እረኛው በጎችን ይዞ ወደ ማደሪያቸው አስገብቶ በሮችን ሁሉ በሚገባ ዘጋው።
የተራቡ ቀበሮዎች በጎቹን ሊበሉ ሲመጡ በሮች ሁሉ በሚገባ ተዘግተው አገኙት።
በሮችን አልፈው መግባትን ተስፋ የቆረጡት ቀበሮዎችም፤ በጎቹን ከበሮች
ቁጥጥር ውጭ ለማድረግ ሴራቸውን ይጠነስሱ ጀመር።
በመጨረሻም ቀበሮዎቹ (የበጎች ነፃነት ይከበር) የሚል መፍክር ይዘው የበጎቹን
ማደርያ ዙርያ ለመዞር ወሰኑ።
በጎችም ለነሱ ነፃነት እንዲከበር ቀበሮዎች ትልቅ አብዮት እንዳቋቋሙ ሲሰሙ
ልባቸው ወደ ቀበሮዎቹ ይሸፍት ጀመር።
የነፃነት አብዮቱን ለመቀላቀል በርካታ በጎችም የግቢያቸውን አጥር በቀንዶቻቸው
ይነቀንቁ ጀመር። ከረጅም ግዜ ረብሻ እና ትርምስ በኋላ በጎቹ ማደሪያቸውን
አፍርሰው አብዮቱን ለመቀላቀል ወደ ጫካዎች ፈረጠጡ።
ቀበሮዎችም ከበጎቹ ኋላ ይሮጡ ጀመር፤ እረኛውም ከኋላ ኋላ እየሮጠ አንዴ
በድምፁ አንዴ በብትሩ ሊመልሳቸው ቢሞክርም ሊሳካለት አልቻለም።
አብዮታዊ ሩጫው ቀጥሏል፤ በጎች ከፊት ቀበሮዎች ከኋላ....ብዙም ሳይርቁ
ቀበሮዎች እና በጎች ያለ እረኛ ያለ ከልካይ ሰፊ በረሃ ላይ ተፋጠጡ።
ያች ቀን የነፃነት አብዮትን ፍለጋ ለወጡት በጎች ጨለማ ስትሆንባቸው፤ ሴራን
ላሴሩት ቀበሮዎች ግን የደስታ እና የፈንጠዝያ ቀን ነበረች።
በማግስቱ እረኛው ተነስቶ ወደ አብዮት የወጡትን በጎች ፍለጋ ወደ በረሃው
ሲያቀና፤ የነፃነት መገለጫ የሆኑ ቀበሮዎች ነፃነትን ፍለጋ የወጡትን በጎች
ስጋዎቻቸውን በልተው፣ አጥንቶቻቸውን በመሰባበር ሜዳው ላይ በትነዋቸው
አገኘው።
_________________________________
ድሮ የሰማናት ተረት ናት አይደል!!!
ግን በአለማችን የሚገኙ የሴቶች የነፃነት አብዮትን እና ቀበሮዎችን ምን ያህል
እንደሚመሳሰሉ አስተውላችሁታል!!!?
የሴቶች ነፃነት አብዮት የሙስሊም ቁጥብ፣ ጨዋ እና እንቁ ሴቶችን በቀላሉ
ሊያገኝ አይችልም።
ምክንያቱም፦ አባቶቻቸው ኮትኩተው አሳድገዋቸዋል።
ምክንያቱም፦ቤታቸውን ጠበቅ አድርገው ይዘዋል።
ምክንያቱም፦ ሂጃብ አድርገዋል።
ለዝያም ነው የሰው ቀበሮዎች <የሴቶች ነፃነት> የሚል መፈክር ይዘው
ሚስተዋሉት። አላማው ግን <የሴቶች ነፃነት> ሳይሆን <ወደ ሴቶች መድረሻ
ነፃነት> ነው።

©Al kewser

ሼር👇👇👇

@theamazingquran
የኦቶማን ስረወ መንግስት የትዳር ህጎች
ፈገግ በሉ ሡና ነው

1፦ በራስ ፍቃድ ትዳር የመያዝ መብት ከ18-25 ነው። ከ25 እድሜ በላይ የሆነ ሰው አፍንጫው ተይዞ ትዳሩን ይይዛታል።

2፦ ከ25 እድሜ በላይ ሁኖት በበሽታ አመካኝቶ ትዳር ያልያዘ ጎረምሳ ካለ፤ የህክምና ምርመራ ይደረግለታል። በሽታው የመዳን ተስፋ ካለው እስኪድን እርዳታ ይደረግለታል፤ ካልዳነ ዐፉ ይባላል።

3፦ጎረምሳው 25 እድሜ ሞልቶት ትዳር አልይዝም ብሎ ቢገግም፤ ከቀን ገቢው 1/4 ለመንግስት ገቢ ያደርጋል። ይሄ ቅጣት ተሰብስቦ ትዳር ፈልገው ብር ለሌላቸው ወጣቶች ጀባ ይባላል።

4፦እድሜው 25 ሞልቶ ያልተዘወጀ ወጣት በፍፁም በመንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር አይፈቀድለትም። የሚሰራበት የመንግስት መስሪያ ቤት ካለም 25 ሞልቶት ካልተዘወጀ ይባረራል።

5፦ እድሜው 50 ሞልቶት ሁለት ሚስት የማግባት economically ም Physically ም አቅም እያለው 2 ሚስት ካላገባ፤ የተለያዩ የማህበረሰብ ችግር ፈቺ ድርጅቶች ላይ እንዲሳተፍ ይገደዳል። አልያም ከ1-3 የቲሞችን እንዲንከባከብ ይታደላል።

6፦ ከ 18-25 ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ሁኖ ምንም ሳይኖረው የሚዘወጅ ማንኛውም ወጣት ከሀገሪቱ የመሬት ባንክ 900 ካሬ ይሰጠዋል።

7፦ ወጣቱ የንግድ ወይም የሙያ ልምድ ካለው ሰርቶ እንዲለወጥ የብድር አገልግሎት ይመቻችለታል።

8፦ ጎረምሳው ለወላጆቹ የሚካድም ሌላ አካል በሌለበት ሁኔታ ትዳር ቢይዝ ለግዳጅ የመዝመት ድንጋጌው ውድቅ ይሆንለታል።

9፦ ጎረምሳው ከ18-25 ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ሁኖ 3 ልጆችን ቢወልድ በሽልማት መልኩ ልጆቹ አዳሪ ትምህርት ቤት በነፃ እንዲማሩ ይፈቀዳል።

10፦ ተማሪ ከሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ትምህርቱን በመከታተል ባለበት ሁኔታ ላይ ተገዶ ትዳር እንዲይዝ አይገደድም። (ምስኪን)

11፦ ሰውዬው በስራ ጉዳይ ከሀገር ለተወሰኑ አመታት ሊወጣ ካሰበ ሚስቱን ይዟት እንዲሄድ ይገደዳል፤ አልያም አሳማኝ ምክንያት ያቀርባል።

#የታደለ_ትውልድ_ነበር☺️ credit ሰፍዋን አህመዲን
Forwarded from UMMI/ኡሚ
ኡሚ የየቲሞች የልማት እና መረዳጃ ተቋም

"ለበጎነት መስፈርት የለውም " ብሎ በ2008 ህዳር 12 በጥቂት በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የተመሰረተችው ኡሚ ዛሬ ላይ ከ4000ሺ በላይ በጎ ፍቃደኛ ቤተሰቦችን ከዛም ውስጥ 750 የምክር ቤት አባላትን ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፣ በስሩም 150 የቲም ፣ 100 የተቸገሩ ምስኪን ፣ 30 አካል ጉዳተኛ እና 20 አረጋወረያን በአጠቃላይ 300 ተረጂ ቤተሰቦች እና 750 ልጆች በአጠቃላይ 1050 የተቸገሩ ቤተሰቦችን በቋሚነት አቅፎ እየደገፈ ይገኛል።

የሰራቸው ስራዎች በጥቂት
★9 ቤቶችን በማደስ ሙሉ ለሙሉ አፍርሶ በመገንባት ለእናቶች አስረክቦዋል
★ 95 እናቶችን ከጥገኝነት አላቆ የስራ ዕድል በመፍጠር ወደ ስራ አስገብቶዋል
★ልጆች ትምህርታቸው ላይ እንዲጠናከሩ አጋዥ መፅሀፍትን በመስጠት እንዲሁም በማስጠናት በተጨማሪም የፈጠራ ችሎታ ያላቸውን ልጆች እድሉን በማመቻቸት እያገዘ ይገኛል
★ከአሊፍ እናስታርቃቸው በሚል በወርሀዊ ክፍያ ምክንያት ከቁርዐን ገበታ የራቁትን ቤት በመከራየት እና የኡስታዝ ክፍያ በመከፍል 300 ልጆችን ቁርዐን አስጀምሮዋል
★ባሳለፍነው 6 ዐመታት ውስጥ ከ3500 በላይ ቤተሰቦችን የአስቤዛ ድጋፍ መስጠት ችለናል
★ኡዱሁያ(አረፋ) በዐል ምክንያት በማድረግ ለ900 እናቶች የስጋ ድጋፍ ለማድረግ ችለናል
★ለ2 ዙር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን በዚህም ከ1000 በላይ አባላት ተሳትፈዋል
★ በጥቁር አንበሳ ፣ ዘውዲቱ ፣ ራስ ደስታ እና ጦርሀይሎች ሆስፒታል ላይ ህሙማን መጠየቅ የተለያዩ ስጦታ እና የፅዳት አገልግሎት እንዲሁም ፋይል የማስተካከል ስራ ሰርተናል
★የእናቶች የየቲሞች የአረጋውያን የጤና ሁኔታ በመከታተል የህክምና እና የመዳኒት ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ ችለዋል
★ በተለያየ ጊዜ ከህብረተሰቡ ያሰባሰብናቸውን ከ5000 በላይ አልባሳት እና የቤት ቁሳቁስ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች ላሉ የቲሞችን፣ችግረኛ ቤተሰቦች እና በተለያዩ ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ለማድረድ ችለናል
★ከ1500 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጐዋል
★በአለም ላይ በተፈጠረው የኮቪድ ወረረሽኝ ምክንያት በችግር ለተጋለጡ 1026 ቤተሰቦች የአስቤዛ ድጋፍ አድርገናል

አሁን ላይ ተቋማችን ኡሚ ተደራሽነቱን ለማስፋት
ዋና መቀመጫውን በአዲስ አበባ ቤተል ላይ በማድረግ ቅርንጫፉን ደግሞ በአዲስ አበባ በአራቱም አቅጠሰጫ ያሰፋ ሲሆን ከአዲስ አበባ ወጪ በአዳማ ፣ በድሬዳዋ ፣ በሻሸመኔ ጅማሬውን አድርጎዋል።

ታዲያ እርሶስ ምን ይጠብቃሉ አባል በመሆን ለየቲም ለተቸገሩ ቤተሰቦች ድጋፍ እንሁናቸው
#በእውቀት
#በጉልበት
#በሃሳብ
#በገንዘብ ይደግፉን
ኑ አብረን ሆነን ወደ ከፍታ እንውጣ
"ለበጎነት መስፈርት የለውም"

ክልል ቅርንጫፍ
አዳማ
ድሬ ዳዋ
ሻሸመኔ
አዲስ አበባ
ቤተል
መገናኛ ሾላ
መዳህኒያለም ፊላንስ
ጀሞ(በመዋቀር ላይ ያለ)
https://www.tg-me.com/ummicharity
https://www.tg-me.com/ummi_charity
እዚህ ተቋም ላይ በገንዘብ በሀሳብ በጉልበት ማገዝ መርዳት እንፈልጋለን የምትሉ ቤተሰቦቻችን ካላችሁ @quraniccbot ላይ አስውቃችሁን መቀላቀል ተችላላችሁ።☺️


ኡሚ የየቲሞች ልማትና መረዳጃ ተቋም
"ለበጎነት መስፈርት የለውም"
ለምን በሙስሊሞች ላይ በረታን❗️
የማስተማር ጥበብን ዘነጋን
ከወቅታዊ ሁኔታችን ጋር የተያያዘ


የመጀመርያ አመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ሳለው በእንግድነት እየመጣ የሚያስተምረን መምህር ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የማካካሻ ትምህርት እየሰጠን ይገኛል የመግሪብ ሰላት ከመድረሱ በፊት ይጨርሳል ብለን ብንጠብቅም ማስተማሩን ቀጠለ የመግሪብ አዛን ሲያስተጋባም ብርሃን በጨለማ ቦታዋን እየተነጠቀች ነበርና ከዚህ በኋላ ብዙ አይቆይም በሚል እሳቤ የመግሪብ ሰላትን አስፈቅደን ወጥተን ለመስገድ እያመነታን ነው።በመሃል ግን አንዲት ሴት ልጅ እጇን አውጥታ ይቅርታ መምህር የሰላት ሰዐት እያለፍብን ስለሆነ 5 ደቂቃ ፍቀድልን ሰግደን እንመለስ ስትል ጠየቀች መምህሩ ደነገጠ ምላሽ ሳይሰጣት ለጥቂት ሰከንዶች አትኩሮ ተመለከታት።ተማሪውም ተገርሞ አትኩሮ እየተመለከታት ነው። ሙስሊም ነሽ? ሲል ጠየቀ መምህሩ በአግራሞት ይህ ጥያቄ የመምህሩ ብቻ ሳይሆን የእኛም ጭምር ነው።ልጅቷ ስሟ የሙስሊም ቢሆንም ገፅታዋ ግን የሙስሊም ሴት አይመስልም።ሂጃብ ለብሳ አታውቅም።ሙስሊምነቷ ያጠራጥር ነበር። ቆንጆ ስለሆነች ነው መሰለኝ መጥፎ አመለካከት ነበር ለሷ ያለን ዝምተኝነቷ እና ከማንም ተማሪ ጋር አለመቀላቀሏን እንደ አስመሳይነት ነበር የምንቆጥረው።አረ እንደውም ምናለ ስሟን በቀየረችው እያልን በተደጋጋሚ በመጥፎ እናነሳት ነበር።ሙስሊም ነሽ ሲል መምህሩ ጥያቄውን ደገመው ሙስሊም ባልሆን ለሰላት አስፈቅድህ ነበር ስትል መለሰችለት። ጥሩ መስገድ ምትፈልጉ ወጥታችሁ መስገድ ትችላላችሁ አለ። በክፍል ውስጥ ካለው።6ወንድ 5ሴት ሙስሊም ተማሪዎች መካከል 3ወንዶች እና ይህችው ለሰላት ያስፈቀደችው እንስት ብቻ ለመስገድ ወጣን ከመማርያው ህንፃ ጀርባ በሚገኝ ሳር ውስጥ ለመስገድ ገባን።ይህች ልጅም ከቦርሳዋ ውስጥ አባያና ሂጃብ አውጥታ ለበሰች።ትንሽዬ ተጣጣፊ መስገጃዋን አንጥፋ ከእኛ ኋላ ፈንጠር ብላ መስገድ ጀመረች ኢቃም ብለን መስገድ ብንጀምርም ሃሳቤ ግን ልጅቷ ጋር ነው። እንዴት ገፅታዋን ብቻ አይተን እንደዛ በመጥፎ ሳልናት!ለምንስ ቀርበን ልናናግራት አልሞከርንም።ከእኛ ተሽላ የሰላት ሰዓት አሳስቧት ማስፈቀዷ ለምን ግርምት ፈጠረብን እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎች በአእምሮዬ እየተመላለሱ ሰላቱን ሰግደን ጨርሰን ወደ ክላስ ተመለስን ክላስ ገብቼ ትምህርቱን ከመከታተል ይልቅ ሃሳቤ ልጅቷ ጋር ነበር ብዙ ሳይቆይ መምህሩ ትምህርቱን ጨርሶ አሰናበተን።ከኋላ ስለነበር የምቀመጠው ልጅቷ ቀድማኝ ስለወጣች እየሮጥኩ ተከተልኩና ስሟን ጠርቼ አስቆምኳት።እህት አለም በአላህ አውፍ በይኝ ስላንቺ በጣም መጥፎ ነገር አውርቻለው።ድንበር አልፌብሻለው አልኳት። መሬት መሬቱን እየተመለከተች በለመጣ ፈገግ አለችና አንተ ብቻ አይደለህም ይህን አይነት አመለካከት ያለህ ሙስሊሙ በሙሉ እንዳንተ ነው።አልያም ከአንተ በከፋ ነው የሚያስበኝ አለች።ጥቂት ዝም ካለች በኋላ ሳግ እየተናነቃት ይገርመሃል አያቶቼ ስለ እስልምናፕምንም አያቁም እኔም የተማርኩት የካቶሊክ ትምህርት ቤት ነው። የትምህርት ቤት ጓደኞቼ በሙሉ ሙስሊም ያልሆኑ ናቸው በእርግጥ አካባብያችን ሙስሊም ስለሚበዛ ሂጃብ ሲለብሱ እመለከት ስለነበር የሙስሊሞች የማንነት መገለጫ ነው ብዬ ሳስብ መልበስ ጀምሬ ነበር።ቤተሰቦቼ ግን አልፈቀዱም የእራሴ ክላስ ስላለኝ እዛ ገብቼ በመቆላለፍ ሰላቴን እሰግድ ነበር።ወደ ዩንቨርስቲ ስገባ የተወሰነ ነፃነቴን ስለማገኝ በተቻለ መልኩ ስለ እምነቴ ለማወቅ እና ለመተግበር ምኞቱ እና ፍላጎቱ ነበረኝ።ግና ዶርሜ ውስጥ የነበሩት ሙስሊም እህቶቼ ጥሩ አልተቀበሉኝም የጁምዓ ሰላት ወቅት ወደ መስጂድ ሳቀና ሰላቱ ምን ያደርግልሻል።ወይ ጥቅልል ብሎ መግባት ወይ መውጣት ሲሉ ተናገሩኝ የሚያቀርበኝ ጠፋ የሚያስተምረኝ ከጎኔ ሆኖ የሚያበረታታኝ አጣው።በተቃራኒው የሚሰድበኝና የሚተቸኝ ግን በርካታ ነው። ኢስላምን የማያውቅ ቤት ውስጥ እንደማደጌ በአንድ ጀንበር ውስጥ ለውጥ ማምጣት ለኔ ከባድ ነው።ይሁን ቢባል እራሱ ስለ ለውጥ ለኔ ቀርቦ የሚያስረዳኝ የለም
በጣም የሚገርመው ሰላታቸውን በትክክል የማይሰግዱ በየፓርቲ ቤቱ በሙዚቃ የሚጨፍሩና በየበግ ተራው ከወንድ ጋር ሲላፉ የሚያመሹ ሁሉ ሂጃብ በመልበሳቸው ብቻ ከእኔ የተሻሉ እንደሆኑ በማሰብ በንቀት አይን ይመለከቱኝ ነበር።ሂጃብ መልበስ በጣም ቀላል ነው።ሂጃብ የሚጠይቀውን ባህሪ መላበስ ግን ከባድ ነው።ሌሎች ከቤተሰባቸው ሲርቁ ሂጃባቸውን ማውለቅ ይፈልጋሉ እኔ ግን ከቤተሰቤ ስርቅ ሂጃቤን ስለመልበስ ነበር የማስበው ግና...አለችና በረጅሙ ተነፈሰች...

እቴዋ ሰልመሽ ያደርሽው ሙእሚኗ የተከበርሽው
ሰብአዊ ክብርሽን አጥተሽ ደም እንባ ያንቆረቆሽው
ስልጡን ዘመን ላይ ተፈጥረሽ እግር
ስር የተረገጥሽው
የኑሮሽ አሻራ በዛ ላይፋቅ ወይ ላይነሳ
ለፆታሽ መብት ተነፍጎ
ለጥቅምሽ ነጋ ደግድጎ
ለጎዳሽ ማረግ ፈልጎ
ላትሰለጥኚ ተጠልፈሽ በሰለጠነ ተልፈሽ
ሃፍረት ማረግሽን ተዘርፈሽ መብትሽ
መብትሽ ለቆጨሽ ተገድፈሽ

ለምታሰሚው ኡኡታ እርቃን አልሆንም ስሞታ
አታድሙኝ ላልሽው አታጥቁኝ በእውቀት አክብሩኝ አትናቁኝ

የሃዋ ዘር ነኝ እወቁኝ!!!


ከአይኖቿ የሚወርዱትን የእንባ ዘለላዎች ጠረገች እና ግና ብላ ንግግሯን መቀጠል ስትጀምር ዳግም እንባዋ ተናነቃት ይቅርታ አለችኝ እና በቆምኩበት ጥላኝ እየሮጠች ሄደች።


....ከአይኖቿ የሚወርዱትን የእንባ ዘለላዎች ጠረገች እና ግና ብላ ንግግሯን መቀጠል ስትጀምር ዳግም እንባዋ ተናነቃት ይቅርታ አለችኝ እና በቆምኩበት ጥላኝ እየሮጠች ሄደች።

ለደቂቃዎች በድንዛዜ ውስጥ ቆሜ ሳስብ ሳስብ እራሴን ነቅንቄ ወደ ዶርሜ መመለስ ጀመርኩ

"ሌሎች ከቤተሰባቸው ሲርቁ ሂጃብ ማውለቅ ይፈልጋሉ እኔ ግን ሂጃብን ለመልበስ ከቤተሰቤ መራቅን ነበር የማስበው ሂጃብ መልበስ ቀላል ነው።ሂጃብ የሚጠይቀውን ባህሪ ግን መላበስ ግን ከባድ ነው።"

እነዚህ ቃላቶችን ደጋግሜ እያሰብኩ ዶርም ደረስኩ ጓደኞቼ ምንም አላሉም ምን ሆንክ እያሉ ሲጮሁብኝ ነበር ከአይኖቼ እንባ እየፈሰሱ እንደነበር ያወቅኩት።ዛሬ ይሃንን ትዝታዬን የቀሰቀሰው ክስተት ደግሞ ይህ ነበር።የፌስቡክ ኖትፊኬሽኔን ስመለከት በርካታ የፌስቡክ ጓደኞቼ ኮሜንት የሰጡበትን ፖስት አገኘው ምን ይሆን ብዬ ወደፔጁ ጎራ አልኩ

#ሃሊማ #አብዱረህማን የምትባል ዘፋኝ ፔጅ ነው።ኮሜንቶቹን ማንበብ ጀመርኩ ሙስሊሞች የሰጡት ኮሜንት በአጠቃላይ እጅግ የሚያሳዝን ነው።
ለምን አንደኛውን አትከፍሪም?ለምን ስምሽን አትቀይሪም?ወደ እሳት ተጣሪ!የሰይጣን ተላላኪ!
መሰል እጅግ ከባባድ ኮሜንቶችና ሌሎች አስቀያሚ ስድቦች ሞልተውታል።

አስደነገጠኝ በተለይም ልጅቷ ለአንዳንድ ኮሜንቶች የሰጠችው ምላሽን ሳነብ የበለጠ ደነገጥኩ።አሁን ይቺ ልጅ ብትከፍር ተጠያቂው ማነው⁉️
የሚገርመው ደግሞ በኮሜንት ውስጥ አንድም ሊያስተምራት የሞከረ የለም።አረ እንደውም የአንዳንድ ተሳዳቢዎችን አካውንት ስመለከት የሂጃብ ትርጉም የሌለው ጨርቅ እራሳቸው ላይ ጣል አድርገው በሜክአፕ ሌላ ፊት ደርበው ጭብጨባ ፍለጋ በርካታ ፎቶዎችን ለጥፈዋል። እጅግ በጣም የሚገርመው የበርካታ ዘፋኞችና የዘፈን ፔጆችን ሳይቀር ላይክ አድርገዋል።👇👇👇
እስልምና ኢቅረዕ በሚል አንቀፅ የሚጀምር እምነት ነው። መጀመርያ መማር ከዚያ ልሎችን ማስተማርን የእምነቱ አስኳል ተጣሪዎች እንጂ ፈራጆች እንዳንሆን ያዙናል።ወደ ኢስላም በመልካም ግሳፄና በጥበብ በመጣራት ሌሎች ወደ ኢስላም እንዲቀርቡ ማድረግ የእያንዳንዳችን ሃላፊነት ሆኖ ሳለ እኛ ግን ሰዎች ላይ በመፍረድ በመስደብና በማሸማቀቅ እያራቅናቸው እንገኛለን ለመሆኑ ግን እኛ ከእነሱ እንደምንሻል በምን ይሆን ያረጋገጥነው!

የአላህ ቃልስ
"ነፍሶቻችሁን አታጥራሩ ከእናንተ ውስጥ አላህን ፈሪ ማን እንደሆነ እርሱ ብቻ ነው የሚያውቀው"
አይደል እንዴ የሚለው!

 یَا أَیُّهَا الَّذِینَ آمَنُوا لا یَسْخَرْ قَومٌ مِنْ قَوْمٍ عَسَى أَنْ یَکُونُوا خَیْرًا مِنْهُمْ وَلا نِسَاءٌ مِنْ نِسَاءٍ عَسَى أَنْ یَکُنَّ خَیْرًا مِنْهُنَّ وَلا تَلْمِزُوا أَنْفُسَکُمْ وَلا تَنَابَزُوا بِالألْقَابِ بِئْسَ الاسْمُ الْفُسُوقُ بَعْدَ الإیمَانِ وَمَنْ لَمْ یَتُبْ فَأُولَئِکَ هُمُ الظَّالِمُونَ﴿١١﴾


"49:11 - እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ሴቶችም ከሴቶች (አይሳለቁ)፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው፡፡"
ሱረቱል ሁጁራት አንቀፅ 11

ኢስላም እንዲኖረን የሚሸው ስብእና ባማረ ስነምግባር ላይ የተገነባ ነው።እራሳችንን አክብረን ሌሎችን እንድናከብር ያዘናል።የኢስላም አላማዎች
"መቃሲደል ሸሪዓ" ከሚባሉት ውስጥ አንዱ የሙስሊሙን ክብር መጠበቅ ነው።

የአላህ መልእክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም

ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱም ከእጁም ሰላም የሆኑለት ሰው ነው ብለዋል ።

ኢብኑ መስዑድ (ረድየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፉት ሌላ ሃዲስ ደግሞ
ሙስሊምን መስደብ ወንጀል ነው።መጋደሉ ደግሞ ክህደት ነው ይላሉ መምህራችን አሽረፈል ኸልቅ!

ሌሎችን በስነ ምግባራችን ጠርተን ወደ ኢስላም ማምጣት ሲጠበቅብን ያሉትን ስህተቶቻችንን እንዲያርሙ በጥበብ ከመንገር ይልቅ በስድብ እንገፋቸዋለን! ከመነሻው እነርሱ እንዲስተካከሉ ቢሆን ኖሮ ደግመን ደጋግመን ጥሪ ባረግንላቸው እና ባስታወስናቸው ነበር።

ግና እኛ ከሌሎች መሻላችንን ማንፀባረቅ ስለሆነ የምንሻው ከማስተማር ይልቅ ስድብና ነቆራን መርጠናል ይህ ሙስሊሞች ላይ ስህተት ስንመለከት ብቻ አይደለም።ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችንም ስለ ኢስላም አንድ ነገር ሲፅፉ አልያም ሲጠይቁ በስነ ስርዓት ከመመለስና ከማስረዳት ይልቅ ስድብን እንመርጣለን። በአንድ ድንበር ውስጥ አብረን የምንኖር የድንበር ወንድሞቻችን ላይ ድንበር በማለፍ እኛንም እስልምናንም እንዲጠሉና እንዲጠራጠሩ በር እንከፍታለን።በእርግጥ ይህ ነገር ከግንዛቤ እጥረት ተነስቶ ሊሆን ይችላል የሚደረገው ግና ፍፁም ስህተት ነው።ሌሎች ወደ ቀናው እንዲመጡ ምክንያት መሆን ባንችል እንኳ ከኢስላም እንዲርቁ ገፍታሪ መሆን የለብንም።ሰዎች ኢስላም ምን ይላል ሚለውን ሳይሆን ቀድመው የሚመለከቱት ሙስሊሞች ምን ይላሉ የሚለውን ነው።ንግግራችንም ሆነ ተግባራችን ኢስላምን የሚወክል በመሆኑ ከኢስላማዊ አስተምሮ የተቀዳ ይሁን አልያም ተናገሩ ብሎ የሚያስ ገድደን የለምና ዝም እንበል

"መድሃኒት ስለወሰድነው ሳይሆን ፈውስ የሚሰጠው በአግባቡ ስንጠቀመው ነው"

እስልምናም ምሉእነት ነው ብለን ስለፎከርን ሳይሆን ውብ ሆኖ የሚታየው በእኛ ህይወት ውስጥ ስጋና ደም ለብሶ ሲከሰት ብቻ ነው።እየናረ የሚገኘውን የስድብ ፍጆታችንን መቀነስ ካልቻልን ስለ ኢስላም የምንፈጥረው ገፅታ በጥላሸት የተሞላ ነው የሚሆነው!

ይህን ፅሁፍ ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር አድርጉት!!

በድምፅ የደረሰኝን መጣጥፍ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘውት በፅሁፍ ገልብጬ አቀርብኩላችሁ።

እኔም ሰዎችን የማስተማር ጥበብ የጎደለን ይመስለኛል!
በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጊዜ አንድ እእራቢይ(ዘላን ወይም የገጠር ሰው)
በሚሰግዱበት መስጂድ ውስጥ ወደ አንድ ጥግ ዞር አለና ሽንቱን መሽናት ጀመረ።ሰሃቦችም በጣም ተቆጥተው እና ገንፍለው አደነባበሩት የአለም እዝነት የሆኑት ነብያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ግን ሰሃቦችን አስቆሟቸውና ተውት ይጨርስ አሏቸው። ሸንቶ እንደጨረሰ ነብያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቀረብ ብለው የሚሰገድበት ቦታ ውስጥ እንዲህ እንደማይደረግ በጥበብ አስተማሩት ያ አእራቢይም እንዲህ ነበር ያለው!

"አላሁመ እርሃም አነ ወሙሃመዳ ወላ ተርሃም መዓና አሃዳ"

"አላህ ሆይ ለእኔና ለሙሃመድ እዘንልን ከእኛ ጋር ለአንድም አትዘን"

እዩት ያደረገው ዱዓን ምን ያክል በሰሃቦቹ ተከፍቶ እንደነበር ያሳየናል።ማስተማር፣ዳዕዋ ማድረግ እና የመሳሰሉት ኸይር ናቸው የምናስተምርበትን መንገድ አለማወቅ ግን አደጋ ነው!


አየህ የሃቢባችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ጥበብ ልቡን እንዴት እንደማረከው!

በኢስላማዊ ጥበብ ህይወታችንን እናሳምር!!

በቪድዮ ለማየት ለምትሹ
👇👇
https://www.facebook.com/belachhizboch/videos/1712446248921929/
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ

ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡

#ደስ_የሚል_ዳዕዋ_በትርጉም

https://www.tg-me.com/theamazingquran
የሳሊም ታሪክ አዲስ የሼኽ ኻሊድ ራሺድ ትርጉም ዳዕዋ//2021

ትርጉም>>በላጭ ሕዝቦች


https://youtu.be/WbJ_roA_E34
https://youtu.be/WbJ_roA_E34
ቃላቶች ተሰሳክተው ሊገልፁት የማይችሉት ሃሴት ሄዶ ሄዶ ዛሬ ላይ አረፈ።ዛሬ የምንጊዜም የህይወት ዓላማችን የሆነውን ቁርዓን ተፍሲር (መሰረታዊ ማብራሪያ) አጠር ባለ መልኩ ለ5 ተከታታይ ወራት ኢማም አል ቡኻሪ ኢስላሚክ አሶሴሽን በርቀት አስተምሮ አስመርቆናል።በዚህ ሂደት ላይ የተሳተፉትን ሁሉ አላህ ጀዛቸውን እጥፍ ድርብ አድርጎ በዱንያም በአኺራም ይመንዳቸው።ቀስ በቀስ እንቁላል በግሩ ይሄዳል ነውና እኛም ለትልቁ የቁርዓን ጉዟችን ይህ መንደርደርያ መሰረት ይሆነናል።ለ5 ወራት በሙሉ 10ፈተናዎችን ሙሉ 30ጁዝ ቁርዓንን ማለትም 114 ምዕራፎችን በፅሁፍ እየፃፍን ስናስገባ ነበር።
ከብዙ የህይወት ሃላፊነቶች እና ውጣ ውረዶች ጋር ይህንን እቅድ በርቀት ማስኬድ ከባድ ነበር።ፈተና ደርሶ ስንፈተን የነበረበት ጊዜ አሁንም አይኔ ላይ በምናብ ይታየኛል።ወላሂ ይናፍቃል!! የአላህ ቃልን እንደኛ ወይም ከኛ በበለጠ ቅርብ ሆኖ ላየው ሰው ወላሂ ጣፋጭነቱ ልብን ይሰረስራል።የላቀ ጌታችን አነገገሩ የስነ ፅሁፍ ጠበብቶችን በዝረራ ማርኮ ጥሏል።
ቁርአንን ለእኛ የሰው ልጆች መግለፁ ከባድ ነው።ስለዚህ አላህ እራሱ ሲገልፀው እንሐልከት።ልዕልናው የላቀው ሃያሉ ጌታችን አላህ ባወረደው ጥበብ በተሞላው መፅሃፉ እንዲህ ብሎ የለ!

وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ......
እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡.....42፥52


አላህ ቁርዓንን ሩህ (እስትንፋስ፣መንፈስ)ብሎ የጠራው ልቦች በርሱ ህያው ስለሚሆኑ ነው።
የሞቱ ልቦች ህይወት ይዘራሉ።


يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَتْكُم مَّوْعِظَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَاءٌ لِّمَا فِي الصُّدُورِ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ

እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡

ለዚህ እኔ አንዱ ምስክር ነኝ።ልቤን ዳግም የተወለድኩ ያህል ህያው ሲያረግ ይሰማኛል።ነገሮችን የምመለከትበን የእይታ አቅጣጫ ለውጦልኛል።


እኔ ሁሌም ማይረሳኝ የተፍሲር ኦድዮ እያዳመጥኩ የጀነት ወስፍን የሚያብራሩ አንቀጾች ሲመጡ ጥልቅ የሆነ ተመስጦ ውስጥ እገባ ነበር።ልክ ሌላ ዓለም ላይ እንዳለው ይሰማኛል።ኡስታዝ አቡ ያሲር(አብዱል መናን) ልቤን ሰለበው እንዴ ያስብላል።ሌላ ተጨማሪ ወራትን ምነው በድጋሜም ቢሆን ተምሬ ባሳልፍ የሚለው ሃሳብ እስካሁን ከአእምሮዬ ላይ ብቅ ካለ ጀምሮ ሊጠፋ አልቻለም።ብዙ ማለት ይቻላል ግን ቃላቶችን ነባብሬ ስሜቴን ልገልፅ ባለመቻሌ እዚህ ጋር ላቁም። ሁላችሁም ዛሬ በኢማም አል ቡኻሪ ተመራቂ ተማሪ የነበራችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ።አላህ በዚህ በተማርነው ለትልቅ እውቀት እንድንደረደር በር የሚከፍትልን ያርገው።አደራ የምለው ይህ የተፍሲር ትምህርትን ኢማም አል ቡኻሪ ገብታችሁ እንድትማሩ ነው።ወላሂ ከቁርዓን ጋር መተሳሰር እጅግ እጅግ እጅግ እጅግ.... ቃላቶች ከሚገልፁት በላይ ደስ ይላል።ነገሩ ከትግልና ከልፋት ጋር ሲሆን ደግሞ የመጨረሻው ውጤት ይበልጥ ውብ ይሆናል።

ይሄ ዋና ቻናላቸው ነው ገብታችሁ መረጃዎችን ታገኛላችሁ፦
https://www.tg-me.com/ethiobukhari2020
https://www.tg-me.com/ethiobukhari2020


ለመመዝገብ ዝግጁ የሆነ 🔑
هزاع البلوشي سورة الكهف
ሀዛዕ አልቡሉሽ 18(ሱረቱል ካህፍ)
هزاع البلوشي سورة الكهف
🎙ሀዛዕ አልቡሉሽ
ሱረቱል ካህፍ🌺
قــال رسول الله ﷺ

‏أكثروا من الصلاة عليّ ليلة الجمعة و ⁧

#يــوم_الجمعة ⁩ فإن صلاتكم معروضة

عليّ حديث صحيح .. ‏ﷺ 🌿
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
https://www.tg-me.com/Qidmeia_le_tewhid
https://www.tg-me.com/Qidmeia_le_tewhid
╔═══════════╗
የአሊሟ ሴት ገጠመኝ
╚═══════════╝

የሸይኽ ሰኢድ ኢብኑ ሙሰዪብን የዕውቀት ገበታን ያዘወትራል። በረሀውን አቆራርጦ በብርድ በቁሩ፣ በሙቀት በግለቱ አንገቱን ሰበር አድርጎ ጆሮውን ቀስሮ ከማዕዱ ይቋደሳል። አቡ ወዳአ ሲሉም ይጠሩታል።
የጀነቱ ጨፌ ከሚቀጠፍበት ሥፍራ ለሁለት ወራት ከራቀ በኋላ ወደ ዒልም ገበታው ዳግም ተመለሰ።
ሰላምታን ከኡስታዙ ጋር ተለዋወጠና የናፈቀውን ትምህርት መከታተል ጀመረ። ደርሱ እንዳበቃ በምን ምክንያት እንደቀረ ለምንስ ሳይናገር እንደጠፋሁ ሸይኹ ጠየቁ። ባለቤቴ ሞታብኝ ሀዘን ላይ መቆየቱን አብራርቶ አስረዳቸው።
ሰው ከበዛበት ቦታ ገለል አድርገው ወሰዱትና እንዲህ በማለት ጠየቁት፦
"አዲስ ሚስት ለማግባት አላሰብክምን?!"
"ለኔ አይነቱ የቲም ሆኖ ላደገ፣ ድሃ ሆኖ ለኖረ ልጁን የሚድር ማን አለ?! ወላሒ አሁን ከሁለት ዲርሃም ሀብትም ሆነ ንብረት የለኝም" በማለት መለሰላቸው።
"ልጄን እድርልሀለው" አሉት።
ታላለቅ ባለስልጣናት ልጃቸውን ጠይቀው አልድርም ማለታቸውን ያውቃልና ይህን ቃል ሲሰማ ምላሱ ተኮላተፈ። ተንተባተበ።
"የችግር ህይወቴን አውቀው ልጅዎን ሊድሩኝኝ?" በማለት በተደናገጠና በተቆራረጠ ድምፅ ጠየቀ።
"አዎ! ልጄን እድርልሃለው ኃይማኖቱና ሥነምግባሩ ያማረ ሰው ካገኘን ልጃችንን እንድንድር እስልምና ያዘናልና አንተ ደግሞ በሥነ ምግባርህ ትሁትን አደብ ያለህ መልካም ሰው ነህ" በማለት መለሱለት።
ለምስክርነት የሚሆኑ ሁለት ሰዎችን ጠሩና ያለችውን ሁለት ዲርሀም መህር አድርገው ኒካሁ ታሰረ።
ከድንጋጤና ከደስታው ብዛት የተነሳ የሚናገረውን ማወቅ ተሳነው። ከተቀመጠበት ብድግ አለ። ቀኑን ፆመኛ ስለነበር መስጂድ ገብቶ የመግሪብ ሰላት ሰገደና ወደ ቤቱ አቀና። ልጅቱን ሳያውቃትና ሳያያት መቀበሉ ገርሞት አንገቱን ነቀነቀ።
ትርክቱን ለባለታሪኩ እንተውለት
"ቤት እንደገባሁ ፋኖሴን አብርቼ የማፈጥርበትን ዘይትና ዳቦ አቀረብኩ። አንድ ሁለት እንደጎረስኩ የቤቴ በር ተንኳኳ። "ማነው?" በማለት ከበሩ ኋላ የቆመውን ሰው ማንነት ለማጣራት ጠየቅኩ። "ሰዒድ" የሚል ምላሽ ሰማሁ። በአላህ እምላለሁ!ሰዒድ በሚል መጠሪያ የማውቃቸውን ሰዎች ሁሉ ሳስብ ኡስታዜ ሰዒድ ኢብኑ ሙሰዪብ ይሆናል ብዬ ፈፅሞ አላሰብኩም። አርባ ዓመታትን ሙሉ ቤቱ ወይም መስጂድ እንጂ ሌላ ቦታ ታይቶ አይታወቅም። አወለሰፍ እንጂ የሰውን ጀርባ እያየ ሰግዶ አያውቅም። በሩን ከፈትኩ ከፊት ለፊቴ ኡስታዜ ቆሟል። ደነገጥኩ። "ልጁን ለኔ አይነቱ መናጢ ድሃ በመዳሩ ተፀፅቶ ሀሳቡን ሊቀይር ነው የመጣው ብዬ አሰብኩ "ያ አባ ሙሐመድ! እዚህ ድረስ በመምጣት ለምን ደከምከ ሰው ልከህ ብታስጠራኝ እመጣ ነበር" አልኩትና ወደ ቤት እንዲገባ ጋበዝኩት።
"ዛሬ መምጣት ያለብኝ እኔ ነኝ። የመጣሁትም ልጄ ሚስትህ ሆናለችና እሷ አባቷ ቤት ብቻዋን አንተም በቤትህ ያለ አጫዋች ስለሷ እያሰብክ ብቻህን መሆንህን ጠልቼ ይዣት መጥቻለሁ" አለና ከጎኑ ወፈቆመችው መልከ መልካም እንስት ዞሮ "ልጄ ሆይ! በአላህ ስምና ረድኤት ወደ ባልሽ ቤት ግቢ" በማለት የአባትነት ትዕዛዙን አስተላለፈ። ከሐያእዋ የተነሳ ወደኔ ስትራመድ ቀሚሷ አደናቅፏት ልትወድቅ ተቃረበች።
አባቷን አንኳ በስርአት ሳልሰናበት እየተጣደፍኩ ወደ ውስጥ ዘለቅኩ። ድህነቴ ስላሳፈረኝ የፋኖሱን ብርሃን አደብዝዤ ዳቦና ዘይቱን አልጋ ስር ደበቅኩት።
የቤቴ ጣራ ላይ ወጥቼ "ሰዒድ ኢብኑል ሙሰዪብ ልጁን ዳረኝ ቤቴ ድረስም ይዞልኝ መጣ" ብዬ ከፍ ባለ ድምፅ አዋጅ አልኩ። ከጎረቤቶቼ መካከል አንዲት አሮጊት በመስኮት በኩል አንገቷን ብቅ አርጋ እንዲህ አለችን፦
"አንተ ሰው! ለመሆኑ የምትናገረውን ታውቃለህ? ሰዒድ ልጁን ድሮህ ከቶውንም ቤትህ ድረስ ይዞልህ ሊመጣ? እሷ እንኳን ላንተ ለድሃው ለታላቁ መሪ ልጅ ወሊድ ቢን አብዱልመሊክ እምቢ ተብላለች ውበቷስ ቢሆን ላንተ ለደሃውማ አትገባም"
"ግቡ ቤቴ ናት ያለችው ተመልከቷት እውነተኛነቴን ታረጋግጣላችሁ" አልኳት።
ከአዲሷ ሚስቴ ጋር የጫጉላ ቆይታዬን ጨርሼ ወደ ቀድሞው የዕውቀት ገበታ ዒልምን ለመቋደስ ስነሳ "አንተ የዓይኔ ማረፊያ የቤቴ ሙሶሶ ባሌ ሆይ! አባቴ ጋር ያለው እውቀት ሁሉ እኔም ጋር አለና ቁጭ ብለህ ቅራ" በማለት በጆሮዬ ሹክ አለችኝ።
ቁርአንን በቃሎ የሸመደደች። የረሱልን ﷺ‎ ሐዲስ የሐፈዘች የጌታዋን ቃል አክባሪ፣ የተማረችውን ዕውቀት ተግባሪ፣ አላህን ፈሪ የባሏን ሀቅ ጠባቂ መልከ መልካምና እጅግ ቆንጆ እንስት ሆና አገኘኋት።

አሚን በሉ ልመርቃችሁ!
የእስልምና አኽላቅን የተላበሰች፣ ልጆቻችሁን በጀግንነት አሳድጋ ለቆራጥ አላማ የምታዘጋጅ እንስትን አላህ ይወፍቃችሁ።
ሴቶችዬ በኢማን የበለፀገ በተግባር የጎለበተ እንደ ሰላሐዲነል አዩቢ አባት ልጆቻችሁን የሚያንፅ ባል ይስጣችሁ
ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ
ረመዷን ሙባረክ

እርሶ ከቁርዓን ጋር ይተዋወቃሉ? የቂርዓቶ ደረጃንስ ማሻሻል ይፈልጋሉ?እነሆ የምስራች በመላው አለም ለምትገኙ ለቁርዐንና ለሀዲስ ትምህረት ፈላጊዎች በሙሉ አልበራሒን ኦንላይን ቁርአን የቦታ ርቀት ሳይገድባቹ ቁርዐንን ባላቹህበት ቦታ አስተካክሎ ለመቅራት ልዩ የኦንላይን ቁርዐን ፕሮግራም አዘጋጅቷል።በተጨማሪም ለርሶና ለልጆችዎ በመልካም ልዩ ትምህርት ( አኽላቅ፣አዝካር፣ ሲራ እና ሀዲስ) የትም መሄድ ሳይጠበቅባቸው በኦንላይን የዘመኑን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ትምህረት ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል። ፈጥነው ይመዝገቡ


እርሶ እኛ ጋር ሲቀሩ ከወጪ ቀሪ የሚገኘው ትርፍ ሙሉ ለሙሉ ኢስላማዊ ስራዎችን ብቻ በመስራት ላይ ላለው አልበራሒን ጀመዓ የሚውል መሆኑ በደስታ እንገልፃለን!ኒያ ካሎት የኸይር ስራ ተቋዳሽም ኖት

ስልክ ቁጥር +251912104750
በኢንቦክስ👇👇
@Fozmohmmed

ግሩፑን ይቀላቀሉ👇👇👇
https://www.tg-me.com/+5c5NKMc7F75hNDQ0
ተክቢር

አሏሁ አክበር!
የክርስትና መምህራን በጥላቻ ቀን ከሌሊት ኢሥልምናን ያጠለሻሉ፥ የእነርሱ የጥላቻ ዲስኩር እጅ እጅ ያላቸው እና ከጉያቸው የነበሩት የኦርቶዶክስ ምእመናት ወደ ዲኑል ኢሥላም እየመጡ ነው። 15 ልጆች ወደ ዲኑል ኢሥላም በሸሀደተይን ገብተዋል። የእኛ መምህራን የተውሒድን ብርሃን ለሙሥሊሙ እና ሙሥሊም ላልሆነው እያስተማሩ ይገኛሉ እንጂ አሉታዊ ነገር ላይ አይጠመዱም። አሏህ ይህንን ዲን ከፈለገ በከሃዲያንም ቢሆን ያጠናክረዋል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 212
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እነሆ ሙሥሊም የሆነች ነፍስ እንጂ ሌላው ጀነትን አይገባትም፥ አላህ ይህንን ዲን ከፈለገ በከሃዲያንም ቢሆን ያጠናክረዋል"። ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﻫُﺮَﻳْﺮَﺓَ، ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﻗَﺎﻝ ﻋﻦ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲّ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﺃﻧﻪ ﻗَﺎﻝَ ﺃَﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﻳَﺪْﺧُﻞُ ﺍﻟْﺠَﻨَّﺔَ ﺇِﻟَّﺎ ﻧَﻔْﺲٌ ﻣُﺴْﻠِﻤَﺔٌ، ﻭَﺃَﻥَّ ﺍﻟﻠﻪَ ﻳُﺆَﻳِّﺪُ ﻫَﺬَﺍ ﺍﻟﺪِّﻳﻦَ ﺑِﺎﻟﺮَّﺟُﻞِ ﺍﻟْﻔَﺎﺟِﺮِ‏

መጪው ዘመን የኢሥላም ነው።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

እርሶ ከቁርዓን ጋር ይተዋወቃሉ? የቂርዓቶ ደረጃንስ ማሻሻል ይፈልጋሉ?እነሆ የምስራች በመላው አለም ለምትገኙ ለቁርዐንና ለሀዲስ ትምህረት ፈላጊዎች በሙሉ አልበራሒን ኦንላይን ቁርአን የቦታ ርቀት ሳይገድባቹ ቁርዐንን ባላቹህበት ቦታ አስተካክሎ ለመቅራት ልዩ የኦንላይን ቁርዐን ፕሮግራም አዘጋጅቷል።በተጨማሪም ለርሶና ለልጆችዎ በመልካም ልዩ ትምህርት (ዓቂዳ፣አኽላቅ፣አዝካር፣ ሲራ እና ሀዲስ) የትም መሄድ ሳይጠበቅባቸው በኦንላይን የዘመኑን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ትምህረት ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።  ፈጥነው ይመዝገቡ


እርሶ እኛ ጋር ሲቀሩ ከወጪ ቀሪ የሚገኘው ትርፍ ሙሉ ለሙሉ ኢስላማዊ ስራዎችን ብቻ በመስራት ላይ ላለው አልበራሒን ጀመዓ የሚውል መሆኑ  በደስታ እንገልፃለን!ኒያ ካሎት የኸይር ስራ ተቋዳሽም  ኖት

ስልክ ቁጥር +251967936098
በኢንቦክስ👇👇
@Ba_Alewi

ግሩፑን ይቀላቀሉ👇👇👇
https://www.tg-me.com/+5c5NKMc7F75hNDQ0
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ


ልዩ የረመዷን መቀበያና የዳዕዋ መዝጊያ እንዲሁም የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግራም በሀሰንና ሁሰይን መስጂድ መሰናዳቱን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው።በእለቱም የተለያዩ ዝግጅቶች ከመኖራቸውም ጋር ከምንጊዜውም በተለየ ፍቅርና አንድነታችንን አጠናክረን የረመዷንን ወር ከኛ ጋር በጋራ እንድንቀበል እንጋብዞታለን።ረመዷን የ11 ወር ጉዟችንን የሚያደስ የደከሙ ነፍሶቻችንን ወደ ከፍታ የሚያወጣ ህይወት የቸረችን ልዩ መሰላል ነው። በወንጀል ባህር የቀዘፉ ነፍሶቻችን ከስጥመት የሚያድን የአላህ ችሮታ ነው።የረመዷን ምሽት አዲሷ ጠረቃ ከመወለዷ በፊት አስቀድመን እንድንቀበላት በሀሰንና ሁሰይን መስጂድ ሀሙስ ከመግሪብ በኋላ ፕሮግራም የኢስቲቅባለ ረመዷን ፕሮግራም አዘጋጅተን እንጠብቆታለን!


መጋቢት 7 የፊታችን ሀሙስ ከመግሪብ በኋላ
ተጋባዥ እንግዶች
ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪና
ኡስታዝ አብዱልቃድር(የሁዳ መስጂድ ኢማም)



መቅረትም ሆነ ማርፈድ ያስቆጫል!ለሴት እህቶቻችንም ቦታ ያዘጋጀን መሆኑን በደስታ እንገልፃለን!

አዘጋጅ አልበራሂን ኢስላማዊ ማህበር
2024/05/06 13:05:09
Back to Top
HTML Embed Code: