Telegram Web Link
{... #የሐዋርያት_አመራረጥ ...}
ቤተ እስራኤል ስትመሰረት 12ቱ አበው እየተባሉ በሚጠሩት ከያዕቆብ አብራክ በተከፈሉ የ12ቱ ነገድ አባቶች ነበር::
አሁንም የእስራኤል ዘነፍስ ማሕበረ ቤተ ክርስቲያን ስትመሰረት በ12ቱ ሐዋርያት ትሆን ዘንድ አምላክ ፈቀደ::

1, #ቅዱስ_ጴጥሮስ ከቤተ ስምኦን (በእናቱ ወገን) እናቱ ትወደው ስለነበር በነገዱዋ ስም ጠራችው➝ በዓለ ዕረፍቱ ሐምሌ 5

2, #ቅዱስ_እንድርያስ ከቤተ ሮቤል (በአባቱ ወገን) አባቱ ይወደው ነበርና ከነገዱ በተወረሰ ስም ጠራው➝ በዓለ ዕረፍቱ ታኅሳስ 4

3, #ቅዱስ_ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ ከነገደ ሌዊ (በአባቱ)➝ በዓለ ዕረፍቱ ሚያዝያ 17

4, #ቅዱስ_ዮሐንስ ከነገደ ይሁዳ (በእናቱ)➝ በዓለ በሞት ፈንታ የተሰወረበት ቀን ጥር 4

5, #ቅዱስ_ፊልጶስ ከነገደ ዛብሎን➝ በዓለ ዕረፍቱ ኅዳር 18

6, #ቅዱስ _በርጠሎሜዎስ ከነገደ ንፍታሌም➝ በዓለ ዕረፍቱ መስከረም 1

7, #ቅዱስ_ማቴዎስ ከነገደ ይሳኮር➝ በዓለ ዕረፍቱ ጥቅምት 12

8, #ቅዱስ_ቶማስ ከነገደ አሴር➝ በዓለ ዕረፍቱ ግንቦት 26

9, #ቅዱስ_ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ ከነገደ ጋድ➝ በዓለ ዕረፍቱ የካቲት 10

10, #ቅዱስ_ታዴዎስ ከነገደ ዬሴፍ➝ በዓለ ዕረፍቱ ሐምሌ 2

11, #ቅዱስ_ስምኦን ቀነናዊ(ናትናኤል) ከቤተ ቢንያም➝ በዓለ ዕረፍቱ ሐምሌ 10

12, #ቅዱስ_ማትያስ (በአስቆሮቱ ይሁዳ የተተካው)➝ በዓለ ዕረፍቱ መጋቢት 8

"አሥራ ሁለቱንም ሐዋርያት በአንድነት ወደ እርሱ ጠርቶ በአጋንንት ሁሉ ላይ ደዌንም ይፈውሱ ዘንድ ኃይልና ሥልጣን ሰጣቸው፤
#እግዚአብሔርንም መንግሥት እንዲሰብኩና ድውዮችን እንዲፈውሱ ላካቸው"፥ ሉቃ.9÷1-2

“በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ #ክርስቶስ_ኢየሱስ ነው፤”— ኤፌሶን 2፥20
👍1
2025/10/28 05:43:17
Back to Top
HTML Embed Code: