Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
12ኛ ክፍል ፈተና -መልስ መስጫው ላይ እንዴት እንደሚሞላና እንደሚቀባ የሚያብራራ ቪዲዮ✍️

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለተመደቡ ተማሪዎች ፈተናቸውን በውጤታማነት ለማከናወን እንዲችሉ ቅድመ ማስገንዘቢያ ተሰጥቷል።

የኢንስቲትዩቱ ፎካልፐርሰን አቶ ታምራት ፈቃደ እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ በዲጂታል መንገድ ፈተና የሚሰጥባቸው ኮምፒውተሮች፣ የኢንተርኔት እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ አስፈላጊ እገዛ የሚያደርጉ ሙያተኞች መኖራቸውን ገልጸዋል።

የጸጥታ አካላት ስርዓቱን ለማስጠበቅ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ፈተናው እንዲከናወን የጸጥታ አካላት በተጠንቀቅ እንደሚሰሩ ተገልጿል።

ተማሪዎች በቆይታቸው ማሟላት የሚገቧቸውን እና የሚያገኟቸውን አገልግሎቶች በተመለከተ በኦረንቴ

በኢንስቲትዩቱ ከ4 ትምህርት ቤቶች 813 ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ለማወቅ ተችሏል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ውድ ደንበኞቻችን ከዚህ በታቹ ካሉት website ላይ ማዘዝ የምትፈልጉትን ማንኛውንም እቃ photo  screenshots በinbox  ይላኩልን 

👨‍💻   Amazon.ae
👨‍💻    Shein.com
👨‍💻    Zara.com
👨‍💻   Noon.com
👨‍💻   Sephora.com

በ 7 ቀን ውስጥ ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ እናደርሳለን

📞0946362749( @eden16mg)

join our telegram channel 🫴🫴

https://www.tg-me.com/edmart24
💡Big ideas start small. Like Bill Gates, you can build the next big thing. Ready?

Apply here 👉 https://www.tg-me.com/Founderacademyapplicationguide
#ESSLCE #Schedule

ነገ የሚጀመረው የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዙር የፈተና መርሐግብር

በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይቆያል።

ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በ2017 ዓ.ም የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለሚወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ እና አጠቃላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ለተፈታኝ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት አዕምሮ ታደሰ(ዶ/ር) ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በሚቆዩባቸው የፈተና ቀናት በፈተና ቦታ፣በማደሪያ እና ከፈተና ውጭ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሰለማዊ በመሆን እና የግቢውን ህግ እና ደንብ በማክበር መፈተን እንደሚገባቸው ገልጸው በራስ አቅም እና ዕውቀት ከኩረጃ እራስን በማራቅ በተቀመጠው የፈተና ህግና ደንብ መሰረት በአግባቡ እንዲፈተኑ አሳስበዋል፡፡

ዶ/ር አዕምሮ አያይዘውም ተፈታኝ ተማሪዎች መፈተኛ ክፍል በሰዓቱ በመገኘት ፈተናውን እንዲወስዱ አሳስበው መልካም ውጤት እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡

ገለጻው በየመፈተኛ ክፍላቸው የተሠጠ ሲሆን ተፈታኞችም በፈተና ቦታ ማድረግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ዝርዝር ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
የትምህርት ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው አስጀመሩ።


የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ የሚኒስቴሩ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ከሾጌ የ2017 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተናን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው አስጀምረዋል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ጠንክሮ ያጠና ተማሪ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚችል በማንሳት ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ አበረታተዋል።

የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና በዛሬው እለት በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምሯል።

ዘንድሮ በወረቀትና በበየነ መረብ ከ608 ሺ በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሃምሌ 08/2017ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/07/05 17:14:15
Back to Top
HTML Embed Code: