንዴት ዛቻ መሰል ይዘት ያለው ንግግር ያደረጉ ሙስሊሞችን ንግግር ደጋግሞና በብዛት ተቀባብሎ በማቅረብ “ሙስሊሞቹ ሊገድሉት ስለሆነ ህይወቱ አደጋ ውስጥ ነው” በማለት ግለሰቡን አጥቂ ሳይሆን ተጠቂ አድርጎ የማቅረብ ስልት ተከትለዋል። ህብረተሰቡን “ጀግናችሁን ተከላከሉ” በሚል አቀራረብ በዙሪያቸው ኃይል ለማሰባሰብ ስሜት ኮርኳሪ ይሆናሉ ብለው ያሰቧቸውን ዘገባዎች በቆርጦ-ቀጥል ስልት በመጠቀም እውነታውን ለማዞር ሲዳከሩ ታይተዋል።
6/ አጀንዳ ማስለወጥ (Agenda Shifting)
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧