Telegram Web Link
ሀሳብ ስጡበት እስቲ
የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ናቹ?
Anonymous Poll
35%
አዎ
65%
አይ
አንድሮሜዳ አስትሮኖሚ (Sirnhatty)
💥 part 2💥 የኳንተም መካኒክስ ውልደት  በሎጂክ የሚመራውን   የclassicalፊዚክስ ሊቃውንቱን አንጎል በጠበጠ ፡፡ የኳንተም ፊዚክስ Physicist የሆነው ኒልስ ቦሐር “ኳንተም ፊዚክስ ግራ ካላጋባህ አልገባህም ማለት ነው” አለ  ተባለ፡፡  አይንስታይን ግን ኳንተም ፊዚክስን አልወደደውም ነበር፡፡ ከምንም በላይ የጠላው ደግሞ ኳንተም ፊዚክስ የተፈጥሮ ሁነትን በተመለከተ የመሆን እድል (Probability)…
❄️❄️💥 part 3 💥❄️❄️
አዲስ የተፈጠረው የኳንተም ፊዚክስ ዘርፍ   Quantum Entanglement ተባለ።ስለ Quantum entanglement እና ስለ ሌሎች የኳንተም ዘርፎች በሌላ ጊዜ በሰፊው እናያለን።አሁን ወደ  የሶልቬይ ኮንፈረንስ በሩጫ እንመለስ🏃‍♀ 🏃አረ ሮጥ ሮጥ በሉ🏃‍♀🏃 የኮንፈረንሱ ዋና መነጋገሪያ የኳንተም ፊዚክስ ትንታኔ ነው  “ኳንተም ምንድነው?  እንዴት ይገለፃል?? እንዴትስ ይተነተናል?? እንዴትስ...እንዴትስ....ይሆናል???????????????? በአጠቃላይ አቶ ፊዚክስ  ከሳይንስ ይልቅ ቅልጥ ያለ ፍልስፍና ሆኖ አረፈው ወይ ፊዚክስ፡፡ ስለዚህም የተከበሩት የስብሰባው አባላቶች i mean የፊዚክስ ሊቃውንቱ ፊዚክስ የሚመራበት ideology ላይ  ከፍ ሲልም ፍልስፍናው ላይ መስማማት ያስፍለገናል ብለው ወሰኑ🥸።ይህ  ለፊዚክስ እድገት በጊዜው  የሞትና የሽረት ያህል ነበር...የኮንፈረንሱ ሁለት ዋንኛ ተቀናቃኞች 🤩አይንስታይን እና🤩 ኒልስ ቦሐር ነበሩ፡፡ ኒልስ ቦሐር የኳንተም ግራ አጋቢነት በጣም የተመቸው ሰው ነበር፡፡ እርግጥ ግራ አጋቢ ነገርን በመውደድ ከአይንስታይን ይብሳል ቢሆንም ግን በኳንተም  ቀመር ውስጥ ያለው  Probability የሚባለው ነገር መኖሩ አይንስታይንን አልተመቸውም፡፡ፊዚክስ እቅጩን ሲናገር እንጂ ይሄ ነገር የመሆን እድሉ 90 % ነው ብሎ ነገር ምን የሚሉት ማወቅ ነው ???ባይ ነው አይንስታይን፡፡ ካወቅክ 100% ታውቃለህ ካላወቅክ አታውቅም እንጂ - የኤሌክትሮኗ ፍጥነት ይሄን ያህል m/s የመሆን እድሏ 75 % ማለት ምን የሚሉት እውቀት ነው?? ?ይሄ ምናምን ፐርሰንት የሚባል ነገር መጥፋት አለበት ነው የሚለው አይንስታይን፡፡ እሱ እንደሚለው እንትን የመሆን እድሉ ምናምን ፐርሰንት ነው። የሚለው የኳንተም እሳቤ ከእውቀት ማነስ የመጣ ነው።እናንተ ምን ትላላችሁ??🤔🤔እውነት የእውቀት ማነስ ነው??😶 እሱ ተፈጥሮን በደንብ ስላልተዳን ነው ባይ ነው፡፡እውነት ግን መላምት የእውቀት ማነስ ነው??እ ወይስ መብዛት?? ደግሞ ያልኩት ኳንተምን ነው ስለ biology ደም ማነስ እና መብዛት  አላወራሁም🙄።ለእነ ቦሐር ደግሞ ተፈጥሮ እንዲህ ከሆነች የምን እንዲህ ካልሆነች ብሎ ድርቅ ነው ነው የሚሉት። ደግሞ እኮ የሚገርመው የአይንስታይን ቀደምት ግኝቶች ናቸው ለኳንተም ፊዚክስ መፈጠር መሰረት የጣሉት። ምንድነበረ<__> ኢትዮጲያዊያን ሲተርቱ የሚሉት ነገር ደርሷበት ነው😁 የምታቁት ካላችሁ ሙሉበት። ስለ ታሪካዊ አመጣጡ ይሄን ያህል ካልኩህ በቀጣዩ ደግሞ በደንብ ስለ ሳይንሱ እናወራለን እንግዲ  ካልገባችሁ ወይም ግራ ካጋባችሁ ፀባዩ ስለሆነ ግር አይበላችሁ። በቀጣይ ጉዟችን ወደ ኳንተም አለም ነው ከኔጋ መጓዝ የሚፈልግ ሻንጣውን ያዘጋጅ።🎒🎒
አዳም እና ሔዋን ቻይናዊ ቢሆኑ😂💀
ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ።

ሌሎቹ የአፍሪካ ሀገራት የነፃነት ቀናቸውን ሲያከብሩ እኛ ኢትዮጵያን ብቻ የድል ቀናችንን እናከብራለን።

🌟128th Ethiopian Victory for Africa🌟⚡️
🇪🇹 128ኛው የጥቁር ህዝብ የድል ቀን የካቲት 23/2016

             🏹Black Victory Day
                        🇪🇹ADWA🇪🇹
https://www.tg-me.com/andromedainfo
''አድዋ የነፃነት ሳይሆን የድል ቀናችን ነው''

🛡 አድዋ ማለት አባቶቻችን በሀይማኖት እና በዘር ሳይከፋፈሉ ለሀገር አንድነት ከጫፍ እስከጫፍ ተነስተው፤ ውድ ህይወታቸውን ሳይሰስቱ መስዕዋት በማድረግ ጣሊያንን አሸንፈው ድል አድርገዋል።

🤜 ይህን የድል ቀን ባይኖር ውብና ድንቅ የሆኑ ባህሎቻችን፣ ቋንቋዎቻችን፣ ሀይማኖታችን፣ ማንነታችን እና ኢትዮጵያዊ ቀለማችን ጠፍተው ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንደሆኑት እንሆን ነበርና ይህም የቆየው በአባቶቻችን ህብራዊ ድል ነው።

🪽 1888 ታላቁ ድል የተገኘበት ቀን ነው ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን! 🫶

              
              የካቲት 23/2016

https://www.tg-me.com/andromedainfo
           🏹Black Victory Day
                      🇪🇹Adwa🇪🇹
ሰሞኑን አነጋጋሪ ስለሆነዉ ስለዚህ የቅርጻቅርጽ ጥበብ አጭር ማብራሪያ!

(በሠዓሊ ወንደሰን ከበደ)

"ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ ዘእምበገደ ይሁዳ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ

ቀራፂው ካሬቢያዊ የባሃማስ ዜጋ ታቫሬስ እስትራቻን ነው።
ቀራፂው የሌዮናርዶ ዳቪንቺ በhigh Renaissance time ላይ 460cm x 880cm በሆነ መጠን የሰራው ክርስቲያናዊ ሥዕል ሆኖ በግራዜ ቅድስት ማሪያም ቤተመቅደስ ላይ ከ1495–1498 የሳለው ነበር።
ይህንንም የዓለም ዝነኛ ከቴምፕራ ቀለም፣ጄሶ ግግር፣ማስቲሽ እና ሙጫ የተሰራ የግድግዳ ሥዕል የድርሰቱን ቅንብር በመውሰድ ወደ ሀውልትነት ቀይሮታል።
በዚህም ኃውልት ላይ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ጥቁር ፈርጦችን ነው እንደገፀባህሪ የተጠቀመው።
ቅርፁ ኃይማኖታዊ እሳቤው ላይ የሚያፌዝ ሊመስል ቢችልም ዋነኛ ጭብጡ በጥቁሮች የተካሄደውን ፀረ ቅኝ ግዛት ተጋድሎ፣ የነፃነት፣የፍትህ፣የአንድነት ፣የሉዓላዊነት እና የህብረት ሀሳቦችን መዳሰስ የፈለገ ሲሆን በቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴን የድርሰቱ ማዕከል አድርጎ ኢትዮጵያን በጉልህ አሳይቷል።ጉዳዩ ፖለቲካዊ ነው።እንጂ በክርስቶስ ላይ ለመዘበት አይመስለኝም።
እኛ የቱ ጋ ነን
ሜታፊሎ METAPHILO ተጀምሯል👇👇
https://www.tg-me.com/metaphilos
ተቀላቀሉ
#March_8

ዛሬ በመላው ዓለም የሴቶች ቀን ታስቦ ይከበራል። እናም እኛ ካሉት አንዲት ጠንካራ ሴት ስለሆነችዋ #Marie_Curie አንዳንድ መረጃዎችን ለማጋራት ወደድን። የተወለደችው Nov 7,1867 በዋርሳው ፖላንድ ሲሆን የNobel Prizeን ከሴቶች ሁሉ ቀድማ በማሸነፍ እንዲሁም ደግሞ በሁለት የተለያዩ ፊልዶች Nobel Prizeን ድጋሚ በማሸነፍ ቀዳሚዋ ሰው ነች።

ወደ ትምህርቱ ዓለም ስትቀላቀል ያኔ በነበረው የተዛባ አመለካከት ምክንያት ከተያዩ ዩኒቨርስቲዎች ወደ እኛ ተቋም አንቀበልሽም በማለት መልሰዋታል። ከዛም ፓሪስ በሚገኘው University of Paris (Sorbonne) በነበራት እምቅ የሆነ የፊዚክስ እና የኬሚስትሪ ዕውቀት PHD በማግኘት የመጀመሪያዋ ሴት ሆናለች። በዚህም ከባለቤቷ Pierre Curie ጋር በመሆን 1903 የኖብል ሽልማትን አሸንፈዋል። በዚህም በዓለም ላይ የሚገኙ ሴቶችን በSTEM (Science, Technology, Engineering, and Mathematics) መነቃቃትን የፈጠረች ሴት ናት።

ካበረከተቻቸው አስተዋጽዎች መካከልም፦

1) Discovery of Polonium and Radium in 1898

2) Championing the use of Radiation in medicine ይሄም ጨረር ያላቸውን Element በመጠቀም ሰውነት ላይ ጉዳትን መጠን ቀንሰው Cancer Cellን በፍጥነት ማስወገድ የሚቻልበትን መንገድ ፈጥረዋል። ለመጀመሪያ ጊዜም Radium chlorideን በመጠቀም ለዚህ መፍትሔ መሆኑን ከባለቤቷ ጋር በጥናት አረጋግጠዋል።

3) Fundamental change in the understanding of Radioactivity

እነዚህ ጥቂቶቹ ሲሆን July 4,1934 በHaute savoie ፈረንሳይ አርፋለች።

በድጋሚ መልካም የሴቶች ቀን 🙏🏽
Forwarded from METAPHILO | ሜታፊሎ
ምድር ላይ እርግጠኛ ሆነን ልንናገር የምንችለው ብሎም ማስረጃ ልናቀርብለት የምንችለው እውነት አለ?
Anonymous Poll
74%
አዎ አለ
26%
የለም
(March 14)አስደናቂ ውልደትወ ሞት

የአለምን ቅርፅ፣ታሪኳንና ስሪቷን በፓለቲካ(historyም ጭምር)፣በሳይንስ እንዲሁም በህክምና(psychology) የቀየሩ 3 የአይሁድ ተወላጆች አሉ፤Karl Marx,Albert Einstein and Sigmund Freud
እኒህ ግለሰብ'ታት ባይኖሩ(ወይንም አሁን በምናውቃቸው መንገድ ባናገኛቸው)ኖሮ አለሚቱንም በዛሬ መልኳ ማሰብ የማይታሰብ ይሆን ነበር።(እስኪ አንስታይን ዳቦ ጋጋሪ ቢሆን ብላቹ ለሰከንድ አስቡት ወይም ፍሮይድን የሆነኛው ክለብ ኳስ ተጫዋች አድርጋቹ ሳሉት)አጀብ ነው መቼም!

ታዲያ የዛሬዋ ንጋት ከህላዌ ልትቀላቅል እና ልትነጥል የፈረደችባቸውን ሁለቱን አንስተን ትንሽ እንበል።

Albert Einstein በዛሬዋ እለት በ1879 ነበር አለምንና ፍጥረታቱን የተቀላቀለው፤ይህ ሰው እንዲሁ በቀላሉ theoretical physicist ብቻ ብለን የምናልፈው አይደለም፤እስከዛሬ ከኖሩ የሳይንስ ሰዎች ውስጥ የሱን ያህል influential ፊዚሲስት አለ ብሎ ለማሰብ ያዳግታል። በተለይም modern physicsን በ20 ክ/ዘመን የመጀመሪያዎቹ 10 አመታት ውስጥ ድጋሚ በመስራት ለአለም ካበረከቱት ሳይንቲስቶች ውስጥ አንስታይን አንዱና ዋነኛው ነበር።በ1921ም ለዚህ ስራው በተለይም photoelectric effectን discover በማድረጉ በፊዚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማትን አግኝቷል።የብሪቲሽ ጆርናልም በ1999 "130 leadings physicist worldwide"ብሎ ባወጣው ፅሁፉ አንስታይንን አንደኛ ደረጃ ላይ አስቀምጦታል።ታዲያ 'discover' ካደረጋቸው መሰረታዊ የፊዚክስ ህግጋቶች ውስጥ ጥቂቶቹ(በጣም ጥቂቶቹ)
General relativity
Photoelectric effect
E=mc²(mass-energy equivalent)
Theory of Brownian motion
Gravitational wave
Cosmological constant ሲሆኑ quantum mechanics ላይም ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል።ታዲያ ይህ ሰው ከፊዚክስ ሊቅነቱ ባልተናነሰ በአስገራሚ ባህሪዎቹ፣ ንግግሮቹ እና iconic በሆኑ ፎቶዎቹም ይታወሳል(እንደኛው ስብሃት አይነት)።ለማስታወስ ያህል ይህን ያህል ካልን... የአቶሚክ ኢንጂነር ቀመርን በማግኘት የታላቅ አእምሮ ባለቤትነቱን ካረጋገጠ በኋላ የኖቤል ሽልማቱን ተቀብሎ ባደረጋት አጭር ንግግር የእሱን ሀተታ ዘግተን ወደ ቀጣዩ ባለታሪክ እንለፍ።"we won the war,but not the peace"!
(በነገራችን መሀል አልበርት ለቅርብ ወዳጆቹ በእኔ የውልደት ቀን በ100 ምናምነኛው አመት ሌላ ጂንየስ ከአፍሪቃ ምድር ትፈጠራለች የሚል ትንቢት ነግሯቸው ነው የሞተው ይላሉ ሊቃውንቱ የዚህ ፅሁፍ ሞንጫሪ ልትሆን እንደምትችል ይጠረጥሯል!😁)

ሁለተኛው የቀናችን ባለታሪክ ደግሞ Karl Marx ናቸው፤ስለዚህ ግለሰብ ብዙ ባንልም በ1818 ተወልዶ ከኖረባት ፣ከተወደሰባት፣ከተወቀሰባትና ካመሳቀላት አለም በሞት የተለየው (March 14) 1883 አ.ም ነበር።ማርክስ አለምን ከዳር እስከዳር የነቀነቀውን እንዲሁም የታሪኳን አዲስ ምዕራፍ የከፈተውን  የpolitical,economical and historical revolution ከግብራበሩ ጋር የመረሰረተና የመራ ጀርመናዊ economist,political theorist,historian,sociologist, journalist ነው።የዚህ ሰው ideology በሀገራችንም ምን ያህል ግልብጥብ እንፈጠረ የሚረሳ አይደለም።ብቻውንም በጋራም ከፃፋቸው መፅሃፍ ውስጥም
  The communist manifesto
  On the Jewish question(essay)
  The German ideology
  Capital
  The poverty of philosophyን መጥቀስ እንችላለን።ታሪከኛ ሰው ነው፤በአጭር ፅሁፍ የሚያልቅ አይነትም አይደለም(ወደ ላይ ከፈለጋችሁት እሱ ላይ የተፃፉ ፅሁፎች አታጡም) በስተመጨረሻም ቀኒቱን እየባረክን በማርክስ አባባል ጥሁፉን እንቋጨው....
"From each according to his abilities,to each according to his want(በኔ የተስተካከለ)"
  ኦሮማይ!

©ፍልስፍና አለም
😭የዛሬ 4አመት Live የፀሐይ ግርዶሽ በዚ ቻናል እያስተላለፍን ብዙወቻቹ ከተለያየ ከተማ ፎቶ ልካቹ ነበር ለትዉስታ ያህል ይመልከቱ👇 ጊዜዉ ይሮጠዋል😞
https://www.tg-me.com/andromedainfo/751
Subscribe Now👆👆👆
ኦሾ
`` It's impossible for the poor man to be spiritual. I don't think to go Ethiopia and teach meditation there. They'll kill me and i'm not suicidal!. ``

ለድሃ ሰው መንፈሳዊ መሆን የማይቻል ነው፤ ኢትዮጵያ ሄጄ meditation የማስተምር አይመስለኝም። ይገድሉኛል እና እኔ ደግሞ እራሴን አላጠፋም።”

ምን ትላላቹ?🧐
Excerpt - Interview - Osho

፦ -Good morning America ABC TV
📽️
ከ Young sheldon series በጣም ምወደው part ነው፤Sheldon ማለት Atheistና ባለ ምጡቅ አእምሮ ልጅ ሲሆን Mary ደሞ እናቱና  አማኝ ናት ።እናም እናቱ በሆነ ሰዓት ላይ ግራ ገብቷት በእግዚአብሔር ለማማን አየተቸገረች በአለችበት ወቅት Sheldon እንዲህ ይላታል

Sheldon ፡ የGravity ኃይል አሁን ካለው በትንሹ የበለጠ ኃይለኛ ቢሆን ኖሮ አጽናፈ ሰማይ(Universe ) እንደ ኳስ እንደሚወድቅ ታውቂየለሽ?

Mary፡ አላውቅም

Sheldon ፡ እንዲሁም የGravity ኃይል አሁን ካለው ኃይል በትንሹ ያነሰ ቢሆን አጽናፈ ዓለሙ (Universe )ተለያይቶ ይበር ነበር እና ምንም አይነት ኮከብ ወይም ፕላኔቶች አይኖሩም ነበር።

Mary፡ ምን ለማስረገጥ እየሞከርክ ነው ያለኸው ሼልደን?

Sheldon ፡ የስበት ኃይሉ የሚፈልገውን ያህል ጠንካራ ባይሆንና  እና የኤሌክትሮማግኔቲክ ሃይል ደሞ ከጠንካራው ኃይል ጋር ያለው ጥምርታ አንድ ፐርሰንት ባይሆን ኖሮ ምንም አይነት ሕይወት አይኖርም ነበር። ዝም ብለሽ ስታስቢው እነዚህ ነገሮች በእራሳቸው የመፈጠር እድላቸው ምን ያህል ነው ?

Mary፡ አንተ እንደሆንክ  በእግዚአብሔር አታምንም፣ለምንድነው በእግዚአብሔር እንዳምን ለማሳመን እየሞከርክ ያለኸው ?

ሼልደን፡ በእርግጥ በእግዚአብሔር አላምንም ፣ ነገር ግን ቢያንስ የአጽናፈ ሰማይ ትክክለኛነት ይሄን ሁሉ የፈጠረ የሆነ ፈጣሪ አለ ብሎ ለመደምደም ምክንያታዊ ያደርገዋል ።
© ከፍልስፍና አለም
ድጋፋችዉን የማዉቀዉ Like 👍 ስታደርጉ ነዉ
888 SUBSCRIBERS 👍
........... 💥GAALAAKSII_💥

🎇Gaalaaksiin gurmii urjiilee,gaazota,dhukkee/awwaara(dust)fi maatara dukkanaa'aa (Dark Matter)iiti.

💧Jechi gaalaaksii jedhu kun
jecha afaan Giriikirraa kan dhufe yoo ta'u afaan Griikiin "galaxya" jedheme beekkama. Hiikni isaas qaama aannan faakkaatu (Milky) jechuu dha.

Gurmiileen Urjii akkamitti gaalaaksii uumuu danda'u?

👉Urjiiwwan gaalaaksii keessa jiran giddu humni harkisaa (Gravity) tu jira. Humnii harkisaa kun urjiiwwan fi plaanetoota walitti hidhee qaba. Kanaaf gaalaaksiin gurmii urjjiwwaniiti jannee dubbachuu dandeenya.

Baballiinsi Hawaa /Expansion of the Universe eessatti dalagamaree?

🌕Baballiinsi hawaa / Expansion of universe kan dalagamu ykn kan iddoo fudhatu gaalaaksiiwwan lama ykn lamaa ol gidduudha malee gaalaaksii keesstti miti.

❄️Akkuma gurmiin urjii gaalaksii uumu gurmiin gaalaaksiiwwani immoo Kilaastara (Galactic cluster) uuma. Maqaan gaalaaksii nuti keessa jirruu Miilkii weey (milky way)yoo ta'u kan argamus kilaastara local gruop jedhamu keessa.
Qaamni gaalaaksii keessa jiru tokko yeroo hunda sochiirra jira.
   
#Goosawwan_gaalaaksii

🔥Gaalaaksiiwwan hammaa fi gosa adda addaatin faca'anii jiran.Hammi isaaniis gaalaaksiiwwan xixiqqoo (dwarf) irraa kaasee amma isaan gudguddaa (giant)jiran ta'uu danda'a.

👉Gaalaaksiiwwan xixiqqoo kan jennuun urjjiiwwan miilyoona kudhanii gadi kan qaban yoo ta'u isaan gudguddoon immo urjii hanga triilyoona dhibbaa (100,000,000,000,000)qabaachuu danda'u.

🌠Akkuma duraan kaasnee tuurreee kilaastarri gaalaaksii gaalaaksiiwwan hedduun walitti dhufuun kan uummamu yoo ta'u Klaastarri urjii immoo urjiileen walitti dhufanii kan uumanidha.

Fakkeenyaaf:- Kilaastarri Gloobuulaar kilaastara dhuma gaalaaksii keenyaa (milky way) irratti kan argamuudha.
               Itti fufa...............
2024/05/20 18:04:11
Back to Top
HTML Embed Code: