Telegram Web Link
የግዕዝ ትምህርት ተቃውሞ ገጠመው

የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍ መምህር የሆኑት ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ የግእዝ ትምህርት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስጠቱ እርባና የለውም ሲሉ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገለፁ !

"ግእዝ የሞተ ቋንቋ ነው" የሚሉት መምህር በድሉ፣ ይህንን ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ መስጠቱ እርባና የለውም ብለዋል።

አንድ ቋንቋ የአፍ መፍቻ ተናጋሪ ከሌለው እና ከ25 ሺህ በታች ተናጋሪ ካለው ሞቷል እንደሚባል የሚናገሩት መምህሩ፣ ይህንን "የሞተ ቋንቋ" ከታች ከፍል ጀምሮ መስጠት የተማሪዎችን ጊዜ ማጥፋት እንደሆነ ገልጸዋል።

ቋንቋን የመማር ወሳኝ ዓላማ ለተግባቦት እና ሕይወትን ለመምራት እንደሆነ የሚናገሩት መምህር በድሉ ግእዝ ለተግባቦትም ሆነ ሕይወትን ለመምራት አሁን ላይ ጥቅም የለውም ብለዋል።

ሆኖም የግእዝ ቋንቋ ጭራሽኑ በትምህርት መልክ መሰጠት የለበትም የሚል አቋም የላቸውም።
የግእዝ ቋንቋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በጀርመን እና በፈረንሳይ ውስጥ ይሰጣል የሚሉት መምህር በድሉ፣ ቋንቋው የሚሰጠው በግእዝ ቋንቋ ምርምር ማድረግ ለሚፈልጉ ብቻ መሆኑን ይጠቅሳሉ።
በመሆኑም ትምህርቱ ይሰጥ ከተባለም መሰጠት ያለበት ከ9 ክፍል ጀምሮ ወይም ለአንትሮፖሎጂ፣ ለታሪክ እና ለቋንቋ ጥናት ፍላጎት ላላቸው የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እንዲሆን መምህሩ ይመክራሉ።

ዩኒቨርሲቲ ከገቡ በኋላ ለአንድ ዓመት የግእዝ ቋንቋ መማራቸውን የሚናገሩት መምህር በድሉ፣ ግእዝ አይጠቅምም የሚል አቋም ባይኖራቸውም፤ የተግባቦት እና የሕይወት ጥቅሙ ውስን የሆነን ቋንቋ ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ መስጠት "ለተማሪዎች የጊዜ ብክነት ነው የሚሆነው" ሲሉ ውሳኔውን ተችተዋል።
"ተማሪዎቹስ ዘጠኝ ዓመት ሙሉ ምንድን ነው የሚማሩት?" ሲሉም በሚኖረው ዝግጅት ላይም ጥያቄ አንስተዋል።

የግእዝ ቋንቋ ትምህርት በሙሉ ትግበራ ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ መሰጠት የተጀመረው ባለፈው ዓመት ቢሆንም በመምህራን እጥረት ምክንያት በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ማዳረስ ሳይቻል መቅረቱን ክልሉ ለቢቢሲ መግለጹ አይዘነጋም። #ቢቢሲአማርኛ

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#ወላይታሊቃ

ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ያስፈተናቸውን ሁሉንም ተማሪዎች በከፍተኛ ውጤት በማሳለፍ ውጤታማነቱን አስቀጥሏል፡፡

የትምርት ቤቱ የዓመቱ ከፍተኛ ውጤት 560/600 (93%) ላይ ሲሆን ይህም በትምህርት ቤቱ ታሪክ ከፍተኛው ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል::

እንኳን ደስ አላችሁ!

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#YihuneWolduMatasebiya

ይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ካስፈተናቸው 52 ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ ውጤት ማምጣታቸው ተገለፀ።

ከነዚህ ውስጥ 21ተማሪ ከ500በላይ ውጤት ያመጡ ሲሆን ቀሪዎቹ ከ408አስከ 499ድረስ ውጤት ያመጡ መሆኑን የትምህርት ቤቱ ምክትል ርእሰ መምህር አቶ ፍቅር በላይ ገልጸዋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#አርሲልዩትምህርትቤት

የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያስፈተናቸው ሁሉም ተማሪዎች (100%) ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ማለፋቸውን ገልጿል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቆ እየጠበቀ መሆኑን ገልጿል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በራሱ መመዘኛና መስፈርት ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩ ይታወቃል።

በመሆኑም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች ከመስከረም 05-09/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በዩኒቨርሲቲው ፖርታል (https://portal.aau.edu.et) አማካኝነት መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡

በቀጣይ ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀው የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፣ ሰዓት እና የፈተና ማዕከላት በተመለከተ በዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ መገናኛ ገፆች እና በተቋሙ ይፋዊ ድረገፅ እንደሚገለፅ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
" የሁለተኛው ዙር የፊዚክስ ፈተና ውጤት ችግር አለበት " - ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኖ ተማሪዎች ውጤታቸውን ሲያዩ ውለዋል።

ነገር ግን ከተፈጥሮ ሳይንስ የሁለተኛው ዙር የፊዚክስ ፈተና ጋር በተያያዘ ችግር እንዳለ ተማሪዎቹ እና ወላጆቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

" ከ60 የታረመው ውጤት ወደ 100 ስኬል ተቀይሮ አልተሰራም። እንዳለ ነው የተቀመጠው። በዚህም የሁለተኛ ዙር ተፈታኞች የፊዚክስ ትምህርት ፈተና ውጤት ዝቅተኛ ሆኖ ተመዝግቧል። የበርካታ ተማሪዎች ውጤት ወርዷል። የሚመለከተው አካል ይይልን፣ ይስተካከል " ሲሉ ጠይቀዋል።

ተማሪዎቹ ስላነሱት ጉዳይ የሚመለከታቸው የትምህርት ተቋማትን  የጠየቅን ሲሆን፤ ሁለት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሪዎቹ ጥያቄ በነሱ ተፈታኞች ላይ ያጋጠመ እንደሆም አመልክተዋል።

የፊዚክስ ፈተና ጉዳይን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጥያቄውን ያቀረበ ሲሆን ምላሽ ሲሰጥ እናቀርባለን።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
" መቶ ፐርሰንት ያደረግነው ዩኒቨርሲቲዎቹን ማመን ስላቃተን ነው ! " - የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሬሜዲያል ፕሮግራምን በተመለከተ ለምን 100% ፈተናው ከማዕከል እንደተደረገ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተውበታል።

ምን አሉ ?

" ሬሜዳያ የጀመርንበት ምክንያት ወድቀዋል እነዚህ ልጆች ወድቀውም ግን እስኪ አንድ ዓመት ቀጥቅጠን እናስተምራቸውና ችሎታውን ይዘው በሚቀጥለው ዓመት ፍሬሽ ማን ሆነው መግባት ከቻሉ ከሌላው ጋር ተወዳድረው መማር የሚችሉ ልጆች ይሆናሉ ብለን ነበር።

በዛ ምክንያት መጀመሪያ ላይ  እዛው ኮሌጅ ውስጥ ስለሚማሩ 30 ፐርሰንት ፈተናው ከዛው ከኮሌጁ ቢሰጥ የተቀረው 70 ፐርሰንት ግን በማዕከል ደረጃ ማትሪክ እንደሚሰጠው ይሰጥ ብለን ነበር።

እና ይሄ የድሮ አመል አለቅ ብሎ አንዱ ያመጣው ችግር ብዙዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች ከ30 ፤ 30 ነው ለሁሉም ተማሪዎች የሰጡት ፤ ማለት ፈተናው ትክክለኛ የብቃት መለኪያ መሆኑ ቀርቶ ዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪ እየቀነሰባቸው ስለሄደ ያንን መሙያ ነበር ያደረጉት።

ለጠየቁ ሰዎች የምትላቸው መቶ ፐርሰንት ያደረግነው ምክንያቱም ዩኒቨርሲቲዎቹን ማመን ስላቃተን ነው። ስለዚህ ከማዕከል ሁሉም እኩል የሆነ ፈተና ቢፈተን ይሻላል።

የምንፈልገው ጥራት ያለው ተማሪ እንዲገባ ነው እዛ ቦታ ላይ፤ የቀየርነው በሱ ምክንያት ነው።

ሁለተኛ ስንጀምርም ያልነው ሪሜዲያል ሁሌም የምናደርገው አይደለም እንደውም ለአንድ ጊዜ ብለን ነበር የጀመርነው። ውጤቱ በጣም አስደንጋጭና የወረደ ስለሆነ ነበር የቀጠልነው አሁን የምናደርገው እየጨመርነው ነው የምንሄደው። በሬሚዲያል የሚገባውን ተማሪ የመግቢያ [ውጤት] ቁጥሩን ከፍ እያደረግነው እንሄዳለን። በተወሰኑ ዓመታት ሬሜዲያል እንዲቆም ነው የምንፈልገው። ሬሚዲያል ቋሚ የሆነ የማስተካከያ መንገድ አይደለም ስለዚህ ኮምፒውተር ተበላሽቶብን ምናምን የሚለውን ተወውና . .  አልፈዋል ወደ 50, 60 በመቶ አልፏል። እያጠራ የምትሄደው እሱን ስታደርግ ነው።

ፈተናውን ጠንከርም ያደረግነው ፍሬሽማን ሲገቡ ከሌሎቹ ዘንድሮ አልፈው ከሚገቡት ጋር ተወዳዳሪ ሆነው መቀመጥ እንዲችሉ ነው። በኋላ እንዲወድቁ አንፈልግም። ገንዘብ ካጠፋንባቸው በኋላ ጊዜ ካጠፋንባቸው በኋላ ዩኒቨርስቲ ከገቡ እንዲያልፉ ውጤታማ ሆነው እንዲጨርሱ ነው የምንፈልገው። ለዛ የሚያስፈልገው ክህሎት እንዲኖራቸው።

ይሄ ከበፊት ጀምሮ ተዛብቶ የነበረው ነገር አላለቀም ገና የቀረ ቅሪት አለ እሱን እያስተካከልን ነው። "

#ቲክቫህ

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#Physics #Second_Round

ከደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለተማሪዎቹ የተሰጠ ማሳሰቢያ

ትምህርት ቤቱ "ሁላችሁም ተማሪዎች ጊዜ ገደቡ ሳያልፍ ቅሬታችሁን በተቀመጠዉ ሊንክ እንድታቀርቡ በማለት እናሳዉቃለን" በማለት አሳስቧል። ነገር ግን Compliant የምታስገቡበት ሊንክ እስካሁን ክፍት አልተደረገም። ከትምህርት ቤታችሁ ተማሪዎች ጋር በመተባበር ችግሩን የትምህርት ቤታችሁ አመራሮች ወደበላይ አካል እንዲያቀርቡ ግፊት አድርጉ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በደብረ ብረሃን ከተማ አስተዳደር በ2017 ዓ.ም ከተፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል የኃይለማርያም ማሞ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሚኪያስ ኪዳኔ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል።

ተማሪ ሚኪያስ ኪዳኔ ግዛው ከ600 መቶ 572 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት የከተማው ትምህርት መምሪያ አስተላልፏል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት!!

ለ2ኛ ጊዜ ያስፈተናቸዉን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ (100%) በማሳለፉ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን ይላል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
Complaint ማስገቢያ ሊንኩ ክፍት ስለተደረገ እየገባችሁ የተፈጠረውን ችግር አስገቡ።

እንደ ትምህርት ቤት የተሳሳተባችሁ ከጓደኞቻችሁ እና ከትምህርት ቤታችሁ ጋር በመሆን አቤቱታችሁን ማስገባት አይረሳ።

በዚህ አመት ጎልተው የታዩ የእርማት ስህተቶች ተስተካክለው ውጤታችሁ እንደገና ይሰራላችኋል።

👉Link http://result.eaes.et

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#AksumUniversity

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለመደበኛ ነባር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የነባር መደበኛ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 15 እና 16/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
ስትማሩ በነበረበት ግቢ በአካል በመገኘት

በ2017 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት በ2018 ዓ.ም ከሚመደቡ አዲስ ገቢ (ፍሬሽማን እና ሪሚዲያል) ተማሪዎች ጋር ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ተገልጿል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#AASTU #ASTU

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅት አጠናቀዋል።

ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ ባዘጋጁት የቅበላ ፈተና ተማሪዎችን አወዳድረው እንደሚቀበሉ ገልፀዋል፡፡

የመግቢያ ፈተናው ከሂሳብ፣ እንግሊዘኛ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ እና ባዮሎጂ የትምህርት ዓይነቶች በእኩል የተውጣጡ ጥያቄዎችን የያዘ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በኦንላይን የመመዝገቢያ አድራሻ፣ የምዝገባ ቀን፣ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፣ የመፈተኛ ጣቢያዎች እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች በቀጣይ ቀናት ይገለጻል ተብሏል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/10/28 04:02:14
Back to Top
HTML Embed Code: