Telegram Web Link
በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን የተመደቡ ተማሪዎች ፈተናቸውን የጀመሩ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር የፈተና አጀማመሩን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዚህም ለፈተና የሚያግዙ መሰረተ ልማቶቹ መሟላታቸውን ተፈታኞችም በፈተና ቦታቸው ላይ መገኘታቸው ተገልጿል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ልጇን በሰላም ተገላግላ የ12ኛ ክፍል ፈተናን በመውሰድ ላይ የምትገኝ ተማሪ


ሙስተሪያ ሙሳ ትባላለች፤ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሚገኘው ጤና ጣቢያ ልጇን በሰላም ተገላግላ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየወሰደች ትገኛለች።

ሙስተሪያ ልጇን በሰላም ከተገላገለች በኋላ አሁን ላይ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደምትገኝና ልጇም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ተማሪ ሙስተሪያ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከግራዋ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጣችው፡፡

ለፈተና ወደ ዩኒቨርሲቲው በገባችበት ወቅት አርብ ምሽት 3 ሰዓት አካባቢ ልጇን በሰላም እንደተገላገለች የምትገልፀው ሙስተሪያ፤ 2.8 ኪ.ግ የምትመዝን ሴት ልጅ በሰላም መገላገሏን ተናግራለች።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በወረቀትና በበይነ መረብ እየተሰጠ የሚገኘውን ፈተና በዛሬው እለት መስጠት ጀምሯል።

በዩኒቨርሲቲው ከተመደቡ 7 ሺህ 29 ተማሪዎች መካከል 4 ሺህ 271 ወንድ እና 2 ሺህ 375 ሴት በድምሩ 6 ሺህ 646 ተማሪዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ።

ለፈተና መጥታ ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ጤና ጣቢያ ውስጥ ልጇን በሰላም የተገላገለች ሙስተሪያም ፈተናውን እየወሰደች ትገኛለች፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በአራት ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ ነው

በትግራይ ክልል የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በክልሉ በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ እየተሰጠ ነው።

ፈተናውን በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ያስጀመሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ናቸው።

ፕሬዝዳንቱ ተፈታኝ ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናውን እንዲወስዱና የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በአራቱም ዩኒቨርሲቲዎች እየተፈተኑ የሚገኙ ተማሪዎች 36 ሺህ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ(ዶ/ር) ናቸው።

ፈተናውን በስኬት ለማጠናቀቅም የክልልና የፌዴራል ፀጥታ አካላት በትብብር እየሰሩ እንደሚገኙ ኃላፊው ተናግረዋል።

በመቀሌ እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ ፈተና እየወሰዱ ካሉት ተፈታኞች መካከል አንዳንድ ተማሪዎች እንደገለጹት በጥረታቸው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመግባት በቂ ዝግጅት አድርገዋል።

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በወረቀትና በኦንላይን እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማሳወቁ ይታወሳል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/06/30 22:38:01
Back to Top
HTML Embed Code: