Telegram Web Link
አንዱ ነው እየተከራከረ.. ለማስረጃ ከጉባዔ ጥራ ይሉታል “ሰበካ ጉባዔ” አለ አሉ..

ያው መከራከር ግድ አይደለም ነው..
አንድ እዚሁ ግሩፕ ላይ ያለ ወዳጃችን “እስቲ ጥያቄ ጠየቅህ ያሸነፈ የዓመት ቴሌግራም ፕሪምየም ልሸልም” አለኝ..

ዌል ይሄ የ50 ወይም የ100 ብር ካርድ አይደለም ስለዛ ቀለል አድርገን ጠይቀን አናልፈውም.. ይልቁንም እኔ አንድ አሳብ አሰብሁ..

አንድ ትንሽዬ መጽሐፍ አለች ከሷ የተወሰነ ክፍሏን በደንብ እንድታነቡና ከዛ ይወጣል ጥያቄው.. ከዛ ያሸነፈ ይሸለማል.. ምናልባት 2 እና 3 የሚወጡትንም ማበረታቻ ወይ እኔ እሸልማቸው ይሆናል.. ያው ምናልባት😁😁

በዛውም ያንን ጽሑፍ እንድታጠኑ ያደርጋችኋል ማለት ነው..

ወይስ ሌላ የተሻለ አሳብ አላችሁ
በቃ የምታነቡትንና ከዛም የምትፈተኑበትን መጽሐፍ ልጠቁማችሁ..

የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ በብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ..

እስከ ገጽ 90 ድረስ ያለውን.. በጣም ትናንሽ ናት ገጿ.. ስለዛ በርትታችሁ በጣም ተረጋግታችሁ በማስተዋል አንብቧት.. በጣም ትጠቀማላችሁ ማርያምን..

መጽሐፉ የልላችሁ PDF ከታች አስቀምጣለሁ.. አልያም ግሩፕ ላይ

ሽልማቱ እንደተጠበቀ ነው👍👍
ጌታችን ኢየሱስ ለዓለም ሁሉ ሞተ በእርሱ በኩል የተሠራው የማዳን ሥራ ለየትኛውም ሰው ነው.. ግን ደግሞ ይህንን የእርሱን የማዳን ሥራ ለማግኘት ሰዎች አሜን ብለው መቀበል አለባቸው.. ካላመኑ ድኀነቱን አያገኙም.. ይልቁንም በብሉይ ኪዳን እንደነበሩ ሰዎች አዳማዊያን ብቻ ሆነው ይኖራሉ.. ይህ ከባድ ቁስል የሚፈወሰው በኢየሱስ እንጂ በሌላ በማንም አይደለም..

ቅዱስ ሄራንዮስ እንዲህ ይላል:

“በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ ሆኖ ወደ ሰማእትነት እንጨት ላይ ከምድር ከፍ ባለው(ኢየሱስ) በእርሱ በማመን ሰው ከቀደመው የእባብ ቁስል እንዲድን እንጂ በሌላ መንገድ አይሆን ዘንድ..”

[Against heresies bk. 4: chap 2: sec 8]
አንዳንድ ክርስቲያኖች ላይ የማየው ድክመት..

በጭፍን እንዲሁ መምህር የተባለውን ሁሉ መከተል ስህተት ውስጥ እንድንወድቅ ያደርጋል.. የሆነ ርእስ ላይ ጥያቄ ከፈጠረባችሁና መላሹ ሲመልስ “የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ” ብሎ የሚመልስ ከሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከአባቶች ሰፋ ያለ ማስረጃ እንዲያቀርብ 👉ጠይቁት..

ሰፋ ያለ ማስረጃ ከሁለቱ ማቅረብ ካልቻለ ቢያንስ ለጊዜው የራሱ የሰውዬው እንጂ የቤተ ክርስቲያን ብላችሁ አትያዙ.. ቅዱስ ትውፊት የሁሉም መመዘኛ ነው..

@Apostolic_Answers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል..

የሉቃስ ወንጌል 24
43፤ ተቀብሎም በፊታቸው በላ።

ጌታችን ከሙታን ከተነሣ በኋላ በደቀመዛሙርቱ ፊት ምግብን በላ.. የትንሣኤ ሥጋን ይዞ ምግብን የበላው ግን እኛም ሞተን ስንነሣ እየበላን ስለምንኖር ነው..?? ወይም የትንሣኤ ሥጋ ምግብ ያስፈልገው ይሆን..?? ጌታም በሌላ ክፍል እንደነገረን በትንሣኤስ ሁላችን እንደ መላእክት እንኖራለን እግዚአብሔርን እያመሰገንን ብቻ..

👉 ይህ ነገር አሁን በደካማው ሥጋችን ስናስበው የማያስደስት ሊመስለን ይችላል.. ያኔ ግን በትእሣኤ ሥጋ ስንሆን ጭራሽ ታይቶም ተሰምቶም የማያውቅ በጌታ የሆነ ደስታ ይሞላናል.. ፍጹም የሆነ የማይጎድል.. አሁንም በጭላንጭል ከቅዱስ ቁርባን እየተሳተፍን experience እናደርገዋለን.. በጭላንጭል ያልሁት አሁን ላይ በድካም ውስጥ ስለምንሆንም ከሚመጣው አንጻር ነው.. እንጂ አሁንም በጌታ የሆነ ደስታ ከእኛ ጋር ነው

ጌታችንም እዚህ ጋር የተመገበው ደቀ መዛሙርቱ ትንሣኤውን ማመን ከብዷቸው ስለነበር ምትሃት መስሏቸው ነበርና በሥጋ እንደተነሣ ለማስረገጥ ነው.. ለዛ ነው ከፍ ብሎ እዛው ላይ እንዲህ የሚለው..

“እነርሱም ከደስታ የተነሣ ገና 👉ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ፦ በዚህ አንዳች 👉የሚበላ አላችሁን? አላቸው።”

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የፕሮቴስታንት መዝሙርን መስማት የማይገባን ምክንያት ሁለተኛ ማጠናከሪያ አሳብ..

https://vm.tiktok.com/ZMMo6j8yF/
አበበ:- እመቤታችን አምላክን ስትወልድ በክብር ላይ ክብር ሆኖላት ታላቅ ክብርን አገኘች.. ትልቁ ክብሯ ወላዲተ አምላክ መሆኗ ነው


ገረመው፣ ደጀኔ እና ቶላ:-ኢየሱስን ስትወልድ አስቀድሞ ያልነበረ ክብርን አገኘች..?? እግዚኦ ምንፍቅና


ምንፍቅና..??
ነቃ ደንገጥ ቆፍጠን ብለን እናንብብ እንማር እንጂ ወገን 😁😁 ከሥር ከሥር ክርስቲያኑን የሚያውኩት ላይ እንዝመትባቸው እንዴ ፕሮቴስታንቱን ትተን😁😁
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል:

“እርሱም፦ ‘መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ’ አላቸው። ስለዚህ ጣሉት፤ በዚህም ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ ሊጐትቱት አቃታቸው።”
[ዮሐንስ 21: 6]

ጌታችን ከሞት ከተነሳ በኋላ ደጋግሞ ተገለጠ.. አሁን የተገለጠው በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ነው.. እና እነዚህ አሥ አጥማጅ ሐዋርያትም በዛን ለሊት ብዙ ቢታገሉም ምንም ሊያጠምዱ አልቻሉም ነበር..

እና ጌታችን መጥቶ “መረቡን በስተቀኝ ጣሉት” አላቸው.. እነሱም እንዲሁ አደረጉና ለማውጣት እስኪከብዳቸው መረቡ በዓሣ ተመላ.. ዮሐንስም ይሄኔ “ጌታ እኮ ነው” አለ.. ጴጥሮስም ራሱን ወዳ ባህር ጥሎ ወደ ጌታ ሮጠ..

ድኀነትን የተጠሙ በዓለም ያሉትን ዓሣዎች ወደ መረብ(ቤተ ክርስቲያን) ለማጥመድ የአገልጋይ ድካም ብቻውን ዋጋ የለውም.. የጌታ ጣልቃ ገብነት ያስፈልጋል..

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“መላጣ ቢሆንም እንኳን ይሁን ብዬ ላገባው የምችለው ሰው አክሊል ነው” የሚል ኮመንት ስታይ
“ኢየሱስ አምላኬና ተስፋዬ ነው
ቅዱስ መስቀሉም
የሃይማኖት በትሬ ነው”

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ: መጽሐፈ ምስጢር
ሰው ከወኃ እንዴት ይወለዳል..?? ውኃን ከዚህ ነገር ጋር ማገናኘት አይከብድም..??

Well ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በጣም የምወድለት መልሱ ለዚህ..

https://vm.tiktok.com/ZMrdDsC5p/

_______
ሰላም ለእናንተ ይሁን ተወዳጆች.. ወንድማችን “መሸ” research እየሰራ አንድ ጉዳይ ላይ እስቲ የምትችሉ ሰዎች ከታች ያለውን ፎርም ሊንክ ውስጥ ገብታችሁ ሙሉለት.. ጥያቄዎቹን እያነበባችሁ ታዲያ

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScgni-IwfQIaA_-e0rO0Gbd2buMEHJIl0DKmqKQTAVXqIzTpQ/viewform?usp=pp_url
“ማኅበረ ቅዱሳን” የተወደደው ማኀበር ሆይ.. አንድ መጽሐፍ በማኀበሩ በኩል ሲታተም.. በማኅበሩ ኤዲቶሪያል ቦርድ “ታርሞ ተፈቅዶ” የወጣ የሚል ነገር መጽሐፉ ላይ ስናይ.. የምር ግን በምን ደረጃ ነው ምትመረምሩት..?? በዛ መጽሐፍ ውስጥ የሚተላለፈው ትምህርት ሁሉስ ማኅበሩን ይወክላል..?? እንደው ይህንን ነገር ላውቅ ወደድሁ..

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ስለምትሰሩ ከእናንተ በተቻለ አቅም ጥርት እና ጽድት ያለ ነገር ነው ምንጠብቀው እወቁልን.. እግዚአብሔር ይህንን ማኅበር ይጠብቅ.. ሁሌም እርሱው ይስራበትም

@Apostolic_Answers
የሚያስሸልመው ጥያቄ ነገ ማታ 2:00 ነው የሚሆነው.. በሉ ተዘጋጁ..

“የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ” በአቡነ ጎርጎርዮስ.. ገጽ 1-90
Forwarded from EOTC Library
Scanner App Lite 17-10-2022 17_53.pdf
54.3 MB
የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ

ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

@eotcLibrary
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“ወደ ቅድስት ጠረጴዛ(መሠዊያ) ቅረብ: እሳት እንደሚያጋሳ አንበሳ ለሰይጣን አስፈሪ ሆነህም ተመለስ”

ይሄንን ጸዴ አንበሳ ሳየው ትዝ አለኝ ከላይ ያለው የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አባባል
2024/06/09 01:39:25
Back to Top
HTML Embed Code: