Telegram Web Link
የትምህርት ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው አስጀመሩ።


የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ የሚኒስቴሩ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ከሾጌ የ2017 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተናን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው አስጀምረዋል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ጠንክሮ ያጠና ተማሪ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚችል በማንሳት ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ አበረታተዋል።

የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና በዛሬው እለት በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምሯል።

ዘንድሮ በወረቀትና በበየነ መረብ ከ608 ሺ በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሃምሌ 08/2017ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
የ12ኛ ክፍል ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ108 የማስፈተኛ ጣቢያዎች ሙሉ ለሙሉ በበይነ መረብ በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ፈተናው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቀደም ሲል ተማሪዎቹ የልምምድ ፈተና እንዲወስዱ መደረጉን እና በቂ ኦረንቴሽን መሰጠቱ እንዲሁም በየመፈተኛ ጣቢያው መሰረተ ልማቶቹን ዝግጁ የማድረግ ስራን ጨምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱ ይታወቃል።

በዛሬው የመጀመሪያ ዙር ፈተና ከ13ሺ በላይ ተማሪዎች በ108 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን በበይነ መረብ በመውሰድ ላይ የሚገኙ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር ዴታ ከወይዘሮ አየለች እሸቴ እና ከምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ዲናኦል ጫላ ጋር በመሆን ፈተናው ከሚሰጥባቸው ጣቢያዎች መካከል አንዱ በሆነው አብረሆት ተገኝተው የፈተናውን አጀማመር በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በበይነ መረብ መሰጠቱ ተማሪዎቹ ፈተናውን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲፈተኑ ከማስቻሉ ባሻገር ከኩረጃ ነጻ የሆነ የፈተና ስርአት እንዲሰፍን የሚያስችል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ጠቁመው ቢሮው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ፈተናው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን በመግለጽ ለተፈታኝ ተማሪዎች የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን የተመደቡ ተማሪዎች ፈተናቸውን የጀመሩ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር የፈተና አጀማመሩን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዚህም ለፈተና የሚያግዙ መሰረተ ልማቶቹ መሟላታቸውን ተፈታኞችም በፈተና ቦታቸው ላይ መገኘታቸው ተገልጿል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/07/04 01:19:43
Back to Top
HTML Embed Code: