#JinkaUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ግቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 18 እና 19/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news

#MattuUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በመቱ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የምዝገባ ቦታ
➫ በ2018 ዓ.ም መቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
➫ በ2017 ዓ.ም በመቱ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርት የተከታትላችሁና ያለፋችሁ በበደሌ ካምፓስ
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኒውክሊየር ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በኒውክሊየር ሳይንስ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝ ያስታወሱት ተቋሙ ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር)፤ በመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ለመቀበል የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት ትምህርቱን ለመስጠት የሚያስችሉ የህንጻ እና የላብራቶሪ ግንባታ እንዲሁም የመምህራን ስልጠና ሲደረግ መቆየቱን ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል፡፡
በተመሳሳይ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኒውክሊየር ሳይንስ በሁለተኛ ዲግሪ ሲያስተምራቸው የነበሩ ተማሪዎችን በተያዘው ዓመት ለመጀመርያ ጊዜ እንደሚያስመርቅ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ለሸገር ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡
መንግሥት የኒውክለር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ መንገድ ለመጠቀም የሚደረግን ጥረት የመምራትና የማስተባበር ኃላፊነት የተሰጠው የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ማቋቋሙ ይታወቃል፡፡
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለዘርፉ የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል ለማፍራት እንደሚሠሩ ለሸገር ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ9-12ኛ ክፍል ይሸፍናል፡፡ - MOE
ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከት ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች እንዲሁም ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ትናንት ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ደብዳቤ ልኳል፡፡
በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ሥራ አስፈጻማ ቴዎድሮስ ሽዋርገጥ (ዶ/ር) የተፈረመው ደብዳቤው፤ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ9-12ኛ ክፍል እንደሚሸፍንና ተማሪዎች የተማሩትን ይዘቶች የሚፈተኑ መሆኑን ይገልጻል፡፡
ብሔራዊ ፈተናው ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍሎች የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይዘቶችን መሠረት ያደረገ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡
በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትምህርት ቤቶች 9ኛ ክፍልን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት፤ ሌሎቹ ደግሞ በቀድሞው ስርዓተ ትምህርት የተማሩ በመሆኑ ፈተናው ከሁለቱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ የሆኑ ይዘቶች ተጣጥሞ የሚወጣ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ሪፎርም መሠረት የሁለተኛ ደረጃ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትግበራ በማካሔድ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ መገባቱ ይታወቃል፡፡