በTheory ደረጃ በአለማችን ላይ ያሉ ሸረሪቶች 🕷️ ተርበው በፕላኔታችን ላይ ያለውን እያንዳንዱን ሰው በሙሉ አድነው ቢመገቡን አሁንም ረሀባቸውን አናስታግስላቸውም
ተመራማሪዎች እንደሚገምቱት የአለም የሸረሪት በየዓመቱ ከ400-800 ሚሊዮን ቶን አድኖ ይመገባል። ለማነፃፀር ያህል በምድር ላይ ያለው የሰዎች አጠቃላይ ክብደት 287 ሚሊዮን ቶን ነው። ስለዚህ በTheory ሸረሪቶች ከፈለጉ አለም ላይ ያሉትን ሰዎች ቢበሉ አይጠግቡም ነው😁 በእርግጥ በተፈጥሮ ሸረሪቶች ሰዎችን አድኖ የመብላት ፍላጎትም ተፈጥሮም የላቸውም እናም ጭራሽ በተቃራኒው የእነሱ አስፈሪ ፍጥረቶች አድርገው ነው እኛን የሚቆጥሩት 🕸️
@Amazing_fact_433

🤯102❤40😁31😱7🙏6👍3✍1
ልጁን በአትላንቲክ ውቅያኖስ ከመስመጥ ያዳነው የዓመቱ ምርጥ አባት
ዲዝኒ ድሪም በመዝናኛው ኢንደስትሪው ዘርፍ ትልቅ ስም ያለው የዋልት ዲዝኒ ንብረት የሆነች በዓለማችን ከሚገኙ 10 ግዙፍ የመዝናኛ መርከቦች መካከል የምትገኝ መርከብ ናት።
1 ሺህ 448 የሚሆኑ የመርከቧ ሠራተኞችን ሳይጨምር 4 ሺህ ሰዎችን የመያዝ አቅም ያላት ዲዝኒ ድሪም ከግዙፍነቷ የተነሳ አጠቃላይ የመርከቧ ስፋት ሶስት የእግር ኳስ ሜዳ ያህላል።
መርከቧ ወደላይ 14 ፎቅ ያላት በውስጧም ከ2 ሺህ በላይ ክፍሎችን የያዘች የቅንጦት መርከብ ናት።
በዚህች መርከብ በየሳምንቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በውቅያኖስ ላይ እየተጓዙ የረፍት ጊዜያቸውን የሚያሳልፉ ሲሆን፤ ከሶስት ቀናት በፊት እሁድ ዕለት የተከሰተው ሁኔታ ግን ትንሽ ለየት ያለና የታላላቅ ሚዲያዎችን ትኩረት የሳበ ነበር።
በዕለቱ ከባሃማስ ደሴት ወደ ፍሎሪዳ በምትጓዘው መርከብ ከትንሽ ልጁ ጋር ለመዝናናት አስቦ የተሳፈረ አንድ አባት 4ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው የመርከቡ ክፍል ላይ ሆኖ ፎቶ መነሳት የፈለገችው ልጁን ፎቶ እያነሳት ነበር።
በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ የ6 ዓመት ሴት ልጁ የተደገፈችው የመርከቡ ብረት አዳልጧት ወደታች ወደቀች።
በዚህ ጊዜ ልጁን መውደቅ የተመለከተው አባት ለሰከንድ ሳያመነታ ወደ ውቅያኖሱ የወደቀች ልጁን ለማዳን ወደ ቀዝቃዛው የውሃ አካል ተወረወረ።
መርከቧ ውስጥ ያሉት ሰዎች በድንጋጤ ተውጠው መጯጯህ ጀመሩ፤ ወዲያውም የመርከቧ የአደጋ ጊዜ ደወል ተደወለ።
ግዙፏ መርከብ በድንገተኛው ክስተት ምክንያት ባለችበት እንድትቆም ተደርጎ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አነስተኛ ጀልባቸውን በመያዝ የነብስ አድን ሥራቸውን ጀመሩ።
ከደቂቃ በኋላም የመርከቧ ሕይወት አድን ሠራተኞች ባለችው ትንሽ የዋና ችሎታ ልጁን ከመስመጥ ታድጎ ለ20 ደቂቃዎች እርዳታ ሲጠባበቅ የቆየውን አባት አግኝተው ከነልጁ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ወደ መርከቧ መልሰዋቸዋል።
ይህ ዜና እንደተሰማም ልጁን በውቅያኖስ ውሃ ከመስመጥ ያዳነው አባት የዓመቱ ምርጥ አባት የሚል ስያሜ አግኝቷል።
ጥቂት ነጥቦች ስለ ዲዝኒ ድሪም፦
57 ሜትር ርዝመት ያላት ዲዝኒ ድሪም የቅንጦት መርከብ 10 ሚሊዮን ኪሎ ግራም ክብደት ያላት ሲሆን፤ ይህ ክብደቷ ከ1 ሺህ 400 የተማሪዎች አውቶቡስ ጋር የሚመጣጠን ነው።
ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለው የዚህች መርከብ ቁመት 340 ሜትር ሲሆን፤ ይህም ከ3 የእግር ኳስ ሜዳዎች ይረዝማል።
መርከቧ ወደላይ 14 ፎቅ ያላት ሲሆን፤ ከዲዛይን ጀምሮ በአጠቃላይ 900 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደወጣባት ይገመታል።

❤140👍13👏11🤯5🙏2🔥1
የድመቶችን ድምጽ በቅጽበት የሚተረጉም አዲስ የኤአይ ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ
አዲስና መሰረታዊ የሆነ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ሲስተም የድመቶችን "ሚያኦ" ድምጽ በቅጽበት እስከ 95% ትክክለኛነት የመተርጎም ችሎታ አለው ተብሎለታል።
ይህ ታላቅ ግኝት ሰዎች ከድመቶቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በእጅጉ ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል ነው የተባለው።
ተመራማሪዎች የድመቶችን የድምጽ ምልክቶች በመተንተን "እርቦኛል"፣ "ትኩረት እፈልጋለሁ" ወይም "ደስተኛ ነኝ" የመሳሰሉ መልዕክቶችን ለመለየት የሚያስችሉ ስልተ ቀመሮችን (algorithms) አዘጋጅተዋል።
የቀድሞ የአሌክሳ (Alexa) ኢንጂነሮች የፈጠሩት "MeowTalk" የተሰኘው መተግበሪያ (app)፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የድመት ድምጾችን በማቀናበር 11 የተለያዩ የድመት ስሜቶችን ለይቶ ማወቅ ችሏል ነው የተባለው።
የአሁን ጊዜ ምርምሮች እንደሚያመለክቱት፣ በቀጣይ እስከ 40 የሚደርሱ የተለያዩ የድመት ድምጾችን መለየት የሚቻልበት ጊዜ ቅርብ ነው ተብሏል።
ለ12,000 ዓመታት ከድመቶች ጋር አብሮ ከኖሩ በኋላ፣ ይህ ቴክኖሎጂ የድመቶችን ቋንቋ ለመረዳት የሚያስችል ትልቅ እርምጃ ነው ተብሎለታል።
የኤአይ ሲስተሙ የሚሰራው የድመትን ድምጽ ወደ ምስላዊ "የድምጽ ካርታዎች" በመለወጥ ነው። ከዚያም እነዚህን ካርታዎች ምስሎችን በሚረዳበት መንገድ በመተንተን ወደ ትርጉም ይለውጣቸዋል ነው የተባለው።
ይህ ቴክኖሎጂ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ፣ የድመት ባለቤቶች የቤት እንስሶቻቸውን ፍላጎትና ስሜት በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ ይረዳቸዋል። ምንም እንኳን የሰው ቋንቋዎችን ለመተርጎም የሚያገለግሉ እንደ "አቢሲኒካ ኤአይ" (Abyssinica AI) ያሉ የአገር ውስጥ የኤአይ ሲስተሞች ቢኖሩም፣ የእንስሳት ድምጽን የሚተረጉም ቴክኖሎጂ ግን አዲስ እና አስደሳች ነው ተብሏል።
ይህ ግኝት በእንስሳት ደህንነት፣ በእንስሳት ህክምና እና በቤት እንስሳት ባለቤቶች እና በጓደኞቻቸው መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር አዲስ እድሎችን ይከፍታል ነው የተባለው።
#menah

😁79❤38👍7🤯3😨3🔥2🙏2
🚨ከወደ እግር ኳስ አለሙ አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል
ተወዳጁ ፖርቹጋላዊው የሊቨርፑሉ አጥቂ ዲዬጎ ጆታ በመኪና አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል💔
ለረጅም አመት በፍቅር ሲጠብቃት ከነበረችው ፍቅረኛው ጋር ከተሞሸረ እንኳን እኮ ሳምንት አልሞላውም😢
የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት ከሆነ ጆታ በስፔን አብሮ እግርኳስ ተጫዋች ከሆነው ወንድሙ አንድሬ ጋር አብረው በሚጓዙበት ጊዜ ከባድ አደጋ እንዳጋጠማቸው እና ወዲያው ሁለቱም ተጫዋቾች ህይወታቸው ወዲያው እንዳለፈ ነው እየዘገቡ ያሉት
ያንን ምትሀተኛ እግሮቹን ለተከላካዮች ራስ ምታት በማንኛውም የገለልተኛ ደጋፊዎች ሳይቀር የሚወደደው ተጫዋች አይተን ሳንጠግበው ላይመለስ ተለይቶናል ፈጣሪ ከእንደዚህ አይነት ድንገተኛ አደጋ ይሰውረን🙏
እኛም በቻናላችን ስም ለቤተሰቡ ፣ ለሊቨርፑል ደጋፊ እና ለእግርኳስ አፍቃሪው በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን R.I.P😢

😱253😭111❤54😨14🙏12👍7🤯5😁2🥰1
ሞተራቸው ተነስቶ ከፍተኛ ፍጥነት ላይ ለመድረስ የሚፈልጉት ጥቂት ሰከንዶችን ነው። ከፍተኛ ፍጥነት ስንል ደግሞ ከ 310 ኪሜ እስከ 325 ኪሜ በሰዓት ማለት ነው። ከቆሙበት በአንዴ 100 ኪሜ በሰዓት ፍጥነት ላይ ለመድረስ የሚፈልጉት ከ3 ሰከንድ ያነሰ ጊዜ ነው።
በጣሊያኑ መኪና አምራች ላምቦርጊኒ የሚመረተው ይሄ መኪና ባለ አስር ሲሊንደር ሲሆን ሞተሩ ሲነሳ በራሱ የተለየ የራሱ የሆነ ግርማ ሞገስ ያለው ድምፅ ያወጣል። አቅሙ በፈረስ ጉልበት ከ572 እስከ 630 የሚደርሰው ይህ መኪና እስከ ሰባት ማርሽ ያለው ሲሆን አሁን ባለው የአለም ገበያ እንደየ ሞዴሉ ከ230,000 ዶላር እስከ 350,000 ዶላር የሚሸጥ ነው። በኢትዮጵያ የባንክ ምንዛሪ ከ32 ሚሊዮን እስከ 50 ሚሊዮን ድረስ ማለት ነው።
ከስር በተቀመጡት ሁለት ፎቶዎች ላይ ልዩነት ያመጣችው አንድ የ500 ዶላር ጎማ ናት።
~
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭231❤70🙏5👍4🤝2
ድሮ ትዝ ይላችኋል?! ምርጥ ስልክ ሲባል አንደኛ ኖኪያ ነበር የሚመጣልን። ያኔ ኔትወርኩ አንደኛ ነበር። አሁን ጭራሽ ከዝርዝሩ ውስጥም የለ። ከቁጥርም አይገባ😭😭😭 ሳምሰንግ ግን ቀሽም ነበር ያኔ። ሳምሰንግ ልክ እንደ ዘፋኟ ትእግስት በቀለ መልክ ብቻ የሆነ ስልክ ነበር🤣🤣🤣
ከ20 አመት በፊት ኖኪያ ትልቅ ካምፓኒ ነበር። ከአለም የስልክ ገበያ 40% ድርሻ በኖኪያ የተያዘ ነበር።
ታዲያ አዲስ ቀን እየነጋ መሆኑን ያላወቁት የኖኪያ ካምፓኒዎች እንቅልፋቸውን ለጥ ብለው ተኝተው ነበር። እነሱ ተኝተው አለም እየተለወጠች ነበር።
ኖኪያ ጃቫ ላይ እንዳንቀላፋ፣ አፕል አይኦኤስ፣ ጎግል ደግሞ አንድሮይድ ፕላትፎርምን እየፈበረኩ ነበር። አለም እየተለወጠ ነበር። ስማርትፎን ገበያውን እየተቆጣጠረ ነበር።
ኖኪያዎች ከእንቅልፋቸው ሲነቁ አለም ተለውጦ ጠበቃቸው። የማያውቁት እንግዳ አለም ሆነባቸው። የገበያ ድርሻቸውን አጥተው ነበር። ምንም ወደ መሆን ደርሶ ነበር።
ታዲያ ያኔ የኖኪያ ማናጀር ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ሰራተኞቹ በለቅሷቸው አጀቡት። አሁን ግን በጣም ረፍዷል። ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ ነው ነገሩ።
አለማችን ፈጣን ለውጥ ውስጥ ናት። በየቀኑ አዳዲስ ነገሮች ይፈለሰፋሉ። ዛሬ አዲስ የነበረው ነገ አሮጌ ይሆናል። ከፈጣኑ ለውጥ ጋር አብሮ መለወጥ ካልተቻለ፣ እጣ ፈንታችን እነደ ኖኪያው ማናጀር ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ነው።
ከእለታት አንድ ቀን ኖኪያ ታላቅ ካምፓኒ ነበር። ዛሬ ግን ታሪክ ሆኗል።

❤218😁18👍15😨10🤯8😭5🙏4🤝3🔥1
አለምን የለወጡት ታዋቂ "ውድቀቶች"!
🔸 ቶማስ ኤዲሰን ከአራት ወራት በኋላ ከትምህርት ቤት ተባረረ መምህሩ የአእምሮ ጉድለት እንዳለበት ገልጾለታል። በኋላም በታሪክ ውስጥ ከታላላቅ ሰዎች አንዱ ሆነ።
🔸 ቻርለስ ዳርዊን ህክምናን እንዲተው ጫና ተደረገበት፡ አባቱ በምሬት እንዲህ አለ፡- "አንተ ከቅዠቶች በስተቀር ምንም አታስብም!" በመጨረሻ በዝግመተ ለውጥ ጽንሰ-ሐሳብ ባዮሎጂን የኢቮሉሺን አብዮት አመጣ።
🔸 ዋልት ዲስኒ "የፈጠራ ክህሎት እጦት የታየበት" በሚል ከጋዜጣ ስራ ተባረረ። ከዚያም በዓለም ዙሪያ በትውልዶች የተወደደ የመዝናኛ ግዛት ገነባ።
🔸 የቤቴሆቨን የሙዚቃ አስተማሪ ፍፁም ተሰጥኦ የለሽ ብሎታል። በዓለም ላይ እጅግ ጊዜ የማይሽራቸው ድንቅ ስራዎችን ሰርቷል።
🔸 አልበርት አንስታይን እስከ አራት አመቱ ድረስ አልተናገረም ነበር እና መምህሩ የአእምሮ እክል እንዳለበት ገልፆታል። በታሪክ ከታላላቅ የሳይንስ አእምሮዎች አንዱ ሆነ።
🔸 የአውግስጦስ ሮዲን አባት የአርት ትምህርት ቤት መግቢያ ፈተና ሶስት ጊዜ ወድቆ "ደደብ" ብሎ ተፈርጇል። ሮዲን አሁን ካሉት ታላላቅ ቅርጻ ቅርጾችን ከሚሰሩት ውስጥ የምንጊዜም ቀረጺ አንዱ ሆኖ ይከበራል።
🔸 ንጉሠ ነገሥት ፈርዲናንድ የሞዛርትን "የፊጋሮ ጋብቻ" "በጣም ብዙ ኖቶች አሉት" ሲል ነቅፏል። ዛሬ ግን የሞዛርት ሊቅነት አጠያያቂ አይደለም።
🔸 ዲሚትሪ ሜንዴሌቭ በኬሚስትሪ አማካኝ ነጥብ ብቻ ቢያገኝም በኋላ ግን የፔሪዲክ ቴብልን ሠንጠረዥን ሠርቷል ሳይንስን በመሠረቱ ለውጦታል።
🔸 ታዋቂው የፎርድ አውቶሞቢል ፈጣሪ ሄንሪ ፎርድ ከመሰረታዊ እውቀት ጋር ታግሏል እና ብዙ ጊዜ መክሰርን አስተናግዷል።
🔸 ማርኮኒ ሬዲዮን ፈልስፎ በአየር ላይ የሚተላለፉ ቃላትን ሲገልጽ ጓደኞቹ አእምሮው እንደተቃወሰ በማሰብ ወደ የአእምሮ ህክምና ባለሙያ ወሰዱት። ከወራት በኋላ የፈጠረው ፈጠራ በባህር ላይ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ህይወት አድኗል።
መቼም ቢሆን የሌሎች ፍርድ ያንተን አቅም እንዲገልጽ አትፍቀድ። ታላቅነት ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው ከውድቀት ነው። በራስህ መተማመንህን ቀጥል!

❤138👍20💯9❤🔥3🔥2🫡2🥰1🙏1
አለማወቅ
ይሄ የምታዩት ፎቶ በደቡባዊ ትግራይ የተነሳ ፎቶ ነው። ፎቶው አማዞን ላይ እስከ 13 ዶላር ይሸጣል። ፎቶው ሳየው ሁሌም የሚገርመኝ እውነት አለው።
እረኛው እና ውሻው ዘና ብለው የተቀመጡት ፈንጂ ላይ ነው። ያልፈነዳ ፈንጂ። አካባቢው ብዙ ጊዜ በጦርነት በመቆየቱ ፈንጂዎች አሉ። የሚገርመው ልጁም ሆነ ውሻው ፈንጂ ላይ መቀመጣቸውን አያቁም።
አለማወቃቸው ምቾት ሰቷቸዋል። አለማወቃቸው ከአሁን አሁን ፈነዳ በሚል ስጋት እንዳይኖሩ አርጓቸዋል። አለማወቃቸው ጭንቀት አስወግዶላቸዋል። አለማወቃቸው ብዙ ጠቅሟቸዋል። ግን አለማወቃቸው ሪስክ አለው። የማይነካ ቦታ ነክተው ቢፈነዳስ? ወይ ሌላ ነገር ቢፈጠርስ?
ባለማወቅ የምንኖርበት ዘመን በቃ እንዲህ ነው። አለማወቃችን ነጻነት ነው። አለማወቃችን መፈታት ነው። ሀዘን ጭንቀት ይፈጠራል። ያወቅን ጊዜ ግን ጭንቀቱ ስጋቱ ውጥረቱ ይመጣል።
ማወቅ አንዳንዴ ጭንቀት ነው። ሀዘን ነው። ንዴት ነው። ነጻነትን ማጣት ነው። የሚያውቅ ሰው ፈሪ ነው.....ጠንቃቃ ነው።

❤355🙏35👍29🫡14😭8👏6🤯3🔥1🤗1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
‼️ ትኩስ ትኩስ ወቅታዊ መረጃዎችን ከፈለጉ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ።
🇪🇹🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም ዙሪያ የተሰሙ ዜናዎች፤ በጉምቱ ተንታኞች የሚቀርቡ ሙያዊ አስተያየቶች እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች።
ስፑትኒክ አማርኛ፤ ያልተነገረዎትን መንገር ጀምሯል!
👉 https://www.tg-me.com/+jEoyKtlGMNlmMWUy

❤21👍1