#ንስሐ ስላለፈው ስህተት አብዝቶ ማልቀስ፣ ያለፈውን የኃጢያት ኑሮ ማውገዝና መኮነን ነው። ኃጢያትን ፈጽሞ በመተው ከልቡናው የኃጢያትን ሃሳብ ጨርሶ ያስወገደ ሰው ልቡ ንጹሕ ስለሆነ ያለፈውን ኃጢያት እያሰበ ያለቅሳል። የቀደመ የበደል ኑሮውንም ይረግማል። ነብዩ ቅዱስ ኢዩኤል "አሁንስ ይላል #እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በለቅሶና በዋይታ ወደኔ ተመለሱ" በማለት የሚመክረን ለዚህ ነው። ት. ኢዩ.2÷12። ሰው በፍጹም ልቡ ካልተመለሰ ስለኃጢያቱ እያዘነ ሊያለቅስ አይችልም።
#ይቀጥላል......
#ይቀጥላል......
#ንስሐ_ፍጹም_የሆነ_ለውጥ_እንጂ_ጊዜያዊ_ስሜት_አይደለም!
ተነሳሒው በስሜት ተነድቶ ለጊዜው የሚያሳየው ፀፀት #ንስሐ አይባልም። በፍጹምና በመላው ሕይወቱ በመለወጥ ወደ #እግዚአብሔር መቅረብ አለበት። ይህ የሕይወት ለውጥ በሩሱ ውስጥ እና ከሰዎች ጋር ባለው ግንኙነት፣ በአስተሳሰቡ መለወጥ፣ በአቋሙና በጠባዩ መለወጥ፣ ስለ ሕይወቱ ባለው አመለካከት መለወጥ፣ በአነጋገር ስርዓቱ መለወጥ፣ ከ #እግዚአብሔር ጋር የነበረው ግንኙነት (ከክህደት ወደ ማመን) በመለወጡ ይታወቃል። በልቡናው መለወጡ ደግሞ የሚወደውን ኃጢያት በመጥላቱና በምትኩ ልቡናው በ #እግዚአብሔር ፍቅር በመሞላቱ የተነሣም መንፈሳዊ የሕይወት ተሐድሶ በማግኘቱ ይታወቃል። ይህንን ለማረጋጥ ነው ቅዱስ ጳውሎስ "በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ" ያለው። ሮሜ.12÷2። ከዚህ በመነሳት ነው እንግዲህ #ንስሐ ፍጹም የሆነ የሕይወት ለውጥ እንጂ በጊዜያዊ ስሜት ላይ የተመሠረተ አይደለም የተባለው።

#ጥቅምት_3
#አንድ_አምላክ_በሆነ_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሦስት በዚህች ቀን የኢትዮጵያዊው ቄርሎስ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ በዓለ ፅንሰቱ ነው፣ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 51ኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባ_ስምዖን አረፈ፣ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሐዲስ የምስክርነቱ መታሰቢያ ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞#✞✞✞✞✞
#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
ጥቅምት ሦስት በዚህች ዕለት ከመጽሐፈ ሰዓታት ውጭ እጅግ ብዙ ድርሰቶችን የደረሰ ፈላስፋም ጻዲቅም ደራሲም መናኝ ባሕታዊም የሆነ ድርሰቶቹንም ለቅዱሳን በነፋስ ጭኖ ይልክላቸው የነበረ የቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ኩራት ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በዓለ ፅንሰቱ ነው፡፡
አባ ጊዮርጊስ ነገረ ሃይማኖትን ጠንቅቆ የተረዳና የሚያስረዳ ስለነበር በዘመኑ የተነሡ የሃይማኖት ክርክሮች ሁሉ እርሱ ከሌለ አይሳኩም ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ በሸዋ በይፋት ራሳቸውን ቤተ እስራኤል እያሉ የሚጠሩ አይሁድ ነበሩ፡፡ ከአቡነ ዜና ማርቆስ ጀምሮ ብዙ መምህራን ወደነዚህ ሕዝቦች እየተሠማሩ ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ክርስትና ለተመለሱት ቤተ እስራኤላውያን በ #እመቤታችን፣ በ #ቅዱስ_ሚካኤል፣ በ #አባ_ኖብና በሰማዕቱ በ #ቅዱሴ_ጊጋር ስም አራት አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተው ነበር፡፡ ሁለቱ የመጀመሪያዎቹ አሁንም አሉ፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ቤተ እስራኤላውያኑ ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስትና አልተመለሱም ነበር፡፡
ከእነዚህ አይሁድ መካከል አንዱ ከክርስቲያኖች ጋር በነገረ ሃይማኖት ለመከራከር ጥሪ አቀረበ፡፡ “ክርስቲያኖች ከረቱኝ ወደነርሱ ሃይማኖት እገባለሁ እኔ ከረታኋቸውም ወደኔ ሃይማኖት ይገባሉ” ሲል ነገሩን ጥብቅ አደረገው፡፡ ዐፄ ዳዊት ይህን ጉዳይ ሲሰማ በጣም ስለ ተናደደ ሊቃነ ካህናቱን፣ ንቡራነ እዱንና የመጻሕፍት ዐዋቂዎችን ሁሉ ከየሀገሩ እንዲሰባሰቡ አዘዘ፡፡ አይሁዳዊው በአንድ ወገን መምህራኑ በአንድ ወገን ሆነው ክርክሩን ጀመሩ፡፡ የመጀመርያው እድል የተሰጠው ለአይሁዳዊው በመሆኑ ቀጥሎ ያለውን ጥያቄ አቀረበ፡- “እናንተ የ#እግዚአብሔር ልጅ ነው የምትሉት #ሎቱ_ስብሕት ይሄ #ክርስቶስ እውነት የ #እግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፣ ወደ ቢታንያ በመጣ ጊዜ አልዓዛር የተቀበረበትን ቦታ ሳያውቅ ቀርቶ 'አልዓዛርን የት ቀበራችሁት?” ብሎ እንደ ጠየቀ በወንጌላችሁ ተጽፏል፡፡ ለዚህ መልስ ስጡኝ፣ እኔንም ከመጽሐፈ ኦሪቴ ጠቅሳችሁ ጠይቁኝ?” ሲል የመከራከርያ ነጥቡን አቀረበ፡፡
በዚህ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ ታሞ አልጋ ላይ ነበር፡፡ ሊቃውንቱም “እንዲህ ያለው ነገር ያለ እርሱ አይሆንምና አባ ጊዮርጊስ ይምጣ” ሲሉ ለዐፄ ዳዊት ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አባ ጊዮርጊስም በአልጋ ላይ እያለ እንዲመጣ ተደረገ፡፡ በአልጋ ላይ ሆኖም በጉባኤው ላይ ተገኘ፡፡ ጉባኤተኞቹ የቀረበውን ጥያቄ ነገሩት፡፡ አባ ጊዮርጊስ የሰጠውን መልስ ገድሉ በሚከተለው መንገድ ይገልጥልናል “እኔ ግን በወንጌል ሳይሆን በኦሪት እከራከርሃለሁ፡፡ የምኩራብ መጻሕፍት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን የታወቁ ናቸውና፡፡ ምኩራብ ዘራች ቤተ ክርስቲያንም አጨደችው፤ ምኩራብ ፈተለችው ቤተ ክርስቲያን ለበሰችው፤ አዳምን በገነት ሳለ አዳም ሆይ ወዴት ነህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? አብርሃምንስ ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? ብሎ የጠየቀው ማነው? እስቲ መልስልኝ? ሰይጣንንስ ከወዴት መጣህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? #እግዚአብሔር_አብ አይደለምን?” በዚህ ጊዜ አይሁዳዊው መልስ አጥቶ ዝም አለ፡፡ ንጉሡ፣ ሊቃውንቱና መኳንንቱም እጅግ ተደሰቱ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ሌላው ያጋጠመው ክርክር ቢቱ ከተባለው ሰው ጋር ያደረገው ክርክር ነበር፡፡ ቢቱ “በምጽአት ጊዜ የሚመጣው #ወልድ ብቻውን እንጂ #አብና #መንፈስ_ቅዱስ አይመጡም” የሚል ኑፋቄ ማስተማር ጀምሮ ነበር፡፡ ቢቱ ከዚህ ኑፋቄው በተጨማሪ የጥንቆላ ሥራም ይሠራ ነበር፡፡ ቢቱ በጥንቆላ ሥራው የተነሣ በቤተ መንግሥቱ ተቀባይነት የነበረው ሰው እንደ ነበረ ገድሉ ይናገራል፡፡ ይህን መሰሉን ተግባር አጥብቆ የተዋጋው ዘርዐ ያዕቆብ እስኪመጣ ድረስ ነገሥታቱ ምንም ክርስቲያኖች ቢሆኑ በዚህ መሰሉ ስንኩል ሕፀፅ ይዋጡ ነበር፡፡
ቢቱና አባ ጊዮርጊስ ወደ ንጉሥ ዳዊት ቀርበው በጉዳዩ ላይ መነጋገር እንደሚፈልጉ ገለጡ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ጳጳሱና ሊቃውንቱ ባሉበት እንዲነጋገሩ ስለ ወሰነ ጳጳሱ እንዲመጡ አዘዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ተንኮለኛው ቢቱ ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ከተከራከረ እንደሚረታ ስላወቀ “ንጉሡ የአባቶቻችንን ሃይማኖት ክዷልና አትምጣ” የሚል ደብዳቤ በአባ ጊዮርጊስ ስም ጽፎ ጳጳሱን ሊጠሩ በሄዱት መልእክተኞች እጅ ላከ፡፡ ወድያውም ለዐፄ ዳዊት ይህንን ነገር አሳበቀ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ፈጣን መልእክተኞች ልኮ የፊተኞቹ መልእክተኞች እንዲመለሱ አደረገና ደብዳቤው ተነበበ፡፡ የቢቱ ተንኮል ያልገባው ንጉሥ ዳዊት ይህን ደብዳቤ ሲመለከት አባ ጊዮርጊስን በደም አበላ እስኪነከር ድረስ እንዲደበደብ አድርጎ ወደ እስር ቤት አስገባው፡፡ ዐፄ ዳዊት እስኪሞትና ልጁ ቴዎድሮስ እስኪነግሥ ድረስም በዚያ ቆየ፡፡ ቢቱ ግን በመልአክ ተቀስፎ ሞተ፡፡
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጸሎት ይማረን በረከታቸው ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ስምዖን
ዳግመኛም በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ኃምሣ አንደኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባ ስምዖን አረፈ።
ይህም አባት ከእስክንድርያ ከታላላቆች ተወላጅ የሆነ ወላጆቹም ሃይማኖታቸው የቀና ነው። እርሱም ከታናሽነቱ የሃይማኖት ወተትን ጠጥቶ አደገ ስለዚህም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተማረ።
የምንኵስናንም ልብስ ሊለብስ በልቡ አስቦ ወደ አስቄጥስ ገዳም በመሔድ ከእርሱ አስቀድሞ ሊቀ ጳጳሳት በሆነ በአባ ያዕቆብ ገዳም መነኰሰ በየጊዜው በሚጨመር ተጋድሎም ሥጋውን እያደከመ አብዝቶ በመጋደል በእርሱ ዘንድ ኖረ።
ዳግማዊ አባ ማርቆስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ይህን አባ ስምዖንን ስለ በጎተጋድሎውና ስለ አገልግሎቱ ከአባ ያዕቆብ ዘንድ ወሰደው እያገለገለውም ከእርሱ ጋር ኖረ።
አባ ማርቆስም በአረፈ ጊዜ አባ ያዕቆብ ተሾመ ያን ጊዜም እያገለገለው ከአባ ያዕቆብ ጋር ኖረ። ከዚህም በኋላ አባ ያዕቆብ በአረፈ ጊዜ ብዙዎች ካህናትና ኤጲስቆጶሳት የሀገር ታላላቆች ሁሉም ይህን አባት አባ ስምዖንን መረጡት። ትሩፋቱንና የአማረ ሥራውን በእነዚህ በሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ በነበረበት ጊዜ ስለተመለከቱ አምላካዊ ፍቅር አነሣሥቷቸዋልና በወንጌላዊ ማርቆስ መንበር ላይ ይዘው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።
ከዚህም በኋላ በሹመቱ ጸንቶ መልካምን ጉዞ ተጓዘ #እግዚአብሔርንም አገለገለው የሃይማኖትንም ሕግ በማስጠበቅ የ #ክርስቶስን መንጋዎች ጠበቀ።
በሹመቱ ወራትም ቤተ ክርስቲያን በጸጥታና በሰላም ኖረች። ከዚህም በኋላ እግሮቹን በጽኑዕ ደዌ ታመመ ፈጣሪ #እግዚአብሔርንም ከዚህ ደዌ ያሳርፈው ዘንድ ለመነው። ክብር ይግባውና #ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ በሰላም በፍቅር አንድነት አሳረፈው የሹመቱ ወራትም አምስት ወር ከዐሥራ አምስት ቀን ነው።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ጸሎት ይማረን በረከታቸው ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሐዲስ (ሰማዕት)

ሰማዕቱ የተወለደው በምድረ ግብጽ አሕዛብ (ተንባላት) በሰለጠኑበት የመጀመሪያው ዘመን ነበር። በተለይ ተንባላቱ ግብፅና ሶርያን ከያዙ በኋላ ባልተጠበቀ ፍጥነት በኃይልም በሰውም ተደራጅተው ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ (ሊቀ ሰማዕታት አይደለም) የተወለደው በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር።
እናቱ የተመሠከረላት ክርስቲያን ብትሆንም እንዳለመታደል አባቱ ተንባላታዊ (አሕዛብ) ነበር። ስሙንም መዛሕዝም ይሉታል። ሕጻኑ እንደተወለደ ያወጡለት ስም አሕዛባዊ ከመሆኑ ባለፈ በሰዓቱ መጠመቅ አልቻለም። የወቅቱ ሕግ ከወላጆቹ አንዱ አሕዛባዊ ከሆነና አጠምቃለሁ ቢባል የሚከተለው ሰይፍ ነበር። በዚሕ ምክንያት ሳይጠመቅ 7 ዓመት ሞላው።
እናቱ ግን ሕጻን ቢሆንም ፍቅረ ክርስትናን ታስተምረው ነበር። ባይጠመቅም ጸበሉን እመነቱን ትቀባው ነበር። ደብቃ ቅዳሴ ታሰማውም ነበር። አንድ ቀን ግን ሕጻናት ሲቆርቡ አይቶ ካልቆረብኩ ብሎ አለቀሰ። ምን ታድርገው? ወደ ውጪ አውጥታ ከአውሎግያ (የሰንበት በረከት) አበላችው። "ጌታዬ ልጄን እርዳው" አለች።
ልክ በአፉ ሲቀምሳት መዓዛ #መንፈስ_ቅዱስ አደረበትና ፍጹም ተደሰተ። ትንሽ ከፍ ሲል ለምን እንደማይጠመቅና እንደማይቆርብ እናቱን ጠየቃት። "ልጄ ሆይ! ይገድሉሃል" አለችው። ከዚህች ቀን ጀምሮ የሚጠመቅበትን ዘዴ ይፈልግ ጀመር።
አስቀድሞ ትምሕርተ ክርስትናን ተማረ። ለአካለ መጠን ሲደርስ አፈላልጐ ጠንካራ ክርስቲያን የሆነች ሴት አገባ። ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ሚስቱን ስለ መጠመቅ አማከራት። "ሌላ ሃገር ሒደህ ተጠመቅ" አለችው። ከግብፅ ተነስቶ ሶርያ ገባ። አባቶችን አፈላልጎ ተጠመቀ። ቀጥሎም መንገዱን ወደ ልዳ አደረገ።
ወደ ደብሩ ተጠግቶ አባቶችን "ስም አውጡልኝ" ቢላቸው #መንፈስ_ቅዱስ አናግሯቸው "ጊዮርጊስ" አሉት። እሱም ደስ እያለው ባጭር ታጥቆ የልዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያገለግለው ገባ። ትንሽ ቆይቶ ሁከት መንፈሳዊ ተሰማው። ማለትም ስለ ሃይማኖቱ ደሙን ማፍሰስ ፈለገና ወደ ግብፅ ተመለሰ።
በዚያ ያሉ አሕዛብ በክርስትና ስም ልብስና ሞገስ ሲመለከቱት ተበሳጩ። ዕለቱኑ አሠሩት። ሌሊት እናቱና ሚስቱ መጥተው አሉት "አደራ! ፍቅረ ዓለም እንዳያታልልህ። ሰማዕት ብትሆን ላንተም ክብር ለእኛም ሞገስ ነው" ብለውም አጽናኑት። እንዲህ ያሉ እናትና ሚስት ማግኘትም ታላቅ እድል ነው::
ሐዲስ ጊዮርጊስም ጸና። ከዚያች ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ደበደቡት አካሉን ቆራረጡት ደሙንም መሬት ላይ አንጠፈጠፉት። በየመንገዱ እየጎተቱ ተሳለቁበት። እርሱ ግን #ክርስቶስን ወዷልና ሁሉን ታገሰ። ሌሊት በሆነ ጊዜም #ጌታችን ተገልጦ "ከሰማዕታት ተቆጠርህ" አለው።
በማግስቱ በአደባባይ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት። ክፋታቸው የጸና ነውና ሥጋውን በእሳት አቃጠሉት። ወደ ባሕርም ጣሉት። እናቱ ከባሕር ስታወጣው ግን ምንም አላገኘውም ነበር። በዚሕች ቀን እናቱና ሚስቱ በክብር ቀብረውታል።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_3 እና #መጽሐፈ_አርጋኖን_መግቢያ)

#የጥቅምት_3_ግጻዌ
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_3_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ቲቶ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር።
² ሽማግሌዎች ልከኞች፥ ጭምቶች፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ በእምነትና በፍቅር በመጽናትም ጤናሞች እንዲሆኑ ምከራቸው፤
³ እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤
⁴-⁵ ቆነጃጅትም የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ፥ ባሎቻቸውን የሚወዱ፥ ልጆቻቸውን የሚወዱ፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ ንጹሖች፥ በቤት የሚሠሩ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው።
⁶ ጎበዞችም እንዲሁ ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው።
⁷-⁸ የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር፥ በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግህ ምሳሌ የሚሆን ራስህን አሳይ፤ በትምህርትህም ደኅንነትን፥ ጭምትነትን፥ ጤናማና የማይነቀፍ ንግግርን ግለጥ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
³ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤
⁴ የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
²⁹-³⁰ ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_3_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"አዋልደ ንግሥት ለክብርከ። ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት። መዝ.45÷9
#ትርጉም፦ “የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።” መዝ.45÷9
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_3_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሉቃስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁸ ሲሄዱም እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው።
³⁹ ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች።
⁴⁰ ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች፤ ቀርባም፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን? እንኪያስ እንድታግዘኝ ንገራት አለችው።
⁴¹ ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥
⁴² የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🌹የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #የሠለስቱ_ምዕት_ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።🌹

#ንስሐ_ኃጢያትን_ሲሠሩ_ከመኖር_ይልቅ_ከእግዚአብሔር_ጋር_መኖርን_መሻት(መምረጥ) ነው!
ከ #እግዚአብሔር ጋር መኖርን መምረጥ ማለት #እግዚአብሔር ማይወደውንና ማይደሰትበትን ኃጢያት ከመስራት ተከልክሎ #እግዚአብሔር የሚወደውንና የሚደሰትበትን ጽድቅ የሚገኝበትን መልካም ምግባርና ትሩፋት በመሥራት እርሱን በማምለክና በማገልገል መኖርን መምረጥ ነው። ሰው ከ #እግዚአብሔር ጋር መኖርን መረጠ ማለትም መንገዱን የ #እግዚአብሔር መንገድ፤ ፈቃዱን የ #እግዚአብሔር ፈቃድ፣ ሃሳቡን የ #እግዚአብሔር ሃሳብ አደረገ ማለት ነው። ሰው የ #እግዚአብሔርን መንግሥት የማያልፈውንም ርስት መረጠ ማለት ነው። #ንስሐም ኃጢያትን የኃጢያት ውጤት የሆነውንም የገሃነምን ኑሮ ትቶ ከ #እግዚአብሔር ጋር በመንግሥተ ሰማይ መኖርን መምረጥ ነው። መባሉ ለዚህ ነው። ከዚህ አንጻር ነው ነብየ #እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት "ለእኔስ ወደ #እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል" በማለት ምርጫውን ከ #እግዚአብሔር ጋር መኖር ያደረገው። መዝ.73÷28።
#ይቀጥላል.......

#ንስሐ_የአእምሮ_መታደስ_ነው!
ኃጢያት የአእምሮ መበላሸት ነውና። ኃጢያትን የሚያመላልስ አእምሮ የተበላሸ ነው። በኃጢያት እድፍ ንጽሕናውን ያጣው አእምሮ የሚታደሰው ኃጢያትን ማሰላሰል የተወ እንደሆነ ነው። ይህም በ #ንስሐ ነው። ይህን ሲገልጥ ቅዱስ ጳውሎስ "በልባችሁ መታደስ ተለወጡ" ሮሜ.12÷2 በማለት ተናግሯል።

"ወደ #እግዚአብሔር ተመለስ፤ ኃጢያትንም ተዋት በፊቱ ጸልይ፥ ለበደልህም #ንስሐ ግባ። ከበደልህም ወደ #እግዚአብሔር ተመለስ፤ ኃጢያትን ሁሉ ጥላ ፈቃዱንም አድርግ። በሕይወት ሳሉ እንደሚገዙለት ሰዎች፥ ልዑልን በመቃብር የሚያመሰግነው ማነው? የሞተ ሰው ግን #ንስሐ እንደ ኢምንት አለፈው፤ በሕይወትህ ደስ እያለህ #እግዚአብሔርን አመስግን። የ #እግዚአብሔር ቸርነቱ ታላቅ ነውና። የሚገዙለትንም ሰዎች ይቅር ይላቸዋል። ሰው ሟች ስለ ሆነ ሁሉ በሰው ዘንድ ሊሆን አይችልም። ከፀሐይ የሚበራ ምን አለ? እርሱም እንኳ ያልፋል። ደማዊና ሥጋዊም ክፉ ነገርን ያስባል። እርሱ የሰማይን ምጥቀት ኃይል ያውቃል፤ ሰው ሁሉ ግን አመድና ትቢያ ነው።
#ቅዱስ_ሲራክ
#ቅዱስ_ሲራክ
#ጥቅምት_4
#አንድ_አምላክ_በሆነ_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም
ጥቅምት አራት በዚች ቀን #ቅዱስ_ባኮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ #ቅዱሳን_ነገሥታት_አብርሃ_ወአጽብሓ ያረፉበትም ዕለት ነው፣ ሐዋርያው #ቅዱስ_ሐናንያ በሰማዕትነት ዐረፈ፣ #አቡነ_በርተሎሜዎስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ባኮስ
ጥቅምት አራት በዚህች ቀን የቅዱስ ሰርጊስ ባልንጀራ ቅዱስ ባኮስ በከሀዲ ንጉሥ አንጥያኮስ እጅ በሰማዕትነት አረፈ።
ይህም እንዲህ ነው እሊህን ቅዱሳን ከሀዲው ንጉሥ መክስምያኖስ በያዛቸው ጊዜ እነርሱ ወታደሮች ነበሩና ትጥቃቸውን ቆርጦ ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው ከዚህም በኋላ ወደ ሶርያ አገር ወደ ንጉሥ አንጥያኮስ ሰደዳቸው። እርሱም ቅዱስ ሰርጊስን አሠረው ቅዱስ ባኮስን ግን ሰቅለው እንዲደበድቡት በአንገቱም ከባድ ደንጊያ አንጠልጥለው ከኤፍራጥስ ወንዝ ከባሕር እንዲጥሉት አዘዘ ንጉሡም እንደ አዘዘ እንዲሁ አደረጉ።
#እግዚአብሔር ግን የቅዱስ ባኮስን ሥጋ ጠብቆ ወደ ወደብ አደረሰው በዚያ ወደብ አቅራቢያም በገድል ተጠምደው የሚኖሩ የአንደኛው ስሙ ማማ የሁለተኛው ባባ የሚባሉ ባሕታውያን አሉ። ለእሊህ ወንድሞችም ከ #እግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጠላቸውና ሒደው የቅዱስ ባኮስን ሥጋ ወደ በዓታቸው እንዲወስዱ አዘዛቸው።
በዚያንም ጊዜ መልአክ እንዳዘዛቸው ሔዱ የቅዱስ ባኮስንም ሥጋ አገኙ በአጠገቡም አንድ ቀንና አንድ ሌሊት ሲጠብቁት የነበሩ አንበሳና ተኵላ አሉ እነርሱም ከሰው ሥጋና ከእንስሳ በቀር የማይመገቡ ሲሆኑ ግን ከልዑል አምላክ ዘንድ ስለታዘዙ ነው። እሊያ ቅዱሳንም የቅዱስ ባኮስን ሥጋ ወሰዱ በታላቅ ክብር እያመሰገኑ እስከ በዓታቸውም አድርሰው በዚያ ቀበሩት።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ባኮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን!!
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_ነገሥታት_አብርሃ_ወአጽብሓ
ዳግመኛም በዚህ ቀን ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሓ ያረፉበት ነው። አባታቸው ታዜር እናታቸው ሶፍያ (አህየዋ) ይባላሉ፡፡ መንትዮች የሆኑት እነዚህ ቅዱሳን የተወለዱት #ጌታችን በተወለደባት ዕለት በታኅሣሥ 29 ቀን 312 ዓ.ም ነው፡፡ በታላቁ አባት በአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን እየተማሩ አድገው በእሳቸው እጅ በ330 ዓ.ም መጋቢት 29 ቀን ተጠመቁ፡፡ በእነርሱም ጊዜ አማናዊው ጥምቀትና ቁርባን መጣልን፡፡ በሀገራችን 154 አብያተ ክርስቲያናትን ያሠሩ ሲሆን 44ቱ ፍልፍል ናቸው፡፡ በተለይም ገርዓልታ ያለው ቀመር ዓርባዕቱ እንስሳ ፍልፍል ቤተ መቅደስ በሩ በራሱ ጊዜ ይከፈታል ይዘጋል እንጂ ሰው አይከፍተውም አይዘጋውም፡፡
አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን በአክሱም ሲኖሩ ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ ቅዳሜና እሁድ ብቻ የዛፍ ቅጠሎችን ከመመገብ በቀር ሌላ ምግብ ባለመመገብ በታላቅ ተጋድሎ ይኖሩ ነበር፤ አህልም አይቀምሱም፤ በየቀኑም አምስት ሺህ ስግደትን ይሰግዳሉ፡፡ በእርሳቸውም የተጋድሎ ዘመን ደጋግ የሆኑ ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃና አጽብሓ ነገሡ፡፡
ነገሥታቱም ሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃንን እጅግ በጣም ይወዷቸው ነበር፡፡ አባታችንም በእንዲህ ዓይነት ተጋድሎ ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን የብርሃን እናቱ #ድንግል_ወላዲተ_አምላክ ለአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ተገልጣላቸው ‹‹ዲቁናና ቅስናን መቀበል ይገባሃል፣ ለጵጵስና ተዘጋጅ፣ #እግዚአብሔር ይህችን ከፍ ያለችውን ማዕረግ ሰጥቶሃልና የልጄ ወዳጅ ሆይ በጸሎትህና በልመናህ በስብከትህም የኢትዮጵያ ሰዎች ሁሉ ይድናሉ፣ በእጅህ ጥምቀትንና ሥጋ ወደሙን ይቀበላሉ›› አለችው፡፡ #ጌታችንም እንዲሁ ተገልጦላቸው ‹‹ወደ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አትናቴዎስ ሄደህ ከፍ ያለችውን ማዕረግ ተቀብለህ የኢትዮጵያን ሰዎች አጥምቅልኝ፣ ነቢዩ ዳዊት ስለ እነርሱ ‹ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ #እግዚአብሔር ትዘረጋለች› ብሎ ተናግሯልና›› አላቸው፡፡ ነገሥታቱ አብርሃንና አጽብሓ ነገረ #ክርስቶስን እያሰቡ ስለ ጥምቀት ልጅነት ይጨነቁ ነበር፡፡ ከሊቀ ካህናቱም ጋር በዚህ ጉዳይ ሲጨዋወቱ ሊቀ ካህናቱ ስለ አቡነ ሰላማ ነገሯቸው፡፡ ነገሥታቱም አቡነ ሰላማን አስጠርተው ስለነገረ #ክርስቶስ ምሥጢር እንዲያስረዷቸው ጠየቋቸው፡፡ አባታችንም ‹‹ነቢያት በ #መንፈስ_ቅዱስ ተቃኝተው አካላዊ ቃል #እግዚአብሔር_ወልድ ይወለዳል ካሉበት ጀምሮ የልደቱን፣ የትምህርቱን የጥምቀቱን፣ የስቅለቱን፣ የሞቱን፣ የትንሣኤውንና የእርገቱን ነገር ሌላውንም ሁሉ ተንትነው አስተማሯቸው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም በ #ጌታ ተሾመው ዓለምን ዞረው ማስተማራቸውን እንዲሁ ተረኩላቸው፡፡ ነገሥታቱም ይህንን በሰሙ ጊዜ እጅግ ደስ ብሏቸው ፍሬምናጦስን ‹‹ወንድማችን ሆይ! ይህን ሥርዓት በሀገራችን እንድታስፋፋ›› አሏቸው፡፡ አባታችን ግን ‹‹ለዚህ የሚያበቃ ሥልጣን ያለው እንጂ ለእኔ አይቻለኝም›› አሉ፡፡ ነገሥታቱም ‹‹ይህን የሚችል ማነው?›› ብለው ቢጠይቋቸው ‹‹በእስክንድርያ ጳጳሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን የሚሾም አባት አለ አሏቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ነገሥታቱ ወደ እስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቅዱስ አትናቴዎስ ደብዳቤ በመጻፍ ‹‹አባታችንና መምህራችን ሆይ! የምንጠይቅህን እሺ በጀ በለን ይኸውም ወደ ጽድቅ ጎዳና የሚመራንን ጳጳስ ሹምልን›› በማለት ብዙ ወርቅና ብር ገጸ በረከት አስይዘው ከብዙ ሊቃውንት ጋር ፍሬምናጦስን ወደ እስክንድርያ ላኳቸው፡፡
ከዚህም በኋላ አባታችን ከነገሥታቱ አብርሃና አጽብሓ ጋር ተማክረው ወደ እስክንድሪያ ሄደው በቅዱስ አትናቴዎስ እጅ በአገራችን ላይ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ታኅሳስ 18 ቀን ተሾሙ፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ ከሾሟቸውና ከመረቋቸው በኋላ ለአቡነ ሰላማና አብረውት ለነበሩ ሊቃውንት መጻሕፍተ ብሉያትን፣ መጻሕፍተ ሐዲሳትንና ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ታቦተ #ማርያምን፣ ታቦተ #ሚካኤልንና ታቦተ #ገብርኤልን አስይዘው ለነገሥታቱም ደብዳቤ ጽፈው ከብዙ ገጸበረከት ጋር በታላቅ ክብር ሸኟቸው፡፡ ቅዱሳን የሚሆኑ ሁለቱ ነገሥታትም አቡነ ሰላማ ከእስክንድርያ ተሾመው መምጣቸውን በሰሙ ጊዜ ‹‹የኢትዮጵያ ሰዎች ሁላችሁ እስከ 40 ቀን ተሰብሰቡ›› ብለው አዋጅ አስነገሩ፡፡ አባታችንንም በደብረ ሲናም ሄደው አገኟቸውና ከዚያች ቀን ጀምሮ ሕዝቡም ሁሉ እስከ 40 ቀን ድረስ ተጠመቁ፡፡ በዚያችም ዕለት #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በዚያች በደብረ ሲና አገር ላይ ወረደና ሕዝቡን ሁሉ ባረኮ ተመልሶ ሲያርግ ከአባ ሰላማ በቀር ያየው አልነበረም፡፡ ወደ አክሱምም ሄደው ቅዱሳን ነገሥታቱም የአድባራት ሁሉ የበላይ የምትሆን የቅድስት ጽዮንን ቤተ ክርስቲያን በወርቅና በዕንቊ ሠሯትና አባ ሰላማ ባርከው ቀደሷት፡፡ ታቦተ ጽዮንም ከድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት አብርሃና አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በ #መንፈስ_ቅዱስ ገብታ ተገኘች፡፡
አባታችን በ #እመቤታችንም በዓለ ዕረፍት ጥር 21 ቀን በውስጧ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀድሱ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በግራ በቀኝ እየተራዷቸው እርሳቸውም ከምድር ሦስት ክንድ ከፍ ብለው ሥርዓተ ቅዳሴውን ፈጽመው ለነገሥታቱና ለሕዝቡም ሁሉ አቆረቧቸው፡፡ የዚያን ዕለትም እጅግ ታላቅ በዓልን አደረጉ፡፡

እነዚህም ቅዱሳን ነገሥታት ትምህርተ ወንጌልን እየሰጡ በአክሱም ቤተ መንግሥታቸው ሳሉ ከዕለታት አንደኛው ቀን #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ በአክሱም ‹‹ማይ ኰኩሐ›› በሚባል ተራራ ላይ ቁሞ አብርሃ ወአጽብሓን ጠርቶ ‹‹በዚህች ቦታ ላይ ቤተ መቅደሴን አንጹልኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም ቦታው ባህር ላይ ነው በየት እናንጽልህ?›› አሉት፡፡ #ጌታችንም በጥበቡ ከገነት ጥቂት አፈር አምጥቶ በባሕሩ ላይ ቢበትንበት ባሕሩ ደርቆ ሜዳ ሆነ፡፡ በዚህ ጊዜ #ጌታችን ‹‹ቤተ መቅደሴን በዚህ ሥሩ›› ብሏቸው ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ #ጌታችንም በቆመባት ዓለት ላይ የእግሩ ጫማ ቅርጽ እስከ አሁን ሳይጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡ ቦታውም ከዚያ ወዲህ ‹‹መከየደ እግዚእ›› እየተባለ ይጠራል፡፡
ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሓ ከመንግሥት አስተዳደሩ ጋር ክርስትናንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በመላ ኢትዮጵያ በማዳረስ እጅግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል፡፡ ካህናትንና ዲያቆናትን ይዘው በመላ ኢትዮጵያ ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ ሕዝቡን ሁሉ እያስተማሩ፣ ሃይማኖትን እያጸኑ፣ ሥርዓተ ጥምቀትን እያስፋፉ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል፡፡ በሀገራችን በአራቱም አቅጣጫ ወንጌልን አስፋፍተው ሕግ ሠርተዋል፡፡ የከበሩ ቅዱሳን ነገሥት አብርሃ ወአጽብሓ በእንዲህ ዓይነት ግብር ጸንተው በመኖር #እግዚአብሔርንም ሰውንም አገልግለው ለሀገራችንም ብርሃን አብርተውላት ነው ያለፉት፡፡
ታላቁ አብርሃ በ364 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን እሁድ ዕለት ዐረፉ፡፡ ከ13 ዓመት በኋላ ታናሹ አጽብሓ በ379 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን ዐረፉ፡፡ ልደታቸውም ሆነ ሞታቸው አንድ ቀን ነው-የዕረፍታቸው ዓመቱ ይለያይ እንጂ፡፡ የተቀበሩበት ቦታም አንድ ነው፡፡ የንግሥና ስማቸው ኢዛናና ዛይዛና ይባላል፡፡
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሐዋርያው_ቅዱስ_ሐናንያ
በዚችም ቀን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ሐዋርያ ቅዱስ ሐናንያ በሰማዕትነት አረፈ ። ይህም ቅዱስ በሐዋርያት እጅ ለደማስቆ አገር ኤጲስቆጶስነት ተሾመ እርሱም ክብር ይግባውና #ጌታችን በደማስቆ ጐዳና ተገልጦለት ለወንጌል ትምህርት በጠራው ጊዜ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስን ያጠመቀው እርሱ ነው ።
እርሱም አስቀድሞ ለግብሪል ወገኖች አስተማረ ብዙዎች በሽተኞችን አዳናቸው ብዙ ሰዎችንም ክብር ይግባውና ወደ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሃይማኖት መለሳቸው ።
ከዚህም በኋላ ስሙ ሉቅያኖስ የሚባል መኰንን ያዘው በምድር ላይ ደሙ እንደውኃ እስከሚፈስ ድረስ ገረፈው ጐኖቹንም በብረት በትሮች ሠነጣጠቀ ደረቱንም በእሳት መብራቶች አቃጠለ ። ከዚህም በኋላ ከከተማ ውጭ አውጥተው በደንጊያ ይወግሩት ዘንድ አዘዘ በዚህም ነፍሱን በ #እግዚአብሔር እጅ ሰጠ ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ሐናንያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_በርተሎሜዎስ
ዳግመኛም በዚህች ቀን አቡነ በርተሎሜዎስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ጻድቁ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ልጆች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ ያመነኮሷቸውና የሾሟቸውም እርሳቸው ናቸው፡፡ የቆባ፣ የጠጠርና የኮረም ኤጲስ ቆጶስ ሆነው ተሹመው በብዙ ድካም አገልግለዋል፡፡ ጻድቁ ደብረ ሊባኖስን የሚያጥኑበት ተራቸው በወርሃ ጳጉሜ ነበር፡፡
ወሎ ራያ ውስጥ ያለችውን ጥንታዊቷንና ባለታሪኳን ደብረ ዘመዳን የመሠረቷት ይኚህ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ የሳላት የ #እመቤታችን ሥዕል ሁልጊዜ ሰዓታትና ማኅሌት በማይታጎልባት በዚህች ጥንታዊ ገዳም ውስጥ ትገኛለች፡፡ እጅግ በርካታ ቅርሶችም ይገኙባታል፡፡ በአካባቢዋም ዘብ ሆነው የሚጠብቋት በርካታ የዱር አራዊት ይገኛሉ፡፡ ጻድቁ በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ኖረው በሰላም ዐርፈዋል፡፡
#ስለ_አቡነ_በርቶሎሜዎስ_ዕረፍት፦ ... ከዚኽ በኋላ በዚያች ቀንና በዚያች ሰዓት #ጌታችን_አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከክብርት እናቱ ከ #እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ከቅድስት ድንግል #ማርያም ጋር ወደ እርሱ መጥቶ ተገለጠለት። ያን ጊዜም መንፈሳዊ አባታችን አባ በርተሎሜዎስ ደንግጦ ወደቀ። እንደምውትም ኾነ። #ጌታችን_አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ደግፎ አንሥቶ "ወዳጄ፤ የእናቴ የድንግል #ማርያምም ወዳጅ በርተሎሜዎስ ሆይ እነሆ ገድልህ ፈጽመሃል። መላእክትህንም በመልካም ተጋድሎ ጨርሰሃል። ስለ ትሕትናህ መረጥሁህ። እነሆ በማይታበል ቃሌ ፍጹም ክብርን ሰጠኹህ። በጸሎትህ አምኖ መቃብርህ ያለበትን ገዳም የሚሳለም ራሱንም ስለ ስምህ ብሎ ዝቅ የአደረገውን ኹሉ ኃጢአቱን ይቅር ብሎ ደስታ የተመላች ገነትን አወርሰዋለሁ"።
"ዝክርህን የዘከረ፣ ስምህን የጠራ፣ መጽሐፈ ገድልህን የጻፈ፣ ይኽንን መጽሐፈ ገድልህንም የጸለየበት፣ በጆሮውም የሰማውን ኹሉ እኔ ስሙን ስምህ በተጻፈበት የወርቅ ዐምደ ሰሌዳ ውስጥ እጽፍለታለሁ። ዕጣንና ዘቢብ መብራት ቅብዐ ቅዱስንም ለቤተ ክርስቲያንህ የሚሰጥ እኔ በመንግሥተ ሰማያት ዋጋውን አላጎድልበትም። መቃብርህ ወደአለበት ወደ ዚኽ ገዳም የሄደ ወይም መቃብርህን የጠበቀውን እኔ የመቃብር ቦታዬ ወደ አለበት እንደሄደ ቆጥሬ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ። በገዳምህ ምንኵስናን ተቀብሎ የመነኰሰውን ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ። አስኬማውንም አስኬማ መላእክት አደርግለታለሁ። በስምህ እንግዳን የሚቀበል ለባልንጀራውም በሚቻለው ኹሉ በጎ ለሚያደርግ ወደ ቀደመ በደሉ ካልተመለሰ በደሉን አላስብበትም። የተጠማን ለሚያጠጣ የተራበን ለሚያበላም በሺህ ዓመት የሚገለጥ የደስታ ሕይወትን ደስ የሚያሰኝ ጽዋዐ ሕይወትን አጠጣዋለሁ"።
"መቃብርህ በአለበት ገዳም የሚቀበረው ኹሉ፤ ስንኳ የሚቀበረውን ተሸክሞው ወደ ገዳምህ የመጡትንም በደላቸውን አላስብባቸውም። ስምህን ጠርቶ በማናቸውም ነገር በጸሎትህ ታምኖ ቢኾን በገዳምህ በመኖር እስከ ዕለተ ሞቱ የአገለገለውን እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ። ወዳጄ በርተሎሜዎስ እነሆ የማይታበል ቃል ኪዳኔን ሰጠኹህ። ብርሕት ሀገርንም አወረስሁህ። አንተ ከወንድሞች መካከል ለአንዱም ስንኳ ገድልህን ሳትነግር በምሥጢር ሰውረህ ነበር፤ እኔ ግን የገድልህን ክብር በዓለም ዳርቻዎች ኹሉ ገልጬ በዐሥራ አምስቱ አህጉራተ ገነት በአምስቱ አህጉራተ መንግሥተ ሰማያትም እሾምሃለሁ"።
#ጌታችንና_አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱ_ከርስቶስ ለአባታችን አባ በርተሎሜዎስ ይኽንን ኹሉ ቃል ኪዳን ሰጥቶት በታላቅ ምስጋና ወደ ሰማያት ዐረገ። ከ #ወልደ #እግዚአብሔር_ክርስቶስ በተሰጠው በዚኽ ቃል ኪዳን ምክንያትም ሰው ሊድን ነውና አባ በርቶሎሜዎስ ስለተሰጠው ቃል ኪዳን እጅግ ተደሰተ። "ለ #አንተና ለ #አባትህ ለ #መንፈስ_ቅዱስ ምስጋና ይገባል ለዘለዓለሙ አሜን በእውነት ይኹን ይደረግ" ብሎ በፈጣሪው በ #ጌታችንና_በአምላካችን_በመድኃኒታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት ወድቆ ሰገደ።
አባታችን አባ በርቶሎሜዎስ ግን በከንቱ ምስጋና በሰው ዘንድ ተወድሶ እንዳይኾንበት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻ ተጋድሎውን ለማንም ቢኾን ሊገልጥ አልወደደም ነበር። እርሱ በትዕግሥትና በትሕትና ፍጹም ልቡናውም በፈሪሃ #እግዚአብሔር የተመላ ነውና። እኔስ የገድሉን ነገር ለገዳማውያኑ እመሰክራለሁ፤ ከዕለተ ልደቱ እስከ ዕረፍቱም ከሃይማኖትና ከስብሐተ #እግዚአብሔር በቀር ከአንደበቱ የዚኽ ዓለም ነገር አልወጣም።

በዘመኑ ወደ ቅድስት ደብረ ዘመዳ ከገባ መቶ ዘጠና ዓመት ከዘጠኝ ወራት ኖረ። አስቀድሞ የነበረበት ግን አልታወቀም። ከዚኽ በኋላ ግን ዕለተ ዕረፍቱ እንደቀበረ በጸጋ #መንፈስ_ቅዱስ ዐውቆ ልጆቹ ገዳማውያን መነኰሳትን ሰብስቦ " #እግዚአብሔር ለመረጠው ይገባልና ለዚኽ ገዳም ሹመት አትሽቀዳደሙ። ኃይለ #እግዚአብሔር የአደረበት የቅድስናውና የትምህርቱ ነገር በዓለም ኹሉ የሚነገርለት ከእኔ በኋላ ታላቅ ጻድቅ ሰው መጥቶ በዚኽች ገዳም ይሾማል። ድንቅ ድንቅ ተአምራትም ይደረጋሉ፤ እናንተ ግን እርሱ የአዘዛችሁን ስሙ" ብሎ የገዳሟን ሥርዐት እንደ ቀድሞው አሳሰባቸው።
ከዚኽ በኋላም አባታችን አባ በርቶሎሜዎስ ትንሽ ታምሞ በወርኀ ጥቅምት በአራተኛው ቀን በሦስት ሰዓት ዐረፈ። ያን ጊዜም #ጌታችንና_አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከእናቱ ከእመቤታችን ከቅድስት #ድንግል_ማርያም ጋራ እልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክትንና ነቢያትን ሐዋርያትንም ጻድቃንንና ሰማዕታትን ኹላቸው ቅዱሳንንም በእየክብራቸውና በእየመዓርጋቸው በእየወገናቸውም አስከትሎ መጣ።
ቅዱሳን መላእክትና ሊቃነ መላክትም የ #እግዚአብሔር ሰው ንዑድ ክቡር ገዳማዊ ደግ ጻድቅ አባታችን አባ በርቶሎሜዎስን የብርሃን አክሊል አቀዳጁት። ከፀሐይ ሰባት እጅ የሚያበራ ልብሰ ብርሃንን አለበሱት። በመዝሙር ዳዊት በአንድ ቃል "የጻድቅ ሰው ዕረፍቱ በ #እግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው። የጻድቅ ዝክርም ለዘለዓለም ይኖራል። ጻድቅስ እንደ ሊባኖስ በዝቶ ያፈራል። እሊኽም በቤተ #እግዚአብሔር የተተከሉ ናቸው"። ይኽንና የመሳሰለውንም ኹሉ እየዘመሩ ወደ ሰማያት አሳረጉት። #ጌታችንና_አምላካችን_መድኃኒታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስም "ንጽሕት ነፍስ ወደ ዕረፍትሽ ግቢ እኔ #እግዚአብሔር ረዳትሽ ነኝና። ከብዙ ፃማ ሥጋም (ደካማ) አሳርፌ ፍጹም ደስታ ወደአለበት ወስጄ በዘለዓለም በዚያ ትኖሪያለሽ" ብሎ የአባታችን የአባ በርቶሎሜዎስን ክብርት ነፍሱን ተቀበሎ ደስ አሰኛት።
የአባታችን አባ በርቶሎሜዎስ ገዳማውያን ደቀ መዛሙርትም ጽኑ ለቅሶን አለቀሱለት። በግምጃ ልብስም ገንዘው በታላቅ ክብር ወደ ቤተ መቅደስ አግብተው በበዐቱ ቀበሩት።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_4
#የአብርሃ_ወአጽብሐ_ታሪክ_በገዳሙ_የታተመ #ከገድላት_አንደበት)