Audio
አቻነት ፍለጋ የ16 ዓመት ጉዞ
❇❇❇❇❇❇❇❇❇
በአሕመዲን ጀበል
🕜🕝🕝🕝🕝
መልክቱ ለሁሉም እንዲደርስ በሁሉም መንገድ ያሰራጩ።
❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌
ሰሞኑን አጀንዳ የሆነው ሙስሊሞችን በማስቆጣት ቀድሞ የታቀደ በሚመስል መልኩ የሆነ ዓላማን ለማሳካት የአላህን መልዕክተኛ (ሰዐወ) በማህበራዊ ሚዲያ የማንቋሸሽ፥ የማነወር እና የማዋረድ ተግባር ሁሉንም ሙስሊሞችን አስቆጥቷል። የድርጊቱ ፈጻሚ ግለሰብም በአስቸኳይ ለሕግ ቀርቦ ተገቢውን ቅጥት ማግኘት ይገባዋል።
በፕሮፓጋንዳ፥ በፖለቲካና በስነ-ልቦና ጦርነት ስልቶች ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በመቆጣጠር የራስን ወገን ወንጀል ለመደበቅ፥ ሌላውን ተከሳሽ አድርጎ ለማቅረብ፥ ተጠቂ በደሉን እንዳያቀርብ ለማፈን፥ አልያም የምላሹን መጠንና የሙቀት ደረጃን ለመለካት ሲባል ሁለት የማይገናኙ ወይም የማይዛመዱ ነገሮችን አሳሳች በሆነ መልኩ ትይዩ አድርጎ አመሳስሎ ለማቅረብ የተለየያዩ ስልቶችና ጥረቶች ይተገበራሉ።
በሰሞኑ የአላህ መልዕክተኛ (ሰዐወ) ክብረ ነክ ስድብ፥ የጥላቻ ንግግርና ማንቋሸሽ ጉዳይ ላይ አንዳንድ ግለሰቦች፥ አክቲቪስቶችና ሚዲያዎች ጉዳዩ ላይ የተከተሏቸውን ስልቶች፥ ጉዳዩን የዳሰሱበትን መንገድና ተያያዥ ነገሮችን ከፕሮፓጋንዳ፥ ከስነልቦና ጦርነትና ከፖለቲካ ስትራቴጂ አንጻር ያስተዋለ ሰው የተገበሯቸውን በርካታ ስልቶች በቀላሉ ይረዳል። በማስከተል የሚከተሉትን ጥቂት ቁልፍ ስልቶቻቸውን እንመልከት።

📌ዛሬ ብንሞት ምን የማይቋረጥ መልካም ስራ አለን?
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይዊ ወሰለም እንዲህ ይላሉ:–
"የሰው ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል። ከሶስት ሲቀር።
① ቀጣይነት ያለው ሶደቃ፣
② ወይም ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት፣
③ ወይ ደግሞ ዱዓ የሚያደርግለት ጥሩ ልጅ።" [ሙስሊም]
የቱ ጋር አለህ? የቱ ጋር አለሽ?
① ከቻልን ህዝብ የሚጠቅም ሶደቃ ጥለን እንለፍ።
② ወይ ደግሞ ወይ አውቀን እናሳውቅ። ወይ የዑለማዎችን እውቀት እናስራጭ።
③ ልጆቻችንን ደግሞ በጥሩ ሁኔታ ኮትኩተን እናሳድግ። ከሁሉም አለመኖር ግን አሳዛኝ ብክነት ነው።
📌 T.me/ahmedin99

“ከመልካም ስራዎች በላጩ ተግባር በሙእሚን ወንድምህ ልቦና ውስጥ ደስታን ማስገባት፣ ወይም እዳውን መክፈል፣ ወይም ምግብ ማብላት ነው።”
ረሱል ﷺ
ረሱል ﷺ
Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል
Photo
የለሊቱን ሰደቃችንን ለአባጅፋር ትምህርት ቤት
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
አሁን ባለንበት ጊዜ እንደምታወቀው አዳዲስ ፈጠራዎች፣ ልምዶች እና የተለያዩ የህይወት መንገዶች ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል ትልቁ መሳሪያ ለሰው ልጅ የሚያስፈልገው ትምህርት ነው። ማንኛውም የትምህርት መስፋፋት እንቅስቃሴ ውጤታማነት የሚወሰነው ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሚያደርጉት የጋራ ጥረት እና ድጋፍ እንደሆነ ይታወቃል።
በዚህ መሰረት በጅማ ከተማ የአባጅፋር ት/ቤት ተጠቃሚ ማህበረሰብ ለማገልገል በ1999 ዓ.ም. ለትምህርት አገልግሎት የሚውል 20,000m2 መሬት በሼህ ጣሂር አብዱልቃድር እና ሼህ መሀሙድ አስተባባሪነት የምመራው የዳዕዋ እና እውቀት በጎ ፈቃደኞች ድርጅት ለጅማ ከተማ አስተዳደር የማህበረሰብ ትምህርት ለማስፋፋት ያለመ ፕሮፖዛል አቅርበው ነበር።
ይህ የዳዕዋ እና እውቀት በጎ ፈቃደኞች ድርጅት በ2003 ዓ.ም ለትምህርት አገልግሎት በወሰዱት መሬት ከኢስላሚክ የዓለም ባንክ (IDB)በጎ ፈቃደኞች ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ባለ አንድ ወለል ፎቅ 8 መማሪያ ክፍሎች፣ 4 የመዋለ ሕጻናት መማሪያ ክፍሎች እና 6 የቢሮ ክፍሎችን በወቅቱ ገንብቶ የመማር እና ማስተማር ስራ ተጀመረ። በዚህም መሰረት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ (ወንድ = 214 ሴት = 212 አጠቃላይ ተማሪዎች = 426 ) ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር የጀመረ ሲሆን፤አሁን በ2017 የተማሪዎች ቁጥር ከ2000 በላይ ሆነዋል፡፡
የህዝቡ ፍላጎት እና ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ትምህርት ቤቱ ወደ ሁለተኛ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል በተመሳሳይ እስላማዊ ዲሲፕሊን ተማሪዎቹ ታንጽው ባሉባት እየተማሩ እንድቀጥሉ ሲጠይቅ ቆይቷል። በተለይም ልጃገረድ ተማሪዎች 8ኛ ክፍል ጨርሰው ሌላ ቦታ ስሄዱ በአለባበስ እና በሰላት ምክንያት ለችግር እየተጋለጡ መሆኑ እየተስተዋለ ያለ እውኔታ ነው።
በዚህም መሰረት የህዝቡ የፍላጎት ሁኔታ እና የተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ እስከ 12ኛ ክፍል ልጆቻቸው በተመሳሳይ ዲሲፕሊን እንዲቆዩ በመፈለግ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቆይቷል። ምንም እንዃ የበጀት ጉዳይ ቀዳዳ ያልተገኝለት ቢሆንም ፤ ምኞቱ እንደቀጠለ ነው፡፡
ባጠቃላይ እነዚህን ችግሮች እና መሰል የአባጅፋር ትምህርት ቤት ችግሮችን ለመቅረፍ በአህመዲን ጀበል አማካኝነት ፤በይበልጥ ሙስሊም ሴት ልጆችን ማዕከል ያደረገ የእገዛ ርብርብ በማድረግ ከአንድ በጎ ፈቃደኛ ድርጅት በተገኘ አምስት ሚሊዮን ብር አባጅፋር ትምህርት ቤትን ወደ ሁለተኛ ደረጃ ለማስፋፋት ባለ አንድ ወለል ፎቅ ለ9ኛ ክፍል ግንባታ የተጀመረ እና መሰረቱ ተጠናቆ እርዳታ ሰጪ ድርጅት እርዳታውን በማቋራጡ እንደተጀመረ በአሳዛኝ ሁኔታ ቆሞ ይገኛል። ስለሆነም በህገር እና ውጭ የሚትገኙ የሙስልም ቤተሰቦች አባጅፋርን ወደ ሁለተኛ ደረጃ በማስፋፋት እስላማዊ ስርዐት የተጎናጸፉ ልጆችን ለማፍራት የምትፈልጉ ሁሉ ህንጻውን በማጠናቀቅ ለሁለተኛ ደረጃ የመማሪያ ክፍሎችን በፍጥነት ማጠናቀቅ እንድቻል እና ይህን በአነስተኛ ክፍያ እና ያለ ምንም ትርፍ ማህበረሰቡን እያገለገለ ላለው ብቸኛው የሙስሊም ቤተሰብ ት/ቤት እንድትደግፉ በአባጅፋር ቤተሰብ ስም በአክብሮት ትብብራችሁን እንጠይቃለን። ምንዳውን አላህ ይክፈላችሁ፡፡
አካውንተ ቁጥር
🔴 1000539605767 CBE የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
🔴 1000032860001 HIJIRA BANK
🔴 ራሚስ 1010047107501
🔴 የኦሮሚያ ህብረት ስራ 1041900329549
🔴 አዋሽ ባንክ 014251537100900
🔴 ወጋገን ባንክ 1049075735101
🔴 አቢሲኒያ ባንክ 211117176
🔴 ዳሽን ባንክ 0021557613011
🔴ዘምዘም ባንክ 005547022010

የሃይማኖት ንጽጽርንና የሃይማኖት ዘለፋን የማምታታት ነገር
🏵🏵🏵🔴🔴🔴🏵🏵🏵🔴🔴🔴
በአሕመዲን ጀበል
ሰሞኑን እስካሁን ለሕግ ባልቀረበው ግለሰብ አማካኝነት የአላህ መልዕክተኛ (ሰዐወ) ከመሰደባቸው ጋር ተያይዞ የሃይማኖት ንጽጽር ጉዳይ አጀንዳ እንዲሆን እየተጉ ያሉ ወገኖች መኖራቸውን መረዳት ይቻላል። ይህ በመሆኑ ስለሃይማኖት ንጽጽር ጉዳይ ጥቂት ማለት በመፈለግ ብዕሬን አነሳሁ። መልካም ንባብ።
የራሱን ሃይማኖት ለሌሎች በማድረስ መስበክ የሚፈልግ ማንኛውም አካል የሃይማኖቱን መልዕክት ለማድረስ ሲነሳ መልዕክቱ የደረሰው ግለሰብ በዚህ ጉዳይ ላይ የራሱ አስተሳሰብ፣ መረዳት፣ እምነትና አቋም እንዳለው ማወቅ ወይም መገመት ይጠበቅበታል። ወደ እምነታችንም እየጋበዝነው ያለነው እምነታችንን የማይከተለው መሆኑም መዘንጋት የለብንም።
ይህ አካል እምነት እንዲቀበል ሲጋበዝ ግብዣውን የመቀበልም ሆነ ያለመቀበል ነጻ ምርጫ አለው። በጉዳዩ ላይ ለሰባኪው መልሶ ጥያቄ የማንሳት፣ የተጋበዘበት እምነት ትክክል አለመሆኑን በማስረጃ የመሞገት መብትም አለው።
እምነቱን ሌሎች እንዲቀበሉ ጋብዞ ወደሀሳብ ገበያ የወጣ ሰው "ለምን በምሰብከው እምነቴ ላይ ጥያቄ ታነሳለህ?" የማለት መብት የለውም። ይህንን ካለ "አንተስ እኔን የመስበክ መብት እንዴት ኖረህ?" የሚል ምላሽ ማግኘቱ አይቀሬ ነው። ለዚህም ነው ሃይማኖትን የመስበክ መብት እስከ ተከበረ ድረስ በዚያ በሚሰበከው ጉዳይ ላይ ስነ ምግባር በተሞላበት ሁኔታ የሌሎችን ሃይማኖትና እምነትን ሳያንቋሽሹ መወያየት፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በማስረጃ መከራከር የስልጡንነት መገለጫ የሚሆነው።
ከዚህ አንጻር ከሰሞኑ የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) መሰደብ ጋር በተያያዘ አንዳንዶች "እኛም እፎይ ነን" በማለት ራሳቸውን መግለጻቸው፣ በሃይማኖት ንጽጽርና ሃይማኖትን በመስደብ መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነትን አደብዝዘው ለማቅረብ ሲዳክሩ ታይተዋል። በመሆኑም በውይይት እና ብሽሽቅ መካከል ስላለን ግዙፍ ልዩነት ግልጽነት መፍጠር ተገቢ ነው።
የሃይማኖት ጥናት፣ ንጽጽርና ክርክር ምንድነው?
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
1) የሃይማኖት ጥናት ምንነት
💥💥💥💥💥💥💥💥
የሃይማኖት ጥናት ማለት በሆነ ሃይማኖት ላይ ግንዛቤን ወይም እውቀትን በማሳደግ ዓላማ በጉዳዩ ዙሪያ ያሉትን ማስረጃዎችን የማወቅ፣ የመማርና የመሸምደድ ሂደት ነው። ለምሳሌ የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ወይም ኢየሱሰ (ዐሰ) ማንነት ላይ ያሉትን ማስረጃዎች ለማወቅ፣ ለመማር፣ ለመረዳት ሲባል የተለያዩ መጽሐፍቶችን ማንበብ።
2) የሃይማኖት ንጽጽር ምንነት
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
የሃይማኖት ንጽጽር የምንለው የተለያዩ ሃይማኖቶችን እምነት፣ ታሪክ፣ መጻሕፍት፣ አተገባበር፣ ዓላማና ፍልስፍና ተመሳሳይነት ወይም ልዩነት በሃይማኖቶቹ መመሪያ መጽሐፍት አማካኝነት ምሁራዊ በሆነ መንገድ በማነጻጸር ለመረዳት ጥረት የማድረግ ሂደት ነው። ግቡም እውቀትን ማጎልበትና ምሁራዊ ትንታቤ መስጠት መቻል ቢሆንም ብዙ ጊዜ የራሰን ሃይማኖት ትክክለኛነት ለማሳየት ሲባል የሚደረግ ነው። ለምሳሌ ቁርአንንና መጽሐፍ ቅዱስን፣ የነቢዩ ሙሐመድን እና የኢየሱሰን ስብዕና፣ ማንነት፣ ደረጃ ወዘተ እያነጸጻጸሩ ለመረዳት ወይም ለማስረዳት መሞከር ሊጠቀስ ይችላል።
3)የሃይማኖት ውይይት/ክርክር ምንነት
⏩⏩⏩⏩⏩⏩⏩⏩⏩⏩⏩⏩
የሃይማኖት ውይይት/ክርክር ስለራስ ሃይማኖት ግንዛቤና እውቀት በመፍጠር እምነታችን ከሌሎች እምነቶች ጋር በተነጻጻሪነት ጥናት ከተደረገበት በኋላ በተገኘ መረዳትና አቋም ላይ ተንተርሶ የአንድን እምነት፣ አስተሳሰብ ወይም ሃይማኖት ትክክለኛ መሆን/አለመሆን ለማሳየት፣ ለማሳመን፣ ወይም ምላሽ ለመስጠት የሚደረግ የመረጃና የሀሳብ ልውውጥ ሂደት ነው። ለምሳሌ በኢየሱስ ፈጣሪ መሆን አለመሆን፣ በነቢዩ ሙሐመድን ነቢይ መሆን አለመሆን፣ በቁርአን ወይም መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ መመሪያ መሆን አለመሆን ላይ ያለንን አቋም በማስረጃ በማሳየት የራስን ትክክለኛነት፣ የሌላውን ስህተትነት ለማስረዳት መሞገት ሊጠቀስ ይችላል።
4/ የሃይማኖት ስድደብና ብሽሽቅ ምንነት
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
ሃይማኖትን መስደብ ወይም ማነወር የአንድን ሃይማኖት እምነቶች፥ ሃይማኖቱ ፈጣሪ ነው ብሎ የሚያስተምረውን አካል፣ ነቢይ፣ የአምልኮ ሥርዓት፣ የሃይማኖት መገለጫ፣ ቅዱሳን መጻሕፍትን፣ ቅዱስ ስብዕና ወዘተ አክብሮት ባልተላበሰ መልኩ መሳለቂያ ማድረግ፣ ሌሎች እንዲሳለቁ ማነሳሳት፣ ሃይማኖቱንና ተከታዮቹን ማዋረድ፣ ጥላቻን ለመግለጽና የተከታዮቹን ሞራል ለመንካት በማለም የሐሰት ውንጀላ መሰንዘር፣ ማናናቅ፣ መሳለቅ፣ ማጣጣል፣ እንዲሁም ሌሎች ተንኳሽ ድርጊቶችን መፈጸም ነው።
ለምሳሌ ስለኢየሱስ (ዐሰ)፥ ስለነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ፣ ስለቁርአን፣ ስለመጽሐፍ ቅዱስ ያሉንን እምነቶች ወይም አቋሞች ትክክለኛ አለመሆን በማስረጃ ከመሞገት ይልቅ የኢየሱስን፣ አልያም የነቢዩ ሙሐመድን (ሰዐወ) ስብዕና ለማነወር፣ ለማሳነስ፣ ለማንቋሸሽ እና ለማጥላላት በተለያዩ መንገዶች ጥረት ማድረግ ሊጠቀስ ይችላል።
ልዩነቱ ግልጽ እንዲሆን ትንሽ እናፍታታው
🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯
1/ "ኢየሱስ ነቢይ ነው፤ ሰው ነው፤ አምላክ ነው፥ የአምላክ ልጅ ነው" ወዘተ የሚሉ አቋሞችን መያዝ የእምነት ወይም የሀሳብ ነጻነት መብት ነው። ለምን እነዚህን አቋሞችን እንደያዙ ማብራራትም መብት ነው።
በተመሳሳይ መልኩ "ሙሐመድ ነቢይ ናቸው/አይደሉም" የሚል አቋሞችን መያዝ መብት ነው። ሆኖም ከዚያ ተሻግሮ የአላህን መልዕክተኛ (ሰዐወ) መስደብ፣ ማነወር፣ በጥላቻ ስብዕናቸውን ማጥላላት የሃይማኖት ክርክር ሳይሆን የጥላቻ ንግግር ነው።
2/ "መጽሐፍ ቅዱስ ወይም ቁርኣን የፈጣሪ ቃል ነው/አይደለም" ብሎ ማመን፣ መለኮታዊነቱን መቀበል/አለመቀበል መብት ነው። ይህንኑ እምነት ለምን እንደያዙ ማብራራት፣ ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎችን ስነ ምግባር በተሞላበት መልኩ ማንሳት መብት ነው። መጸሐፍቶቹን ማነወርና መሳለቅ ግን ሃይማኖትን መስደብ ነው።
3/ አንድ ሰው ሌሎችን "ኢየሱስ ሰው ነው አትበሉ! ነቢይ ነው አትበሉ!" ሊል አይችልም። ወይም "ነቢዩ ሙሐመድ ነቢይ አይደሉም አትበሉ" ብሎ የመከልከል መብት የለውም። በኢየሱስ ነቢይ ወይም ሰው መሆንና አለመሆን ላይ የራሱን እምነት በነጻነት ማራመድ መብቱ እንደሆነው ሁሉ ሌሎችን እስካላስገደደ ድረስ ማንም ሰው በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ከሌሎች የተለየ አቋም/እምነት የመያዝ መብት እንዳለው መረዳት ተገቢ ነው። "ኢየሱስን ሰው/ነቢይ ነው አትበሉ" ማለት "እኔ እንደማምነው ኢየሰሱስ ሰው ሳይሆን አምላክ ነው ብላችሁ እመኑ"፣ ወይም "እንደኔ ክርስቲያን ሁኑ" ማለት ነው። ይህ ደግሞ ሌሎች ምን ማመን እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው ማስገደድ ነው።
በተመሳሳይ መንገድ "ነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) እኛ ነቢይ ናቸው ብለን ስለምናምን ነቢይ አይደሉም አትበሉ" ማለት የግድ "እንደኛ ሙስሊም ሁኑ" ማለት ነው። ይህ ደግሞ ሌሎች ከእኛ የተለየ እምነትና አቋም እንዳይይዙ ማስገደድ ነው። የአስተሳሰብና የእምነት ነጻነትን መጋፋት ነው።
ከዚህ አንጻር አንዳንዶች በጉዳዩ ላይ ያለውን ልዩነት ያልተረዱ ሰዎችን ለማሳመን ሙስሊሞች ኢየሱስ ሰው ነው ብለን ማስተማራችንን እንደ ትንኮሳ ለማቅረብ ሲታትሩ ማየት ይደንቃል።

4/ በሃይማኖት ንጽጽር ውስጥ በማስረጃ፥ በትንታኔና በአመክንዮ የሚደረግ የሃይማኖት ማመሳከር፣ ጥናትና ማስረጃ ልውውጥ ሲኖሩበት ትኩረቱ ግለሰቦች ራሳቸው ሳይሆኑ ስለግለሰቦቹ ነው። ለምሳሌ የኢየሱስን ማንነት ካየን የትኩረት ማዕከሉ ስለኢየሱስ እንጂ ራሱ ኢየሱስ አይደለም። በኢየሱስ ማንነት ጉዳይ የተለያዩ አካላት ያሳመናቸውን ሀሳብ በነጻነት መያዝ፣ በማስረጃ መከራከር፣ ያሳመናቸውን ሀሳብ መደገፍ፣ ያላሳመናቸውን ደግሞ ለምን እንዳላሳመናቸው መግለጽ የማሰብ ነጻነትና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ አካል እንጂ ኢየሱስን ማነወር አይደለም።
5/ የአንድን ሰው የፖለቲካ አቋም ትክክል አለመሆን በማስረጃ፥ ማሳየት፣ ስነ ምግባር በተሞለበት መንገድ መተቸት የማሰብና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ አካል ነው። ነገር ግን ሀሳቡን ትቶ የፖለቲከኛውን ስብዕና ለማነወር መሞከር ግለሰባዊ ጥቃት ነው። በሃይማኖት ጉዳይም ተመሳሳይ ነው። የትኛውም ሃይማኖታዊ እሳቤ ትክክል ነው ወይም አይደለም ብሎ መተንተን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አካል ነው። ነገር ግን የአምነቱን መሪ ስብዕና፣ አልያም በእምነቱን ቅዱስ ተብሎ የሚታሰብን ነገር መሳለቂያ ማድረግ ግን ጥቃት ነው። የአላህን ፈጣሪነት አለመቀበል፣ የነቢዩ ሙሐመድን (ሰዐወ) ነቢይነት አለማመን እና ለምን እንደማያምኑ ማብራራትም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አካል ነው።
6/ አንድን እምነት "ትክክል ነው/አይደለም" ብሎ ማመን መሠረታዊ የእምነት ነጻነት አካል ነው። በ2004 የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር "ትክክለኛ እምነት የራሴ እምነት ብቻ ነው ብሎ ማመን አክራሪነት ነው" የሚል አጓጉል ፍረጃ ይዞ መጥቶ ቀውስ ፈጥሮ ነበር። የየትኛውም ሃይማኖት ተከታዮች ትክክለኛውና የሚያድነው የሕይወት ጎዳና እነሱ የያዙት እምነት ብቻ እንደሆነ ያምናሉ። ሙስሊሞችም በአላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ትክክለኛ እምነት ኢስላም ብቻ መሆኑን ያምናሉ። ክርስቲያኖችም ትክክለኛ እምነት የእነሱ ብቻ እንደሆነ ያምናሉ። የሰው ልጆች ሁሉ እነሱ ትክክለኛ የሚሉትን እምነትን ቢቀበልም በእጅጉ ይደሰታሉ። ይህ ጤናማ እይታ ነው። ለራስ የሚወዱትን ለሌሎች መውደድ ክፋት የለውም። ሆኖም ያለ ሰዎች ነጻ ፈቃድና ፍላጎት የእኛን ሃይማኖት እንዲከተሉ የማስገደድ መብት የለንም።
ፈጣሪ ለሰው ልጆች የፈለጉትን የማመን እና የመከተል ነፃነት ሰጥቷል። ይህ ነፃነት የተቸረው በምድረ ዓለም ሳሉ ብቻ ነው። በቀጣዩ ዓለም ግን የነጻ ምርጫቸውን ሽልማት አልያም ቅጣት ይቀበላሉ። ያላመኑት ባለማመናቸው ምክንያት ስለማይድኑ ለፈጸሟቸው ጥፋቶች ተጠያቂ ይሆናሉ። አማኞች ደግሞ በእምነታቸውና በመልካም ሥራቸው ይመነዳሉ። በምድረ ዓለም ግን የማመንና ያለማመን የሰው ልጅ ነፃነት የተጠበቀ ነው። ማንም ሊገረስሰው የማይችል መብት ነው። የፈለገ ያምናል። ያልፈለገ ይክዳል።
ስብከትና የሌሎችን ሃይማኖት የማነወር መዘዝ
🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮
ስብከት (ሃይማኖታዊ ጥሪ) የራስን ሃይማኖት፣ አስተሳሰብ እና እምነት ሌሎች እንዲቀበሉ፥ በአዎንታዊነት እንዲያዩ እና ትክክለኛነቱን እንዲመረምሩ የመጣራት ተግባር ነው። ይህ ተግባር ዓላማው ሌሎች እኛ ዘንድ ያለውን እምነት እንዲቀበሉ ወደራስ መሳብ ነው። ሆኖም ይህ ተግባር ሌሎች እምነታችንንም ሆነ አካሄዳችንን በአዎንታዊነት አይተው ልቦናቸውን ክፍት እንዲያደርጉ፣ ሰበካውንም ጆሯቸውን ከፍተው በፈቃዳቸው እንዲሰሙ ማድረግን ይጠይቃል።
ሰበካው (ዳዕዋው) የሚደረገው በይዘቱም ሆነ በአቀራረቡ መልዕክቱ እንዲደርሳቸው የታሰቡትን አካላት በሚያስከፋ ፥ በሚያስቆጣ እና እንዳይሰሙት በሚያደርግ መልኩ ከሆነ ፈጽሞ የታለመውን ግብ ከዳር ማድረስ አይችልም። በተቃራኒው ስለእምነቱ በፊት ከነበራቸው አስተሳሰብ፥ እይታና አቋም ላይ ሌላ አሉታዊ እይታ በመጨመር መልዕክቱን ለማድመጥ፣ ለመፈተሽና ለመቀበል ልቦናቸው ዝግ እንዲሆን ያደርጋል።
በስብከት ሂደት የሌሎችን ሃይማኖት መሳደብ፣ ማንቋሸሽና ማናናቅ የራስ ወገን በእምነቱ እንዲፀና በር መዝጋት ይችል ይሆናል ተብሎ ቢታሰብ እንኳ መልዕክቱ እንዲደርሳቸው በታለመላቸው አካላት ላይ ግን አሉታዊ ስሜት፣ ጥላቻና ተቃውሞ መፍጠሩ አይቀርም። ብዙ ጉዳቶችም አሉት። የተወሰኑትን እንመልከት...
1/ ጥላቻና ቂም ይፈጥራል
🔶🔶🔶🔶🔶🔶🔶🔶🔶
ሀ/ ስለ ልቦናዊ ምላሽ - ሰዎች በጽናት የሚያምኑበት እምነት ላይ ሲሾፍና ሲቀለድ ተደፈርኩ የሚል ስሜት ስለሚፈጠርባቸው ምላሻቸው ንዴት፣ ቂምና ራስን መከላከል ይሆናል።
ለ/ የስሜት ጉዳት - እምነት የሰዎች ማንነት ምንጭ፣ የመኖራችን ትርጉም፣ የሕይወታችን ግብ ምንጭ በመሆኑ ሃይማኖቱ ሲሰደብ ሰዎች ስድቡን በራሳቸው ላይ እንደተቃጣ ጥቃት ይቆጥራሉ።
መ/ በቀል - ጠላትነትን ያቀጣጥላል። ይህ ደግሞ ቃላዊ፥ ማህበራዊ እና አካላዊ ግጭቶችን ሊያስከትል ይችላል።
2/ መልዕክቱን የመቀበል ተነሳሽነትንና የመልካም ዉይይትን በር ይዘጋል
❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌
ሀ/ ሰዎች ለሚተላለፈው መልዕክት ልባቸውን እንዲዘጉ ይገፋፋል። ማንም ሰው እምነቱ ሲሰደብ ልቦናውን ከፍቶ ያለቅሬታ ስብከት አያደምጥም። አይቀበልምም።
ለ/ ለዚያ ግለሰብና እምነት ጥላቻን ያዳብራል። ስድብ የቀላቀለ ስብከት ሲደረግለት ማንም ሰው ግለሰቡንም ሆነ የሚጣራበትን እምነት እንደ መልካም አይመለከትም።
መ/ ጤናማ ውይይትን ያደናቅፋል። ስድብና ማነዋር የተቀላቀለበት ስብከት ጤናማ ውይይት እንዳይደረግ በር በመዝጋት በዚያ እምነት ውስጥ ሊኖር የሚችለውን እውነት ከማየት ይልቅ የራሱን እምነት ወደ መከላከል እንዲገፋፋ ያደርጋል።
3/ የሃይማኖት ግጭትን ያቀጣጥላል
🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒
ሀ/ ክፍፍልን ያበረታታል - የሃይማኖት ዉይይት ስነ-ምግባርን ካልተከተለ፣ ንቀት ከተቀላቀበት ይበልጥ ክፍፍል፥ መራራቅና መቦዳደን ይፈጥራል።
ለ/ ሰዎችን ወደአክራሪነት ይገፋል - የራስን እምነት ያለአግባብ የማጥበቅና ሌሎችን የማገለል ሂደት በመፍጠር ወደቡድናዊ ግጭት ይመራል። በታሪክ የተፈጠሩ ግጭቶች፣ ጦርነቶችና ጭቆናዎች የሌላን እምነት ከማነወር የመነጩበት ሁኔታ አለ።
የሃይማኖት ንጽጽር እውነትን በማወቅና በማሳወቅ ዓላማ፣ ስነ ምግባርን በተከተለ መልኩ የሃይማኖቶችን የተለያዩ ገጽታዎች ልዩነትና ተመሳሳይነት የሚያጠና ሲሆን ዘለፋ ግን የሌሎችን ሃይማኖት ለማነወርና ለማንቋሸሽ በማለም የጥላቻ ንግግር ማድረግ ነው። ሁለቱ እጅግ የተለያዩ ነገሮች ናቸው።
እርግጥ አልፎ አልፎ ሁለቱን ደባልቀው የሚተገብሩ ጥቂት አካላት መኖራቸው የሚካድ አይደለም። በሃይማኖት ንጽጽር ሙግት ማስረጃ ያጠራቸው፣ የተወያዩን ሙግት መቋቋም ያቃታቸው አካላት የሌሎችን ሃይማኖት በመሳደብና ተከታዮቹን ስሜታዊ በማድረግ ሽንፈታቸውን ለማካካስ ሊጥሩ ይችላሉ። የመሰል ውይይቶችን በር ለመዝጋትና "ምእመን እንዳይሸሽ" ለማድረግ የሌሎችን ሃይማኖት ወደ መዝለፍ እንደሚገቡ በተደጋጋጋሚ ታይቷል። በውይይት ወቅት ገንፍሎ የሚወጣ ጥላቻም ለዘለፋ መንስዔ የሚሆንበት ጊዜ አለ።

በሕዝቦች መካከል መቃቃር፣ ግጭትና ጥላቻን ለመፍጠር የሚያልሙ አካላት የሌሎችን ሃይማኖት ማንቋሸሽን እንደዘዴ ይጠቀማሉ። ማህበራዊ ሚዲያውን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ራሳቸውን ደብቀው መሰል ጥፋቶች ላይ የሚሰማሩ አካላት ሲበዙ የችግሩ መፈጠር ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ድርጊቱ ወንጀል በመሆኑ ለድርጊቱ ተገቢውን ቅጣት የሚጥል ጠንካራ ህጋዊ ማዕቀፍ ያስፈልጋል። እስከዚያው በሥራ ላይ ባሉት ሕግጋት አጥፊዎቹ ለህግ መቅረብ ይገባቸዋል።
በዚህ ረገድ ሀገራችን "የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት አዋጅ ቁጥር 1185/2ዐ12" የተሰኘ አዋጅ አውጥታለች። ይህ አዋጅ የጥላቻ ንግግርን እንዲህ ይተረጉመዋል...
"‘የጥላቻ ንግግር’ ማለት በአንድ ሰው ወይም የተወሰነ ቡድን ላይ ያነጣጠረ፣ ብሄርን፣ ብሄረሰብንና ህዝብን፣ ሀይማኖትን፣ ዘርን፣ ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ ጥላቻን፣ መድልዎን ወይም ጥቃትን የሚያበረታታ ንግግር ነው።"
አዋጁ ሃሰተኛ መረጃን ሲተረጉም ደግሞ እንዲህ ይላል...
"‘ሃስተኛ መረጃ’ ውሸት የሆነና የመረጃውን ውሸት መሆን በሚያውቅ፣ ወይም መረጃውን የሚያሰራጨው ሰው ካለበት አጠቃላይ ሁኔታ አንጻር የመረጃውን ሃሰተኝነት ሊያውቅ ይገባ ነበር የሚያስብል በቂ ምክንያት እያለ የሚሰራጭ ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት፣ ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ከፍ ያለ ንግግር ነው።"
ይህ እና ሌሎች ተያያዥ አዋጆች ወጥተው በሥራ ላይ ባሉበት የተለያዩ ግለሰቦች በነቢያችን ሙሐመድ (ሰዐወ) እና በሃይማኖታችን ላይ መሰል ወንጀሎችን በተደጋጋሚ ሲፈጽሙ የሚመለከተው አካል እርምጃ ሊወስድ ይገባል። እንኳንስ አቤቱታ ቀርቦለት ይቅርና ባይቀርብለት እንኳ ለሀገር ሰላምና ደህንነት ሲባል እንደተቋቋመ አካል ወንጀል ፈጻሚዎቹ የየትኛውም ጎራ አባል ቢሆኑ ሕጉን የማስከበር ኃላፊነቱን መወጣት ግዴታው ነው። ከዚህ አንጻር የቀረበለትን አቤቱታ ችላ በማለት ሕጉን ለማስፈጸም ዳተኝነት ማሳየቱ ለከፍተኛ ትዝብት የሚያጋልጠው ነው።
ባለፉት ጊዜያት የተፈጸሙት ወንጀሎች ለአንዳቸውም ተገቢውን መፍትሄ ሳይሰጣቸው ተዳፍነው በመቅረታቸው በኢስላምና ሙስሊሞች ላይ መሰል ጥቃቶች እየተለመዱ ይገኛሉ። የህግ አካላት ዝምታም ይህ እንዲደረግ በተዘዋዋሪ ተባባሪ እየሆኑ ነው ወደሚያስብል ደረጃ እያደገ ነው። በመሆኑም ሕዝበ ሙስሊሙ በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ መፍትሄ እየጠበቀ መሆኑን በአጽንኦት ለማሳሰብ እንወዳለን።

ሰሞኑን እስካሁን ለሕግ ባልቀረበው ግለሰብ አማካኝነት የአላህ መልዕክተኛ (ሰዐወ) ከመሰደባቸው ጋር ተያይዞ የሃይማኖት ንጽጽር ጉዳይ አጀንዳ እንዲሆን እየተጉ ያሉ ወገኖች መኖራቸውን መረዳት ይቻላል።
...
እምነቱን ሌሎች እንዲቀበሉ ጋብዞ ወደሀሳብ ገበያ የወጣ ሰው "ለምን በምሰብከው እምነቴ ላይ ጥያቄ ታነሳለህ?" የማለት መብት የለውም።
...
"ኢየሱስ ነቢይ ነው፤ ሰው ነው፤ አምላክ ነው፥ የአምላክ ልጅ ነው" ወዘተ የሚሉ አቋሞችን መያዝ የእምነት ወይም የሀሳብ ነጻነት መብት ነው።
በተመሳሳይ መልኩ "ሙሐመድ ነቢይ ናቸው/አይደሉም" የሚል አቋሞችን መያዝ መብት ነው።
...
"ኢየሱስን ሰው/ነቢይ ነው አትበሉ" ማለት "እኔ እንደማምነው ኢየሰሱስ ሰው ሳይሆን አምላክ ነው ብላችሁ እመኑ"፣ ወይም "እንደኔ ክርስቲያን ሁኑ" ማለት ነው።
...
ይህ ደግሞ ሌሎች ከእኛ የተለየ እምነትና አቋም እንዳይይዙ ማስገደድ ነው።
ከዚህ አንጻር አንዳንዶች በጉዳዩ ላይ ያለውን ልዩነት ያልተረዱ ሰዎችን ለማሳመን ሙስሊሞች ኢየሱስ ሰው ነው ብለን ማስተማራችንን እንደ ትንኮሳ ለማቅረብ ሲታትሩ ማየት ይደንቃል።
🏵🏵🏵🔴🔴🔴🏵🏵🏵🔴🔴🔴
በአሕመዲን ጀበል
ሰሞኑን እስካሁን ለሕግ ባልቀረበው ግለሰብ አማካኝነት የአላህ መልዕክተኛ (ሰዐወ) ከመሰደባቸው ጋር ተያይዞ የሃይማኖት ንጽጽር ጉዳይ አጀንዳ እንዲሆን እየተጉ ያሉ ወገኖች መኖራቸውን መረዳት ይቻላል።
...
እምነቱን ሌሎች እንዲቀበሉ ጋብዞ ወደሀሳብ ገበያ የወጣ ሰው "ለምን በምሰብከው እምነቴ ላይ ጥያቄ ታነሳለህ?" የማለት መብት የለውም።
...
"ኢየሱስ ነቢይ ነው፤ ሰው ነው፤ አምላክ ነው፥ የአምላክ ልጅ ነው" ወዘተ የሚሉ አቋሞችን መያዝ የእምነት ወይም የሀሳብ ነጻነት መብት ነው።
በተመሳሳይ መልኩ "ሙሐመድ ነቢይ ናቸው/አይደሉም" የሚል አቋሞችን መያዝ መብት ነው።
...
"ኢየሱስን ሰው/ነቢይ ነው አትበሉ" ማለት "እኔ እንደማምነው ኢየሰሱስ ሰው ሳይሆን አምላክ ነው ብላችሁ እመኑ"፣ ወይም "እንደኔ ክርስቲያን ሁኑ" ማለት ነው።
...
ይህ ደግሞ ሌሎች ከእኛ የተለየ እምነትና አቋም እንዳይይዙ ማስገደድ ነው።
ከዚህ አንጻር አንዳንዶች በጉዳዩ ላይ ያለውን ልዩነት ያልተረዱ ሰዎችን ለማሳመን ሙስሊሞች ኢየሱስ ሰው ነው ብለን ማስተማራችንን እንደ ትንኮሳ ለማቅረብ ሲታትሩ ማየት ይደንቃል።
🛑 ለይለተልቀድር ለሰጋጆችና መስጂድ ውስጥ ላለ ብቻ አይደለም
የወር አበባ ደም ላይ፣ የወሊድ ደም ላይ ያሉ፣ መንገደኞች...የዚች ለሊት ትሩፋት አይለፋችሁ። በዚክርና መሰል ዒባዳዎች ልትበራቱ ይገባል።በዚያች ለሊት ዱዓእ ማብዛትም አትዘንጉ። ለይለተልቀድር ለሰጋጆችና መስጂድ ላይ ላለ ብቻ አይደለም።
ብዙ ሰው መስጂድ ካልሄደ ይሄን ምንዳ የሚያገኙ አይመስለውም። ይህ ስህተት ነው! ዋናው ከእኛ የሚጠበቀው በኢባዳ ላይ መሆናችን ነው። ለቻለ እና አቅሙ ላለው ሰው ግን የተወዳጁን ነብይ ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና(ፈለግ) ለመከተል መስጂድ ላይ ብንሆን ይመረጣል፣ ይወደዳል። ካልቻልን ባለንበት ቦታ ስራ ላይ የሆነም በስራው ላይ እቤቱ የሆነም በቤቱ በኢባዳ ልንበረታ ይገባል!
አላህ ለይለተል ቀድርን ይወፍቀን!

“ሌሊት መስገድን አስቦ ወደ ፍራሹ የሄደ ከዚያም እስከ ንጋት ዓይኑ ያሸነፈችው ያሰበውን አላህ ይፅፍለታል፤ እንቅልፉም ከጌታው ዘንድ ሶደቃ ይሆንለታል”
ረሱል ﷺ
(ነሳኢ 1787ና ኢብኑ ማጀህ 1344)
ረሱል ﷺ
(ነሳኢ 1787ና ኢብኑ ማጀህ 1344)
🛑 ታላቅ ሰው ለመሆን ታዋቂ መሆን አይጠበቅብህም።
🛑 አብዛኞቻችን ሱደይስን እናደንቀዋለን፣ እናውቀዋለን፤ ፋቲሃን ግን ማን እንዳስተማረው አናውቅም።
🛑ብዙዎቻችን ኢብን ተይሚያን እናውቃቸዋለን፤ ማንበብና መፃፍን ግን ማን እንዳስተማራቸው አናውቅም!
🛑 አላህ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ታላላቅና የተከበሩ ነብያትን ልኳል፣ለኛ የጠቀሰልን ግን ከ 25 አይበልጡም! እንዲህ ይላል
(وَرُسُلًۭا قَدْ قَصَصْنَٰهُمْ عَلَيْكَ مِن قَبْلُ وَرُسُلًۭا لَّمْ نَقْصُصْهُمْ عَلَيْكَ..)
🛑 ከሃሰን አልበስሪ፣ከሻፊዒ፣ከአህመድ፣
ከአቡ ሃኒፋ፣ከነወዊ፣ከኢብን ሃጀ፣ከኢብን ባዝ፣ከኢብን ዑሰይሚን፣ከዶክተር ጀይላን፣ከሃጅ ራፊዕ፣ከሃጅ ሳኒ ሀቢብ...ኃላ ማን እንደነበርስ፣ ማን ያግዛቸው እንደነበርና ማንስ ለዚህ እንዳበቃቸው እናውቃለን? አናውቅም! ስለማናውቃቸውስ ምን ቀረባቸው? ምንም! ስለዚህ
🛑 ወንድሜ አላህ ካወቀህ በቂህ ነውና የሚጠበቅብህን አድርግ፤ ከማንም ምንም ሳትጠብቅ አሻራህን አኑር!

🛑 Nama guddaa ta'uuf beekkamaa ta'uun sirraa hin eegamu.
🛑 irra baayyeen keenya sudaysiin ni diinqisiifanna, hinbeeknas, faatihaa ennu akka isa barsiisee garuu hinbeeknu.
🛑 baayyeen keenya ibnu taymiyaa ni beeyna, barressuu fi dubbisuu eennu isaan akka barsiise garu hin beeknu
🛑 Rabbiin Anbiyoota guguddoo fi kabajamoo kuma dhibbaatamaan lakkaahaman ergee jira, ka nuuf ibsee garuu digdami shan hincaalan
(وَرُسُلًۭا قَدْ قَصَصْنَٰهُمْ عَلَيْكَ مِن قَبْلُ وَرُسُلًۭا لَّمْ نَقْصُصْهُمْ عَلَيْكَ..)
🛑Hasan Albasri, shaafi'i, Ahmad, Abu Haniifaa, Nawawi, Ibnu Hajar, Ibnu Baaz, Ibnu Usaymiin, D/r Jaylaan, Haaji Raafi'i, Haaji saani Habiib..... isaan kana duuba eennu akka jiru, bakka kana akka gahaan eennu akka isaan gargaaraa ture ni beeyna? Hin beeynu! Waan isaan kana hinbeekneef maaltu isaanirraa hafe? Wamaa. Kanaafuu
🛑 obboleessa kiyya Rabbi yoo sibeeke gahaa dha. Kanaafuu waan sirraa eegamu hunda godhi, waan tokko namarraa osoo hin eegin gahee kee bahadhu.