Telegram Web Link
ATC NEWS
#MattuUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በመቱ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ ➫ በ2018 ዓ.ም መቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ…
#MattuUniversity #ማስተካኪያ

የምዝገባ ቦታ

➫ በ2018 ዓ.ም መቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በዋናው ግቢ

➫ በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በመቱ ዩኒቨርሲቲ በደሌ ካምፓስ የተከታትላችሁና ያለፋችሁ በበደሌ ካምፓስ ፤ በመቱ ካምፓስ የተከታተላችሁና ያለፋችሁ በመቱ ካምፓስ

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#Update

የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ይዘቶች ይፋ ሆኑ፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ተማሪዎች፣ የተማሪ ቤተሰቦች፣ መምህራንና የትምህርት አመራር ለፈተና ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ፈተና የሚሸፍናቸው የይዘት አካባቢዎች ይፋ አድርጓል።

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ከፍል ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር የሚከተሉትን ያካትታል፡፡ 

1. የትምህርት ዓይነቶችን በተመለከተ

ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ፦
- እንግሊዘኛ፣
- ሒሳብ፣
- እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣
- ኬሚስትሪ፣
- ፊዝክስና ባዮሎጂ

ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ፦
- እንግሊዘኛ፣
- ሒሳብ፣
- እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣
- ታሪክ፣
- ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው።

2. ፈተናው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ደረጃዎችን እና በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች ይሸፍናል፡፡

3. ከ10ኛ – 12ኛ ክፍል ሁሉም የትምህርት ዓይነት ፈተና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት እየተዘጋጀ ያለ ሲሆን የ9ኛ ክፍል ደግሞ የሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ፈተናዎች ከቀድሞውና ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘቶችን ብቻ አካቶ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

4. ፈተናው ማንኛውም ተፈታኝ ተማሪ ከተማረው ሥርዓተ ትምህርትና ከተማሪው መጽሐፍ ላይ ብቻ ተመስርቶ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

5. የፈተናው አስተዳደር በበይነ መረብና በወረቀት ጎን ለጎን የሚሰጥ ሲሆን አብዛኛው ተፈታኝ በበይነ መረብ እንዲፈተን እየተሠራ ያለ በመሆኑ ተፈታኞች እራሳቸውን በበይነ መረብ ለመፈተን ሊያዘጋጁ ይገባል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#ቴምርፕሮፐርቲስ

⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል።

📍 ሊሴ ገ/ማርያም

ባለ 1 መኝታ
👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000)
👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500)

ባለ 2 መኝታ
👉 78 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,970,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (897,000)
👉 99ካሬ ሙሉ ክፍያ = 11,385,000
                ቅድመ ክፍያ = 10% (1,138,500)

ባለ 3 መኝታ
👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000
                   ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000)
👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000)

📍 አያት (ፈረስ ቤት)

ባለ 2 መኝታ
👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000
                 ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000)

ባለ 3 መኝታ
👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000)
👉 121 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 11,495,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,149,500)
👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000
                   ቅድመ ክፍያ = 10% (1,570,000)

📍 ተክለሐይማኖት (ሱማሌ ተራ)

ባለ 3መኝታ
👉 110ካሬ ሙሉ ክፍያ = 12,100,000ብር
                  ቅድመ ክፍያ = 10% (1,210,000) ብር

📍ሀይሌ ጋርመንት
ባለ 3መኝታ
👉 139ካሬ ሙሉ ክፋያ =14,595,000 ብር
           ቅድመ ክፋያ 10%= (1,459,500ብር)

⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251936650128
+251994495655
#ETA

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመራቂ ተማሪዎቻቸውን ዝርዘር መረጃ ያላኩ እንዲልኩ ጠይቋል።

ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣቸው ትምህርት መስኮች፣ ትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ በድኅረ-ምረቃ እና በቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም በ2017 ዓ.ም መጨረሻ የተመረቁ
ተማሪዎች መረጃዎችን ከዚህ በፊት በተላከው ቅጽ መሰረት ከጥቅምት 14-30/2018 ዓ.ም በሶፍት እና በሀርድ ኮፒ እንዲልኩ አሳስቧል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#ETA

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት/ኮሌጆች የሰልጣኞቻቸውን ዝርዝር መረጃ እንዲልኩ ጠይቋል።

ተቋማቱ በስልጠና ዓመቱ የመዘገቧቸውን የሰልጣኞች ዝርዝር መረጃ ለይተውና አደራጅተው በሀርድ እና ሶፍት ኮፒ እስከ ህዳር 15/2018 ዓ.ም ድረስ እንዲልኩ አሳስቧል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MoE

በጥር 2018 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ከዚህ በፊት የመውጫ ፈተና ያልተሰጠባቸው አዳዲስ ፕሮግራሞች ካሏችሁ እስከ ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም በኢ-ሜይል አድራሻ [email protected] እንዲልኩ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጠይቋል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ 0913673404

በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በቀን ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፉት ደብዳቤ፤ በጥር 2018 ዓ.ም ለሚሰጠው ሁለተኛ ዙር የመውጫ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጀመራቸው ተጠቁሟል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#TVTI

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ ነባር መደበኛ ተማሪዎች የ2018 ትምህርት ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ምዝገባ ከጥቅምት 19-21/2018 ዓ.ም መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል፡፡

በመሆኑም ሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ የተቋሙ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ብቻ ምዝገባ እንድታደርጉ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/10/24 15:28:07
Back to Top
HTML Embed Code: