Telegram Web Link
“ከዝሙት ሽሹ” - [1ቆሮ 6:18]

የትኛውም ክርስቲያን ማግባት ካለበት ወይ ያገባል እንጂ በሌላ ነገር ብንደክም እንኳን ከተለያየ ሴት ጋር እየዘሞትን ግን ልንኖር አይገባም..

እውነቱን ለመናገር ይሄ አይመጥንምም.. የኢየሱስ ነን.. ስለዛ እንዲህ የምናደርግ በጊዜ በንስሐ እና ቅዱስ ቁርባን መመለስ ይኖርብናል..

አንዳንድ ልጅ ባለጌ ከሆነ “ቤተሰብ አሰዳቢ” ይባላል.. እኛ ደግሞ እግዚአብሔር አባታችንን እንዳናሰድብ በጣም ጥንቃቄ ይፈልጋል..

@Apostolic_Answers
ወላጆች ልጃቸውን በተሳካ ሁኔታ ያሳደጉ ሚመስላቸው ያው አሳድገው አስተምረው ምናምን ከዛ ሲመረቅ ነው😁😁

ግን ትልቁ ድል ልጅን ከቅዱስ ቁርባን ሳያርቁ የእግዚአብሔርን ቃል እያስተማሩ በመንፈሳዊ ሕይወቱ አሳድጎ ቅዱስ ልጅ ሲያደርግ ነው..

ለዘላለም የሚኖረው የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሳይሆን የእግዚአብሔር መንግሥት ነው.. ስለዛ እሱ ላይ በጣም ይሠራ..

@Apostolic_Answers
አንዱ “ጊዮርጊስ ለአጃው/ለራሱ ጉዳይ ነው የተገዘገዘው ምን አገባኝ እኔ” እያለ በንዴት ሲደነፋ አየሁት.. ማለት ሌላው ቢቀር አሁን ይሄ እሱን ምን አናደደው..?? ጳውሎስ ለራሱ ነው የተሰየፈው ምን አገባኝ እያሉ እንደመደንፋት ማለት ነው ይሄ.. ቢያንስ እንደሱ መታመን አለብኝ አይባልም..??

ጋይስ ማርያምን በጣም ነው ሚሰለቸው ግን ሁሉም ነገር.. ብቻ ጌታ ይርዳን እንጂ በስመአብ..
አንድ ታዋቂ መምህር በየዋሕነት ለእመቤታችን ካለው ፍቅር የተነሳና ያው ሰዎች የጠፋባቸውን የእግዚአብሔርን ምሳሌ በጌታ በኩል ከማግኘታቸውም አንጻር በማለት እንደው እንዲህ አሉ:-

[ማርያም የጌታ ባሪያ አይደለችም.. ለትህትና ነው ራሷን “እነሆኝ የጌታ ባሪያ” ያለቸውም..]

ጋይስ ያው ግን ወላዲተ አምላክ እውነተኛ የእግዚአብሔር ባርያ ናት.. ለእርሷ ይህም ክብሯ ነው.. ጌታችን ራሱ ራሱን ዝቅ አድርጎ በሥጋ ስለመምጣቱ እንደዛ ተብሏል.. ብቻ ያው እንደዛ ነው..

@Apostolic_Answers
😆😆 ከክርስቲያን ኤዲተሮች ማንም አያመልጥም

https://vm.tiktok.com/ZMSRLeQuD/

———
እንዲህም ያለ ደግሞ ጥሩ አሳብ ያለው ፕሮቴስታንት አለ..

https://vm.tiktok.com/ZMSRhPLmn/

በእርግጥ አሉን ግን አሁን ላይ በብዛት የሚያስፈልጉን አገልጋዮች..


- ጌታ ኢየሱስን ከልባቸው የሚወዱና የስብከታቸውም ማእከል ሁሌ እርሱ የሆነ

- ከቅዱስ ምስጢር(ቁርባን) ያልራቁና የጸሎት ሕይወት ያላቸው..

- የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለይተው ከጥንቱ አንጻር በደንብ የተማሩ

- ፍቅርን ከሕግ የሚያስቀድሙ.. ስለዚህም ለክርስቲያን ወንድም እህቶቻቸውም ሆነ ለሌሎችም ፍቅር ያላቸው

- ስለ ነፍሳት መዳን ግድ የሚላቸው.. የነፍሳት መጥፋትም የሚያንገበግባቸው

- አገልግሎት ለሰማያዊ ክብር እንጂ ለምድራዊ ክብር እንዳልሆነ የተረዱ.. ስለዚህም በምድራዊ ነገር አብዝተው ያልተያዙ

- በየሄዱበት የቤተ ክርስቲያን ነገር የሚያሳስባቸውና አንዳንድ ጉድለቶችን ለመሸፈን የማይታክቱ..

እንዲህ ያሉ አገልጋዮች ለቤተ ክርስቲያን ያስፈልጓታል

@Apostolic_Answers
አሜሪካ ያሉ ወንድሞች (እነ ምህረት) ሲጠያየቁ ሰምቼ ነው እና እናንተን እስቲ ልጠይቃችሁ..

መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ካሉ ሰዎች ውስጥ ከአንዱ ጋር እራት ለአንድ ቀን አብራችሁ ብሉ ብትባሉ ማንን ትመርጣላችሁ እና ደግሞ ለምን..?? መጠየቅ ከፈለጋችሁም ምን ልትጠይቁ ትችላላችሁ..??

ከጌታችንና ከወላዲተ አምላክ ውጪ ማለት ነው..
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፈረደብኝ ሶዬ ሎል..

በቃ ላይቭ ገብተን ትንሽ ስለ ኢየሱስና ቅዱስ ቁርባን እንማማራ..
ድብ ወይስ የሚደፍርና የሚገድል ወንድ..??

ምንም ጥያቄ የለውም እንዲህ ያለው ወንድ ምንም እንኳን ክቡር ሆኖ ቢፈጠርም እንደ እንሰሳ ሆኗልና(መዝሙረኛው ዳዊትም እንደሚናገረው) ከድብ ጋር ቢነጻጸር ምንም አይገርመንም..

ከእንደዚህ ዓይነት “ሰው” ጋር በተለይ ክርስቲያን ከሆነ እንደውም መብል እንኳን አብረነው እንዳንበላ በመጽሐፍ ታዝዘናል.. ያው በንስሐ እስካልተመለሰ ድረስ ማለት ነው..

—————//////————-

ድብ ወይስ ማንኛውም የማናውቀው ወንድ..??

ይሄ ህክምና የሚያስፈልገው ነው በእውነት.. በቃ አብዛኛው ወይም ሁሉም ወንድ ገዳይና ደፋሪ ነው የሚል አሳብን ይዘው የተነሱ ፌሚኒስቶች አሳብ ነው ይሄ.. ስለዛ ክርስቲያኖች ከዚህ ከሁለተኛው እንጠንቀቅ.. እህቶች ከጥቃቶች መጠበቅ አለባቸው ግን በየመንገዱ ያለውን ክርስቲያን ወንድሞቻቸውን ሁሉ ይሄም እንደዛው ነው በሚል ዓይን እያየች መሆን የለበትም.. አብረሽው ምትቆርቢው ወንድምሽ ነውና ነገሩን ጠቅላላ እንዳናቦካው..

@Apostolic_Answers
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል:

የዮሐንስ ወንጌል 14
1፤ ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።
2፤ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤

.
.
.
6፤ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።

- ለዘላለም የምንኖርበት በአብ ዘንድ መኖሪያ አለን.. ይህ ትልቅ ተስፋ ነው.. አዲሱ ሁሌም አዲስ የሚሆነውም የማያልቀው ሕይወት ከፊታችን አለ..

- ጌታ ኢየሱስ ደግሞ መንገዳችን ከሆነ እርሱ እውነትም ከሆነ ራሱ ደግሞ ሕይወትም ከሆነ እንግዲያውስ ኢየሱስን ይዘን ልባችን አይታወክ አንፍራ.. በዚህ መንገድ የሚሄድ ይህንን እውነት የያዘ ይህንን ሕይወት ያገኘ ሁሉ በአብ ቤት ለዘላለም ይኖራል..

- በኢየሱስ መንገድ የምንሄደው ግን የእርሱን ፈለግ በመከተል በቅድስና ሕይወት ሊሆን ይገባዋል.. ከቅዱስ ምስጢር ያልራቀ ፍሬ ያለበት ሕይወት..

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
ትምህርት ላይ ጾመኛ የሆነው መንፈስ

የጴንጤዎቹ መንፈስ ለአገልጋዮቹ የአበበችን አክስት ስም ያሳውቃል ስልክ ቁጥር ይናገራል እና ሌላ ሌላም ማለት ነው..

ይህን ሁሉ የሚናገረው መንፈስ ግን ያው በዛ ደረጃ ከተናገራቸው አይቀር ለምን ብዙዎችን ስላለያዩ ትምህርቶች ትክክለኛውን አይናገርም..?? አስባችሁታል መካነ ኢየሱስ ያለው መንፈስ “ጥምቀት ያድናል” ብሎ ሙሉ ወንጌል ያለው መንፈስ ደግሞ “ኧረ አያድንም” ሲል.. ከዛ ኦንሊ ጂሰስ ጋር ያለው ደግሞ ቀበል አድርጎ “ሥላሴ ሚባል ነገር የለም” ሲል😭😭

ችግሩ ትምህርት ላይ ጾመኛ ነው

@Apostolic_Answers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እኔ ምላችሁ ጋይስ.. ዝም ብዬ ሳስበው በጌታ ምህረትና ቸርነት እዚህ ቻናል ላይ ያለን ክርስቲያን ወንድም እህቶች በመንግሥተ ሰማያትም የምንገናኝ ይመስለኛል..

እስቲ እናድርገው የምር ሁላችንም እየቆረብን ንጹሕ ልብን ይዘን በመኖር
አንዳንዴ በበሽታ ተጠቅተን ምናምን ግን ደግሞ በሽታውን ሳናውቀው ለጊዜውም የህመም ስሜት ሳይሰማን በብዙ ውስጣችን ሊጎዳ ይችላል..

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም እንደዛ እየሆነች ነው.. ብዙ ሕዝብ ይዛለች ምናምን እና በዛ ምክንያት ሰላም ሊመስል ይችላል ግን ደግሞ ሕዝቦቿ በአብዛኛው ከንስሐ ሕይወትና ከቅዱስ ቁርባን የራቅን.. ቤተሰብ ስንመሰርት ስናገባ እንኳ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ውጪ ያለ ቅዱስ ቁርባን.. በአጭሩ የልምድ ብቻ ክርስቲያን ሆነናል..

እረኛ እንኳ ብዙም የላት.. ያሉት በዘር እና በገንዘብ የተተበተቡና ሰው ሲጋደል ራሱ ግድ ማይላቸው.. የምእመናን የድኅነት ጉዳይ ግድ ማይሰጣቸው ይመስላሉ.. ምን አለፋአችሁ ቤተ ክርስቲያን በጣም አደጋ ውስጥ ናት..

ስለዛ በዚህ ጊዜ ሁላችን በያለንበት የራሳችንን ሃላፊነት እንወጣ.. ጌታ ይርዳን..

@Apostolic_Answers
የጌታችን እርገት ለእኛ ምንድን ነው..??

ይሄ ተስፋ በጣም ነው ደስ የሚለኝ

https://vm.tiktok.com/ZMSMrfgDp/

————
2025/06/28 10:17:14
Back to Top
HTML Embed Code: