Telegram Web Link
በወጣትነቱ፣በስራዉ መባቻ አንድ ወጣት ወላጆቹ የኢንሱሊን መግዣ በማጣታቸው ሲሞት ያየው ዶ/ር የኔ የምቾት ህይወት ይቅርብኝ አለ።

ግብፃዊው ዶ/ር ሙሀመድ ማሻሊ የደሀዎች ዶክተር።

ለአስርት አመታት በአንድ ትንሽየ ክሊኒኩ ሀቅም ካላቸው በጣም ተመጣጣኝ ክፍያ፣ከሌላቸው ደግሞ በነፃ እያከመ ስጋዊ ፍላጎቱ ሳያሸነፈው ህዝቡን እያገለገለ ኖረ።

አብረውት በዶ/ርነት የተመረቁት ቅንጡ ቪላ ውስጥ ሲኖሩ አሱ ግን ቤቱንም ክሊኒኩንም አንድ ላይ አድርጎ ለአመታት ህዝቡን እያገለገለ ይገኛል።

"ህክምና ማግኘት ሰብዓዊ መብት ነው።" የሚለው ዶ/ር ሙሃመድ አውነተኛ ሀብት በገንዘብ ሳይሆን ለሌሎች በኖርነው ልክ መሆኑን አሳይቶናል።

#inspiration #healthcare #humanity
የዛሬው የአለም መነጋገሪያ ፍቶ
አንዳንዴ በልቦለድ ጅግና ሁነው የሚተውኑ ሰዎች በውኑ ዓለምም ጀግንነታቸውን ይደግሙታል።

ባት ማንን ሁኖ የተወነው ክርስቲያን ቤል ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት እህትና ወንድሞቻቸውን ማጣት የለባቸውም በሚል ወላጆች የሞቱባቸው ወንድማማቾች ወይም እህትና ወንድሞች አንድ ላይ የሚያድጉበት መንደር በ22 ሚሊየን ዳላር ካሊፎርኒያ ላይ ገንብቷል።

"አስቡት እስኪ ህፃናቱ ወላጆቻቸውን ማጣታቸው ሳያንስ እህትና ወንድሞቻቸውን በተለያዩ ማሳደጊያ ድርጅቶችና ጉዲፈቻዎች መበታተናቸው የሚፈጥርባቸውን ጭንቀትና ብቸኝነት" ያለው ቤል በተቻለን መጠን ይህን ችግር ለመቅረፍ እንሰራለን ብሏል።

በምናብ አለም ያለ ጀግንነት የመንፈስ እርካታ አይሰጥምና ስምና ዝና ያላችሁ የሀገራችን ታዋቂ ሰዎችም ከቤል ልምዱን ወስዳችሁ በሀገራችን ካሉ መልከ ብዙ ችግሮች ውስጥ ያቅማችሁን ብታቃልሉ ከዝናው ጋር አብሮ ማይጠፋ ስም ትተክላላችሁ።

#ChristianBale#መልካምነትለራስነው
ለጠቅላላ ዕውቀት

በዓለም ላይ ዋጋው እጅግ ውድ ነው የሚባለው ፈሳሽ የጊንጥ መርዝ ነው። ከአልማዝና ዕንቁ የበለጠ ውድ ነው። Yellow Mediteranian see Scorpion (ቢጫ የሜዲቴርያን ባሕር ጊንጥ) የሚያመነጨው መርዝ አንዱ ሌትር እስከ 10 ሚሊዮን € ድረስ ይሸጣል። በነገራችን ላይ መርዙ ጭራው ላይ ነው ያለው።
ይህን ያውቃሉ

የኳታሩ ንጉስ ሼክ ተሚም ቢን ሀሚድ አልታኒ. . ለሜሲ የሰጡት የክብር ልብስ. .ጥለቱ ( ፍሬሙ ) . ከንጹህ ወርቅ የተሰራ ሲሆን ፡

ዝም ብሎ የሚሰጥ ሳይሆን
ለንጉሳውያን ቤተሰቦችና  እጅግ በጣም ለሚያከብሯቸው ሰወች ፡ " አንተ ከኛ መሀል አንዱ ነህ " ለማለት የሚሰጡት ትልቅ የክብር ሽልማት ነው ።


@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ይህ የ12 አመት ታዳጊ እምባው እንደጎርፍ የሚወርደው ሙዚቃው የሚያስለቅስ ሁኖ ሳይሆን ህይወቱን ከመከራ ያወጣው ሙዚቃ ያስተማረው የተሻለ ህይወት እንዲኖር ያደረገው ሰው ሞቶበት ነው።

መምህሩ ተስፋ ያልነበረውን ዲዮጎ ፍራዛዎ ብራዚል ውስጥ ማፊያዎች በብዛት ከሚኖሩበት የተጎሳቆለ ሰፈር ውስጥ ጎዳና ላይ አንስቶ ተስፋ እንዲኖረው አደረገ።

ነገር ግን የሱን ህይወት የታደገው ሰው ሂወቱ አለፈች። በዚህን ሰዓት በቀብር ስነስርዓቱ ላይ ሙዚቃ እንዲያቀርቡ የሟች ተማሪዎች መድረክ ላይ ሲወጡ ከሌሎች ተማሪዎች በተለየ ውለታውን ያረሳው ታዳጊ ስሜቱን ከቫዮሊኑ በላይ በእንባው ሲገልፅ የብዙዎች ስሜት ተነካ።

መልካምነት በሰዎች ልብ ላይ የሚታተም ዘላለማዊ ቅርስ መሆኑን ክፉና ደጉን በቅጡ የማያውቀው ታዳጊ ለዓለም አሳየ
ይህ አቡ ፋኑስ ይባላል ይህ ሰው ሳይሆን ሰይጣን ወይም ጂኒ ነው∎ የሚገኘውም በሳዑዲ በረሀ ላይ እንዲሁም በሊቢያ በረሀ ላይም ይገኛል

☑️∎ ትንሽዬ ጭላንጭል መብራት በማሳየት ሰዎች እንዲከተሉት ያደርጋል! ነገር ግን በዚህ ወጥመድ ወድቆ መብራት መስሎት ለተከተለው ሰው መጨረሻው የሚያምር አይሆንም
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የሳይንስ ፊክሽን ሊመስል ይችላል ነገር ግን አውነት ነው።

ይህ ኔዘርላንዳዊ የጉልበት ቀዶ ጥገና አድርጎ ሲነቃ የአፍ መፍቻ ቋንቋውን ሙሉ በሙሉ ረስቶ ሁለተኛ ቋንቋው የሆነውንና ት/ቤት ብቻ የሚጠቀምበትን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቻ ነበር የሚናገረው። አሜሪካ እንዳለም ነበር የሚያስበው። አንድም የደች ቋንቋ ቃል የማያውቅ ሲሆን ቤተሰቦቹንም ማስታወስ አልቻለም።

መጀመሪያ ላይ ዶክተሮች ማደንዘዣው የሚያቃጀው መስሏቸው ነበር ነገር ግን ልጁ በዛው በመቀጠሉ

በአለም ላይ እስካሁን በ9 ሰዎች ላይ ብቻ የተከሰተው Foreign Language Syndrome (FLS) - መሆኑን ተረድተዋል። ትክክለኛው ምክንያት ባይደረስበትም የማደንዘዣ ጎንዮሽ ጉዳት ሊሆን እንደሚችል ዶክተሮች ገምተዋል
ይህ የሲጃራ ማጨስ መዘዝ ነው 😱

እኒህ ጄኔ እና ሱዛን የተባሎ ሴቶች መንትያ ናቸው።

ነገር ግን ጄኔ በፍፁም አጭሳ አታቅም። በተቃራኒው ግን ሱዛን ለ16 አመታት አጭሳለች።

እና አሁን ላይ በመሀከላቸው የ10 አመት ልዩነት ያለ ነው ሚመስለው።

ተመልከቱ የአኗኗር ዘይቤያችን ምን ያክል ህይወታችን ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ!

የሚያጨሱ ሰዎች እንዲያቆሙና ጤናማ ህይወት እንዲኖሩ ይህንን መልዕክት ሼር እናድርግላቸው🙏🙏🙏
ልብ ሰባሪው አደጋ ወደ ማይታመን ተስፋ ተቀየረ።

ሎሪ እና ክሪስ ሶስት ህፃን ልጆቻቸው(ሁለት ሴቶች አንድ ወንድ) በአሰቃቂ የመኪና አደጋ ሲሞቱባቸው ሰማይ የተደፋባቸው ያክል ነበር ተስፋ የቆረጡት

ይሁን እንጅ በአመቱ ፈጣሪ እራሱ ነው የልጆቻችንን ምትክ የሰጠን ብለው የሚያምኑበትን በሶስት መንታ ልጆች ተባረኩ(ሁለት ሴት አንድ ወንድ)

አሁን ላይ ጥንዶቹ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩ፣ የህግ መአቀፎች እንዲሻሻሉ የግንዛቤ ስራ የሚሰሩ ሲሆን ብዙ ለውጦች እንዲመጣም አድርገዋል።

ፈጣሪ ሁሌም አጠገባችን ነውና ልባችን በተሰበረ ሰዓት እሱን ተስፋ እንናድርግ።
ፕሮፌሰር ፒ.ኤል.ኦ. ሉሙምባ ስለ ሙስና እና ተጠያቂነት በተለያዩ የአለም ክፍሎች ያለውን ልዩነት እንዲህ ሲሉ ገልጸውታል፦

- ጃፓን ውስጥ አንድ ሙሰኛ (ባለስልጣን) ስህተቱን ሲያምን ራሱን ያጠፋል። (ይህም የክብር እና የሃላፊነት ስሜትን ያሳያል)።
- ቻይና ውስጥ ሙሰኛ ከተገኘ ይገደላል። (እዚያም ቅጣቱ እጅግ ከባድ ነው)።
- አውሮፓ ውስጥ ደግሞ ሙሰኛ ይታሰራል። (የህግ የበላይነት የሚከበርበት ሥርዓት አለው)።
- አፍሪካ ውስጥ ግን ሙሰኛ ለምርጫ ይወዳደራል። (እናም አንዳንድ ጊዜ ይመረጣል!)🤔
ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊነትን ለወላይታ ዲቻ እንዲመልስ በፌደሬሽኑ ተወሰነ::

I የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የታገዱ ተጫዋቾችን በማሰለፍ ያሸነፈው የኢትዮጵያ ዋንጫ በፎርፌ ተሸናፊ ሆኖ ዋንጫው ለወላይታ ድቻ ተመላሽ እንዲደረግ ተወስኗል።

#ስፖርት #FastMereja
የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ የነበረው የሲዳማ ቡና ቡድን ተጫዋቾች እና ኮችንግ ስታፍ ትናንት ለ17 ቡድን አባላት በሀዋሳ ከተማ ለእያንዳንዳቸው 200 ካሬ ሜትር ቤት መስሪያ መሬት ርዕሰ መስተዳደሩ መሸለማቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ፌዴሬሽኑ ዋንጫውን ለወላይታ ዲቻ በመስጠቱ ሽልማታቸው እንዴት ይሆናል በማለት በርካቶች እየጠየቁ ሲሆን ሽልማቱን አስመልክቶ ክልሉ እስካሁን ያለው ነገር የለም።
ይህን ሰው ተዋወቁት👆👆

ብሃራት ጄን ይባላል አለም ላይ አሉ ከሚባሉ ሀብታሞች ተርታ ይሰለፋል ያለው የሀብት መጠን በእኛ ወደ 140 ሚሊዮን ብር እንዳለው ይገመታል።

ታዲያ ጄን ይሄንን ሁሉ ሀብት ያካበተው በትምህርት ወይ ባለው የእጅ ሙያ እና ተሰጥኦ አሊያም ደግሞ በውርስ ወይም ሎተሪ ባለ እድለኛ ሆኖ አይደለም። የዚህ ሁሉ ሀብት መሰረቱ ለ40 አመታት ሳያቋርጥ በሞምባይ ጎዳናዎች ላይ እየለመነ ባገኘው ገንዘብ ነው

ጄን ሲናገር በቀን እስከ 2,500 ሩፒ(3220 ብር) እንዲሁም በወር እስከ 75000ሩፒ(120ሺህ ብር) በልመና ብቻ እንደሚያገኝ ለህንድ መገናኛ ብዙሀን አሳውቋል።

ልመናን የገቢ ምንጩ ያደረገው ጄን አሁን ላይ የራሱ 2 አፓርታማ እና የተለያዩ የንግድ ሱቆችን የከፈተ ቢሆንም አሁንም መለመን ማቆም እንደማይፈልግ እና በተለያዩ ከተሞች ላይ እየተዟዟረ መለመን እንደሚፈልግ ተናግሯል።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
እንግሊዘኛን በመማር ያለህን እውቀት ማስፋት ትፈልጋለህ?

እንግዲያውስ ይህ ቻናል ላንተ ነው Join በል እና ፈታ ብለህ ተማር!👇

JOin 👉 @EnglishLearn_Ethiopia
ፊሊፒንስ 7,641 ደሴቶችን ያቀፈ ነው። በእያንዳንዳቸው ላይ አንድ ቀን ካሳለፍክ ሁሉንም ለመጎብኘት ወደ 21 አመታት ሊወስድብህ ይችላል።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
2025/07/04 12:27:40
Back to Top
HTML Embed Code: