Telegram Web Link
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያ በሚሰጠው የፈተና ገለጻ/Orientation/ ላይ መገኘት እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦላይን ለመስጠት በቂ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በከተማ አስተዳደሩ የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦላይን ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸዉን እንዲሁም ፈተናው ከሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ የገለጹ ሲሆን ተማሪዎች በፈተና መስጫ ጣቢያዎች በወጣው መርሀ ግብር መሰረት በመገኘት ፈተናዉን ሊወስዱ ይገባል ብለዋል፡፡

አቶ ዲናኦል አክለዉም የፈተና አሰጣጡን አስመልክቶ ገለጻ በፈተና ጣቢያዎች የሚሰጥ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ የሁለተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት የሚሰጠውን የፈተና ገለጻ/Orientation/ መከታተልና የመፈተኛ ቦታቸዉንና ክፍላቸዉን ማየት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ፈተና ማዕከላት እየገቡ ነው

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ፈተና ማዕከላት እየገቡ ነው አለ የክልሉ ትምህርት ቢሮ።

በቢሮው የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ታገሰ ለፋና ዲጂታል እንደገለጹት፤ ዘንድሮ 35 ሺህ 246 የክልሉ ተማሪዎች ሀገር አቀፉን የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ።

ከሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ወደ ተዘጋጁ የፈተና ማዕከላት መግባት መጀመራቸውን ተናግረዋል።

ለ35 ሺህ 246 ተማሪዎች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል በቂ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።

በበይነ መረብ ፈተና ለሚወስዱ 7 ሺህ 211 ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች እና በአዳሪ ትምህርት ቤቶች ዘጠኝ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ገልጸው፤ ተማሪዎቹ ስለ ፈተና አሰጣጡ ስልጠና ማግኘታቸውን አስታውሰዋል።

በወረቀት የሚፈተኑ 28 ሺህ 35 ተማሪዎች ደግሞ በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ልምምድ አድርገዋል ብለዋል።

በወረቀት የሚፈተኑ ሁሉም ተማሪዎች ፈተውን የሚወስዱት በዩኒቨርሲቲዎች ብቻ መሆኑንም አመላክተዋል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በአዲስ አበባ የ28 ትምህርት ቤቶች እውቅና ለምን ተሰረዘ?

በየሁለት ዓመቱ በሚደረገዉ የእዉቀና እድሳት ከደረጃ በታች ሆነው የተገኙ 28 ትምህርት ቤቶች እዉቅና መሰረዙን፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ሥራ አስኪያጅ ኢዘዲን ሙስባህ ገለፁ።

ከደረጃ በታች በሆኑ ትምህርት ቤቶች ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ስለማይሰጥ እና ትወልድን አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ፤ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

በ2017 የትምህርት ዘመን ላይ በማስጠንቀቂያ እንዲያስተምሩ ጊዜ ቢሰጣቸውም፤ የእድሳት ፍቃድ ምዘና ውጤታቸው ባለመሻሻሉ ብሎም ዝቅተኛ እና ከደረጃ በታች በመሆኑ እውቅናቸው ተሰርዟልም ነው ያሉት።

ወላጆች ይህን በመገንዘብ ልጆቻቸዉን በሌሎች ትምሀርት ቤት እንዲያስመዘግቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር አሳውቋልም ብለዋል።

የትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻል እና የትምህርት ጥራት ችግሮችን መቅረፍ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ75ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን ዛሬ ያስመርቃል


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን ተመራቂዎች ለ75ኛ ጊዜ ያስመርቃል፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና የክብር እንግዶች እንደሚገኙ ከወጣው መርሐ-ግብር ለመረዳታ ተችሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት 3334 የመጀመሪያ ዲግሪ፣ 2859 የሁለተኛ ዲግሪ፣ 304 የሦስተኛ ዲግሪ እና 352 የስፕሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊቲ በአጠቃላይ 6849 ተማሪዎችን ያስመርቃል፡፡

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ይጀምራል፡፡


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ATC NEWS
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ75ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን ዛሬ ያስመርቃል አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን ተመራቂዎች ለ75ኛ ጊዜ ያስመርቃል፡፡ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና የክብር እንግዶች እንደሚገኙ ከወጣው መርሐ-ግብር ለመረዳታ ተችሏል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት 3334 የመጀመሪያ…
የ6ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች ለእናቷ የገባችውን ቃል ያሳካችው ተመራቂ


የአብስራ ሽፈራው ትባላለች። የ6ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእናቷ ምርቃት ላይ ተገኝታ ነበር።

ያኔ ታዲያ "በዚህ ግቢ ተምሬ እመረቅበታለሁ" ስትል ለእናቷ ቃል ገብታላት ነበር።

እንሆ ዛሬ የአብስራ ያን ቃሏን አሳክታለች። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል 3.5 በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ በዲግሪ ተመርቃለች።

አካል ጉዳተኝነት ያልበገራት የአብስራ በመምህሮቿ የተመሰገነች ታታሪ ተማሪ ስትሆን፤ ለዚህ ስኬቷ ደግሞ የእናቷ አበርክቶ ትልቅ ድርሻ ይወስዳል።

በ4 ዓመታት የዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ እናቷ እርሷን በማመላለስ እና በማበረታታት ለዚህ አብቅታታለች።

የአብስራ እናት፥ "ልጆቻችን አካል ጉዳተኞች ናቸው ብለን በየቤቱ ደብቀን ይበልጥ ከምንጎዳቸው፤ መስዋዕት ከፍለን ካሰቡበት እናድርሳቸው" ስትል ለወላጆች መልዕክት አስተላልፋለች።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ውድ ደንበኞቻችን ከዚህ በታቹ ካሉት website ላይ ማዘዝ የምትፈልጉትን ማንኛውንም እቃ photo  screenshots በinbox  ይላኩልን 

👨‍💻   Amazon.ae
👨‍💻    Shein.com
👨‍💻    Zara.com
👨‍💻   Noon.com
👨‍💻   Sephora.com

በ 7 ቀን ውስጥ ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ እናደርሳለን

📞0946362749( @eden16mg)

join our telegram channel 🫴🫴

https://www.tg-me.com/edmart24
2025/07/05 17:15:08
Back to Top
HTML Embed Code: