Telegram Web Link
የመውጫ ፈተና የስድስተኛ ቀን ፈተናዎች እየተሰጡ ነው።

የዛሬ ሰኔ 9/2017 ዓ.ም ፈተናዎች ጠዋት እና ከሰዓት በሁለት ክፍለ-ጊዜ እንደሚሰጡ የወጣው መርሐግብር ያሳያል።

ነገ ማክሰኞ ሰኔ 9/2017 ዓ.ም በክረምት የመምህራን ስልጠና መርሐግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ 5,521 መምህራን የመውጫ ፈተና እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።

መምህራኑ የመውጫ ፈተናውን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተዘጋጁ 35 የፈተና ማዕከላት ስልጠና በተከታተሉባቸው 24 የትምህርት ፕሮግራሞች እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ተፈታኞች በዛሬው ዕለት ፈተና ለመውሰድ የሚያስችላቸውን User Name እና Password ከሚፈተኑባቸው ተቋማት እየወሰዱ ይገኛሉ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ስትጠብቁት የነበረው የ12 ክፍል ማትሪክ ፈተና አጋዥ አፕሊኬሽናትችን አሁን playstore ላይ ይገኛል። ዳውንሎአድ አድርጎ መጠቀም ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ።
በነጻ
አዲሱን ስር አተ ትምህርት ያካተተ
አጫጭር ኖቶችና አጋዥ ቪድዮዎች የያዘ
አሁኑኑ ይሞክሩት!!!!!!!!!

  መተግበርያውን ለማግኘት👇                                                             
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.exam_time.exam

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት Telegram ቻናላችን ይቀላቀሉ
@thinkhub

#ethiopia #ethiopian #ትምህርት #grade12 #Ethiopians #entranceexam #examtime #time #education #matric #Ethiopians
ፈተናውን ከስርቆት በጸዳ መልኩ እንዲሰጥ በማድረግ ውጤታማና ተወዳዳሪ ትውልድ መፍጠር ይገባል – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ከስርቆት በጸዳ መልኩ እንዲሰጥ በማድረግ ውጤታማና ተወዳዳሪ ትውልድ መፍጠር ይገባል አሉ።

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ሂደትን በተመለከተ የጸጥታ ዕቅድና ኦሬንቴሽን መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ኃላፊዎች፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የክልልና ከተማ መስተዳድሮች ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተወካዮች እና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት፤ የ12ኛ ክፍል ፈተና በአግባቡ እንዲሰጥ ትኩረት የተሰጠው የተሻለ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር መሆኑን ገልጸው፤ ፈተናውን ከስርቆት በጸዳ መልኩ እንዲሰጥ በማድረግ ውጤታማና ተወዳዳሪ ትውልድ መፍጠር ይገባል ብለዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ችግሮችን በማረም ፈተናውን በተሻለ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህም የጸጥታ አካላት ሚና ትልቅ መሆኑን ጠቁመው፤ 12ኛ ክፍል ፈተና ከነበረበት ችግሮች ተላቆ በተሻለ መልኩ እንዲሰጥ የጸጥታ ተቋማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

ዘንድሮ ፈተናው ለ150 ሺህ ተማሪዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ ፈተና አሰጣጡ ወደ ዲጂታል እንዲሸጋገር እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው፤ ፖሊስ የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም እንዲካሄድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሥነምግባር የታነጸ ትውልድ ለሀገር ሰላም ግንባታ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸው፤ በፈተና አሰጣጥ ሂደቱ የጸጥታ ተቋሟት መሳተፍ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አለው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በትግራይ ክልል የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምንም አይነት የክፍያ ጭማሪ እንዳያደርጉ ተከለከሉ

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች በቀጣይ አመት 2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ክፍያ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ጭማሪ እንዳያደርጉ መከልሉን አስታወቀ።

ትምህርት ቢሮ የጻፈው ደብዳቤ እንደሚያሳየት በክልሉ የሚገኙ በቀን፣ በማታም ሆነ በርቀት የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች ክፍያቸውን ከተያዘው የ2017 ዓ.ም ክፍያ መብለጥ እንደሌለበት አሳስቧል።

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል 49 በመቶ የሚሆኑ ህጻናት በትምህርት ገበታ ላይ እንደማይገኙ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የማህበራዊ ጉዳይ እና መልሶ መቋቋም ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ሜጀር ጀነራል ዘውዱ ኪሮስ አስታውቀዋል። በክልሉ ከተካሄደው ጦርነት በፊት 95 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት በትምህርት ገበታ ላይ ይገኙ እንደነበር ተጠቁሟል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
እስከ ሰኔ 15 ብቻ በሶስቱም ቅርንጫፎቻችን ( መገናኛ፣ ሜክሲኮና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸዉ  ስልጠናዎች በ Advanced level እና 90% practical በሆነ ካሪኩለም እንዲሁም ዘመኑ ያፈራቸዉን ሙሉ የላብራቶሪና የስቱዲዮ እቃዎችን በማሟላት ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለዉጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕዉቅና ካለዉ ሰርተፊኬት ጋር!

እኛጋ ለመሰልጠን ኮምፕዩተር መግዛት አያስፈልግዎትም!

የብዙ አመት ልምድ እና ብቃት ባላቸዉ አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe photoshop
🎯 Fullstack Web app development 
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign & Local Languages

አድራሻ:-
1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303

2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 639 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304

 3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️0991926707

Join telegram https://www.tg-me.com/topinstitutes

tiktok https://Tiktok.com/@topinstitute

Facebook https://www.facebook.com/Topinstitutes
#ማትሪክ_ደርሷል!
አትጨነቁ!
ለዝግጅታችሁ አሪፍ መፍትሄ እኛ ጋር አለ!

#ESSLCE_With_Model_Exams: ከ2012 እስከ 2016 ዓ.ም የማትሪክ ፈተና ጥያቄዎች ከነመልሶቻቸውና ሙሉ ማብራርያ፣

#Concise_Summary_With_Model_Exams: ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ያሉትን ትምህርቶች አጫጭር ማስታወሻዎች፣

#Ethiopian_New_Curriculum_All_Subjects: በከፍተኛ ጥራት የተቀረጹ  ቪዲዮዎች፣ Virtual Labs  ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) የታገዙ ትምህርቶች፣ እና እየተዝናኑ የሚማሩበትን ጌሞችን ያካተተ።

#Short_Notes: ለእያንዳንዱ ትምህርት  ዋና ነጥቦችን አጠቃሎ የያዘ

ይፍጠኑ ይህ እድል እንዳያልጥዎ
www.selectacademy.edu.et በመመዝገብ ዝግጅቶን አሁኑኑ ይጀምሩ።
መልካም እድል ለመላው ተፈታኞች

ለበለጠ መረጃ
+251 926 913 404 | 9521

Join Our Telegram

@Select_Academy
🗣️ Learn Arabic & Refresh Your Mind

🌿 Join our Arabic Speaking Course at our Wellness-Inspired Skill Center!

What you get:
✔️ Speak with native Arabic tutors
✔️ Support in Amharic, English ,French, Tigrigna, German & Somali.
✔️ 2-month course (online or in-person)
✔️ Relaxing space with herbal teas & calm vibes
✔️ Certification & 1-on-1 support available

🌱 Learn – Grow – Refresh
Start your language journey in a space that cares for your mind, body, and growth.

📞 Register now & transform your learning experience!

For more information and registration :
          ☎️
0989747878
0799331774

For more information and skills :
@merahyan
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄዷል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስተር በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ተማሪዎች ከፈተና ስርቆትና ኩረጃ በመውጣት አጥንቼ አውቄ ፈተናውን ማለፍ አለብኝ የሚል አስተሳሰብ ያለው ምክንያታዊ የሆነ ትውልድ መፍጠር አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከመከላከያ ሠራዊት እና ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር ለአራት ዓመታት የ12ኛ ከፍል መልቀቂያ ፈተና ስርዓት እንዲይዝ እና ተማሪዎች የለፉበትን ውጤት እንዲያገኙ በማድረግ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል።

ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ቀደም ባሉት ጊዜያት በስርቆትና በኩረጃ ይታወቅ የነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ስርዓት እንዲይዝ የለውጡ መንግስታችን በወሰደው ቁርጠኝነት የፖሊስ ለውጥ በማድረግ አሁን ላይ ተማሪዎች ስርዓት ይዘው በመፈተን ያጠኑትን፣ ያነበቡትንና የለፉበትን ውጤት እንዲያገኙ ከማስቻልም በላይ በዩኒቨርስቲዎች በተመሳሳይ ሰዎች ለፍተው ጥረው አንብበው የሚበቁበት ሀገር የሚገነባበት ሥርዓት እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡

በቀጣይም ትውልዱ በእውቀቱና በችሎታው መድረስ ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ትውልድን መቅረፅ ለሀገር እድገትና ለፀጥታ ሁኔታ መሻሻል ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዓመታት በተሻለ መልኩ የጸጥታ መዋቅሩ አስቀድሞ መዘጋጀት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡


በተጨማሪም ተማሪዎች ለፈተና ሲጓዙ እንደሀገር ስጋትና ዜጋ ጨራሽ የሆነው የትራፊክ አደጋም የፈተና ስርዓቱን ሊያስተጓጉል ስለሚችል የክልል የጸጥታ አካላት ፈተናውንም ሆነ ተፈታኝ ተማሪዎችን ይዘው የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ አድርገው እንዲያሽከረክሩ መደረግ አለበት ብለዋል።

ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በበኩላቸው ባለፉት አመታት ከነበሩ ችግሮች በመነሳት በርካታ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን የዩኒቨርሲቲ ጥበቃ ፖሊስ በማቋቋም የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ ማድረግ ተችሏል መባላቸውን ኢ.ፌ.ፖ.ሚ ዘግባል፡፡


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MoE

የመውጫ ፈተና የሰባተኛ እና የመጨረሻ ቀን መርሐግብር (ሰኔ 10/2017 ዓ.ም)

ፈተናው በ31 የትምህርት ፕሮግራምች በሁለት ክፍለ-ጊዜ ይሰጣል፦

ፈረቃ 1: ጠዋት ከ2:30-6:00 ሰዓት
ፈረቃ 2: ከሰዓት ከ9:00-12:00 ሰዓት


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
መስፈርት ማሟላት ባልቻሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ- ባለሥልጣኑ


መስፈርት አማልተው ባልተገኙ 85 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
የባለስልጣኑ ቁጥጥርና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ኢሮ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል እንደገለጹት፤ መስፈርት አማልተው ባልተገኙ 85 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡
ከ375 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል በተደረገው ክትትል በ85ቱ ላይ በተገኘ ጉድለት ከትምህርት ሥርዓቱ እንዲወጡ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
47 ተቋማት የተቀመጠውን አሠራር ጥሰው በመገኘታቸውም ከከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እስከ ሙሉ በሙሉ ከዘርፉ እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን ከ2 እስከ 4 ዓመት ድረስ ፍቃድ እንዳያገኙም መደረጉን አብራርተዋል፡፡
የተሰጣቸውን ቅጣት የማያከብሩ ተቋማት ደግሞ በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡
ከተሰጣቸው የተማሪ ቁጥር በላይ የሚያስተምሩ ኮሌጆች መኖራቸውን አንስተው ይህም በትምህርት ጥራት ላይ ከፍተኛ ጉድለት ማስከተሉን ተናግረዋል፡፡ 40 ተማሪ እንዲያስተምሩ ተፈቅዶላቸው 5ሺ ተማሪ ተቀብለው ከአቅማቸው በላይ የሆነ ተግባር የሚፈፅሙ መኖራቸውን አክለዋል፡፡
ህጋዊ ያልሆኑ የትምህርት ማስረጃዎች ወደ ተቋሙ እንደሚመጡ የተናገሩት ኃላፊው አሁን ላይ እነዚህ ችግሮች እንዳይፈጠሩ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በአግባቡ የተማረ ሰው የልፋቱን እንዳያጣ እና ተጭበርብረው የመጡ ሰነዶች ደግሞ አልፈው እንዳይገኙ በጥንቃቄ እነሠራለን ብለዋል፡፡
መሰል የማጭበርበር አካሄዶችን ለመግታት አንድ ነጥብ 3 ሚሊዮን የተማሪ ማስረጃዎች በዲጂታል ሥርዓት መመዝገቡን አስታውቀዋል፡፡ አሠራሩ የትምህርት ማስረጃዎችን በአግባቡ የማረጋገጥ ሂደት ላይ ለውጥ እንዲመጣ አስችሏል፡፡
በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ አጣርተን ጨርሰናል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ውጤቱን ለመንግስት የማቅረብ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ያልተሟላ እና ህጋዊ ባልሆነ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው በሥራ ላይ ያሉ መኖራቸውንም አክለዋል፡፡
ተቋሙ በማጣራት ሂደት ያገኘውን ውጤት የሚያሳውቅ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ውሳኔው ግን የመንግስት ይሆናል ነው ያሉት፡፡
በፌደራል ተቋማት ላይ ሥራው መጠናቀቁን ገልጸው በቀጣይም በመጀመሪያ ምዕራፍ በኦሮሚያ ክልል፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ሲዳማ ክልል ላይ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
ትምህርት እንደ ንግድ ተቆጥሮ ሲሰራ የነበረበት አካሄድ ከእንግዲህ እንደማይኖርም ነው ያስገነዘቡት፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ስትጠብቁት የነበረው የ12 ክፍል ማትሪክ ፈተና አጋዥ አፕሊኬሽናትችን አሁን playstore ላይ ይገኛል። ዳውንሎአድ አድርጎ መጠቀም ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ።
በነጻ
አዲሱን ስር አተ ትምህርት ያካተተ
አጫጭር ኖቶችና አጋዥ ቪድዮዎች የያዘ
አሁኑኑ ይሞክሩት!!!!!!!!!

  መተግበርያውን ለማግኘት👇                                                             
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.exam_time.exam

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት Telegram ቻናላችን ይቀላቀሉ
@thinkhub

#ethiopia #ethiopian #ትምህርት #grade12 #Ethiopians #entranceexam #examtime #time #education #matric #Ethiopians
2025/07/04 06:07:28
Back to Top
HTML Embed Code: