Telegram Web Link
“ በተያዘው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የሪሜዲያል ተፈታኞችን እቀበላላሁ ” - ኢንስቲትዩቱ

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በ2018 ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ የሪሜዳል ተፈታኞችን እንደሚቀበልና አዲስ የተቀረጹ የስልጠና መርሃግብሮችንም ይፋ እንዳደረገ ገልጿል።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ እስከ 3 ዲግሪ ባሉት ደረጃዎች እንደሚያሰለጥን ያስታወቀው ተቋሙ፣ በዚሁ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የሪሚዳል ተፈታኞችን እንደሚቀበልም ጠቁሟል፡፡

በመደበኛው በቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በክረምት የስልጠና መርሃግብሮች ከደረጃ ስድስት እስከ 8 (ከመጀመሪያ እስከ 3ኛ ዲግሪ) የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አንደሚሰጥ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞችን የሚቀበልባቸው አራት መንገዶች ምን ምን ናቸው?

- ደረጃቸውን ለማሻሻል የቴክኒክና ሙያ አመራሮችና ሰልጣኞችን፣
- የኢንዱስትሪ ቴክኒሻኖችን በማታው፣ በቅዳሜና እሁድ ፕሮግራሞች፣
- የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ያመጡትን፣ እንዲሁም የሪሜዳል ተፈታኞችን (ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ) እንደሚቀበል ነው የገለጸው፡፡

ተደራሽነቱ ምን ይመለስላል?

ኢንስቲትዩቱ በአዲስ አበባ ከሚገኘው ዋና ካምፓሱ በተጨማሪ የሀዋሳ ካምፓስና የብየዳ ስልጠና ልህቀት ማዕከል ካምፓሶች፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚገኙ 16 የሳተላይት ተቋማት በደረጃ 6 ወይም በመጀመሪያ ዲግሪ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን አስረድቷል፡፡

አዲስ የተቀረጹት አጫጭር የስልጠና መርሃግብሮች ምንድን ናቸው?

በዘንደሮው አመት 11 አዳዲስ የስልጠና ፕርግራሞች ከመታከላቸው በተጨማሪ አዳዲስ የተቀረጹ የአጭር ጊዜ የስልጠና መርሃ ግብሮችም ይፋ ተደርገዋል፡፡ በዚህም፦
- በሲቪል ቴክኖሎጂ፣
- በኤሌክትሪክ እና አይሲቲ፣
- በመካኒካል ቴክኖሎጂ፣
- በቴክስታይል እና አፓረል፣
- በአግሪካልቸራል እና አግሮፕሮሰሲንግ፣
- በሉባን ወርኪንግ የሚሰጡ ሲሆኑ፣ በእነዚህ ስር ያሉ ዝርዝሮችና ሌሎች የስልጠና ዝርዝሮች ከላይ ተያይዘዋል፡፡ (ቲክቫህ)


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
🛑 ሊያመልጦት የማይገባ እድል..

📣 25% ብቻ በመክፈል በማንኛውም እድሜ: ፆታ: የትምህርት ደረጃ ያለ ሰው ሊወስዳቸው የሚችሉ ለውጥ ፈጣሪ ኮርሶችን እንደ Graphics design, video Editing, Digital Marketing, Upwork የምትወስዱበት የዘውድ ቴክ 9ተኛ ዙር ምዝገባ እንዳያመልጣችሁ።

የስራ እድል
ጥራት ያለው ስልጠና በ professional አስተማሪዎች
አንዴ ከፍለው 4 ስልጠናዎችን የሚወስዱበት
3 certificate ያለው

⚠️ ️ያሉት ቦታዎች ውስን ስለሆኑ አሁኑኑ ከታች ባለው የዘውድ ቴክ ቻናል ሊንክ ተቀላቅለው እዛ ላይ ባሉት ስልክ ቁጥሮች መልዕክት መላክ ወይንም መደወል ይችላሉ።

👇ቻናል ሊንክ

https://www.tg-me.com/zewdtech/43
ሰላም ሚኒስቴር ከአምስት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የሚሰጠው 14ኛው ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ስልጠና የመክፈቻ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ተካሒዷል።

ስልጠናቸውን ለመከታተል ጅማ፣ ሀዋሳ፣ ወሎ፣ ወልቂጤ እና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች የገቡ ሰልጣኝ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማሳተፍ በስነ-ምግባር፣ በክህሎት እና በሥራ ፈጠራ ግንዛቤ የሚያዳብር ስልጠና በመስጠትና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በማሰማራት የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#ሓሸንገ_ሃይቅ

🕯ዩኒቨርሲቲ ሊገባ የመግቢያ ቀኑን እየተጠባበቀ የነበረው ተማሪ ለሽርሽር በወጣበት ሓሸንገ ሃይቅ ላይ ህይወቱ አለፈ።

በኦፍላ ሓሸንገ ሃይቅ ምንድነው ያጋጠመው?

ተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን በትግራይ ደቡባዊ ዞን ኮረም ከተማ አሉ ከሚባሉ ብርቱ ተማሪዎች አንዱ ነው።

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈትኖ 430 ነጥብ በማምጣት ጅማ ዩኒቨርሲቲ ደርሶት ለመግባት ቅድመ ዝግጅቱ አጠናቆ በመጠባበቅ ላይ ነበር።

ጅማ ዩኒቨርስቲ የሚገባበት ቀነ ቀጠሮ መቅረቡን የተገነዘቡት ጓደኞቹ የመሸኛ ሽርሽር ዛሬ እሁድ ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በሓሸንገ ሃይቅ አዘጋጁለት።

ሆኖም ዝግጅቱ ተጨናገፈ ፤ ባለራዕዩ ተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን ሓሸንገ ሀይቅ ላይ ህይወቱ አለፈ።

የተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን አስከሬን ከብዙ ፍለጋ በኃላ ዛሬ ከቀኑ 11:30 ተገኝቷል።

የተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን የቀብር ስነ-ስርዓት ነገ ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም በኮረም ከተማ ይፈፀማል።

#ቲክቫህ

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በፀሐይ ኃይል የሚሰራው አውሮፕላን 40,000 ኪሎሜትር በረራ አደረገ

የፀሐይ ብርሃንን ብቻ በመጠቀም ነው
ስዊዘርላንድ ውስጥ የተሰራው "ሶላር ኢምፐልስ 2" ሙሉ በሙሉ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የዓለማችን ትልቁ አውሮፕላን ነው።

በስዊዘርላንድ መሐንዲሶች በበርትራንድ ፒካርድ እና በአንድሬ ቦርሽበርግ የተነደፈው ይህ አውሮፕላን አንድም ጠብታ ነዳጅ ሳይጠቀም 40,000 ኪሎሜትር በዓለም ዙሪያ በመብረር ታሪካዊ ተልዕኮውን አጠናቋል።

ከ17,000 በላይ የፀሐይ ሴሎች በአውሮፕላኑ ላይ ተያይዘው አራት የኤሌክትሪክ ሞተሮችን ኃይል ይሰጣሉ፣ ይህም ቀንና ሌሊት መብረር ያስችለዋል። ይህ ስኬት ታዳሽ ኃይል ለረጅም ጊዜ በአቪዬሽን ዘርፍ ሊሠራ እንደሚችል በተግባር ያሳያል።

ይህ ስኬት ደግሞ ትኩረትን ወደ አዲስ ምርምር—በፀሐይ ኃይል የሚሰሩ የማንቀሳቀሻ ዘዴዎች እና ኃይል ቆጣቢ ቁሳቁሶች እንዲያዞር አድርጓል።

ሶላር ኢምፐልስ 2 ለወደፊቱ ዘላቂ እና ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ ለሆነ የአቪዬሽን ዘርፍ መሠረት ጥሏል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MoE

የ2018 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም አመልካቾች የመግቢያ ፈተና (NGAT) በጥር ወር ይሰጣል። - ትምህርት ሚኒስቴር

29 ሺህ በላይ አመልካቾች ዛሬ የተሰጠውን የመጀመሪያ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) ወስደዋል።

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት፣ የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ እና የፖሊሲ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ፈተናው በ53 የፈተና ማዕከላት መሰጠቱን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ኢዶሳ ተርፋሳ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ለመቀጠል የተዘጋጁ 29,248 አመልካቾች የመግቢያ ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን፤ ሁለተኛው ዙር የNGAT መግቢያ ፈተና በጥር 2018 ዓ.ም ይሰጣል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#HaramayaUniversity
#የጥሪ ማስታወቂያ

ሀረማያ ዩኒቨርስቲ ለአዲስ ተማሪዎቹ ጥሪ አደረገ


በ2018 በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ የፍሬሽማን ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በሪሜዲያል (Remedial) ፕሮግራም በዩኒቨርሲቲያችን ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተሰጠው ፈተና አማካይ ውጤት 50% እና በላይ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ በ ጥቅምት 17 እና 18፣ 2018 ዓ.ም. ሀረማያ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በአካል ተገኝታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናስታውቃለን።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ
የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች፦ በዋናው ግቢ 
የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች፦ በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
➫ የስፖርት ትጥቅ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#ደሴ

“ ህይወቷ በማለፉ አዝነናል ነገር ግን ተማሪዋ የደሴ ካምፓስ ተማሪ አይደለችም ” - ወሎ ዩኒቨርሲቲ

➡️ “ የምርመራ ኬዝ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ” - ጉዳዩን የሚከታተሉት ኢንስፔተክር


ተማሪ ሊዛ ደሳለ የተባለች ወጣት ሰሞኑን በደሴ ከተማ “ የአስገድዶ መድፈርና ግድያ ጥቃት ተፈጽሞባት ” መገኘቷ ተሰምቷል፡፡

መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ወጣቷ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ/ም ስልኳን ለማሰራት በደሴ ከተማ ወደ ፒያሳ በወጣችበት አልተመለሰችም፡፡

ይህን ተከትሎ ፍለጋ ሲደረግ ግን “ተደፍራና ተገድላ ተገኝታለች” የተባለ ሲሆን፣ “ፍትህ ለተማሪ ሊዛ” የሚል ጥያቄዎች ኢንተርኔቱን አጨናንቀውታል።

ወጣቷ “ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ናት ” የሚሉ መረጃዎች መሰራጨታቸውን ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የጠየቃቸው አንድ የዩኒቨርሲቲው አካል ጉዳዩን አጣርተው በሰጡት ምላሽ፣ “ የተማሪዎች አገልግሎት ጋር ደውየ ነበር፤ 'እንዲህ አይነት ነገር እኛ አልተከሰተም፡፡ ተከሰተ የሚባለውም ከወይዘሮ ስህን ኮሌጅ ነው' ” እንዳሏቸው ገልጸዋል፡፡

እኝሁ የዩኒቨርሲቲው አካል፣ “የደሴ ካምፓስ ተማሪ አይደለችም፡፡ የወይዘሮ ስህን ኮሌጅ ተማሪ ናት፡፡ የኛ ተማሪ አለመሆኗን አሁን ከተማሪ አገልግሎት ደውዬ አጣርቻለሁ ” ሲሉም አክለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በማህበራዊ ሚዲያ ስሙ በሀሰት መነሳቱን ገልጾ ይህን ባደረጉት ላይ ተጠያቂነት እንደሚከተል ገልጿል።

በሊዛ ደሳለ ሞት ማዘኑንም ገልጾ ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የተማሪዋን ቤተሰቦች ለማግኘት ያደረገው ጥረት ባይሳከለትም፣ ከቆቦ ከተማ ነዋሪዎች ባደረገው ማጣራት ግን ተማሪ ሊዛ ደሳለ በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ ቆቦ ከተማ ታዲጊ መሆኗን ለማወቅ ችሏል፡፡

የወይዘሮ ስህን ኮሌጅ ኃላፊዎችን ፣ የደሴ ከተማ ፓሊስን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

የደሴ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ነስረዲን ኃይሌ፣ " መድረክ እየመራሁ ነው " በማለታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም። ኃላፊው ቆየተው በላኩት የፅሑፍ መልዕክት ዝርዝር መረጃ ይሰጧችኋል ሲሉ ኮማንደር ሰይድ የሚባሉ አካል ጠቁመዋል።

" ጉዳዩን ተከታትለውታል " የተባሉት ኮማንደር ሰይድ አሊ ምላሽ ብንጠይቃቸውም፣ “ እኔ አልሰጥም፤ ፖሊስ ነው መግለጫ የሚሰጠው፤ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊው ናቸው የሚሰጡት ” ብለዋል።

“ የምርመራ ኬዝ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ” ያሉት እኝሁ አካል፣ የምርመራውን ሂደት ሳይሆን የግድያውንና ሁነት እንዲያስረዱ ስንጠይቃቸው ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ቲክቫህ
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MoE

በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር የመግቢያ ፈተና ያለፈችሁ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ትምህርት ቤት በተመዘገባችሁበት ሊንክ በመግባት ማየት የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

የጤና እክል ያለባችሁና የሐኪም ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ቅሬታችሁን ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ማስገባት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሪፖርት የምታደርጉበት እና ትምህርት የምትጀምሩበት ቀን ወደፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦
0948863359 / 0900647104

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#MoE

" ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል " - ትምህርት ሚኒድቴር

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲሰጥ የነበረው የ2018 የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ፈተናው ለመውሰድ ከተመዘገቡ 29 ሺ491 አመልካቾች መካከል 96 በመቶ ፈተናውን እንደወሰዱ አመልክቷል።

በ2017 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ይሰጥ የነበረው የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. በ53 የፈተና ማዕከላት ነው የተሰጠው።

የፈተናው ውጤትም በቅርቡ ለተማሪዎች ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሌሎች አገር አቀፍ ፈተናዎች የተለየና የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን መቀጠል የሚፈልጉ አመልካቾች ለትምህርቱ ምን ያክል ዝግጁ ናቸው የሚለውን ለማረጋገጥ ደረጃውን ጠብቆ የሚሰጥ ምዘና ነው።

#DrEbaMijena

መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/10/22 19:47:44
Back to Top
HTML Embed Code: