Telegram Web Link
ከሚከተሉት ምስሎች አንዱ ትክክለኛ ፎቶ ሲሆን ሶስቱ በAI የተሰሩ ምስሎች ናቸው። ትክክለኛውን ፎቶ ቁጥር ኮሜንት ላይ አስቀምጡ ዳይ!😀
👍53🤯4221
አሜሪካና እንግሊዝ ኢራቅን ለነዳጅና ለሀብቷ ሲሉ ለመውረር ባሰፈሰፉበት ወቅት ላይ በ 2003 ጃንዋሪ 27 በወቅቱ የአለም አቀፉ አቶሚክ ኤነርጂ ሀላፊ የነበሩት መሀመድ አል ባራዲ ፡ እውነታው እናንተ እንደምትሉት አይደለም አሉ ።
.......
ኢራቅ ለሰላማዊ ግልጋሎት የገነባችውን ፡ የአቶሚክ መሰረተ ልማት በሚገና ፈትሸናል ። ግን ኒውክሊየርን ለጦር መሳሪያነት ለመጠቀም እንደተዘጋጀች የሚያሳይ አንድም ማረጋገጫ አላገኘንም ሲሉ ተናገሩ ።
....
ሆኖም የአቶሚክ ሀላፊው ማረጋገጫ ሰሚ አጣ ።
.....
ከ 18 ቀናት በኋላ በፌብሪዋሪ 14. . የአቶሚክ ሀላፊው በድጋሚ ኢራቅ እናንተ እንደምትሉት ለአለም ስጋት አይደለችም ፡ ምንም አይነት የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ እየሰራች አይደለም ሲሉ ተናገሩ ።
....
ኢራቅን ለመውረር አንዴ ቆርጠው የተነሱት አሜሪካና አጋሮቿ ግን በድጋሚ የተሰጣቸውን ማረጋገጫ ከመስማት ይልቅ ፡ ኢራቅን ለመውረር መዘጋጀታቸውን ቀጠሉ ።
......
የአቶሚክ ሀላፊው መሀመድ አልባራዲ ሰሚ ያጣውን የኤጀንሲውን ማረጋገጫ እንደገና ከ23 ቀናት በኋላ በማርች 7 ለሶስተኛ ጊዜ ተናገሩ ።
እባካችሁ የእኛን ቃል ስሙ ፡ ኢራቅ ምንም አይነት የኒውክሊየር መሳሪያ እየሰራች አይደለም በማለት ሰሚ ያጣውን ጩኸታቸውን አሰሙ ። ሆኖም ይህ ምስክርነት በአሜሪካና እንግሊዝ መንግስታት ውድቅ ሆነ
......
ይህ የመጨረሻው የመሀመድ አልባራዲ ምስክርነት በተሰማ በ13 ኛው ቀን በማርች 20 /2003 ኢራቅ ምንም አይነት አውዳሚ መሳሪያ እንደሌላት የተነገረውን ማረጋገጫ ችላ ብለው የኢራቅ ከተሞችን በቦንብ መደብደብ ጀመሩ ጥንታዊ ስልጣኔ ከዘመናዊው ጋር አጣምራ ውብ የሆነችውን ባግዳድን ጨምሮ ፉልጃ ፡ ባስራ ፡ ሞሱል ፡ ራማዲ ፡ ቲክሪት ፡ ነጃፍ ፡ ካራባላና ፡ ኪርኩክ የሚባሉት ከተሞችን ጨምሮ ፡ አብዛኛው የኢራቅ ምድር ፡ በአሜሪካና እንግሊዝ አዝማችነት ፡ ከሰማይ በሚዘንብ ቦንብ ታረሱ ፡ ሀያላኑ ሀገራት 29 ሺህ 199 ጊዜ እየተመላለሱ ኢራቅን በአውሮፕላን ደበደቡ ።

26 ሚሊዮን ኪሎ የሚገመት ቦንብ የወረደባት ኢራቅ በአሳዛኝ ሁኔታ ወደመች ።
መቶ ሺህ ዜጎቿ ሞቱባት ።
......
ኢራቅ እንዳልነበር ሆነች ።
......
መሪዋ የነበሩትን አዛውንቱን ሳዳም ሁሴንን ፡ ለዛውም በበአል ቀን ፡ የአረፋ እለት በገመድ ሰቅለው ገደሏቸው ።
........
ይህ ከሆነ ከአመታት በኋላ ጆርጅ ቡሽ ብቅ ብሎ ፡ ኢራቅ የኒውክሊየር መሳሪያ እንዳላት የደረሰን መረጃ የተሳሳተ ነበር ሲል ቀለል አድርጎ ተናገረ ።
....
በወቅቱ የእንግሊዝ ጠ/ሚኒስትር የነበረው ቶኒ ብሌየርም ፡ የተሳሳተ መረጃ ተቀብለው በኢራቅ ላይ ስለተወሰደው እርምጃ ሲያስብ ፀፀት እና ሀዘን ይሰማኛል አለ ።
.....
ይህ ከሆነ አመታት አለፈ. .. ያቺ cradle of civilization ትባል የነበረችው ኢራቅ ብዙ አመታትን ወደኋላ ተመለሰች ።
እስከዛሬም ድረስ ከህመሟ አላገገመችም ።
.....
እንግዲህ ይህን ሁሉ ያደረጉ ሀገራት ዛሬም ኢራንን ሊበሉዋት ከበዋት ቆመዋል ።
የአለም አቀፉ አቶሚክ ኤነርጂ ሀላፊም ኢራን እንደምትሉት የአቶሚክ ቦምብ እየሰራች አይደለም ሲሉ ደጋግመው እየተናገሩ ነው ።
ግን ማንም ሊሰማቸው አይፈቅድም

አለም እንዲህ ነች ።
😢17060🤣10💔9🙈5👍4
"ግድባችን በህዝባችን ገንዘብ እንጂ በውጭ እርዳታ አልተሰራም" ሲሉ የውሀ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ ለትራምፕ ጽሑፍ ምላሽ የሚሆን በማህበራዊ ገጻቸው ላይ አስፍሯል።
🤣274🔥66👏47👍2015💯2
"ገንዘብ የለኝም ብለክ አትዘን
ማዘን ብቻ በቂ አይደለም
  ለቅሶም ጨምርበትና ወጥረክ ስራ 😂🤣"

👍የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ😁
🥰433😁145👍4115🔥12🫡10👏7
🙊ጣልያናዊ ዜግነት ያለው ሰርጂዮ ቦዲኒ ከ 115 የተለያዩ ሀገራት 1 ሺህ 444 የተለያየ ይዘት ያላቸውን ጋዜጦች በመሰብሰብ ስሙን በአለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ማስፈር ችሏል፡፡እንደ ቦዲኒ ገለፃ ጋዜጦችን መሰብሰብ የጀመረው ገና የ 10 አመት ታዳጊ እያለ ነበረ!!!😱
136🤯37👍18👏8😎4
‹‹የድመት ሰው እሸቴ››
(The Cat Man Eshete) የተሰኘ አዲስ ዘጋቢ ፊልም

የዓለም የስደተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ በኒውዮርክ ከተማ ለተፈናቀሉ ድመቶች የሚሆን ጊዜያዊ መጠለያ ያቀረበውን ኢትዮጵያዊ ስደተኛ እሸቴ እና ይህን ስራ እንዲሰራ ያደረገውን ሙሉ ታሪክ የሚያሳይ ዶክመንተሪ ፊልም ለዕይታ በቅቷል።

ይህም በአካዳሚ ሽልማት በእጩነት በተመረጠችው የፊልም ባለሙያዋ ላውራ ቼክዌይ የተሰራ ‹‹የድመት ሰው እሸቴ›› (The Cat Man Eshete) የተሰኘ አዲስ ዘጋቢ ፊልም ነው፡፡

"አንዳንድ ሰዎች ግድ የላቸውም። ቤት የለሽ ህይወትን ለማሸነፍ የምጥር ጎበዝ አድርገው ነው እኔን የሚያዩኝ" ሲል እሸቴ በዚህ ዶክመንተሪ ላይ ተናግሯል።

ኢትዮጵያዊው ስደተኛ እሸቴ በ1974 የጀመረውን የእርስ በርስ ጦርነት ሸሽቶ ከጎንደር ወደ ሱዳን የሄደ በመጨረሻም ወደ አሜሪካ አቀና ሰው ነው።

ይህ ዘጋቢ ፊልም ግን ስለ እሸቴ መሰደድ ብቻ ሳይሆን ምንም እንኳን እሼቴ በመኖሪያ ቤት እጦት ሲሰቃይ ቢቆይም፤ እሱ ተፈናቃይ ሆኖ ሳለ ለተፈናቀሉ ድመቶች ጊዜያዊ መጠለያን በመስራት ማሳደጉ የኢትዮጵያዊነትንና የሰው መሆንን ትርጉም በጉልህ ያሳያል፡፡

ከ10 ዓመታት በላይ ሲንከባከባቸው የቆዩት የእሸቴ ድመቶች፣ በህዝብ ስምና እሱ በሚያደንቃቸው ወይም በሚወዳቸው ቦታዎች እና ሀገራት ነው የተሰየሙት።

ከዚህም ውስጥ በአልበርት አንስታይል ስም የተሰየመ ድመት አለው፡፡ እሸቴ የመኖሪያ ቤት ድጎማ ቢኖረውም የድመቶቹን ደህንነት ለማረጋገጥ ሲል አብሯቸው ብዙ ቀናትን በጎዳና ላይ ያሳልፋል።

የፊልም ባለሙያዋ ላውራ ቼክዌይ፤ በዶክመንተሪው እሸቴ ዓለም ውስጥ የገቡት በራሱ ዓይን እና በራሱ አንደበት የመረጠውን ታሪክ በማካፈሉ እንደሆነ አንስታለች።

ፊልሙን ሰርቶ ማጠናቀቅ ቀላል እንዳልነበር የምትናገረው ላውራ ቼክዌይ፤ ቀረጻ በሚደርግበት ወቅት እሸቴ ሞባይል ስላልነበረው በስፍራው መኖሩን በእግር እየሄደች ስታረጋግጥ እንደነበር ተናግራለች፡፡

ለእሸቴ ደግሞ ታሪኩን በዓለም ላይ ማውጣቱ በጣም የተደሰተበት ጉዳይ ነው።

"ይህ አንዳንድ የህይወቴንና የስደት ጉዞዬን ያሳያል። በዚህም ለምወዳቸው ድመቶቼ እና ለምወዳት ውብ እናት ሀገሬ ኢትዮጵያ ያለኝን ፍቅር ለመግለጽ እድል አግኝቻለሁ" ሲል ለኦኬይ አፍሪካ ተናግሯል።

ሁሉም ከፍቅር የመነጨ እንደሆነና የልጅነት ጊዜውም በፍቅር እና ደስታ የተሞላ መሆኑን ይገልፃል።

በልጅነቱ ጎረቤቶቹ ሁሉንም ነገር ተሳስቦና እስከ ቁራሽ እንጀራ ድረስ ተካፍለው ሲበሉ እንደነበር ያስታውሳል።

ድመቶቹን አሰባስቦ የመንከባከብ ስሜቱም የመጣው ከዚህ ነው፡፡
“መንከባከብ ተፈጥሮዬ ነው፤ ይህንን ደግሞ እናቴም ታውቃለች፣ እኔ ስለ ሌሎች መስዋዕትነት እከፍላለሁ ቤተሰቦቼ ተፈጥሮዬን በትክክል ያውቃሉ። ይህ መቼም አይለወጥም“ ሲል ገልጹዋል፡፡

እሸቴ በሱዳን የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ለአምስት ዓመታት ኖሯል፤ በዚህ ጊዜ በተስፋ ማጣት እና በቤተሰብ ናፍቆት ብዙ ጨለማ ቀናትን አሳልፏል።

እሸቴ የስደት ጉዞውን ለመግለጽ የተጠቀመው ቃል “የምድር ላይ ሲኦል” የሚለውን ነው። እያንዳንዱ ሰከንድ አደገኛና በማንኛውም ጊዜ ምን ሊፈጠር እንደሚችል እንደማይታወቅ ገልጿል።
123👍14🔥4❤‍🔥2🥰2👏2🙏1
ከሰሞኑ በህንድ ሀገር የሚገኝ አንድ የተኩላ እና ልዩ የሆነ የካውሺያን ሼፐርድ ድቅያ የሆነውን ውሻ በዓለማችን ውድ በሆነ ዋጋ ተሸጧል።

ይህን ውሻ የገዛው ሰው ውሻ የሚያረባ እና በዓለም ላይ ከሚገኙ ብርቅዬ ከ150 በላይ ውሻዎችን በመሰብሰብ ይታወቃል።

ሳቲሽ እንደተናገረው  ከሆነ ለዚህ ውሻ ያወጣው 5 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር እንደሚገባው ተናግሯል።

ከዚህ በተጨማሪም ይህ ውሻ አስደናቂ የሆነ ዝርያ ያለው መሆኑን እና ገና በ 8 ወሩ 75 ኪሎግራም የሚመዝን እንዲሁም  76 ሴንቲ ሜትር እንደሚረዝም ተናግሯል።

ውሻው ብዙም የሚገኝ ዓይነት ዝርያ አደለም  ያለው ባለቤቱ ስታየው ራሱ ተኩላ ነው የሚመስለው። ይህ ዝርያ ከዚህ በፊት በዓለም ላይ ተሸጦ አያውቅም ብሏል።

(Oddity centeral)
ለአንድ ውሻ ይህን ያህል ዋጋ መውጣቱ ተገቢ ነው ብለው ያስባሉ? ሀሳብዎን ቢያጋሩን👍
👍54🙉3931🤯13🙈5🫡2
🤯 Daniel Tammet የተባለው ግለሰብ የሚያስደንቅ አእምሮ ባለቤት ሲሆን ተፈጥሮ በ እንግሊዘኛ high-functioning autism and the savant syndrome. የተባሉ ነገሮችን የሰጠጭጕ ሲሆን Daniel Tammet 22514 የ pi ዲጂቶችን በ 5 ሰአት ከ 9 ደቂቃ ማስታወስ የሚችል ከመሆኑም በተጨማሪ 11 ቋንቋዎችን መናገርም ይችላል😱
😱113👍2923👏12🤯5🙏3
ስለ Sapio ሰዎች እናውራ Sapiosexuality means that a person is sexually attracted to highly intelligent people

sapio ሰስለሆኑ ሰዎች ስናወራ ምሳሌ ማድረግ የምንችላቸው ብዙ ሰዎች ይኖራሉ በእድሜም በብዙ ነገር የማይገናኙ ምኗን ወዶ ወዳ ነው የምንላቸው ጥንዶች ይኖራሉ ብዙ ግዜ ወደ አይምሯሯችን የሚመጣው financially የሆነ ገንዘብ ስላለ ሊመስለን ይችላል ይሄ ግን ልክ አደለም

ለዚ ምሳሌ ያመጣሁላቹ የፈረንሳዩን ፕሬዝዳንት ነው ባለቤቱ በእድሜ በሃያ አምስት አመት የምትበልጠው የሰባ አመቷ የቀድሞ መምህርቱ ናት

President of France Emmanuel Macron his wife Brigitte Macron

ለሳፒዮ ሰዎች A person's physical attraction means nothing if they don't have a beautiful mind ጥሩ ጭንቅላት አይምሯቸውን የሚያነቃቃ እውቀት የሌለው ሰው ውበት መልክ ቁመናው ዴንታቸው አይሆንም በተቃራኒው ቻሌንጅ የሚያደርጋቸው እውቀት ያለው ሰው ምንም ሊሆን ቢችል እድሜው አቋሙ ሳያስቡት ያንን ሰው ያፈቅራሉ የነሱ መስፈርት intelligent Sapiosexuality refers to those who are attracted to another person's intelligence and believe this to be their most attractive quality
78😁29👍6🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🚀ወባ የሚያክለው ድሮን‼️

የቻይና ወታደራዊ ኃይል የወባ ትንኝ የሚያክል ድሮን አስተዋውቋል‼️

ገንቢዎቹ እንዲህ ዓይነቱ ድሮን ለመለየት ፈጽሞ የማይቻል በመሆኑ ለመረጃ መሰብሰቢያ ተስማሚ ነው ብለዋል።በተጨማሪም እንደ ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘገባ ከሆነ፣ ድሮኑ ለድብቅ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች እና ስለላ እንደሚውል ተገልጿል

Join @amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🤯13537😁12🫡11😱9👏6👍1🙏1
የኖርዝሮፕ ግሩማን ቢ-2 ስፒሪት ስውር ቦምብ

🛩️ B-2 spirit ምንድን ነው?

B-2 spirit በአሜሪካ አየር ኃይል የሚጠቀመው ወታደራዊ አውሮፕላን ነው። በጠላት ራዳር ሳይታይ ለመብረር የተነደፈ በመሆኑ ስውር ቦንበር ይባላል።

1. የሚበር ክንፍ ቅርጽ

ጭራ የሌለው ትልቅ ጠፍጣፋ ትሪያንግል ይመስላል።

ይህ ቅርፅ አየሩን በተቃና ሁኔታ እንዲቆርጥ እና ከራዳር እንዲደበቅ ይረዳዋል ።

2. ድብቅ ቴክኖሎጂ

B-2 የራዳር ምልክቶችን በሚወስዱ ልዩ ቁሶች የተሸፈነ ነው፣ ይህም ለእይታ የማይታይ ያደርገዋል።
በሙቀት ሴንሰሮች ወይም ራዳር ላይ እንዳይታዩ ሞተሮቹ እንኳን በውስጣቸው ተደብቀዋል።

3. ረጅም ሬንጅ

ነዳጅ ሳይሞላ በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎሜትር ሜትሮችን ይበርራል ይህም ማለት ወደ ጠላት ግዛት ዘልቆ safely መመለስ ይችላል።

4. ክሩዉ

በB-2 የሚበሩት ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው እሱም ፓይለት እና ሚሽን ኮማንደር!

🦅 Inspired የሆነው በተፈጥሮ ነው
ለስላሳ የበረራ ቅርፁ - inspired የሆነው ከ ጭልፊት ወይም falcon ከተባለው ወፍ ነው።በአየር ውስጥ በብቃት እንዲንሸራተት እና ተደብቆ እንዲቆይ ይረደዋል - ይህ biomimicry ይባላል።
102👍22🔥13👏1🙏1
በአንድ ፔንሲዮን አልጋ ይዘው የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወታቸዉ ማለፉ ተገለፀ

ትላንት ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 9:05 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 6 ሳሪስ በአንድ ፔንሲዮን በተነሳ የእሳት አደጋ የ30 ዓመት ወንድና የ25 ዓመት ሴት በጭስ ታፍነው መሞታቸው ተገልጿል።

⚫️ለጓደኛዬ ስነግረው "ደስታና ሀዘን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው" ብሎኛል

Join @amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁233😢8320🤣19🤯7🤷‍♂4
ካሜሩን ዲያዝ ትባላለች። አሜሪካ ውስጥ ስመጥር ከሚባሉ ሰዎች ተርታ የምትሰለፍ ናት። ተዋናይት፣ፀሐፊ፣ስራ ፈጣሪ እና ሞዴሊስት ናት።

እና እቺ ስመጥር፣ሀብታም ሴት በህይወቷ ሜካፕ የሚባል ፊቷን አስነክታው አታቅም። ለምን እንደሆነ ስትጠየቅም የኔ ያለሆነውን ወጣትነት ከማየው፣የራሴን እርጅና ባየው እመርጣለሁ ነበር ያለችው።

ዛሬ ላይ 53 አመቷ ቢሆንም እንደሚታየው ግርማሞገስ ያላት ወይዘሮ ናት።
👏34961🔥14😘12👌7😁6🙏4👍3🫡3
የአየር ሀይል አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ
🤣766😁40👍2814🤯10🫡9🙊6😎4😨3🆒2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
‼️ በዙሪያዎ እየተከናወኑ ስላሉ ጉዳዮች የራስዎን አስተያየት ይያዙ። ምልከታዎችን አንጭንም፣ እውነት አናዛባም፣ ሃስተኛ ዜናዎችን እናሰራጭም፤ የተሟላና ትክከለኛ መረጃ ብቻ።

🇪🇹🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም ዙሪያ የተሰሙ ዜናዎች፤ በጉምቱ ተንታኞች የሚቀርቡ ሙያዊ አስተያየቶች እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች።

ስፑትኒክ አማርኛ፤ ያልተነገረዎትን መንገር ጀምሯል!

👉 https://www.tg-me.com/+jEoyKtlGMNlmMWUy
18👍1
❤️⚽️❤️⚽️⚽️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😢29638❤‍🔥5😁2🙏1💔1
2025/07/14 21:47:05
Back to Top
HTML Embed Code: