Telegram Web Link
እንዲህም ያጋጥምሃል አንዳንዴ

@Apostolic_Answers
🤣438😁54👍2017😢14🥰7👏1
የፕሮቴስታንቱ ምላሾች😁😁 እስከመጨረሻው እዩት..

https://vm.tiktok.com/ZMrsMHbgW/
116👍13🙈7👏5
“አቤቱ አንተ አባታችን ነህ”

የምርም እግዚአብሔር አባታችን ነው እኛም ልጆቹ ነን.. ያውም ኢሳይያስ እንዳለው ያለ ዓይነት ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ በኩል የሆነ ልጅነት..

“አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ”

እናመሰግንሃለን..
483🙏37👍22🥰18😢3🤣3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አጠር ባለ ቨርዠን የትላንቷ😁😁
201👍23🔥11🙏10😁3
የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሁንም ሰሞኑን እመቤታችን ተገለጠች እየተባለ ነው.. እና ግን ግብጽ በጣም ደስ የሚሉት የምርም ተገልጣለች ወይስ መስሏቸው ነው የሚለውን ራሷ ቤተ ክርስቲያኒቱ ጥብቅ የሆነ ምርመራ አድርጋበት ከዛ ታሳውቃለች እንጂ እንዲሁ ኦፊሻል አይደረግም..

በዘይቱን ያኔ የተገለጠችውንም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ውጪ የሆኑ ሳይቀር ተሳትፈውበት ነበር ጉዳዩ ላይ.. እና ጥንቃቄዋ ደስ ይላል

@Apostolic_Answers
408👍45🥰23🙏14🤣5
ቤተ ክህነቱ ሪፖርት እያስደረገብኝ የሚከታተለኝ ሰው ቀነሰብኝ እያለ ነው ኤርሚያስ😆😆

ማይ ብራዘር ገድላት ተዓምራት ስትል አሁን ሰዉ ስቆብህ ነው ሚያልፈው.. ተስፋ አድርገው ሚዲያ ላይ የመጡት እሱን ነበር ግን አልተሳካም😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMrswWqMA/
😁16857👍22🙈3🙏1
የጌታ ተአምር ለሙስሊሞች

ሙስሊምም ፕሮቴስታንትም ወንድም እህቶቻችን በንግግር ብናሳስዝናችሁ ይቅርታ..

https://vm.tiktok.com/ZMrGQtM6R/
180👍21🙏13😁3
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል

“የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?”
[ሉቃስ 1:43]

5 ነጥቦች😊😊

1. “የጌታዬ እናት” ብላለችና ኢየሱስ ጌታ ነው.. ይህም ጌትነት በሌሎች ክፍሎች ላይ እንደተነገረው “የጌቶች ጌታ፣ አንድ(ብቸኛ) ጌታ” እንደመሆኑ ስለሆነ አምላክነቱን ያሳያል..

2. እመቤታችን የጌታ እናት መባሏ የአምላክ እናት መባሏ ነው.. ያው ከላይ እንዳልነው ለኢየሱስ ጌታ ሲባል አምላክነቱን ስለሚያሳይ.. ስለዚህም እመቤታችን የአምላካችን እናት ናት ቃልን በሥጋ ጸንሳዋለችና

3. የአምላክ እናት እንደመሆኗ እመቤታችን ያላት ታላቅ ክብር:— ቅድስት ኤልሳቤጥ ምንም እንኳ “በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ” እንደነበረች ይኸው ወንጌል ቢናገርም.. እግዚአብሔርም ታላቅ ተአምርን ቢያደርግላትም.. እመቤታችን ወደሷ ስትመጣ ግን “የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?” አለች.. የእመቤታችን ክብር ከእርሷ በጣም በእጅጉ ይበልጣልና..

4. ይህ ጌታ የኤልሳቤጥ ጌታ ብቻ ሳይሆን የፍጥረት ሁሉ ጌታ ነውና ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን “የጌታችን እናት” ይላል.. ስለዚህም በክብር እመቤታችን ከኤልሳቤጥ ብቻ ሳይሆን ከፍጥረት ሁሉ ትበልጣለች..

5. በቅድስት ኤልሳቤጥ ላይ የወረደው መንፈስ በትህትናዋ ተገልጧል.. መንፈስ ቅዱስ የትሕትና መንፈስ ነው.. “ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ አይገባኝም” አስባላት..

ስለዚህ እኛም ይህ ትህትና በሕይወታችን ውስጥ ይታይብን ዘንድ ይገባል.. ጌታችንም “ከእኔ ተማሩ እኔ የዋሕ በልቤም ትሑት ነኝና” ብሏል.. ትሑት ሰው የእግዚአብሔርን ድንቆች በሕይወቱ ውስጥ ያያል.. በነገር ሁሉ የእግዚአብሔርንም እርዳታ አያጣም..

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
508🙏66👍32🥰21😢7
እንደዚህ ያለ ታላቅ ሃጢአት ሲደረግ ከቤተ ክርስቲያንስ ምን ይጠበቃል..??

አቤት ቅዱስ ጳውሎስ አሁን ቢኖርና በኢትዮጵያ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ቢጽፍ ምን ይል ይሆን

https://vm.tiktok.com/ZMrtWXWep/
😢17361👍16🥰7🙏5
ፌሚኒስት እያሉ ራሳቸውን የሚጠሩ እህቶች(ምናልባት ወንድሞችም) አንዳንዴ የሚጠቀሟቸው ቃላት በጣም አደገኛና ወንድን በማኅበረሰብ ውስጥ በጣም እንደ አውሬ እንዲታዩና ፀረ ወንድ አስተሳሰብ ቀስ በቀስ እያደገ እንዲሄድ ሊያደርግ የሚችል ነገር ያለ ይመስላል..

ይሄ ደግሞ እህቶች ለወንድ ጥላቻ እንዲኖራቸው ያደርጋል ብዬ አስባለሁ.. ለምሳሌ አንድ ወንድ እና ሴት ቢቸገሩ አንዲት ሴት ማንን ትረዳለች..?? “ደግሞ ለወንድ” ብላ አትተወውም እሱን..?? እና ወደዚህ እንዳናመራ በጣም በጥንቃቄ ቢሆን.. እና መፋቀርን የሚያጠፋ መርዝ እንዳይሆን.. ያው በአንዳንዶች ችግሮች ምክኒያት

@Apostolic_Answers
358👍112🤔17🙏9😢8👏4🔥3
ከወንድ እና ድብ..??
ከሴት እና ውሻ..??

ቆሻሻ እና አጋንንታዊ ጥያቄዎች

https://vm.tiktok.com/ZMrWoeUMp/
👍80😢2813🔥1
አንዱ ወዳጄ የድቡን ኬዝ ከሰማ በኋላ ምን አለ..

እየደረሰ ያለውን ጥፋት ከቀረፍን በኋላ ግን የእህቶቻችንን ልብ ያስሸፈተውን ድብ በግል የምናናግረው ነገር ይኖራል አንሰማውም የምር..

@Apostolic_Answers
🤣293😁2614👍10🤔5👏2
እንኳን ለእመቤታችን ፍልሰተ ሥጋ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

የእመቤታችን ፍልሰተ ሥጋዋ እንዴት እንደተከናወነ ባናውቅም ያው እንደ ካቶሊክ ለጥጠን ዶግማ ባናደርገውም.. በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ግን የሚታመንበት እውነታ ነው..

በስፋት የሚሰጠው እይታ ያው ጌታችን ሞቶ በመነሳት የትንሳኤያችን በኩር ነው.. ስለዚህም ሁላችንም ደግሞ ሞተን አንቀርም እንነሰላን.. ይህንን ነገር እኛ የምናገኘው በትንሳኤ ሰዓት ኋላ ላይ ነው.. ይህንን እኛ የምናገኘውን ነገር ለእመቤታችን ቀድሞ ሰጥቷታል ነው..

መልካም በዓል

@Apostolic_Answers
582👍52🙏25🥰21🤣11😁4🤔4🙈3👏1😱1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዘይቱና እመቤት
ለ3 ዓመታት የታየው ተአምር
524🔥30🥰23🙏21👍19🤣12
ቁርአኑ ግደሉ አይልም..??

“ገድል ነው” ይለኛል እንዴ😁😁 ገድል ብሎ አዘናግቶ ቢገድለኝስ ሎል
🤣191👍15🙈3👏1
እስቲ እንሞክረው ዝም ብለን.. ያው ለሰው አላጋራውም እያለ ነው ቲክቶክ.. ጠምዶኛል ሰሞኑን😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMrvANhPb/
👍8135😁15😢5
በቁርአንህ ማፈር ከጀመርክ ነው መዋሸት የምትጀምረው.. እውነቱን ነግረህ ሰውን እስላም ማድረግ ስለማትችል..

በብሉይ ኪዳን ያሉ ውጊያዎችን እንዴት እንያቸው ከሐዲስ ኪዳን አንጻር

https://vm.tiktok.com/ZMrvbnrj3/
148👍23🤩7🔥5🤣4😢1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኧረ በቅዱስ ሚካኤል ምን እንደሰሩብኝ እዩልኝ ብቻ🤣🤣 የኔስ መከራ በዛ ሎል
🤣58058😁26👍17🔥9😢6🙈4
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል

“ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቷልና።”
[ሉቃስ 1: 47]

እመቤታችን ስትናገር ጸሎቴን ወይም ጽድቄን ተመልክቷል ሳይሆን “የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቷል” አለች.. ይህም ዝቅ ማለትን ነው.. ይህ ታላቅ ትህትና ነው.. አያችሁ የኔ ተወዳጆች ሰው ትህትና ሲኖረውና በመንፈስ ደሃ በሆነ ቁጥር እግዚአብሔር ደግሞ አብዝቶ ጸጋውን ይሰጠዋል ከፍ ከፍም ያደርገዋል..

ዲያቢሎስን አስታውሱት.. የወደቀው በትእቢት ነበር.. ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ኤጲስ ቆጶስ ሹመት ሲናገር ምን ዓይነት ሰው መሾም እንዳለበት ሲናገር እንዲህ አለ:

“በትዕቢት ተነፍቶ በዲያቢሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።”
[1ጢሞ 3: 6]

የትህትና መንፈስ(መንፈስ ቅዱስ) ትእቢትን ብቻ ሳይሆን የውሸት ትህትናዎችንም ሁሉ ከልባችን አውጥቶ እውነተኛ ትህትናን በልባችን ይሙላ.. መንፈስ ቅዱስ ይርዳን

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
437🙏64👍29🥰17🔥1🤔1😢1
2025/07/10 18:53:31
Back to Top
HTML Embed Code: