#በዕረፍታቸው ዕለት ጥቅምት 4 ቀን በዋዜማው የቤተ መቅደሱ ምሰሶ ማርና ወተት ያፈልቅ የነበረው ጥንታዊው የ #አብርሃ_ወአጽብሓ ፍልፍል ቤተ መቅደስ!
በአገራችን 154 አብያተ ክርስቲያናትን ያሠሩ ሲሆን 44ቱ ፍልፍል ናቸው፡፡በተለይም ገርዓልታ ያለው ቀመር ዐርባዕቱ እንስሳ ፍልፍል ቤተ መቅደስ በሩ በራሱ ጊዜ ይከፈታል ይዘጋል እንጂ ሰው አይከፍተውም አይዘጋውም፡፡ በዚህ በፎቶው ላይ የሚታየው ጥንታዊው የአብርሃ ወአጽብሓ ፍልፍል የቤተ መቅደሱ ምሰሶ በዕረፍታቸው ዕለት ጥቅምት 4 ቀን በዋዜማው ማርና ወተት ያፈስ ነበር፡፡በእነርሱም ዘመን አማናዊው #ጥምቀትና #ቍርባን ለመጀመሪያ ጊዜ መጣልን፡፡
ቅዱሳን ነገሥታቱ የአድባራት ሁሉ የበላይ የምትሆን የአክሱም #ቅድስት_ጽዮንን ቤተ ክርስቲያን በወርቅና በዕንቊ ሠሯትና አባ ሰላማ ባርከው ቀደሷት፡፡ #ታቦተ_ጽዮንም ከድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት አብርሃና አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በ #መንፈስ_ቅዱስ ገብታ ተገኘች፡፡የከበሩ ቅዱሳን ነገሥት አብርሃ ወአጽብሓ #እግዚአብሔርንም ሰውንም አገልግለው ለአገራችንም ብርሃን አብርተውላት ነው ያለፉት፡፡ #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ለአብርሃ ወአጽብሓን ተገልጦላቸው ‹‹በዚህች
ቦታ ላይ ቤተ መቅደሴን አንጹልኝ›› ብሎ ያዘዛቸው እነዚህ ቅዱሳን ነገሥታት በሞት ያረፉት በሰማዕትነት ነው፡፡ ሰይጣን በደቡብ አንድ ኢአማኒ በማስነሣት ጦርነት ከፍቶ ሰውን ሁሉ እየገደለ በክርስቲያኖች ላይ ክፉ በደል እየፈጸመ መሆኑን ቅዱስ አብርሃ በ #መንፈስ_ቅዱስ ተገልጾለት ዐወቀ፡፡ በዚኽም ጊዜ በመረረ ኀዘን ወደ #እግዚአብሔር ጸሎት አቀረበ፡፡ እርሱም በሰማዕትነት ያርፍ ዘንድ #ጌታችንን ለመነው፡፡ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ጋር መጥቶ ቃል ኪዳን ከሰጠው በኋላ በሰማዕትነት እንደሚሞት ነግሮት በክብር ዐረገ፡፡ ከዚኽም በኋላ ቅዱስ አብርሃ ወደ ጦርነቱ ገባ፡፡ ዐላማው ሰማዕትነትን ለመቀበል ስለነበር በእጁ ጋሻ ጦር አልያዘም፣ሰይፍም በወገቡ አልታጠቀም፡፡ ያንጊዜም አንድ አላዊ ግንባሩን በጦር ወጋውና ንጉሥ አብርሃ ነፍሱን #ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡ አላዊውም አንገቱን በሰይፍ በቆረጠው ጊዜ ደም ውኃ ወተትና ማር ከአንገቱ ፈለቀ፡፡ ቅዱስ አብርሃ በሰማዕትነት ቢያርፍም ጦርነቱ ቀጠለና ክርስቲያኖች ድል አደረጉ፡፡ ንጉሥ አብርሃን የገደለውን ዐላዊ ወንድሙ ቅዱስ አጽብሓ ፊት ባቀረቡት ጊዜ ወንድሙ አብርሃ አስቀድሞ ነግሮት ነበርና በቍጣ ሳይሆን በፍቅር ተመለከተው፡፡ ሃይማኖትንም አስተምሮ አሳምኖት አጠመቀው፡፡ የወንድምን ገዳይ በፍቅር ተቀብሎ አስተምሮ ማጥመቅ እንዴት ያለ ፍቅርና ሐዋርያነት ነው በእውነት! ንጉሥ አጽብሓም እንደ ወንድሙ አብርሃ ሕይወቱን በድንግልና ለማሳለፍ ዐላማው ነበር፡፡ ነገር ግን ዘር ይተካ ዘንድ #እግዚአብሔር ስላዘዘው በ53 ዓመቱ ቅዱስ ጋብቻ ፈጽሞ ሚስቱ ወዲያው ፀነሰች፡፡ ወንድ ልጅም ወለደችና ስሙን አስፋህ ብለው ሰየሙት፡፡ ከ12 ዓመት በኋላ የክብር ባለቤት #ጌታችን ለቅዱስ አጽብሓ ተገልጦለት ቃልኪዳን ገባለትና እርሱም እንደወንድሙ በሰማዕትነት እንደሚያርፍ ነገረው፡፡ ንጉሥ አጽብሓ ስለቀናች ተዋህዶ ሃይማኖቱ ክብር ሲል በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ሰማዕት የሆነውም በሀገረ ጅማ አብያተ ክርስቲያናትን እያጠፋ ይመዘብር ክርስቲያኖች ይገድል የፈጣሪን ክብር ይግባውና ስም ይሳደብ ከነበረ አንድ ከሃዲ ጋር በተደረገ ጦርነት ነው፡፡ በዚህም ጦርነት ቅዱስ አጽብሓ ሰማዕት ቢሆንም ክርስቲያኖች ግን ዳግመኛ ድል ማድረግ ችለዋል፡፡ በ #ክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ያረፉ የቅዱሳኑ ነገሥታት የአብርሃ ወአጽብሓ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!

#ምድሪቱን ባርከው ወተት ያፈለቁት ጻድቅ!
አባታችን #በርተሎሜዎስ የጎንደር አውራጃ ምድረ እንፍራንዝን ተሻግሮ ምጽራሓ በሚሏት ደሴት ውስጥ አደረ፡፡ በዚያም የአባ አኖርዮስን ልጅ ቅዱስ አባ ጌርሎስን አገኘው፡፡ ከእርሱ ጋራም ብዙዎች ቀናትን ኖረ፡፡ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡለት፡፡ አንዱ ተአምርም አባ ያፍቅረነ እግዚእና አባ በርተሎሜዎስ በአንድነት ቆመው ሳለ መንፈሳዊ አባታችን ጻድቅ በርተሎሜዎስ በቆመበት በኩል ከምድር ወተት መነጨ፡፡ አባ ያፍቅረነ እግዚእ በቆመበት ሥፍራም ውኃ መነጨ፡፡ አባታችን አባ በርተሎሜዎስም ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆንበት ‹‹ሰይጣን ወተትን ከምድር በማመንጨት ለማሳት እንደዚኽ ይፈታተነኝን!›› ብሎ እያሰበ ስለዚኽ ነገር እጅግ አዘነ፡፡ አባ ያፍቅረነ እግዚእም በ #መንፈስ_ቅዱስ ዐውቆ ‹‹ይኼ በ #እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ ከሰይጣን ስላልኾነ ስለምን ታዝናለህ? #እግዚአብሔር እኮ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ አድርጎ መርጦሃል›› አለው፡፡
አባታችን አባ በርተሎሜዎስ በከንቱ ምስጋና በሰው ዘንድ ተወድሶ እንዳይኾንበት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ተጋድሎውን ለማንም ቢኾን ሊገልጥ አልወደደም ነበር፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ #ጌታችን ቃልኪዳን ሲሰጣቸው ‹‹አንተ ከወንድሞች መካከል ለአንዱም ስንኳ ገድልህን ሳትነግር በምሥጢር ሠውረህ ነበር፤ እኔ ግን የገድልህን ክብር በዓለም ዳርቻዎች ኹሉ ገልጬ በዐሥራ አምስቱ አህጉራተ ገነት በአምስቱ አህጉራተ መንግሥተ ሰማያትም እሾምሃለሁ፡፡›› ዘመኑም ወደ ቅድስት ደብረ ዘመዳ ከገባ መቶ ዘጠና ዓመት ከዘጠኝ ወራት ኖረ፡፡
ንዑድ ክቡር አባታችን አባ በርተሎሜዎስ ታቦቷን ወደ ዋሻው ቤተ መቅደስ ውስጥ በአገባበት ጊዜ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም የአደረገችለት ተኣምር ይኽ ነው፡- መቆሚያውን በዋሻው በር እጅግ በደረቀች ዐለት ላይ አደረገ፡፡ በአንዲት ዕለትም ቆሞ ሳለ ጣዕሙ ወተት የሆነ ነጭ ውኃን ከእግሩ በታች አፈለቀችለት፡፡ ወንድሞቼ ሆይ! #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ለወዳጆቿ የምታደርገው ዕፁብ ድንቅ ነው! ለዚኽ ተኣምርም አንክሮና ምስጋና ይገባዋል፡፡ ንዑድ ክቡር አባታችን አባ በርተሎሜዎስም ጣዕሙም እንደ ወተት የኾነ ነጭ ውኃ በአየ ጊዜ ይኽን ተኣምር አደነቀ፡፡
ጻድቅ አባታችን አባ በርተሎሜዎስም ይኽንን አይቶ ለእመቤቱ ለ #ድንግል_ማርያም ‹‹ቀድሞ ለሌሎች ቅዱሳን ያልተደረገን ለእኔ ከአደረግሽልኝስ እለምንሻለሁ፤ እሺ በይኝና ከእግሬ በታች ያመነጨሽውን ይኽንን መልኩን ለውጠሸ ጣዕሙም በልክ እንዲኾን አድርጊልኝ፡፡ ይኽ ዛሬ የመነጨ ውኃማ ለዘወትር ከኾነ የሀገሩ ሰዎችና መኳንንቱ ለራሳቸው መሻት ይቀሟቸዋል እንጂ ለልጆቼ ገዳማውያን አይጠቅማቸውምና ጣዕሙ በልክ ይኹን፡፡ ለገዳማውያን ልጆቼ ተስፋ ይኾናቸው ዘንድ ግን ሀብተ ረድኤትሽ አይለየን›› ብሎ ለመናት፡፡
#እመቤታችን_ወላዲተ_አምላክ ቅድስት ድንግል #ማርያምም ልመናውን ኹሉ የምትቀበል ናትና ወተትነቱን ወደ ውኃ ለወጠችው፡፡ የእመቤታችን የ #ወላዲተ_አምላክ የቅድስት ድንግል #ማርያም ጸሎቷና በረከቷ፤ የጻድቁ አባታችን የአባ በርተሎሜዎስም ቃል ኪዳን ኹላችንን ከድንገተኛ ሞት ያድነን፤ ሀገራችንን ሰላም ያድርጉልን አሜን።

#የአባ_ሎጥ ደቀ መዝሙር አባ ጴጥሮስ ስለ አባ አጋቶን እንዲህ ብሏል፦ አንድ ጊዜ በአባ አጋቶን በአት እያለሁ አንድ ወንድም መጣና አባ አጋቶንን "ከወንድሞች ጋር መኖር እሻ ነበር፤ እስቲ አብሬያቸው መኖር እንዴት እንዳለብኝ ምከረኝ" ሲል ጠየቀው። አባ አጋቶንም "በኑሮህ ሁሉ የእንግዳ ሰው አይነት ልቡና ይኑርህ፤ ልክ በመጀመሪያ ያገኘሃቸውን ቀን የምትሆነውን አይነት። በጣምም አትቅረባቸው፣ በጣምም አትራቃቸው"። አለው በዚህን ጊዜ አባ መቃርዮስ "ይህ መቀራረብ ምን ያስከትላል"? ሲል ጠየቀው። አባ አጋቶንም "ያማ እንደ አውሎ ነፋስ ያለ ሃይለኛ ነው"! ሊንሳፈፍ የሚችለውን ሁሉ እያነሣ የዛፎችን ፍሬ ያበላሽባቸዋል። አባ መቃርዮስም "ያለ መጠን መናገር ይህን ያህል ይጎዳል እንዴ" ብሎ ጠየቀ አባ አጋቶንም "የማይቆጣጠሩትን ምላስ ያህል መጥፎ ፆር የለም፤ እርሷ የፈተና ሁሉ እናት ናት። ስለሆነም እውነተኛ የሥራ ሰው አይጠቀምባትም፤ አንዲት ትንሽ አልጋ የነበረችው አንድ ወንድም አውቃለሁ፤ እርሱ በበአቱ ለረዥም ዘመናት ከኖረ በኋላ "ያችን አልጋ ሳልጠቀምባት ከበኣቴ ወጣሁ፤ ምክንያቱም እዛ መኖሯን የነገረኝ ሰው አልነበረምና" ይል ነበር። ጠንካራ መነኩሴ ማለት ተዋጊ ነው።
#በበረሓ_ጉያ_ውስጥ
#በበረሓ_ጉያ_ውስጥ
#ንስሐ_በቀራንዮ_በመስቀል_ላይ_እኛን_ለማዳንና_ከኃጢያት_ባርነት_ነጻ_ለማውጣት_የፈሰሰልንን_የክርስቶስ_ደም_እንድናስብ_የሚያደርግ_መንፈሳዊ_ሃብት_ነው!
#ንስሐ ኃጢያትን የምንቃወምበት ልቦናችንን ከሥጋዊ ፈቃድ የምናነጻበትና ነገረ መስቀሉን ለማሰብ የሚያስችለውን ጥልቅ መንፈሳዊ ፍቅር የምናገኝበት መንፈሳዊ ስጦታ ነው። በ #ንስሐ ከኃጢያት ያልነጻ ልቡና ፍቅረ #እግዚአብሔር ስለማይኖረው የተደረገለትን አምላካዊ ቸርነት አያስተውልም። ስለዚህ #ንስሐ ገብተን ልቦናችንን ለፍቅረ #እግዚአብሔር ማዘጋጀት ይገባናል።
#ይቀጥላል......

#ጥቅምት_5
#አንድ_አምላክ_በሆነ_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም
ጥቅምት አምስት ቀን የታላቁ አባት #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ (ገብረ ሕይወት) የዕረፍታቸው መታሰቢያና ቃልኪዳን የተቀበሉበት ቀን፣ የቊስጥንጥንያው #ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ጳውሎስ እረፍት፣ የሐዋርያው #ቅዱስ_ያዕቆብ_ወልደ_እልፍዮስ መታሰቢያው፣ የከበረ ጳጳስ #ቅዱስ_ኪራኮስ ከእናቱ #ከቅድስት_ሐና ጋራ በሰማዕትነት ያረፈበት ቀን ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ
#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ፦ ትውልድ አገራቸው ደቡባዊ ግብፅ ከቆላው ልዩ ስሙ ከንሒሳ አካባቢ ነው፡፡ አባታቸው ስም ቅዱስ ስምዖን እናታቸው ስም ቅድስት አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ወላጆቻቸው በ #እግዚአብሔር ፊት ደጋጎች የነበሩ ቢሆኑም አቅሌስያ መካን ሆና ልጅ በማጣቷ እያለቀሰች 30 ዘመን ኖራለች፡፡
ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ እናታቸው ቅድስት አቅሌስያ የ #አብ የ #ወልድ የ #መንፈስ_ቅዱስ ሥዕል ካለበት ፊት ለፊት በመቆም #እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣት ዘንድ አልቅሳ ስትለምን ያንጊዜ ከሥዕሉ ቃል ወጥቶ "ክቡሩ ከሰማይ ከምድር ከፍ ከፍ የሚል፣ ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር በክብር የሚተካከል ክህነቱ እንደ መልከጼዴቅ ንጽሕናው እንደ እንደ ነቢይ ኤልያስ፣ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ የሆነ በክብር ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር የሚተካከል ልጅ ትወልጃለሽ" አሏት። ይኸውም ለአንቺ ብቻ አይደለም ለዓለሙ ሁሉ ነው እንጂ። ያን ጊዜ ከሦስቱ አንዱ ተነሥቶ በእጁ ባርኮ በሰላም ወደ ቤትሽ ግቢ አሏት"። እርሷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ገባች፡፡
ቅድስት አቅሌስያም በመጋቢት 29 ቀን ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ቀን ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ እንደወለደች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ "የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ #መንፈስ_ቅዱስ ይሁን" አላት፡፡ ወዲያውም ሕፃኑ ተነሥቶ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለ #አብ ለ #ወልድ ለ #መንፈስ_ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገደ፡፡ ዳግመኛም "ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለ #አብ ለ #ወልድ ለ #መንፈስ_ቅዱስ ምስጋና ይሁን" አለ፡፡
ከ3 ዓመት በኋላም #እግዚአብሔር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን እንዲህ ብሎ አዘዘው፡- "ሕፃኑን ከእናቱ ክንድ ተቀበል፣ ብዙ ገዳማውያን ወዳሉበት ገዳም ውሰድና ከበራቸው አስቀምጠው፣ አበ ምኔቱንም ዘመደ ብርሃንን ከበር አንሥተህ ካንተ ዘንድ አኑረው ስለ ልብሱ ስለ ምግቡ አታስብ ሕፃኑ የ #መንፈስ_ቅዱስ ማደሪያ ነውና ምግቡም መንፈሳዊ ነው ይኸውም ከ #እግዚአብሔር የሚወጣ ቃል ነው፣ ሰው በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ዕወቅ በለው" በማለት አዘዘው፡፡ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም እንደታዘዘው ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን ከእናቱ ክንድ ወስዶ በክንፎቹ አቅፎ ስሞ እስከ ሰባቱ ሰማይ አውጥቶ በ #ሥሉቅ_ቅዱስ ፊት አቅርቦት አስባረከው፡፡ #እግዚአብሔርም መልአኩን "ወደ እናቴ ወደ #ማርያም ውሰደውና ትባርከው" አለውና ወስዶት እመቤታችንም ባረከችው፡፡ ዳግመኛም ከአዳም ጀምሮ ኄሮድስ በግፍ እስካስፈጃቸው ሕፃናት ያሉት ሁሉም ቅዱሳን ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግልና መነኰሳት ሁሉም እንዲባርኩት አደረገው መልሶ ከ #እግዚአብሔር ፊት አቆመው፡፡ #መድኅን_ጌታም ሕፃን ገብረ መንፈስ ቅዱስን "በመንግሥቴ ከእኔ ጋር ትነግሣለህና ደስ ይበልህ፣ በርታ የሚደርስብህን ሁሉ ታገሥ ብዙ ነፍሳት በአንተ ምክንያት ይድናሉ፣ ሰላሜ ከአንተ ጋር ይሆናል" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ መልአኩ አባ ዘመደ ብርሃን ወዳለበት ገዳም አወረደውና ሕፃኑን ከበር ላይ አስቀምጦ እርሱ ወደ ውስጥ ገብቶ #እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉን ነገረው፡፡
አባ ዘመደ ብርሃንም ሕፃኑን አስገብቶ በእንክብካቤ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ እያስተማረ አሳደገው፡፡ ሕፃኑም ትምህርቱን በጨረሰ ጊዜ ዲቁና ተቀብሎ እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ሞገስን የተመላ ሆነ፡፡ ፍጹም የ #እግዚአብሔር ጸጋ አድሮበታልና ሥራው ሁሉ በዕውቀት የተመላና የተቃና ሆነ፡፡ አባ ዘመድ ብርሃንም በሕፃኑ ላይ ያደረበትን ጸጋ እያየ እጅግ ደስ ይለው ስለነበር እንደ ቅዱስ እንጦንስ አስኬማን ሰጠው፡፡ ከዚህም በኋላ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቅስናን ተቀበሉና በጾም በጸሎት ተጠምደው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ እንደ ሐዋርያትም የተአምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጣቸውና ድውያንን የሚፈውሱ፣ ሙታንን የሚያነሡ፣ አጋንንትን የሚያወጡ ሆኑ፡፡
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዳግመኛ ተገልጦላቸው ወደ ሰማይ አሳረጋቸውና ከ #እግዚአብሔር ፊት አቆማቸው፡፡ ያን ጊዜም #ጌታችን ክቡራን የሆኑ እጆቹን ዘርግቶ ከባረካቸው በኋላ "በጸሎትህ ከሲኦል የምታወጣቸው ብዙ ነፍሳት አሉ፤ ድውያንንም ትፈውሳለህ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ገብተህ ከአንበሶችና ከነብሮች ጋር ኑር" አላቸው ቁጥራቸውም ስልሳ ነብርና ስልሳ አንበሶች፡፡አባታችንም #ጌታችንን "የሰጠኸኝ እነዚህ አንበሶችና ነብሮች ምን ይመገባሉ?" አሉት፡፡ #ጌታችንም "የረገጥከውን መሬት ይልሳሉ በዚያም ይጠግባሉ፡፡ ወደ እኔም እስክትመጣ ድረስ ይኸው ምግብ ይሆናቸዋል" አላቸው፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ይህንን በሰሙ ጊዜ ደስ አላቸው፡፡ #ጌታችንም መልአኩን ወደ ቀደመ ቦታቸው ይመልሳቸው ዘንድ አዘዘው፡፡ ከዚህ በኋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከራሳቸው እስከ እግራቸው ድረስ ጠጉር በቀለላቸው፡፡ የጠጉራቸውም ርዝመቱ አንድ ክንድ ከስንዝር ነው፡፡ አባታችንም በታላቅ ተጋድሎ ሲኖሩ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨመረላቸው፡፡ከዕለታት በአንድ ቀን የፈወሳቸው ሕሙማን ብዛታቸው እልፍ ሆነ፡፡ የሀገሩ ሰዎችም ሥራቸውን ስላወቁባቸው አዘኑ፡፡ "ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆንብኝ ተነሥቼ ሰው ወደማያውቀኝ አገር እሄዳለሁ" ብለው ተነሥተው ሄዱ፡፡ሕዝቡም አባታችን እንደተሰወሩ ባወቁ ጊዜ በሀዘን አለቀሱ፡፡
ከዚህም በኋላ አባታችን ወደ ጫካ ገብተው ብቻቸውን የበጋውን ሐሩር የክረምቱን ቁር ታግሰው ምንም ልብስ ሳይለብሱ ራቁታቸውን ሆነው በተጋድሎ ኖሩ፡፡ ከጽኑው ተጋድሎአቸውና ከጫካው ቅዝቃዜ የተነሣ ሰውነታቸው አልቆ ከአጥንታቸው ጋር ተጣበቀ፡፡ ፍራፍሬም ሆነ ምንም ነገር አይመገቡም ውኃም ፈጽሞ አይጠጡም ነበር፡፡ አባታችን በምድረ በዳ እንደሰው ሳይሆን እንደመላእክት ኖሩ፡፡ ቅዱሳን መልእክትም ዘወትር ይጎበኟቸው ነበር፤ ስለምግባቸውም ሰማያዊ ኅብስት አምጥተው ይሰጧቸዋል ነገር ግን አባታችን ያንን ኅብስት አይመገቡትም ይልቁንም ጽዋውን ባሸቱት ጊዜ እንዲሁ ይጠግባሉ ይረካሉ፡፡
ዕድሜአቸው 300 ዓመት በሆነ ጊዜ #ጌታችን "ወደ ኢትዮጵያ ሂድ በዚያም ከደይን የምታወጣቸው ነፍሳት አሉ" አላቸው፡፡ አባታችንም "አምላኬ ሆይ ወደዚያች አገር ማን ያደርሰኛል?" አሉት፡፡ #እግዚአብሔርም "እኔ በሥልጣኔ አደርስሃለሁ" ካላቸው በኋላ ከእርሳቸው ተሰወረ፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን ስድሳ አንበሶችና ስድሳ ነብሮች እየተከተሏቸው ወደ አገራችን ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም ከእነዚሁ ተከታዮቻቸው ጋር በነፋስ ሠረገላ ጭኖ ምድረ ከብድ አደረሳቸው፡፡ ዳግመኛም "ደብር ቅዱስ" ወደሚባለው ወደ ዝቋላ ወሰዳቸው፡፡ አባታችንም በውኃው ዳር ቆመው ምሥራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣ ደቡቡን በመለከቱ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰዎች ኃጢአታቸው በፊታቸው የተገለጠ ሆነ፡፡ ሰው የገዛ ፊቱን በመሥታወት እንደሚያይ የኃጥአንም ሥራቸው በአባታችን ፊት እንዲሁ የተገለጠ ነውና፡፡

0አባታችንም የኢትዮጵያን ሰዎች ኃጢአታቸውን በግልጽ በተመለከቱ ጊዜ ተወርውረው ወደ ባሕሩ በመግባት ተዘቅዝቀው መጸለይ ጀመሩ፡፡ "ከባሕር እንዳልወጣ፣ በእግሬም እንዳልቆም በሕያው ስምህ ምያለሁ" ብለው አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ቆዩ፡፡ በ40ኛ ቀናቸው የታዘዘ መልአክ መጥቶ "ስምህን የጠራ መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ ብሎሃ" አላቸው፡፡ አባታችንም መልአኩን "መላ ኢትዮጵያን ካልማረ ከዚህ ባሕር አልወጣም" አሉት፡፡ መልአኩም ከእሳቸው ተለይቶ ከሄደ በኋላ አባታችን በዚያ ባሕር ውስጥ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖሩ፡፡
አባታችንም በባሕሩ ውስጥ ተዘቅዝቀው መቶ ዓመት ሲጸልዩ ከኖሩ በኋላ ደማቸው ፈሶ አለቀና ውኃው ደም መሰለ፡፡ ሥጋቸውም አልቆ አጥንቶቻው እንደበረዶ ሆኑ፡፡ ሰባት ሺህ እልፍ ሦስት መቶ የሚሆኑ አጋንንትም ከአራቱም አቅጣጫ እየመጡ ሰውነታቸውን በፍላፃዎቻቸው ይወጓቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ #ጌታችን ወደ አባታችን መጥቶ ከባሕሩ ዳር በመቆም "ወዳጄ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! መላ ኢትዮጵያን ምሬልሃለሁና ተነሥ ከባሕሩ ውጣ" አላቸው፡፡ አባታችንም አጥንታቸው እንደመርፌ ቀዳዳ ተበሳስቶ ፈጽመው ደክመው ነበርና #ጌታችን በክቡራን እጆቹ ሁለንተናቸውን ቢዳስሳቸው እንደቀድሞው ደህና ሆኑ፡፡ #ጌታችንም ከባረካቸው በኋላ ወደ ምድረ ከብድ እንዲሄዱ ነገራቸው፡፡
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ምድረ ከብድ እንደደረሱ እንደ ዓምድ ተተክለው ሰባት ዓመት ቆመው ጸለዩ፡፡ በዚህም ጊዜ ሰይጣን በቁራ ተመስሎ መጥቶ ሁለት ዐይኖቻቸውን አንቁሮ አጠፋቸው ነገር ግን አባታችን ጸሎታቸውን ሳያቋርጡ ሁለት ሳምንት በጸሎት ቆዩ፡፡ ከ2 ሳምንት በኋላ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው በዐይኖቻቸው ላይ እፍ ብለው ብርሃናቸውን ከመለሱላቸው በኋላ አባታችንን "ከሰማይ ፍጹም ኃይል ይሰጥሃልና ጠላቶችህን ትበቀል ዘንድ ወደ ዝቋላ ሂድ" ብለዋቸው ዐረጉ፡፡
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም እንደታዘዙት ወደ ዝቋላ እየሄዱ ሳለ በመንገድ ላይ ከዛፍ ሥር ያረፉ ሦስት ሽማግሌዎችን አገኙ፡፡ አባታችንም ባዩአቸው ጊዜ ለመሰወር ቢያስቡም ሽማግሌዎቹ ግን ይመጡ ዘንድ ጠሯቸውና "በ #እግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነናል ሦስታችንንም በጀርባህ አዝለህ አንድ አንድ ምዕራፍ ሸኘን" አሏቸው፡፡ አባታችንም ሽማግሌዎቹን በቀረቧቸው ሰዓት ሽበት የከበባቸው የደከሙ ሽማግሌዎች ሆነው አገኟቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን አንደኛውን ሽማግሌ አዝለው ከአንድ ምዕራፍ አደረሷቸው፡፡ ያም ሽማግሌ "ከዚህ አሳርፈኝ፣ አንተ ደክመሃል የማትበላ የማትጠጣ ነህና" አሏቸው፡፡ አባታችንም "አባ የት ያውቁኛል?" አሏቸው፡፡ ሽማግሌውም "አሁን ደግሞ ሄደህ ጓደኞቼን አምጣልኝ" አሏቸው፡፡ አባታችንም የቀሩት ሁለቱ ሽማግሌዎች ካሉበት ደርሰው ሁለቱንም በየተራ እያዘሉ የመጀመሪያውን ካደረሱበት ቦታ አደረሷቸው፡፡ ከዚህም በኋላ እነዚያን ሽማግሌዎች "አባቶቼ ሆይ! ከየት ነው የመጣችሁት?" አሏቸው፡፡ ሦስቱም ሰዎች ተነሥተው ቆሙና ለአባታችን በአንድነት በሦስትነት ተገለጡላቸው፡፡ አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ ሆኑ፡፡ #ሥሉስ_ቅዱስ ለአብርሃም በመምሬ አድባር ሥር በአንድነት በሦስትነት እንደተገለጡለት ሁሉ አሁንም ለአባታችን ለገብረ መንፈስ ቅዱስ በአንድነት በሦስትነት ተገለጡላቸው፡፡ በጀርባቸውም አዘሏቸው፡፡ የ #እግዚአብሔርንም ክብር ስላዩ አባታችን ፊታቸው እንደፀሐይ አበራ፡፡ ቅዱሳን መላእክት ወርደው እንደሻሽ ተነጥፈው ሲያመሰግኑ ሰማይና ምድር ተነዋውጠው ተራሮች ኮረብቶች ዓለቶች ተሰነጣጠቁ፡፡ በዚያችም ሰዓት ታላቅ ፍርሃት ሆነ፡፡ አባታችንም ዙሪያቸውን በከበባቸው በምሥጢራት ጎርፍ ተውጠው ተንቀጥቅጠው በግንባራቸው ወደቁና እንደ በድን ሆኑ፡፡በራእይ ውስጥም ሆነው እነዚያ ሽማግሌዎች አባታችንን እስከ ሰባተኛው ሰማይ እንዳደረሷቸው ተመለከቱ፡፡ ከዚህም በኋላ #ጌታችን ሐዋርያትን እንደ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደቀሰቀሳቸው አባታችንንም ቀሰቀሳቸውና "ወደ ዝቋላ ውረድ መቶ ዓመት ሙሉ አጥንትህን ሥጋህን እየነደፉ የተዋጉህን አጋንንት ታጠፋቸው ዘንድ፡፡ እነሆ እኔ እንደወሰድኩህ ባለማወቃቸው በትዕቢት ላይ ናቸውና "በባሕር ውስጥ አለ" ይሉሃል፡፡ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ይረዱሃል፤ መባርቅትም በፊት በኋላ ይከተሉሃል" አላቸው፡፡
ያንጊዜም አባታችን በመብረቅ ላይ ሆነው እነዚያ አጋንንት ወዳሉበት ወረዱ፡፡ አጋንንቱንም ደመናት ከበቡአቸው፣ መላእክትም በእሳት ሰይፍ መተሩአቸው፣ በመብረቅ አጨዷቸው፤ አመድ ሆነው በነፋስ በተኗቸው፡፡ የእነዚያም አጋንንት ቁጥራቸው ሰባ ሺህ እልፍ ከአንድ ሺህ ነበር፡፡ ሁሉም በአንድ ጊዜ አልቀዋልና ከእነርሱ ሸሽቶ ያመለጠም አልነበረም፡፡ ሰባቱ ሊቃነ መላእክትም ወደ ሰማይ ዐረጉ፡፡ አባታችንም አንበሶችና ነብሮች፣ ድብና ዘንዶ ወዳሉበት ምድረ ከብድ ተመለሱ፡፡
አባታችንም ወደ ምድረ ከብድ ከተመለሱ በኋላ #መንፈስ_ቅዱስ የጠራቸው ሦስት ቅዱሳን ሁሉም በየአንበሶቻቸው ላይ ተቀምጠው ወደ ምድረ ከብድ መጡ፡፡ እነዚህም ቅዱሳን የዋልድባው አቡነ ሳሙኤል፣ የአዘሎው አቡነ አንበስ እና ከላዕላይ ግብፅ ተነሥቶ የመጣው አቡነ ብንያም ናቸው፡፡ ነገር ግን አባታችን እነዚህን ቅዱሳን ስለተሰወሯቸው ቅዱሳኑ እስከ ሰባት ቀን ድረስ በምህላ ሰነበቱ፡፡ የአባታችን የሚያስፈሩ አንበሶች ወጥተው የቅዱሳኑን አንበሶቻቸውን ገድለው ደማቸውን አፍስሰው ሥጋቸውን በሉ፡፡ ሦስቱም ቅዱሳን በዚህ ፈጽመው ደንግጠው ሳለ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ 60 ነብሮችንና 60 አንበሶችን አስከትለው ተገለጡላቸውና "ሰላም ለእናንተ ይሁን የ #እግዚአብሔር ቅዱሳኑ አትፍሩ" አሏቸው፡፡ ቅዱሳኑም "አባታችን ሆይ! ጸሎትህ ቅድስት እንደሆነች ባወቅን ጊዜ በ #እግዚአብሔር ፈቃድ እንባረክ ዘንድ ወደ አንተ መጣን፡፡ ነገር ግን ባላገኘንህ ጊዜ እስከ ሰባት ቀን አለቀስን" አሏቸው፡፡ ዳግመኛም "የእርስዎም አንበሶች መጥተው አንበሶቻችንን በሉብን" አሏቸው፡፡ አባታችንም አንበሶቻውን "እስከ ዕለተ ሞቴ ድረስ በእግሬ ከረገጥኩት ምድር በቀር #እግዚአብሔር ያላዘዛችሁን ለምን በላችሁ? አሁንም የበላችሁትን ትፉ" አሏቸው፡፡ እነዚያም አንበሶች አፋቸውን ከፈቱና የበሉትን የአንበሶቹን ሥጋቸውን አጥንታቸውን ከደም ጋር ተፉ፤ በሆዳቸውም የቀረ የለም፡፡ አባታችንም ወዲያው ወደ ምሥራቅ ዞረው #እግዚአብሔር ካመሰገኑ በኋላ "አቤቱ አልዓዛርን ከሞት ያስነሣኸው አንተ ነህና አሁንም እነዚህን አናብስት ከሞት አስነሣቸው፤ ለባሮችህም የድካማቸውን ማረፊያ ይሆኑላቸው ዘንድ የሰጠሃቸውን አትከልክላቸው… " እያሉ ጸለዩ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ብለው ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ የአንበሶቹን ሥጋቸውን በ #መስቀል ምልክት ባርከ "በ #ጌታዬ_በፈጣሪዬ_በኢየሱስ_ክርስቶስ ኃይል ተነሡ"አሏቸው፡፡ አንበሶቹም እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥነው ተነሡና እንደቀድሞው ሆኑ፡፡ ለአባታችንም እጅ ነሥተውና ሰግደው የእግሩን ትቢያ ላሱ፡፡ አባታችንም ወደ ጌቶቻቸው መለሳቸው፡፡

እነዚህም ሦስቱ ቅዱሳን በአባታችን ላይ አድሮ ድንቅ ነገርን የሚሠራ #እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ የዋልድባው አቡነ ሳሙኤልም አባታችንን "አባት ሆይ በዚህች ቀን ድንቅ ሥራን አየን፣ አርአያህ የ #እግዚአብሔርን መልአክ አርአያ ይመስላል፣ ቅድስናህ ፍጹም ነው፣ የጸሎትህ ኃይል ሙታንን ያስነሣል፣ የተበሉ አንበሶችን ከአንበሶች ሆድ አወጣህ" አሏቸው፡፡ ቅዱሳኑም ሥራቸውን እያደነቁ በልተው ጠጥተው ጠገቡ፡፡ በማግሥቱም አባታችን ቅዱሳኑን "በሰላም ሂዱ " ብለው መርቀው ሸኟቸውና የ #እግዚአብሔር ሥራ እያደነቁ ወደየበዓታቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡
በመጨረሻም ከዚህ ዓለም የሚለዩበት በቀረበ ጊዜ እንሆ የክበር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ እነሆ ተገለጠላቸው። ስማቸውን ለሚጠራና መታሰቢያቸውን ለሚያደርግ እስከ ዐሥራ አምስት ትውልድ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጣቸው። ዐሥራ ሁለት አክሊል ሰጣቸው። ቅዱስ ሚካኤል ሦስት አክሊሎች፣ ቅዱስ ገብርኤል ሦስት አክሊሎች፣ ቅዱስ ሱራፊ ሦስት አክሊሎችና ቅዱስ ኪሩብ ሦስት አክሊሎችን አቀዳጇቸው። የዕድሜያቸውም ዘመናት አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሲሆን መጋቢት5 በሰላም በፍቅር ዐረፉ። #ጌታችንም ነፍሳቸውን ተቀቡሎ አቅፎም ሳማት በመላእክትና በቅዱሳን ሁሉ ምስጋና አሳረጋት። ከአባትችን ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!።
ምንጭ፦ የመጋቢት 5 ስንክሳርና ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ጳውሎስ
ጥቅምት አምስት በዚች ቀን የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጳውሎስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከእርሱ አስቀድሞ በቁስጥንጥንያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ለነበረው ለአባ እለእስክንድሮስ ደቀ መዝሙሩ ነው። አባ እለእስክንድሮስም በሞተ ጊዜ በርሱ ፈንታ ይህ አባት አባ ጳውሎስ ተሾመ።
በጵጵስናውም ወንበር በተቀመጠ ጊዜ የአርዮስን ወገኖች ከቊስጥንጥንያ አገር ከአውራጃውም ሁሉ አውግዞ አሳደዳቸው። ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ከሞተ በኋላ ልጁ ሁለተኛው ቈስጠንጢኖስ በቊስጥንጥንያ አገር ላይ ነገሠ ወንድሙ ቊንስጣም በሮሜ ሀገር ነገሠ። ይህ ቈስጠንጢኖስም አርዮስን ይወደዋል በረከሰች ሃይማኖቱም ያምናል ቅዱስ አባ ጳውሎስም አርዮሳውያንን አውግዞ እንዳሳደዳቸው ሰምቶ እጅግ አዘነ።
አባ ጳውሎስንም ከእንግዲህ የአርዮስን ወገኖች ተዋቸው አታውግዛቸው አለው እርሱ ግን ንጉሡን አልሰማውም ስለዚህም አባ ጳውሎስን ከቊስጥንጥንያ አገር አሳደደው።
እንዲህም ሆነ ከእርሱ አስቀድሞ ከእስክንድርያ ሀገር አባ አትናቴዎስን አሳድዶት ነበርና በሮሜ አገር በሊቀ ጳጳሳት በቅዱስ አባ ዮልዮስ ዘንድ ሁለቱም ተሰበሰቡ። እርሱም በመልካም አቀባበል በፍቅር ተቀበላቸው ወደ ንጉሡም ወደ ሁለተኛው ቈስጠንጢኖስ እንዲህ ብሎ መልእክትን ጻፈላቸው "እነርሱ እውነተኞች የተማሩ አዋቂዎች ሃይማኖታቸውም የቀና ናቸው ልትቀበላቸው ልታከብራቸውም ይገባል።"
ሊቃነ ጳጳሳቱም አባ ጳውሎስና አባ አትናቴዎስ ወደ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በደረሱ ጊዜ የመልእክቱን ደብዳቤ ሰጡት አነበባትም ከሮሜው ሊቀ ጳጳሳት ቃል የተነሳ ፈራ። ተቀብሎም በየቦታቸው በሹመታቸው ወንበር አኖራቸውና ጥቂት ቀኖች በእነርሱ ላይ ታገሰ።
ከዚህም በኋላ ሁለተኛ አሳደዳቸው እነርሱም ወደ ሮሜ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ዮልዮስ ተመልሰው ንጉሡ በእነርሱ ላይ ያደረገውን ሁሉ ነገሩት ሊቀ ጳጳሳት ዮልዮስም ወደ ወንድሙ ወደ ንጉሥ ቊንስጣ ይዟቸው ገብቶ ወንድሙ ቈስጠንጢኖስ በእነርሱ ላይ ያደረገውን ነገረው።
ይህም ንጉሥ ቊንስጣ ይቀበላቸው ዘነድ ወደ ወንድሙ መልእክትን ጻፈ እንዲህም ብሎ አዘዘው። እሊህን አባቶች ካልተቀበልካቸው ከእንግዲህ በመካከላችን ፍቅር አንድነት አይሆንም ሊቀ ጳጳሳቱም እንዲሁ ሁለተኛ ደብዳቤ ጻፈ።
ንጉሥ ቈስጠንጢኖስም የወንድሙን የንጉሥ ቊንስጣንና የሊቀ ጳጳሳቱን መልእክት ተቀበሎ ወደ ሹመታቸው ወንበር መለሳቸው።
ንጉሥ ቊንስጣም በአመጸኞች እጅ ከተገደለ በኋላ ያን ጊዜ ቈስጠንጢኖስ አባ ጳውሎስን ወደ አርማንያ አገር አጋዘውና በዚያ ጥቂት ቀን አሠረው። ከዚህም በኋላ ከአርዮስ ወገን አንዱን በእሥር ቤት በሥውር አባ ጳውሎስን ይገድለው ዘንድ አዘዘው አንዱ አርዮሳዊም በሌሊት ገብቶ አንቆ ገደለው መላ ዕድሜውም አርባ ዓመት ነው።
#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሐዋርያው_ቅዱስ_ያዕቆብ_ወልደ_እልፍዮስ
በዚች ቀን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የእልፍዮስ ልጅ የከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ያዕቆብ በሰማዕትነት ያረፈበት መታሰቢያው ነው። ይህም ሐዋርያ በብዙ ሀገሮች ውስጥ ከሰበከ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ ወደ ምኲራብም ገብቶ የክብር ባለቤት የ #ጌታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ሃይማኖት በግልጥ አስተማረ። ከእርሱ ለሚሰሙትም ሁሉ ብዙ ተአምራትን አደረገ። ንጹሕ በሆነ ልቡናም በ #እግዚአብሔር አመኑ። ራሳቸውንም አጸኑ። ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብም በልቡናው አሰበ፡፡ እንዲህም አለ። ሕዝቡ ከእርሱ ሰምተው እንዴት ያምናሉ አለ። እርሱም ሕዝቡ ወደተሰበሰቡበት ወደ ምኩራብ ገባ። ከአይሁድም የተቀመጡ የተሰበሰቡ ብዙ ሰዎችን አገኘ። በፍጹም ታላቅ ደስታ ያስተምራቸው ዘንድም በመካከላቸውም ገባ። ለሁሉም በቃሉ ማስተማሩን አበዛ። ያለመፍራትም ሃይማኖቱን ገለጠ። አንድ ለሆነው ለ #እግዚአብሔር ልጅ ምስክር ሆነ። "የሕይወት ቃል ነው። #ኢየሱስ_ክርስቶስ የዓለም ሁሉ አምላክ ነው። በእውነትም የ #እግዚአብሔር ልጅ ነው። እርሱ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ ከ #አብ ጋር ነበርና። እርሱ በ #አብ አለ፤ #አብም በእርሱ አለ። እርሱ የ #አብ_ቃል ነው። እርሱ ሰውን በአርአያችንና በምሳሌያችን እንፍጠር አለ። እርሱ በሰማይ አለ። እርሱ ከአባቱ ጋር አለ። እርሱ በኪሩቤል ሰረገላ ይቀመጣል። ሱራፌልም ያመሰግኑታል። እርሱ በድንግል #ማርያም ማሕፀን የተወሰነ በልዕልና በገናንነቱ ሥልጣን ነው። እርሱ ድንግል #ማርያም የወለደችው #ጌታችን_እግዚአብሔር_ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው። ሰው የሆነ አምላክ ነው"። አንድ ሰው ስንኳን ሳይፈራ በተሰበሰቡት መካከል የሐዋርያው ምስክርነት ይህ ነበር። በእውነት አንድ ለሆነው ለ #እግዚአብሔር ልጅ ልደትም ምስክር ሆነ። እርሱ ነበርና። በሞቱም፣ በትንሣኤውም፣ ወደ አባቱ ወደ ሰማይ ስለማረጉም ምስክር ሆነ። ለተሰበሰቡትም በ #ክርስቶስ ስለማመን አስተማራቸው።
የተሰበሰቡትም የሐዋርያውን ትምህርት በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ጋር ካለው ከአባታቸው ከሰይጣን የተነሳ በ #ጌታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ሐዋርያ ላይ ፈጽመው ተቆጡ። ሁሉም ተሰብስበው ተቀመጡ። የተሰበሰቡት ሁሉ ደሙን ፈለጉ። ነገሩን የሰሙትም የተባረከ ሐዋርያን ያዙት። ከንጉሥ ከቀላውዴዎስም ወሰዱት። የሐሰት ምስክሮችንም በእርሱ ላይ አስነሡ። ለንጉሡም "ይህን ጥፋተኛ ሰው በሀገሩ በአውራጃው ይዘናል" አሉት፤ "እኔ የ #እግዚአብሔር_የኢየሱስ_ክርስቶስ አገልጋይ ነኝ ይላቸዋል። ለንጉሡ እንዳይገዙም ይከለክላል" አሉት። ስለተባረከው ሐዋርያ ይህን ነገር በሰማ ጊዜም እስከሚሞት ድረስ በድንጋይ ይወግሩት ዘንድ አዘዘ። አይሁድንም #እግዚአብሔር ረገማቸው። ንጉሡ አይሁድን እንዳዘዛቸውም በድንጋይ ወገሩት። ከዚህ በኋላ ቡሩክ የሚሆን የእልፍዮስ ልጅ የሐዋርያው የቅዱስ የያዕቆብ ምስክርነት የካቲት ዐሥር ቀን ሆነ። በኢየሩሳሬም ቤተ መቅደስ ተቀበረ።

#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው በቅዱስ ያዕቆብ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ካራኮስ
በዚችም ቀን የከበረ ጳጳስ ኪራኮስ ከእናቱ ከሐና ጋራ ሰማዕት በመሆን በከሀዲው ንጉሥ በኤልያኖስ እጅ ተገደለ። ከሀዲው ንጉሥም ይህን ቅዱስ ወደ አደባባይ በአቀረበው ጊዜ ሰዎች አማልክትን እንዳያመልኩ እየጻፈች የምትከለክል ይቺ እጅህ ትቆረጥ ዘንድ ይገባታል አለው። ቅዱስ ኪራኮስም ልብ የሌለህ ውሻ መልካም አደረግህ አለው።
ኤልያኖስም ሰምቶ እርሳስ አፍልተው በአፉ ውስጥ እንዲያፈሱት ደግሞ በጋለ የብረት ዐልጋ ፍም በተጐዘጐዘበት ላይ እንዲአስተኙት ጨውም እንዲነሰንሱበት በመጐተትና በማገላበጥም ሆዱንና ጀርባውን በብረት በትሮች ዐጥንቶቹ እስቲሰበሩ እንዲደበድቡት አዘዘ።
ቅዱስ ኪራኮስም ይህን ሁሉ ታግሦ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ጸለየ ያሮክስ ለያማውታ ያለክ አሲያር ለሜዶር ኤሎሄ ናውና ያዮል ያቤል ቊራም ቤተል አዶናይ ኤሎሄ ሙታ።
ከዚህም በኋላ ፈትተው በእሥር ቤት እንዲያኖሩት እናቱንም ሐናን እንዲአመጧት በጠጉርዋም ሰቅለው ሦስት ሰዓት ያህል ሥጋዋን እንዲሠነጣጥቋት በእሳትም እንዲአቃጥሏት አዘዘ በእሳት ውስጥም እየጸለየች ነፍሷን አሳለፈች።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ኪራኮስን አምጥተው እባቦችና እፍኝቶች ከአሉበት ታላቅ ጉድጓድ ውስጥ ይጨምሩት ዘንድ አዘዘ ሲጨምሩትም ምንም የጐዳው ነገር የለም። ከወታደሮችም አንዱ ስሙ አድሞን የሚባል የ #ክርስቶስን ማዳን አይቶ አደነቀ። ክብር ይግባውና በ #ጌታችንም አመነ ንጉሡንና ጣዖታቱንም ረገመ ያን ጊዜም ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ ንጉሥ ኤልያኖስ አዘዘ እርሱም የኪራኮስ አምላክ ነፍሴን ተቀበላት እያለ አንገቱን አስተካክሎ ለሰይፍ ሰጠ ምስክርነቱንም ፈጸመ።
ቅዱስ ኪራኮስንም ከዘይት ጋር ዝፍት ከፈላበት ምጣድ ውስጥ እንዲጨምሩት ሁለተኛም ደረቱን በጦር እንዲወጉት አዘዘ። እንዲህም ምስክርነቱን በዕለተ ሰንበት ፈጸመ።
በተጨማሪ በዚች ቀን የቅዱሳን #አይድራዮስ_አዋርስ_ሰማዕት_አልድራክዎስና #አድሮኖስ መታሰቢያቸው ነው።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_5

🌹የመስከረም_5_ግጻዌ
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_5_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ተሰሎንቄ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ስለዚህም የመልእክትን ቃል እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በምታምኑ ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን።
¹⁴ እናንተ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በይሁዳ የሚኖሩትን በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን የእግዚአብሔርን ማኅበሮች የምትመስሉ ሆናችኋልና፤ እነርሱ ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበሉ፥ እናንተ ደግሞ ያንን መከራ ከአገራችሁ ሰዎች ተቀብላችኋልና።
¹⁵ እነዚያም ጌታን ኢየሱስን ደግሞ ገደሉ ነቢያትንም እኛንም አሳደዱ፥ እግዚአብሔርንም ደስ አያሰኙም፥ ሰዎችንም ሁሉ ይቃወማሉ፥
¹⁶ ሁልጊዜ ኃጢአታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ አሕዛብ እንዲድኑ እንዳንናገራቸው ይከለክሉናልና። ነገር ግን ቍጣው ወደ እነርሱ ፈጽሞ ደርሶአል።
¹⁷ እኛ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ በልብ ያይደለ ፊት ለፊት ለጥቂት ጊዜ አጥተናችሁ፥ በብዙ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት እጅግ ሞከርን፤
¹⁸ ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበርና፥ እኔ ጳውሎስም አንድና ሁለት ጊዜ፥ ሰይጣን ግን አዘገየን።
¹⁹ ተስፋችን ወይስ ደስታችን ወይስ የትምክህታችን አክሊል ማን ነው? በጌታችን በኢየሱስ ፊት በመምጣቱ እናንተ አይደላችሁምን?
²⁰ እናንተ ክብራችን ደስታችንም ናችሁና።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤
¹³ ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።
¹⁴ ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።
¹⁵ ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጒዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤
¹⁶ ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።
¹⁷ ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?
¹⁸ ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው?
¹⁹ ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ሕዝቡም አብረው ተነሡባቸው፥ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ፤
²³ በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥ የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።
²⁴ እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው።
²⁵ በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር
²⁶ ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።
²⁷ የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_5_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወቀተሉ ዕቤረ ወእጓለ ማውታ። ወቀተሉ ፈላሴ። ወይቤሉ ኢይሬኢ እግዚአብሔር"። መዝ. 93(94)፥6-7።
#ትርጉም፦ "ባልቴቲቱንና ድሀ አደጉን ገደሉ፥ ስደተኛውንም ገደሉ። #እግዚአብሔር አያይም፥ የያዕቆብ አምላክ አያስተውልም አሉ"። መዝ. 93(94)፥6-7።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ጥቅምት_5_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቈጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች።
²⁴ መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።
²⁵ የሚከፍለውም ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ።
²⁶ ስለዚህ ባሪያው ወድቆ ሰገደለትና፦ ጌታ ሆይ፥ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው።
²⁷ የዚያም ባሪያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፥ ዕዳውንም ተወለት።
²⁸ ነገር ግን ያ ባሪያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና፦ ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው።
²⁹ ስለዚህ ባልንጀራው ባሪያ ወድቆ፦ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ ብሎ ለመነው።
³⁰ እርሱም አልወደደም፥ ግን ሄዶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወኅኒ አኖረው።
³¹ ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው እጅግ አዘኑ፥ መጥተውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው ገለጡ።
³² ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ፦ አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤
³³ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው።
³⁴ ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው።
³⁵ ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🌹ሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ሠለስቱ_ምዕት_ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል፣ የቅዱስ ኪራኮስ የእናቱ ቅድስት ሐና፣ የአባ ጳውሎስ ሰማዕትና የቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ ወልደ እልፍዮስ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

Forwarded from ቅዱሳን ንዑዳን
#ንስሐ_ከኃጢያት_የሚያነጻ_ቅዱሳን_ሱራፌል_ከመንበረ_ሥላሴ_የወሰዱት_የእሳት_ፍም_ነው!
በእርሱ የኃጢያተኛው ኃጢያት ተወግዷልና #ንስሐም ኃጢያታችን የሚወገድበት ሰይጣንን የምናቃጥልበት እሳት ነው። ኢሳ.6÷4። #ንስሐ ከሕይወታችን ኃጢያትን የምናስወግድበት ብቻ ሳይሆን ከፍርድ መዝገብም ኃጢያታችንን የምናስፍቅበት ብቸኛ መንገድ ነው። #እግዚአብሔርም በነብዩ ኤርሚያስ አድሮ "በደላቸውን እምራቸዋለሁና ኃጢያታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና"። ኤር.31÷34 በማለት የተናገረው ቀድሞ የሠራነውና በፍርድ መዝገብ የተጻፈው ኃጢያታችን የሚደመሰሰው በ #ንስሐ አማካኝነት መሆኑን ሲያስተምር ነው። #መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም በዘመነ ሥጋዌው " #ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ" በማለት ከፍርድ ለመዳን የሚቻለው በ #ንስሐ አማካኝነት ከኃጢያት በመለየት መሆኑን አስረድቷል። ሉቃ.13÷3
#ይቀጥላል.......

#ቃልኪዳን_የጥቅምት_5_አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ
#አንድ_አምላክ_በሆነ_በአብ፣ #በወልድ፣ #በመንፈስ_ቅዱስ ስም አሜን!
፩, የመነኮሳት አባት፣ ጽኑ ተጋዳይ፣ የባሕታውያን አለቃ በሆነ በአባታችን በገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል "ጥቅምት 5" ቀን የሚነበብ ቃልኪዳን ይህ ነው።
፪, ወደ ረጅም ተራራ ሲወጣ ከዕፀ አድኅኖ ጥላ ሥር በሺበት የተሸፈኑ በሦስት ሽማግሌዎች አምሳል " #ሥላሴ"ን አገኛቸው። በጀርባው አዝሎ ወደ ዝቋላ ተራራ አወጣቸው። የ " #ሥላሴ" ስዕል ከተሳለባት ከዕፀ ሥርየት ሥር አስቀመጣቸው።
፫, ከዚህ በኃላ #ሥሉስ_ቅዱስ እስከ ሰባተኛው ሰማይ ድረስ አወጡት። ያክንት መረግድ በተባለ ዕንቁ የተሸለመች የሰማያዊት ኢየሩሳሌምን የሕንፃዋን ጌጥ ውበት አሳዩት። ከእነርሱም ተባረከ። የዝቋላና የምድረ ከብድ ኮከብ፣ ማር፣ እንኮይ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ÷ በ #ሥሉስ_ቅዱስ እጅ ያለውን #መስቀል ተሳለሙ። አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ የኢትዮጵያ መብራት ነው።
፬, ወደ ምድር ከወረደ በኃላ የዐይኖቹ ሽፋሽፍት ሳይከደኑ ሰባት ወር ከ አምስት ቀን ኖረ። #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በወንጌል ከልብ በመነጨ ፍቅር የሚወደኝን እኔ በአእላፍ መላዕክት ፊት እወደዋለሁ። የጠላቶቹን የአጋንንትን መውደቅ አሳየዋለሁ ያለውን አስቦ እንዲህ ሆኖ ኖረ።(ዮሐ.14÷21)
፭, የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልም መጥቶ፣ ጠላቶችህን አጋንንትን ታጠፋቸው ዘንድ ውረድ፣ ከፈጣሪህ ከ #እግዚአብሔር ዘንድ ኃይል ተሰቶሀልና አለው። ቃሉን አልሰማም፣ አልታዘዘለትምም፣ ክፉም ቢሆን በጎም ቢሆን አልመለሰለትም።
፮, ከዚህም በኃላ #መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ መጥቶ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን በደብረ ታቦር አምሳል ወደተጠራ ዝቋላ ኸደ ሚባል ቅዱስ ተራራ ና ውረድ አለው፣ እስከ 100 አመት ድረስ የአባታችን የገብረ መንፈስ ቅዱስ ደም የፈሰሰባት፣ በብርሃን ወደ ተሸለመች ባሕርም።
፯, እመቤታችን ድንግል #ማርያምም የአጋንንትን ጥፋት ታይ ዘንድ ከዚያ ባሕር ዳር ተቀመጠች። መልዐኩ ቅዱስ ራጉኤልም ከሠራዊቱ ጋር የመባርቅት ልብሶችን ለብሶ መጣ፣ ቅዱሳን ሚካኤልና ገብርኤል፣ የመላእክት ወገን ሁሉ የእሳት ነበልባል ለብሰው መጡ። ቦታው እስኪጠባቸው ድረስ ዙርያውን ከበቧት። መላእክት ጭፍቅ እንዳለች እንደሮማን ፍሬ ተጨናነቁ፣ የእግር ጫማ መረገጫ ያህል ቦታስ እንኳ አልተገኘም።
፰, ከመላእክት ብቻ በቀር ሁለመናዋ አይታይም ነበር፣ በእሳት ሰይፎች ታጥራ ነበር እንጂ። በውስጧ የነበሩትን አጋንንትን ሁሉ አጠፏቸው፣ ፍለጋቸውም አልተገኘም። በነፋስ ፊት እንዳለ ትቢያ ሆኑ፣ በበረሃ መካከል እንደሚነድ ጢስ ጠፉ፣ በአሸዋና ሙጫ እንደተደፈነች ጉድጓድም ሆኑ።
፱, የሰው ሥጋ የለበሰ ስራው ክፉ የሆነ፣ አንድ ጋኔን አምልጦ፣ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ የሚወደው ጽኑ ተጋዳይ በሚሆን በገዳማዊ አባ ፍሬ ቅዱስ በአት ትይዩ ባለችው አንዲት ገደል መካከል ተደበቀ። አባታችንም ያቺን ገደል ከሁለት ሰነጠቃት፣ አፏንም ከፈተች።
፲, በዚያች ገደል ላይ ወድቆ፣ ተጥሎ አገኘው፣ በመብረቅ መታው፣ በክፉ አሟሟትም ሞተ። ለእንስሳ ለአራዊት ሁሉ በሽታ እንዳይሆን በመሬት ውስጥ አልተቀበረም፣ ለመጪው ትውልድ ታላቅ ምልክት ይሆን ዘንድ የዋሻው ስንጥቅ እስከዛሬ አለ።
፲፩, ሕዝብ፣ አሕዛብ፣ ነገሥታት፣ መኳንንት፣ ሽማግሌውች፣ ሕጻናት፣ ደናግል፣ መነኮሳት፣ ልዩ ልዩ ልብስ የለበሱ፣ በሐር ልብስ ያጌጡ፣ የከበሩ ወንድች ሴትችም ያዩታል። በተሳሉ ደንጊያዎች አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን እየደበደበ ሲያሰቃየው የነበረ የዚያ ጋኔን አጥንቶቹ፣ መላ ሰውነቱ ሁሉ ወድቆ ይታይ ነበር።
፲፪, አባታችን ይህንን ከፈጸመ በኃላ ከ #ጌታችን_ከመድኃኒታችን_ከኢየሱስ_ክርስቶስ ቃልኪዳን ተቀበለ፣ በአባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገድል የተቀደሰች ይህችን ገዳም የሚሳለሟት ደጅ የሚጠኗት ሁሉ በመንግስተ ሰማያት ተስፋ ያገኛሉ። ከሩቅም ከቅርብም የጻድቁን በዓል ለማክበር ወደ እርሷ የሚመጡትንም ኀጢያት አንዳላገኘው እንደ 40 እንደ 80 ቀን ሕጻን ይሆናሉ።
፲፫, እንደ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፣ 70 ዘመን ሙሉ በሐዘን ፊቱ እንደጠቆረ በምሥጢር ባሕር እንደ ዋኘ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ይሆናሉ።
፲፬, ይህንን ሁሉ አስቦ ከአባታችን በዓላት ከፍ ባለች በከበረች በጥቅምት "5" ቀን የአባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን በዓል ያከበረ ሁሉ፣ በሰው ሁሉ እንደታወቀች እንደ መጋቢት "5" ቀን የሚያያት የሚያከብራትንም ሁሉ #እግዚአብሔር_አብ ከአንተ ጋር የእሳትን ባሕር በግልጥ ይለፍ፣ የመለአከ ሞት የዲያብሎስን ፊት አያይም ብሎ ቃል ገባለት።
፲፭, ከዚህ በኃላ " #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ" ብርሃን በማይታይባት ባሕር ላይ ለሰው ሁሉ መድኃኒት ትሆን ዘንድ የምሕረት ጽዋ አፈሰሱባት።
፲፮, መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል መጥቶ ክብር ይግባውና የ #ጌታችን_የመድኃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስን ደም በባሕር ላይ ጨመረ።
፲፯, ሕንጻዋ ያማረ በ #ሥላሴ ስም የታነጸች አንዲት ቤተ መቅደስ አለች፣ የሕንጻዋ ውበትም ከፀሐይ ሰባት እጅ ያበራል። ያችንም ባሕር ቅዱሳን ይጠብቋታል። ሥጋቸውም ለአይን እንደሚያስደንቅ በምሥራቅ እንደሚወጣ እንደንጋት ኮከብ ይሆናል።
፲፰, ስማቸው የማይታወቅ ብዙ ስውራን ቅዱሳን መጥተው፣ ከገነት አፈር አምጥተው፣ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከክፉ ነገር ምንም ምን በውስጧ እንዳይገባ በዝቋላ ገዳም ላይ በተኑት። የአባታችን የጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸሎትና በረከት በእኛ በገዳሙ ልጆችና በመላው ሕዝበ ክርስቲያን በሀገራችን በኢትዮጵያ ላይ ለዘለዓለሙ ጸንቶ ይኑር። አሜን!
#ምንጭ፦ #ገድለ_ብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ!