ስሙ ደግሞ በፊት ጥርሳችሁ ስል የተወሰነ ለመዋጥ እንዲያመቸን ነው ግን ወደ ውጭ በጭራሽ እንዳይወጣ በጣም ጥንቃቄ ይፈልጋል.. ወደ ውስጥ አድርጋችሁ አላምጡት.. እና ደግሞ እንደተቀበላችሁ በጨርቅ መሸፈን አትርሱ.. በእጃችሁ ራሱ ለመንካት ስለማይፈቀድ በነጠላችሁ አልያም ለዚህ አገለግሎት ብቻ ምትጠቀሙበት ነጭ ትንሽ ጨርቅ አዘጋጁ
የዛሬው የማርቆስ ወንጌል ንባባችን
ምእራፍ 8
- ጌታችን ኢየሱስ ሰባት እንጀራ እና ጥቂት አሣን አበርክቶ ሲከተሉት ለነበሩት 4000 ሰዎች “የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ” በማለት አበላቸው..
- ፈሪሳውያን ጌታችንን ሊፈትኑት ተአምር እንዲያሳይ ጠየቁት ጌታችን ግን ከለከላቸው
- ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ ከሄሮድስ እና ከፈሪሳውያን እርሾ እንዲጠበቁ አዘዛቸው.. እነርሱም በጊዜው አንዲት እንጀራ ብቻ ይዘው ነበርና “እርሾ” ሲላቸው ቀጥታ እርሾ መስሏቸው ነበር.. ጌታም ያው ምግቡንማ ማበርከት እንደሚያውቅበት ሁለቱንም ያበረከተበትን ጊዜ በማንሳት አለማስተዋላቸውን ይወቅሳል..
- ጌታችን በቤተ ሳይዳ ዓይነ ስውሩን ፈወሰው
- ጌታችን “ሰዎች እኔ ማን እንደሆንሁ ይላሉ?” በማለት ጠየቀ.. ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ(መሥህ) መሆኑን ጴጥሮስ መሰከረ
- ኢየሱስ እንደሚሞት እንደሚነሣም በግልጥ ይነግራቸው ጀመር.. ጴጥሮስ አይሁንብህ ባለ ጊዜም ጌታችን ገሰጸው
- ጌታን መከተል የሚወድ መስቀሉን ሊሸከም እንዲገባ ይነግራቸዋል.. ስለዚህም በዚህ ዓለም ውስጥ ስንኖር ለጌታ ብቻ ልንኖር እንደሚገባ
መልካም ውሎ
@Apostolic_Answers

ክርስቶስ ኢየሱስ የማይታይ የማይሞት ተብሎ ይነገርለታል..??
አዎ በመለኮቱ የማይሞት ነው በሥጋ ግን ሞት ይስማማዋልና ሞቷል ደግሞም ተነሥቷል.. ስለዛ ከአብ ጋር አንድ እንደ መሆኑ አዎን የማይሞት ነው ከእኛ ጋር አንድ እንደ መሆኑ ደግሞ በፈቃዱ ስለሁላችን በሥጋ ሞተ..
ትናንት ከአንድ ሙስሊም ወንድም ጋር እያወራሁ በጢሞቴዎስ ላይ የማይሞት የተባለለት ማን ነው..?? የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር በወሬ መሃል እና ቀጥታ ጥቅሱ ስላልተነገረና ተመሳሳይ አሳብ ያላቸው ሁለት ጥቅሶች ስላሉ ጢሞቴዎስ ላይ አንደኛውን የአብን በመያዝ ከአብ አንጻር አውርቼ ነበር እስቲ ሁለቱንም ላንሳና እንዴት ይህ ቃል ለአብም ለወልድም ሊነገር እንደሚችል እንይ.. ግን ደግሞ ለወልድ ሲነገር ከአብ የሚለየውንም አሳያችኋለሁ..
1. "ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይሞተው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።"
[1ጢሞ 1፡17]
ይህ ለአብ የተነገረ ነው ግን ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ለአብ ብቻውን የማይሞት ስለተባለ ወልድ የማይሞት አይደለም ማለት ነውን?" እያለ እየጠየቀ ለመናፍቃን ያብራራል..
2. "እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።"
[1ጢሞ 6:16]
ጥቅሱ ከላይኛው ጋር በእጅጉ ተመሳሳይ ነው ግን ይህ ደግሞ ለወልድ የተነገረ ነው.. ታድያ ወልድ "አይታይም አንድ ሰው እንኳ አላየውም አይሞትምም" ከተባለ ስብከታችንን ከንቱ አያደርግም ወይ..?? አያደርገውም። ጌታችን ሰው እንደ መሆኑ በሥጋ መገለጡንና መታየቱን እንዲሁም መሞቱን የሚክድ አይደለም.. ይልቁንም በሥጋ ሞተ ታየም አዎ በመለኮት ግን "ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል" ስለዚህም በመለኮቱ ማንም አይቶት አያውቅም አያየውምም አይሞትምም ተብሎ ሊነገርለት ይችላል።
ማሳሰቢያ፡ መለኮቱን እና ሥጋውን ነጣጥለን መለኮት እንዲህ ነው ሥጋ እንዲህ ነው እያልን አምላክ አልሞተም ማለት አንችልም.. ያ የማይሞተው አምላክ የሚሞት ሥጋን ይዞ በዛ በሥጋው ሞተ ተብሎ ይነገራል እንጂ.. ስለዛ ሥጋው ሩቅ አይደለም..
ስለዚህም አንዱ ጌታ ኢየሱስ የሚታይም የማይታይም፤ የሚሞትም የማይሞትም፤ የሚዳሰስም የማይዳሰስም ነው።

የእለቱ የማርቆስ ወንጌል ንባብ ክፍል
ምእራፍ 9: 1-29
- ጌታችን ወደ ረጅም ተራራ ያዕቆብ ዮሐንስን እና ጴጥሮስን ይዞ ወጣ.. በፊታቸውም ተለወጠ ልብሱም አንጸባረቀ
- ኤሊያስና ሙሴ መጥተው ከጌታ ጋር ይነጋገሩ ነበር
- አብ ከደመና ውስጥም “የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት” አለ
- ከተራራው ከወረዱ በኋላ ዲዳ መንፈስ የነበረበትን ሐዋርያቱ መፈወስ ያቃታቸውን ሰው ጌታ ነጻ አወጣው..
የማርቆስ ወንጌል 9
29፤ ይህ ወገን በጸሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም፡ አላቸው።

ምእራፍ 9: 30-ፍጻሜ
- ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው እንደሚሞትና እንደሚነሣ ለሁለተኛ ጊዜ ነገራቸው(አያስተውሉትም ነበር)
- ደቀ መዛሙርቱ በመንገድ ላይ ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን..?? እያሉ ተነጋግረው ነበርና ጌታችን “ፊተኛ ሊሆን የሚወድ ከሁሉ በኋላ አገልጋይ ይሁን” አላቸው.. ሕጻንንም አቅፎ በሱ ምሳሌ ሰጠ
- አንድ ሰው ከኢየሱስ እና ሐዋርያቱ ጋር አብሮ ሳይጓዝ በኢየሱስ ስም አጋንንትን ሲያወጣ ነበርና ሐዋርያቱ ከለከሉት አበእሯቸው ስላልተከተላቸው.. ጌታችን ግን “የማይቃወመን እርሱ ከ እኛ ጋር ነው” አላቸው(ስለዚህም አብሮ ባይጓዝም ትምህርት ላይ አይቃወምም እና አትከልክሉት ነው)
- ለሰው መሰናክል ልንሆን እንደማይገባና ራሳችንንም ከክፍ ልንጠብቅ እንደሚገባ
የማርቆስ ወንጌል 9
50፤ በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።

ኧረ በቅዱስ ሚካኤል አንዱ ፕሮቴስታንት ተሐድሶ የጻፈውን መጽሐፍ አይቼ ገና ከመግለጤ ከማውጫው ላይ ወደ አንድ ቦታ ሄጄ ተገረምኩ.. ኧረ በጌታ እዚ ቴሌግራም ላይ የምንጽፋቸው አጫጭር ጽሑፎች በስንት ጣእማቸው..
ዮሐንስ አፈወርቅ ለጨፍጫፊው ሂትለር አሳብ ምንጭ እንደሆነ እያስረዳ(አስቡት ምን ዓይነት አደገኛ claim እንደሆነ)
1. ከራሱ ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አንድም አልጠቀሰም😭😭
2. እዚህ ጉዳይ ላይ አንድ የጻፈ ሰው አግኝቶ መሰለኝ የዛን ሰው መጽሐፍ ገጽ 9 ብቻ ነው ሚጠቅሰው😭😭
3. Guess what.. የጸሐፊውን ስም ራሱ አልጠቀሰም🤣🤣
ይቅርታ ግን መጽሐፍ እንዲህ አይጻፍም🙌😁
ከታች ኮመንት ላይ ፎቶውን ላሳያችሁ ቆይ
👇👇

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በአይሁዳውያን ላይ ከባድ ቃላትን እየተጠቀመ መጻፉ ለዚህ ዓይነት ከሂትለር ጋር የማያያዝ የጅል መላምት ከዳረገ.. እንግዲያውስ መጥምቁ ዮሐንስ እና ጌታችን ኢየሱስ አይሁዳውያን ላይ የተጠቀሙትን ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ቢያዩ ምን ሊሉ ነው😁😁
አሁን አሁን ግን ላይቭ አብዝቶ መቀላለድ ቢቀርብኝ ይሻላል.. አሁን ባለፈው ከአንድ ሙስሊም ወንድሜ ጋር እያወራሁ በጣም ማይሆን ነገር እያወራ ትንሽ አዛገኝ.. ከዛ ደግሞ ጭራሽ አንዳንድ የብሽሽቅ ቃላትን መጠቀም ጀመረ እና ከራሴው ወንድሞች ጋር ሙድ እንደምንያያዘው ልጁ ላይም ሄድኩበት.. ያው ወንድሞች ላይ ቢሆን ኖርማል ነው ሁሌም ነው ምናደርገው.. ሌላን ሰው ግን የሚያስከፋ ነው.. እና የምር በጣም ነው የደበረኝ..
በእርግጥ የፈጠነ በውስጥ ሄጄ የይቅርታ ደብዳቤ ጽፌለታለሁ ለልጁ.. ግን እንዲ መቀላለድ ባይበዛ ይሻላል መሰል

አንድ ነገር ላስቸግራችሁ ነው እስቲ..
የድኅነት ትምህርት ላይ መጻፍ ከጀመርኩ በጣም ቆየሁ ያው እዚህ ላይ ራሱ ጫፍ ጫፉን ከነገርኳችሁ ሁለት አመት ሊሆነው ነው😁😁 እና ግን ሙሉ የድኅነት ትምህርት በአንድ መጽሐፍ ውስጥ ለመጨረስ ይበዛል እና ለሰውም ለማንበብ የማያነሳሳ እንዳይሆን ብዬ አሰብኩ..
የጥምቀት ፓርቱ ራሱን ችሎ ሰፊ ነው እና ደግሞ በዚህ ጉዳይ በዋናነት ምላሽ የሰጠሁትም በኢትዮጵያ ፕሮቴስታንታዊ እቅበተ እምነት ውስጥ ምናልባትም ፈር ቀዳጅ በሆኑት ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ ለተጻፈ አንድ መጽሐፍ ነው።
እናማ አሳቡ "በእንተ ጥምቀት" ራሱን ችሎ ከ200 ገጽ በላይ ስለሆነ ለዶ/ር ተስፋዬ ምላሽ አድርገን አውጥተነው ሌላውን ለብቻው እናዘጋጅ ወይስ መጽሐፉ ቢተልቅም ዝምብለን የተወሰነ አጨቅ እናድርገው..??
ፍላጎታችሁን ምታሳዩበት ፖል አዘጋጅላችኋለሁ እስቲ ትመርጣላችሁ

ከላይ የተጻፈውን አንብቡና ከታች እስቲ አሳባችሁን በvote ግለጹ
Anonymous Poll
45%
በእንተ ጥምቀት ምላሽ ለዶር ተስፋዬ ሮበሌ ይውጣ
58%
ሌሎችም የድኅነት ትምህርቶች ተጨምረውበት ይውጣ
የእለቱ የማርቆስ ወንጌል ክፍል ንባብ
ምእራፍ 10: 32-ፍጻሜ
- ጌታችን ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ስለ ሞቱና ትንሣኤው ለ3ኛ ጊዜ ነገራቸው
- የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብ እና ዮሐንስ ጌታችንን “በክብርህ ጊዜ አንዳችንን በቀኝህ አንዳችንን በግራህ አስቀምጠን” እያሉ መለመን ጀመሩ..
- ጌታችን ግን ሲመልስ ታላቅ ሊሆን የሚወድ አገልጋይ ባሪያ እንዲሆን ይነግራቸዋል
- ጌታችን የበርጤሜዎስን ዓይን ስለማብራቱ [በር-ጤሜዎስ ማለት ወልደ ጤሜዎስ ወይም የጤሜዎስ ልጅ ማለት ነው.. “ጤሜዎስ” የአባቱ ስም ሲሆን “በር-” ምትለዋ የፊት ቅጥያ እኛ “ወልደ-“(ልጅ) እንደምንለው ነው]