Telegram Web Link
#ESSLCE

ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ የመጀመሪያ ዙር ፈተና ተጠናቋል።

በኦንላይን እና በወረቀት የተሰጠው ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ ተፈታኞች ወደየመጡበት መመለስ ጀምረዋል።

ሁለተኛ ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና ከነገ ሐምሌ 04/2017 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል። ፈተናው ነገ አርብ ተጀምሮ ከሁለት ቀናት ዕረፍት በኋላ ሰኞ የሚቀጥል ይሆናል።

ከ299 ሺህ በላይ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሁለት ዙር እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።

ምስል፦ ደምቢ ዶሎ፣ አሲሰዩ፣ ሰመራ፣ ቦንጋ፣ ወልቂጤ፣ አምቦ፣ ድሬዳዋ፣ አሶሳ፣ ዋቸሞ እና ሐረማያ ዩኒቨርሲቲዎች

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
የሶሻል ሚዲያ ግብር‼️
መንግስት ሶሻል ሚዲያ ላይ ግብር ሊጥል ነው‼️

ዩቲዩብ ፣ ቲክቶክና ከሌሎች የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ሊጣል ነው

በኢትዮጵያ ለዘጠኝ ዓመታት ስራ ላይ የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ለመጣል የሚያስችል ንዑስ አንቀጽ መካተቱ ታውቋል።

በታቀደው የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ መሰረት፣ ከማህበራዊ ሚዲያ የሚገኝ ገቢ (ለምሳሌ ከዩቲዩብ፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ቲክቶክ እና ሌሎችም መድረኮች) ፣ በኢንተርኔት ከሚሰራጩ መረጃዎች እንደሚሁም ከሚፈፀሙ ግብይቶች፣ ከስፖንሰርሺፕ እና ከመሳሰሉት የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ ግብር እንደሚጣልባቸው በዝርዝር ያስቀምጣል።

በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዉይይት እየተደረገበት የሚገኘዉ ይህ ረቂቅ አዋጅ ፤ እነዚህ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በመደበኛነት የሚከናወኑ ከሆነ፣ የሚገኘው ገቢ በንግድ ስራ ገቢ ስር የሚመደብ ሲሆን፣ የንግድ ስራ ገቢ ግብርም የሚከፈልበት መሆኑን ይገልጻል።

ሆኖም፣ በአዋጁ የተቀመጡትን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ፣ ገቢው “ሌሎች ገቢዎች” በሚለው ስር ተመድቦ ከጠቅላላ ገቢው ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር እንዲከፈልበት ይደረጋል ይላል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ለዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክስ ባለስልጣኑ የመላክ ግዴታ እንደሚኖርባቸው ያስቀምጣል።

ይህን ተከትሎም፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት፣ ገቢያቸውን የማስታወቅ እና ሌሎች የታክስ ከፋይ ግዴታዎችን የመወጣት ሃላፊነት እንደሚጠበቅባቸው ያስገድዳል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
📣አሁኑኑ ተመዝገቡ!!!
Course Contents:

Cyber Security Fundamentals
Programming ( Python, bash, HTML ) – basic + For hackers
Networking for hackers
Linux/UNIX Systems
Web Security Fundamentals
Defensive Security Fundamentals
System Penetration Testing
Network Penetration Testing
Report and Documentation

🔥 ለ 100 ሰው ቦታ ነው ያለዉ
ለመመዝገብ 🫴 https://course.geezsecurity.com

ለበለጠ መረጃ👇👇
Contact Us
@geezsecsupport
📞 +251953537820
📬 [email protected]
#geeztech #gtstv2 @geeztechgroup
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Ethiopia🇪🇹

ከዩቲዩብ ፣ ቲክቶክና ከሌሎች የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ሊጣል ነው።

በኢትዮጵያ ለ9 ዓመታት ስራ ላይ የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ለመጣል የሚያስችል ንዑስ አንቀጽ ተካቷል።

በታቀደው የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ መሰረት፣ ከማህበራዊ ሚዲያ የሚገኝ ገቢ ለምሳሌ ፦
- ከዩቲዩብ፣
- ፌስቡክ፣
- ኢንስታግራም፣
- ቲክቶክና ሌሎችም መድረኮች
- በኢንተርኔት ከሚሰራጩ መረጃዎች
- በኢንተርኔት ከሚፈፀሙ ግብይቶች፣
- ከስፖንሰርሺፕ ከመሳሰሉት የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ ግብር እንደሚጣልባቸው በዝርዝር ያስቀምጣል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዉይይት እየተደረገበት የሚገኘዉ ይህ ረቂቅ አዋጅ ፤ እነዚህ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በመደበኛነት የሚከናወኑ ከሆነ፣ የሚገኘው ገቢ በንግድ ስራ ገቢ ስር የሚመደብ ሲሆን፣ የንግድ ስራ ገቢ ግብርም የሚከፈልበት መሆኑን ይገልጻል።

ሆኖም፣ በአዋጁ የተቀመጡትን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ፣ ገቢው " ሌሎች ገቢዎች "  በሚለው ስር ተመድቦ ከጠቅላላ ገቢው ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር እንዲከፈልበት ይደረጋል ይላል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ለዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክስ ባለስልጣን የመላክ ግዴታ እንደሚኖርባቸው ያስቀምጣል።

ይህን ተከትሎም፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት ፣ ገቢያቸውን የማስታወቅ እና ሌሎች የታክስ ከፋይ ግዴታዎችን የመወጣት ሃላፊነት እንደሚጠበቅባቸው ያስገድዳል።

#CAPITAL

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ

ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የመምህራን ቅጥር


ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተሰጥኦ እና ብቃት ያላቸውን ተማሪዎች ለመልመልና ልዩ ትምህርትና ስልጠና ለመስጠት የሚያስችሉ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በመላ ሀገሪቱ በማቋቋም ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

በመሆኑም በነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ብቃት ያላቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መምህራንን ከመላ ሀገሪቱ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

ለመወዳደር የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፦

አካዳሚያዊ ብቃት/የትምህርት ዝግጅት
➫ በሚያስተምሩበት የትምህርት ዓይነት በመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ የተመረቁ

የሥራ ልምድ እና ችሎታ
➫ በ2ኛ ደረጃ ትምህርት መምህርነት አምስት ዓመትና ከዚያ በላይ ያገለገሉ
➫ የመምህራንን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት ተመዝኖ ሰርትፍኬት ያለው/ያላት

መልካም ስነ-ምግባር እና ቁርጠኝነት
➫ በሥራ ላይ ያላቸውን ቁርጠኝነት እና ትጋት ሊመሰክር የሚችል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

➦ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለሚመዘገቡ ዕጩዎች የጽሁፍ ፈተና፣ የቃል ምዘና፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎት ምዘና እንዲሁም የማህደር ጥራት ዋነኛ የምልመላና ምዘና መስፈርት መለኪያዎች ሆነው ያገለግላሉ።

የምዝገባ ሒደት
➫ የምዝገባው ጊዜ በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ እና ዘመገናኛ ብዙሃን ላይ ይለቀቃል። ምዝገባው እስካሁን አልተከፈተም።

ለምዝገባ ብቁ የሆናችሁ መምህራን አስፈላጊ ሰነዶቻችሁን/መረጃዎቻችሁንና የፌዴራል መታወቂያችሁን አስቀድማችሁ ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅባችኋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
🧑‍💻 #GTSTv2 Round_12

በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው የ GeezTech Security Tester(GTST)  Round 12 ምዝገባችን በይፋ ተጀምሯል !🎉🎉

ቀድማችሁ ቦታችሁን ለማስየዝ፥  https://course.geezsecurity.com

👑 ትምህርት ሐምሌ 7 ይጀመራል

ለበለጠ መረጃ👇👇
Contact Us
@geezsecsupport
📞 +251953537820
📬 [email protected]
#geeztech #gtstv2 @geeztechgroup
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#EthiopianDefenceUniversity

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በቢሾፍቱ እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በምህንድስና፣ በጤና ሳይንስ እና በማኅበረሰብ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚገባ በትምህርት ሚኒስቴር መገለፁ ይታወቃል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በ2018 የትምህርት ዘመን ከ100 እስከ 260 በመቶ ጭማሪ የጠየቁ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን ተነገረ

የአዲስ አበባ ትምህርት ጥራት ባለስልጣኑ በ2018 የትምህርት ዘመን የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ላይ ከተማሪ ወላጆች ጋር ባልተስማሙና በልዩነት ባጠናቀቁ ት/ቤቶች ላይ በአገልግሎት ክፍያ አሰራር ስርዓት ደንብ ቁጥር 194/2017 መሰረት ውሳኔ አስተላልፏል ።

ጉዳዩን አስመልክቶ በተደረገ ውይይት  የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ዘላላም ሙላቱ እንደገለጹት  እንደየ አካባቢውና እንደየ ማህበረሰቡ ሁኔታ በርካታ ት/ቤቶችና ወላጆች በጋራ በመወያየት የክፍያ ጭማሪውን አጽድቀው በጋራ በመግባባት ተለያይተዋል፡፡ ባልተስማሙ ት/ቤቶችና ወላጆች ላይ ደግሞ  ባለስልጣኑ የውሳኔ አካል በመሆን በጋራ በመምከር ውሳኔውን አስቀምጧል፡፡

በትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሰራር ስርዓት ደንብ መሰረት ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑ ት/ቤቶች ከወላጆች ጋር በመግባባት የተስማሙ ሲሆን  ቀሪዎቹ ደግሞ ባለመስማማታቸው አቤቱታቸውን ለባለስልጣኑ ማቀረባቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።   በዚህ መሰረት ባለስልጣኑ የወላጆችንም የመክፈል አቅም የትምህርት ተቋማቱንም ስራቸውን በአግባቡ የማስቀጠል አቅም ሚዛናዊ በማረድግ ውሳኔውን እንደሚያሳልፍ ገልጸዋል፡፡

ተቋማቱ ያቀረቡትን የጣራ ክፍያ፣በውይይቱ ወቅት ወላጅ ያቀረበውን ዋጋ፣እንዲሁም ባለስልጣኑ ያስተላለፈውን እያንዳንዱን የክፍያ ውሳኔ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ ውሳኔውንም ለት/ቤቶቹ በደብዳቤ እንደሚሠጥ ተገልጿል ፡፡     

በተጨማሪም ምክንያታዊ የሆኑ ጭማሪዎች አስፈላጊ መሆናቸውን የገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በሌላ በኩል ከ100 እስከ 260 በመቶ ጭማሪ የጠየቁ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን መግለጹን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
📍 Gambella

የጋምቤላ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፈጣን ምድብ ችሎት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሌሎች ተማሪዎች ለመፈተን ሲሞክሩ በተያዙ 18 ተማሪዎች ላይ የእስር ቅጣት ውሳኔ አሳለፈ።

18 ተማሪዎች በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በሌላ ተማሪ ስም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ሲሞክሩ በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸን የጋምቤላ ብዙሃን መገናኛ አገልግሎት ዘግቧል።

በዚህም የጋምቤላ ከተማ ከተማ ፍትህ መምሪያ ከፍተኛ ዐቃቤ ህግ በተከሳሽ እነ ዋው ጊው (ዘጠኝ ሰዎች) እና በተከሳሽ እነ ሯች ጆክ (ዘጠኝ ሰዎች) የፈጸሙትን ወንጀል ተመልክቷል።

ዐቃቤ ህግም ጉዳዩን ለጋምቤላ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፈጣን ምድብ ችሎት አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱ በቀን 05/11/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾቹ በተከሰሱበት የአታላይነት ወንጀል እያንዳንዳቸው በአንድ ዓመት ጽኑ እስራት እና ሦስት ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል። #GMMS

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
👑 40% ቅናሽ ላመለጣችሁ

20% discount የሚቆየው እስከ ሐምሌ 6 (እሁድ) ድረስ ብቻ ነው

ጊዜው ሳያልቅባችሁ ቀድማችሁ ቦታችሁን ለማስያዝ፥ ለመመዝገብ 🫴
https://course.geezsecurity.com

ለበለጠ መረጃ👇👇
Contact Us
@geezsecsupport
📞 +251953537820
📬 [email protected]
#geeztech #gtstv2 @geeztechgroup
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#UniversityOfGondar

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከምሥረታው ጀምሮ ላለፉት 66 ዓመታት ያስመረቃቸው ከአንድ መቶ ሺህ በላይ የቀድሞ ተማሪዎች እንዲሰባሰቡ ጥሪ አቀረበ።

የቀድሞው የጎንደር ሕዝብ ጤና አጠባበቅ ኮሌጅና ማሠልጠኛ፣ የአሁኑ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ተማሪዎችን ካስመረቀበት 195ዐ ዓ.ም እስከ 2016 ዓ.ም 107,860 ተማሪዎችን በተለያዩ መርሐግብሮች ማስመረቁን የተቋሙ ፕሬዝዳንት አሥራት አፀደወይን (ዶ/ር) ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዓመታት በሰርተፊኬት፣ በዲፕሎማ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በዶክትሬት ዲግሪ፣ በስፔሻሊቲና ሰብስፔሻሊቲ፣ እንዲሁም በፖስት ዶክትሬት ዲግሪ በማስመረቅ ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ገልፀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከ3ዐዐ በላይ በሆኑ መርሐግብሮች በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊና በጤናው ዘርፍ ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት ላይ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ አክለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲውን 7ዐኛ ዓመትና የማስተማሪያ ሆስፒታሉ 1ዐዐኛ ዓመት በማስመልከት ከጥር ወር ጀምሮ በተለያዩ መርሐግብሮች ሲያከብር የቆየ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው ሐምሌ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ዘርፎች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል፡፡

የምርቃት መርሐግብሩን ምክንያት በማድረግ በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዘርፎች የተማሩና ለዩኒቨርሲቲው ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከቱ አካላት በ11 ዘርፎች የዕውቅናና ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡ #ሪፖርተር

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/07/14 04:59:19
Back to Top
HTML Embed Code: