Telegram Web Link
እነዚህ በ UAE የሚገኙ ጭልፊቶች ፡ ዝም ብሎ ጭልፊት አይደሉም ። ፓስፖርት አላቸው ፡

በኋላኛው ላባቸው በኩል የመገናኛ አንቴና ተገጥሞላቸዋል ። ከተወለዱ ጀምሮ በየጊዜው ሪከርድ የሚደረግ medical history አላቸው ። በካሊፎርኒያ ከሚገኝ ፡ አንድ የማይክሮ ቺፕ አምራች ኩባንያ የተገዛ የማንነት መለያ ( AVID microchip system ) በሰውነታቸው ውስጥ ተቀብሮባቸዋል ።

✅️ በአጋጣሚ ከሌላ ሰው እጅ ቢገቡ እንኳን ፡ ከጭልፊቱ ባለቤት በቀር ማንም ይዟቸው ከሃገር እንዳይወጣ ቁጥጥር ይደረጋል ።
..............................

በዱባዩ አሚር ሼክ ሃምዳን ቢን ራሽድ አል መክቱም ልዩ ትእዛዝ የተገነባ ልዩ ሆስፒታልም አላቸው ። በካታርና አቡዳቢም ተመሳሳይ ደረጃቸውን የጠበቁ የጭልፊቶች መታከሚያ ሆስፒታሎች የተገነቡ ሲሆን ፡ በተለይ በዱባይ ፋልከን ሆስፒታል ፡ በውስጡ አለም የደረሰበት ዘመናዊ የህክምና ቴክኖሎጂና ፡ ከፍተኛ የሚባል ደሞዝ የሚከፈላቸው የጀርመን የህክምና ዶክተሮችና ጠቢባን የሚመራ ነው ። እናም በዚህ ሆስፒታል በተለያየ ምክንያት ህመም ላጋጠማቸው ጭልፊቶች ፡

✅️በዘመናዊ መሳሪያዎች እስከ ቀዶ ጥገና የሚደርስ የህክምና አገልግሎትና ፡ የጤና እንክብካቤ ይደረግላቸዋል ። እዚህ ላይ ግልፅ ለማድረግ ያህል ጭልፊት ከንስር የሚያንስ የአሞራ ዝርያ ነው ።
...........................

ወደ ካታር ስንመጣ በካታር መዲና ዶሀ ውስጥ አንድ ግዙፍ ሱቅ አለ ፡ በዚህ ግዙፍ ሱቅ ውስጥ ከተለያዩ የአለም ሀገራት የተገኙ ፡ የተለያየ ዝርያ ያላቸው ፋልከኖች ይሸጣሉ ፡ በተጨማሪም ፡ የፋልከን ምግብ ፡...ፋልከኖችን በእጅ ላይ ለመያዝ የሚሆን ጓንት ( ይህ ጓንት በጭልፊቶቹ ጥፍር ከመቧጨር የሚከላከል ነው ). ....የጭልፊቶች ፡ የአይን መሸፈኛ ጭምብልና ተያያዥ የሆኑ ቁሶች ይሸጡበታል ።

በርግጥ እነዚህን ሱቆች የሚደፍሩት ሃብታም ሰወች ቢሆኑም ፡ ሁሉም ኳታራውያን በሚባል መልኩ ለጭልፊት ያላቸው አመለካከት ከፍተኛ ነው ።

እናም በዚህ ፋልከን የክብር መገለጫ በሆነባት አረባዊት ሀገር ግዙፉን የአለም ዋንጫ ከማዘጋጀቷም በፊት ቢሆን ፡ የአለም ዋንጫን ያህል ትኩረት ባይስብም ፡ እስከ አንድ ሚሊየን ቱሪስቶች ከመላው አለም እየመጡ የሚከታተሉት ፡ አንድ አመታዊ የጭልፊቶችና የአደን ውድድር አላት ።

ይህ ውድድር ምንም እንኳን የሚካሄደው ፡ በቢሊየነር ሀብታሞች እና በአረቡ አለም ንጉሳውያን ቤተሰቦች መሀከል ቢሆንም ፡ ቀላል የማይባል ተመልካች ያለው ስፖርት ውድድር ነው ። ። ስለሆነም በየሀገሩ በሚካሄደው ፌስቲቫል ላይ አሸንፎ ትልቅ ስም እና ክብር ለማግኘት ብዙ ዝግጅት ያደርጋሉ ።

✅️እና በዚህ አመታዊ የካታር ውድድር አሸናፊ የሆኑ ልኡላንና የዘይት ነጋዴ ሚሊየነሮች በውድድሩ ሲያሸንፉ ትልቅ ክብር ይሰጣቸዋል ። ከነዚህ መሀከል ደግሞ አንደኛው የዱባዩ ልኡል ናቸው

አብዛኛዎቹ የአረብ ንጉሳውያን ቤተሰቦች ፡ ለፋልከን ያላቸው ፍቅር የተለየ ቢሆንም ፡ የዱባዩ ልኡል ሼህ ሀምዳን ቢን መሀመድ ደግሞ ከሁሉም ይበልጣል ። ወጣቱ የዱባይ ልኡል የእረፍት ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ከፋልከኖች ጋር ነው ። በዱባይ ተደርጎ በነበረው የዚህ አመት የጭልፊት አደን ውድድርም አሸንፈዋል ።

በአረብ ባለሀብቶችና በንጉሳውያን ቤተሰቦች ይህ ጉዳይ እንደሆቢ የያዙት ሺህ አመታትን ያስቆጠረ ልማድ ነው ። ጭልፊት በአረብ ህዝቦች ዘንድ ዝም ብሎ የወፍ ዝርያ አይደለም ። ከሺህ አመታት ጀምሮ እስካሁን ድረስም ፡ ጭልፊት ለአረባውያን የጥንካሬ ፡ የክብር ፡ የውበት ፡ የታማኝነት ፡ የአንድነትና የመተማመን ተምሳሌት ነው
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በዚምባቡዌ የሚገኙ ሁለት የእግር ጣት ብቻ ያላቸው ጎሳዎች አሉ። ይህም ዛፍ ለመውጣት በጣም እንደሚረዳቸው ይነገራል

Genetics 🧬💫

@Amazing_fact_433
ኮሊንዳ ጋርበር የክሮሽያ ፕሬዝደንት

ኮሊንዳ ጋርበር ነች ። እና ፈታ ማለት ስለምትወድ ፡ ካሪቢያን ደሴቶች ላይ እንዲህ በጡት ማስያዣ እና በፓንት ሆና ዝንትንት እያለች ባገኛትና ሰላም ብላት ብለህ አስበው .....

ሃይ እንዴት ነሽ ስትላት እሷም ደስ ከሚል ፈገግታ ጋር ሰላም እንዴት ነህ ትልሃለች ፡

ከዛ በቁምጣ ሆነህ ከባህሩ ዳር ከሷ እርምጃ እኩል እየተራመድህ ወሬ ለመጀመር ያህል እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ፡ ትንሽ ስራዬ ውጥረት የሚበዛው በመሆኑ መዝናናቱ ላይ ብዙም አይደለሁም ፡ ስትላት ኦው ጥሩ ነው ኢትዮጵያን በስራ አጋጣሚ አውቃታለሁ ትልህና ፡ ምን ላይ እየሰራህ ነው ብላ ትጠይቅሃለች ፡

እኔ የግብርና ምርቶችን ኤክስፖርት አደርጋለሁ ፡ አንቺስ ? ቅድም ኢትዮጵያን በስራ አጋጣሚ አውቃታለሁ ስትይ ሰምቻለሁና ፡ ስራሽ ምንድነው ? ብለህ ስትጠይቃት

ልብን በሚያሞቅ ፈገግታ ተሞልታ ፡ እኔማ የክሮሽያ ፕሬዝደንት ነኝ ፡ በዛ አጋጣሚ ነው ሃገራችሁን የማውቃት ብላ ዞር ስትል አንተ ፌንት አርገህ ወድቀሃል. .... አትሰማትም ።
..............
🔵ኮሊንዳ በርገር ፡ በዩናይተድ ስቴትስ አሜሪካ የክሮሽያ አምባሳደር ሆና ሃገሯን አገልግላለች ከዚያም የመጀመሪያዋ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የክሮሽያ የአውሮፓ ጉዳዮች ሃላፊ በመጨረሻም እስከባለፉት ሁለት አመታት ድረስ ለአምስት አመታት ሃገሯን በፕሬዝደንትነት ያገለገለች ለሃገሯ ፡ ለልጆቿ ለቤተሰቦቿ አሁን አሁን ደግሞ ለአለምም ጭምር በጎ ነገር ለማውረስ የምትጥር ጠንካራ ሴት ናት ።

ከፕሬዝደንቷ ከለቀቀች በኋላም በተለያዩ አጋጣሚዎች ሃገሯን እየወከለች ትገኛለች

፡ ከሁለት ወራት በፊት በዱባይ ኤክስፖ ላይ ክሮሽያን ወክላ ሄዳ ነበር ፡ ደግሞ ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ሃገሯ ከፈረንሳይ የነበራትን ጨዋታ ለመመልከት ፓሪስ ተገኝታ ነበር ፡ ይህ ጨዋታ ፈረንሳይን 1-0 ያሸነፍንበት ምርጥ ጨዋታ ነበር በተይም የ 2018 የአለም ዋንጫ ላይ በደንብ ትታወቃለች ።
.......
እና ያንን ጨዋታ ለመመልከት አንተ የክሮሽያ ደጋፊ ሆነህ በፈረንሳይ ስታዲየም እንዳጋጣሚ አጠገቧ ብትቀመጥና ፡ ልክ ተጨዋቾች ለረፍት ሲወጡ አጠገብህ ነጭና ቀይ ስኩየር ማልያ ለብሳ ቁጭ ያለችውን ቀለል የምትል ሴት ዞር ብለህ አየት አድርገሃት ፡ የትም እንደማታውቃት ልብህ እያወቀው ለወሬ መክፈቻ. . የሆነ ቦታ አውቅሻለሁ ልበል ? ስትላት ፡

ተግባቢዋ ኮሊንዳ ..አይደል ? እኔምኮ ገርሞኝ የት ነው የማውቀው እያልኩ ሳስብ ነበር አሁን ነው ትዝ ያለኝ. ...

ከሁለት አመት በፊት የክሮሽያ ፕሬዝደንት ሆኜ ካሪቢያን ደሴቶች ላይ ተገናኝተን ፌንት ያረከው ግን ምን ሆነህ ነው ብትልህ. .. ሁለተኛውን የጨዋታ አጋማሽ ፡ በሃፍረት ጥለህ ትወጣለህ ? ወይስ በምን አይነት ሙድ ሆነህ ኳሱን እንደምትከታተል ብቻ እግዜር ይወቅ ።
..................
እንዲህ አይነት ራሳቸውን ሰማይ ጥግ የማይቆልሉ ፡ ተጫዋች ተግባቢ ፡ ሰው ሰው የሚሸቱ ፡ እኔ ብሆን ኖሮስ ብለው ራሳቸውን በህዝብ ቦታ የሚያስቀምጡ. .. ሁሉም የሚቀናባት ባለስልጣናት
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የparanormal expert እንደሚሉት ከሆነ ተኝተን የሞተ ዘመዳችንን ወይም ጓደኛችንን በህልማችን ካየን

የነሱ መንፈስ(ghost) ክፍላችን ውስጥ አለ ማለት ሲሆን በዛው በህልማችን ባየናቸው ሰአት ቀጥታ እኛ ላይ አፍጥጠዋል ማለት ነው


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
የአለማችን አጭሩ ዶክተር - ጋኔሽ ባራያ - የጽናትና ይቻላል ተምሳሌት

91 ሴንቲሜትር የሚረዝመው ጋኔሽ የማህበረሰቡ ይደርስበት የነበረው ማሳቀቅ የልጅነት ምኞቱን ከማሳካት አላገገደውም

የህክምና ትምህርት እንዳይከታተል የተጣለበትን እገዳም ፍርድቤት ተመላልሶ በማሻር ያፌዙበትን ሁሉ ህይወት በሚታደግ ሙያ ተሰማርቷል

የ23 አመቱ ህንዳዊ ጋኔሽ ባራያ በምድር ላይ የማይቻል ነገር የለም የሚለውን አባባል ማረጋገጫ ተምሳሌት ሆኗል።

በጉጃራት ታላጃ ታሉካ በተባለ አካባቢ የተወለደው ጋኔሽ እስከ አራት አመቱ ድረስ እንደማንኛውም ህጻን ጤናማ አስተዳደግ ነበረው። በጭንቅላቱ መጠን ከፍ ማለትና በቁመቱ እድገት መቆም ግራ የተጋቡት ቤተሰቦቹም ወደ ህክምና ተቋማት ደጋግመው ቢወስዱትም ለውጥ ማየት አልቻሉም

የቁመቱ ማጠር እና የጭንቅላቱ መጠን ማነስ በትምህርት ቤት ጓደኞቹ ጭምር ጣት የሚጠቋቆሙበትና የሚዘባበቱበት ልጅ መሆኑ ቢረብሸውም በትምህርቱ ላይ ማተኮርን መረጠ።

ለተማሪዎቹ ሽሙጥ ቦታ ከመስጠት ይልቅ ዶክተር የመሆን ህልሙን ለማሳካት በትምህርቱ ላይ በረታ ይላሉ ወላጆቹ።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ወደ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ውጤት ሲገባ ግን ከትምህርት ቤት እስከ መንደሩ ያሰለቸው አድልኦ ዳግም ፈተና ሆነበት።

በዩኒቨርሲቲ ህክምና ለማጥናት ያቀረበው ጥያቄ በውጤቱ ሳይሆን በቁመቱ ውድቅ ተደረገበት፤ የህንድ የህክምና ምክርቤት 91 ሴንቲሜትር ቁመት ያለው ጋኔሽ ድንገተኛ ታካሚዎችን እንደልብ ተሯሩጦ ማከም አይችልም አለ።
ጥያቄው ውድቅ የተደረገበት ጋኔሽ ተስፋ አልቆረጠም፤ ከጉጃራት የትምህርት ቢሮ እስከ ግዛቱ ፍርድ ቤት ድረስ በመዝለቅ አቤቱታውን አሰማ።

የጉጃራት ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ጥያቄውን ውድቅ የሚያደርግ ውሳኔ አሳለፈ።
የያኔው ታዳጊ ግን ይግባኝ ጠይቆ በ2018 በህንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምኞቱን የሚያሳካበት ውሳኔ እንዲተላለፍ ታግሏል።
በ2019ም የህክምና ትምህርቱን ጀምሮ በቅርቡ ተመርቋል፤ ባሃቭጋር በተባለ አካባቢም ስራ መጀመሩን ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል።

“ከልጅነቴ ጀምሮ የጓጓሁለትን ዶክተር የመሆን ምኞት በብዙ ፈተና አልፌ አሳክቸዋለሁ፤ አዎ እኔ የተለየሁ ነኝ፤ ግን እንደማንኛውም ሰው ደስተኛ ህይወት መምራትና ቤተሰቦቼን ማኩራት እፈልጋለሁ” ብሏል ጋኔሽ።

በትምህርት ቤት በጓደኞቹ ይደርስበት የነበረው ተጽዕኖ በስራ ባልደረቦቹና በታካሚዎች ጭምር ባይጠፋም ያሳለፈው ፈተና ብርታት ሆኖት ለበርካቶች ምሳሌ የሚሆን ተግባሩን ገፍቶበታል


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ይህንን ያውቃሉ ?

አርሰናል የሚባል ክለብ በኢንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ እ.ኢ.አ በ1893 ከደቡብ እንግሊዝ የመጣ የመጀመሪያው ክለብ ሲሆን በ1904ም ወደ አንደኛ ዲቪዚዮን መድረስ ችለዋል ።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433group
አዲስ መረጃ

አደጋ የደረሰባት የኢራን ሄሊኮፕተር ፍለጋ

ኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲን አሳፍራ ነበር የተባለችውን ሄሊኮፕተር በመፈለግ ላይ ናት።

ሄሊኮፕተሯ አርስፓራን በተባለ ጫካ ውስጥ “በአደገኛ ሁኔታ” ማረፏ የተገለጸ ሲሆን፥ የነፍስ አድን ስራተኞችም በአካባቢው ደርሰው ፍለጋው ቀጥሏል ተብሏል።

የአካባቢው የአየር ሁኔታ ጭጋጋማ መሆን ግን የፍለጋ ስራውን ፈታኝ እንዳደረገው ነው የተነገረው።

ኢራናውያን ፕሬዝዳንታቸው ከአደጋው እንዲተርፉ ተሰባብሰበው እየጸለዩ መሆኑንም ከቴህራን የሚወጡ ዘገባዎች ጠቁመዋል።
ይህን ያውቃሉ።

የራስን እስትንፋስህን በማፈን እራስህን ማጥፋት አይቻልም፡፡

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ይህንን ያውቃሉ paranormal expert በቅርቡ አስደንጋጭ እውነታ አውጥቷል

ውሻ በጣም ረቂቅ ነገሮችን የማየት አቅም አለው አንድ ሺ እጥፍ ከሰው የበለጠ የማሽተት ሀይልም አለው
ከ ሰውም  4 እጥፍ ድምፅ ይሰማል።

ነገር ግን ከእነዚህ ችሎታዎች በላይ መናፍስት እና ረቂቅ ነገሮችን ማየት እንደሚችል በጥናት ተረጋግጧል

ስለሆነም ቤታችን ያለ ውሻ እና ድመት መናፍስትን በደንብ ሊያዩ ሊያዩ ይችላሉ።

ይህንንም ለማረጋገጥ

1. ውሻ ወይም ድመታችን ብቻ በለተየ መልኩ አንድ ጥግ  ቦታ  አፍጥጠው ካየናቸው ወይም አይናቸው የሆነ ነገር የሚከተል ከመሰለን

2 ውሻችን ምንም ነገር ሳያይ ዝም ብሎ የሚጮህ ከሆነ

3 ውሻ ወይም ድመት አጠገባችን ሆኖ እየጠራናቸው ትኩረታቸውን ግን ሌላ ቦታ ከሆነ መንፈስ ቤታችን ውስጥ እንደሚኖር ዋናው ምልክት ነው


@Amazing_fact_433
ይህን ያውቃሉ

የኳታሩ ንጉስ ሼክ ተሚም ቢን ሀሚድ አልታኒ. . ለሜሲ የሰጡት የክብር ልብስ. .ጥለቱ ( ፍሬሙ ) . ከንጹህ ወርቅ የተሰራ ሲሆን ፡
ዝም ብሎ የሚሰጥ ሳይሆን

ለንጉሳውያን ቤተሰቦችና ፡ እጅግ በጣም ለሚያከብሯቸው ሰወች ፡ " አንተ ከኛ መሀል አንዱ ነህ " ለማለት የሚሰጡት ትልቅ የክብር ሽልማት ነው ።


@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
በአንዳንድ የህንድ አካባቢዎች የላም ሽንት በጠርሙስ ታሽጎ ይሸጣል

@Amazing_fact_433
2024/06/16 11:42:04
Back to Top
HTML Embed Code: