ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ.. በጌታ ስም የሚምጣ የተባረከ ነው

መሲሕ ኢየሱስ አድነን(ሆሣዕና).. በአህያ ላይ ተቀምጠህ በጌታ ስም የመጣህ የተባረክ የዳዊት ልጅ ሆይ ሆሣዕና አንተ መድኃኒት ነህና

ከቅዳሴ ምናምን በኋላ እንገናኝ እንዳትቀሩ ከቅዳሴ😊🤗
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል..

የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡና፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው፡ እያሉ ጮኹ።
[ዮሐንስ 12: 13]

የጌታችንን ንግሥና እየመሰከረች ኢየሩሳሌም ተቀበለችው.. እርሱም ወደ እርሷ ትሁት ሆኖ በአህያ ውርንጫ ተቀምጦ ገባ..

ዛሬም እኛም ኢየሩሳሌምን መስለን የክብርን ጌታ እንደ ንጉሥ ወደ ልባችን ይገባ ዘንድ እንቀበለው.. እርሱም እንደ ትህትናው ወደ እኛ ልብ ይግባ በልባችንም ይንገስ..

መልካም የንጉሣችን ቀን

@Apostolic_Answers
ኢየሱስ ተስፋችን

ያለን ኢየሱስ ብቻ ነው..
ተስፋችንም እርሱው ነው
ራቅ ብለን😁 መልካም ቅዳሴ
ክርስቶስ ተንሥአ እምውታን በአብይ ኃይል ወሥልጣን

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት:

“አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት(የመጀመሪያ) ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።”
[1ኛ ቆሮንቶስ 15: 20]

ሞት ኢየሱስን ሊይዘው አልቻልም.. ጌታችን ሞትን ያለበት ድረስ ሄዶ ኃይል አሳጣው.. እርሱ ራሱ በባህሪው መሞት መነሳት ያልነበረበት ሲሆን በፈቃዱ ስለ እኛ ሲል ሞተ ተነሣም.. ኢየሱስ የትንሳኤያችን በኩር ነው.. እርሱ ተነስቷልና እኛም እንነሣለን..

ስለርዚህም የእርሱ ትንሳኤ ትንሳኤያችን ነው

እኛስ የተሰቀለውን ይልቁንም ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንሰብካለን

እንኳን አደረሳችሁ እናንት የእግዚአብሔር ምርጦች

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
ዌል አሁን ደግሞ ጺማችንን እንቆረጣለን.. ምክንያቱም የራሳችን ወንድሞች እውነተኛው ፍየል(the real GOAT) ይሉን ጀመር

https://vm.tiktok.com/ZMMnwcKkj/
የየኔታ በትረማርያም ማብራሪያ

ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክም ሰውም እንዳልነው ሁሉ ፈጣሪም ፍጡርም እንለዋለን። ይህንንም ግልጽ በሆነ አነጋገር ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ጽፎልናል። "ፍጡር ወኢፍጡር" እንዲል (ሃይ. አበ. ፴፭)። ፍጡር ሥጋ ፍጡርነቱን ሳይለቅ ፈጣሪ ሆነ። ፈጣሪ መለኮትም ፈጣሪነቱን ሳይለቅ ፍጡር ሆነ። በሃይማኖተ አበው ምዕራፍ ፴፮ እንደተገለጸው ኢያፍለሰ ትስብእቶ ፍጡረ ለከዊነ ፈጣሪ ወኢያፍለሰ ፈጣሪ መለኮቶ ለከዊነ ፍጡር ተብሏል። ፍጡር ሥጋ ፍጡርነትን ሳይለቅ ፈጣሪነትን ገንዘብ አድርጓል። መለኮትም ፈጣሪነትን ሳይለቅ ፍጡር ሥጋን ገንዘብ አድርጓል።
ይህ የየቀድሞ ማንነትን ሳይለውጡ ሌላውን ገንዘብ ማድረግ ተዋሕዶ በተዐቅቦ ይባላል።

ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ይባላል። ይህም ማለት ሥጋው ቅድመ ዓለም የነበረ ሳይሆን የተፈጠረ ነው ማለት ነው።

አርዮስ ክርስቶስ በመለኮቱ ፍጡር በማለቱ ታላቅ ክሕደትን ካደ። ለዚህም ሠለስቱ ምእት በመለኮቱ ፈጣሪ መሆኑን ለመግለጽ ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ ብለው መልሰውለታል። በሥጋው ፍጡር እንደሆነ ግን እነ ቅዱስ ቄርሎስ፣ እነ ቅዱስ ጎርጎርዮስና ሌሎችም ቅዱሳን ሊቃውንት የጻፉት ነው። አንዳንዱ ክርስቶስን አምላክም ሰውም፣ ፈጣሪም ፍጡርም ስንለው እንደ ካቶሊክ የምንታዌ ትምህርት አድርገው ያስቡታል። ግን ስሕተት ነው። አንድን ሰው በነፍሱ ረቂቅ በሥጋው ግዙፍ ስንለው ሁለት እያደረግነው አይደለም። ያው አንዱ አካል ረቂቅም ግዙፍም መሆኑን መግለጽ ነው እንጂ።

አንዳንዶች ከተዋሕዶ በኋላ ሥጋ ፍጡርነቱን ለቋል የሚሉ አሉ። ነገር ግን ሃይ. አበ. ፴፮ ላይ በግልጽ ተጽፏል። ሲዋሐድ ቅድመ ተዋሕዶ የነበረውን እንቲኣሁነት (የራሱን ገንዘብነት) ሳይለቅ ነው። በተዋሕዶ ጊዜ ፈጣሪ ቃል ወደፍጡር ሰውነት አልተለወጠም። ፍጡር ሥጋም ወደ ፈጣሪ መለኮት አልተለወጠም። አይ ከተዋሕዶ በኋላ ፈጣሪ ብቻ እንለዋለን ከተባለ ግን ይህ የአውጣኪ ክሕደት ነው። መለኮት ሥጋን ውጦታል ያሰኛል። ክርስቶስን ከተዋሕዶ በኋላ ሰው ካልነው ፍጡርም እንለዋለን ማለት ነው። ሰው ስንለው ግን እንደሌላው ዕሩቅ ብእሲ (ሰው ብቻ) አንለውም። አምላክም ሰውም ፈጣሪም ፍጡርም እንለዋለን እንጂ።

© በትረማርያም አበባው

(የመጻሕፍተ ሊቃውንት የመጻሕፍተ ብሉያትና የመጻሕፍተ መነኮሳት ትርጓሜ መምህር)

@betremariyamabebaw
@betremariyamabebaw

☝️☝️☝️☝️

የሳቸው ቴሌግራም ቻናል ነው ተቀላቀሏቸውና ሌሎችንም ትምህርቶች አግኙ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከጉባኤ ኬልቄዶን በኋላ ከተነሱ ድንቅ የተዋሕዶ ነገረ ክርስቶስ(miaphysite christology) ተንታኞች ውስጥ ግምባር ቀደሙ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ ነው.. ጉባዔ ኬልቄዶን ከተደረገ ከ15 ዓመት በኋላ የተወለደ ነው.. እና ከቄርሎስ በኋላ በሚገባ ነገረ ክርስቶስን ያብራራ ሰው ነው.. ለኬልቄዶናውያንም ብዙ መልስን መልሷል..

እና ኬልቄዶንን እንደ ንስጥሮሳዊ ጉባዔ ስለሚያየው “የኬልቄዶን ደጋፉዎችን(አባቶችን) የሚያያቸው የአውጣኪያዊነትን ሰይጣን በንስጥሮሳዊ ብዔልዜቡል ለማውጣት እንደሚሹ ሰዎች ነበር” 🤭🤭 ይመቸው..

በረከቱ ይደርብን የዚህ ሊቅ ቅዱስ አባት

@Apostolic_Answers
የፕሮቴስታንት እምነትን እንድንጠየፈው ከሚያደርጉን ምክንያቶች(ሰዎች) መካከል🤦‍♂️🤦‍♂️

https://vm.tiktok.com/ZMMWQotrs/
አንዱ ብሮ ቴሌግራም ላይ ጽፎልኝ ያው ብዙ ስለሚላክ አጋጣሚ አላየሁትም እና እንዳየው ምን ቢያደርግ..?? ቴሌግራም የዓመት premium 🎁 ላከልኝ.. ምን ጉድ ነው ብዬ ሳየው ይኸው እያወራኝ ነው.. ጉበኛ ሰው ነው😁😁

አሁን በቃ የምጠቀማቸው ኢሞጂዎች ራሱ እናንተ መጠቀም የማትችሏቸውን ነው😁😁
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“ሉተርን ተቹ” ብለው የሚከሱ ሰዎች ካልቪንን ሲከሱ😁😁

ትንሽ ሲበሳጩ የሚሰድቧቸው አባቶች ነው ያሏቸው አንዳንዶቹ😁😁

https://vm.tiktok.com/ZMM7FANgW/
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖቷን ዘርዝራ እንደ ካቶሊክ አላስቀመጠችም ስለዛ ሃይማኖቷ የቱ እንደሆነ ለማወቅ ያስቸግራል ለሚሉ..

እኛ በ እርግጥ እያንዳንዱን ነገር define እናድርግ አንልም.. ግን ደግሞ ሃይማኖታችን በተገለጠልን ልክ በግልጽ ተነግሯል.. ለምሳሌ የኒቂያው እና የቁስጥንጥንያው ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ የተደነገገው ሁሌም የምንጸልየው “የሃይማኖት ጸሎት) እሱ ነው ሃይማኖታችን..

እዛ ላይ የተነገሩት ደግሞ በስፋት በጥንታውያን አባቶች ለምሳሌ በቅዱስ አትናቴዎስ በኩልም ተብራርተዋል.. ከዛ በተረፈ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ 5ቱ ዓዕማድ ምስጢራት ተብሎ የሚሰጥ ትምህርት አለ እሱንም መመልከት..

@Apostolic_Answers
የሃይማኖት ችግር ተገኝቶብኝ አይደለም ተሃድሶ የተባልኩት ነበር ያለው..??😁😁

ሌዲስ ኤንድ ጀንታላ ሜን.. ዊ ጋት ሂም😄😄

https://vm.tiktok.com/ZMMv23HVM/
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/05/14 03:55:38
Back to Top
HTML Embed Code: