Telegram Web Link
#DVLOTTERY2022

የ2022 የፈረንጆቹ ዓመት የዲቪ-ሎተሪ ምዝገባ ትናንት መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሯል‼️

↘️ከአሜሪካ ውጪ የሚኖሩ የሌሎች ሀገራት ዜጎች፣ በዕጣ ቋሚ የአሜሪካ የነዋሪነት እና የዜግነት መብት የሚያገኙበት የዲቪ-ሎተሪ ትናንቱን እንደመጀማመሩ፣ ምዝገበው ከ-1 ወር ከ3 ቀናት በኋላ ማለትም፣ በህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም ያበቃል።

↘️በዚሁ መሰረት፣ ለዲቪ ሎተሪ የሚያመለክቱ ኢትዮጵያውያን ቢያንስ የ10ኛ ከፍል ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ መሆን እንዳለባቸው ተገልጧል።

↘️በግዛቷ የሚኖሩ የተለያዩ ሀገራት ስደተኞችን ብዛት እና ዜግነት ለማመጣጠን አስባ፣ አሜሪካ ከ1995 የፈረንጆቹ ዓመት አንስቶ ስራ ላይ ባዋለችው የዲቪ-ሎተሪ መርሀ-ግብር፣ በየዓመቱ 55 ሺህ የሚጠጉ ዕድለኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

↘️አሜሪካ የዲቪ-ሎተሪው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የምትፈቅደው፣ በግዛቷ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች የሚኖሩባቸውን ሀገራት ነው።

↘️ስለሆነም በዚህ ህግ መሰረት፤ የብራዚል፣ የካናዳ፣ የቻይና፣ የህንድ፣ የብሪታንያ፣ ደቡብ-ኮሪያ እና ናይጄሪያ ዜጎች፣ በዘንድሮው የዲቪ-ሎተሪ መሳተፍ እንደማይችሉ፣ ኬንታኪ የሚገኘው የዲቪ-ሎተሪ ተቆጣጣሪ ቢሮ አስታውቋል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
#ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከካቢኔ አባላቶቻቸው ጋር በመሆን የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና ደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ / ምክትል ፕሬዝዳንት ሆሴፕ ቦረል ፎንትለስና የልዑካን ቡድናቸው ጋር የሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ጠዋት ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

#ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ብርሀን ከፀሀይ የላይኛው ክፍል ወደ ምድር ለመድረስ 8 ደቂቃ ከ22 ሰኮንድ ይፈጅበታል። ብርሀኑ የተላከው ከፀሀይ የውስጠኛው ክፍል (core) ቢሆን ግን ብርሀኑ ምድር ላይ ለመድረስ 100,000 አመታትን የፈጅበታል።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊያን ዓመታዊ ገቢ ከ2 ሺህ ዶላር በላይ ለማድረስ እንደሚሰራ ብሔራዊ የፕላን ኮሚሽን አስታወቀ።

የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ የመጭዎቹን 10 ዓመታት አቅድ አስመለክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።

ዶክተር ፍጹም በዚህ ጊዜ እንዳሉት አሁን ላይ የአነድ ኢትዮጵያዊያን የነፍስ ወከፍ ገቢ 1 ሺህ 177 ዶላር ሲሆን ከ10 ዓመት በኋላ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ዜጋ ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢውን ወደ 2022 ዶላር ከፍ ለማድረግ አቅድ ተይዟል።

እቅዱን ለማሳካትም በስራ እድል ፈጠራ፣የንጹህ መጠጥ ውሃ፣የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እና የመንገድ መሰረተ ልማቶችን በሚገባ ማሳካት የሚያስችሉ ዝርዝር እቅዶች ተዘጋጅተው ወደ ስራ መገባቱንም ኮሚሽነሯ ተናግረዋል።

Via Ethio FM

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
🖍እንደምን አደራችሁ?

ውድ #የአክሱም ኢንተርቴይመንት ወዳጆችና ቤተሰቦች እንደምን አደራችሁ? ከዚህ ሰዓት አንስቶ የተለያዩ የአገር ውስጥና የውጪ ዘገባዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን። ሽፋን ሊሰጣቸው ይገባል የምትሏቸው የፖለቲካ፣ ማኅበራዊ፣ የምጣኔ ሀብት፣ የኪነ ጥበብ፣ ስፖርታዊ እና ሌሎችም ርዕሰ ጉዳየችን በዚህ👉 @axumentertainment1bot አካፍሉን።

ራሳችሁን እና ቤተሰባችሁን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግም አትዘንጉ።

መልካም አርብ!
መልካም ጁማአ!
ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
#የዓለም ባንክ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ከአንድ መቶ ሚሊየን በላይ ሰዎች ለከፋ ድህነት ሊጋለጡ እንደሚችሉ አስጠነቀቀ፡፡

ድርጅቱ ኮሮና ባስከተለው የዓለም ምጣኔ ሀብት ውድቀት የተነሳ ከ1 መቶ 15 ሚሊየን የሚበልጡት ሰዎች የከፋ ድህነት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ሲል ነው ያስጠነቀቀው፡፡
በአሜሪካ በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ተጠርጥሮ ለወራት በእስር ላይ የቆየው አሜሪካዊ የቀድሞ ፖሊስ አባል በዋስ ከእስር መለቀቁ ተሰምቷል፡፡

ዴሪክ ቻውቪን የተባለው ነጭ የቀድሞ የፖሊስ አባል የጥቁር አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድ አንገት በጉልበቱ ለስምንት ደቂቃዎች ያህል ወደ መሬት በመጫኑ ፍሎይድ መተንፈስ አቅቶት መሞቱ ይታወሳል፡፡
በዘንድሮው የኖቤል ሽልማት በስነ ጽሁፍ ዘርፍ አሜሪካዊቷ እንስት ገጣሚ ሉይዝ ግሉክ ተሸላሚ ሆነች፡፡

የኖቤል የሽልማት ኮሚቴ የአሜሪካዊቷ ገጣሚ ሉይዝ ግሉክ ዘመን አይሽሬ የግጥም ስራዎቿ የ2020 የስነ ጽሁፍ ዘርፍ ተሸላሚ መሆኗን አስታውቋል፡፡

@axumentertainment1
#የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአንድ ቀን ውስጥ ከአንድ ባንክ ወይም የገንዘብ ተቋም ማውጣት በሚቻለው የጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ማሻሻያ አደረገ።

ባንኩ በ27/1/2013ዓ.ም ለሁሉም ባንኮችና የፋይናንስ ተቋማት በላከው ደብዳቤ፣ ማንኛውም ግለሰብ በአንድ ቀን ውስጥ ከአንድ ባንክ ወይም የገንዘብ ተቋም ማውጣት የሚችለው ጥሬ ገንዘብ 50 ሺህ ብር እነደሆነ አስፍሯል፡፡

ሕጋዊ ሰውነት ባላቸው አካላት ወይም በተቋማት ደረጃ ደግሞ በአንድ ቀን በጥሬ ማውጣት የሚችሉት ገንዘብ 75 ሺህ ብር መሆኑን መመሪያው አስቀምጧል።
ባንኩ ባለፈው ግንቦት ባወጣው መመሪያ መሰረት አንድ ግለሰብ በአንድ ቀን ከአንድ ባንክ ወይም የፋይናንስ ተቋም የሚያወጣው ጥሬ ገንዘብ እስከ 200 ሺህ ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ተቋማት ደግሞ በአንድ ቀን እንዲያወጡ የሚፈቀደው ጥሬ ገንዘብ 300 ሺህ ብር ያህል እንደነበር የሚታወስ ነው።
በብራዚል አሁንም ድረስ ተባብሶ በቀጠለው የኮሮና ወረርሽኝ በቫይረሱ የተያዙ ዜጎች ቁጥር ከ5 ሚሊየን አልፏል

የብራዚል የጤና ሚኒስቴር በሀገሪቱ እየተስፋፋ በቀጠለው የኮቪድ 19 በሽታ ከተጠቂዎች በተጨማሪ በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ዜጎች ቁጥር ወደ 1 መቶ 50 ሺ እየተጠጋ ነው

@axumentertainment1
ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል !

(የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን)

በባህር ዳር አዲሱ ሀሠተኛ የብር ኖት ተያዘ።

በባህርዳር ከተማ አንድ ግለሰብ የ90 ሺህ ብር እህል ተገበያይተዋል።

ነጋዴው ግለሰብ በተሰጠው ብር ላይ ጥርጣሬ ስላደረበት ለባንክ ባለሙያዎች ሲያሳያቸው ሀሰተኛ የብር ኖት መሆኑ ተረጋግጧል።

ግለሰቡም ወዲያውኑ ለባህርዳር ከተማ ፖሊስ አዲሱን የሀሰተኛ ብር ኖት አስረክቧል።

ፖሊስ አሁን ላይ 90 ሺህ ብሩን ሰጥቶት በተሰወረው ግለሰብ ላይ ክትትል እያደረገ ይገኛል።

አሁን ላይ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች አዲሱ የሀሰተኛ የብር ኖት በፖሊስ እየተያዘ ይገኛል።

ስለሆነም ማንኛውም ግብይት በሚደርግበት ጊዜ ብሩ ብዙ ከሆነ የገንዘብ ልውውጡ በባንክ ቢሆን ይመረጣል።

የደህነት መጠበቂያ ምልክቶችንም በደንብ መመልከት ያስፈልጋል።
ለአትሌት ለተሰንበት ግደይ አቀባበል ተደረገላት !

ዛሬ አርብ መስከረም 29 ማለዳ 12፡00 ላይ የስፔን ቫሌንሺያ የ5,000 ሜ ሪከርድ ባለቤትዋት ጀግኒት አትሌት ለተሰንበት ግደይ ከዋና አሰልጣኟ ኃይሌ እያሱ ጋር በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ስትደርስ ፦

• ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀ/ም/ፕሬዝዳንት

• ኮማንደር አትሌት ማርቆስ ገነቲ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዝዳንትና አቶ ቢልልኝ መቆያ የፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በስፍራው ተገኝተው አቀባባል አድርገዋል፡፡
በቱርክ ካረኩም በረሀ የሚገኘው ያለማቋረጥ የሚነደው እሳት (የሲኦል በር)

ይህ የምታዩት እሳት የተፈጠረው የሩሲያ ባለሙያወች ነዳጅ ለማውጣት በሚቆፍሩበት ጊዜ የሚቴን ክምችት ያለበትን ቦታ በመንካታቸው ምክንያት በዚች የቅፅበት ስህተት ምክንያት ማሽኖቹንና እነሱን ሊውጣቸው ችሏል።ከዚች ገዜ በኋላ ይህ ቦታ በእሳት ተከቧል እሳተ ገሞራ አይደለም ደረቅ እሳት ነው እንጂ ነገር ግን እሳቱ አመትም ከአመትም በላይ ኖረ ሀይሉ እየጨመረ ሄደ እንጂ ሊጠፋ ግን አልቻለም ።ይህ ቦታ በቱርካውያን ቀርቶ በቱርክ መንግስት እንኳን የሲኦል መግቢያ በር ተብሎ ነው የሚጠራው ።ብዙ ሰወች ይህን ቦታ ለማዬት ስለሚመጡ የቱርክ መንግሥት ከቱሪስቶች ብዙ ዶላር ያገኛል ።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
/Russia/ Sarychev volcano ሲፈነዳ በ ISS(International space station) ካሜራዎች የተነሳ አስደናቂ ፎቶ...

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
🖍ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በእንጦጦ ፓርክ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

• ለፓርኩ ግንባታ ድጋፍ ያደረጋችሁ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ፡፡

• ፓርኩን በዓለም አቀፍ ስታንዳርድ ለሰሩ ባለሙያዎች ምስጋና አቀርባለሁ፡፡

• ይህ አገር ሊቀየር ይችላል፤ በተፈጥሮ የበለጸገች አገር ስለሆነች ከተባበርን
በየዓመቱ እንደዚህ ዓይነት ድንቅ ስፍራ መስራት እንችላለን፤ የሚያስፈልገው
ትብብር ነው፡፡

• አርት ወሳኝ ነው፤ የአርት ሙያ ያላቸው ግን ቦታ ያጡ ሰዎች አሉ እና በፓርኩ
የአርት ጋለሪን የሰሩ አካላትና በፓርኩ ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን የሰሩ አካላትን
አመሰግናለሁ፡፡


• መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለገበታ ለሸገር ያደረጋችሁትን አስተዋጽኦ ከዚህ በኋላም
በገበታ ለአገር እንዲትቀጥሉ እጠይቃለሁ፡፡

• ከእርዳታና ከልመና የምንወጣበትን ስራ መስራት አለብን፡፡

• ብዙ እንጦጦዎችን፣ ብዙ ሸገሮችን፣ ብዙ የሚያማምሩ ስራዎችን ለመስራት
እንተጋለን፡፡

©EBC

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
በበረሀ አንበጣ ዙርያ ከኢጋድ የወጣ መረጃ!

• ዘንድሮ በምስራቅ አፍሪካ በተከሰተው የበረሀ አንበጣ ሳቢያ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰብል ውድመት እየተከሰተ ይገኛል፣ ይህም ዘንድሮ ከነበረው ከፍተኛ የዝናብ መጠን ጋር ይገናኛል።

• በሰሜን ኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና ሰሜናዊ ሶማልያ የነበረው ከመጠን በላይ ዝናብ ችግሩን በዋነኝነት ፈጥሯል፣ ወደፊትም የበረሀ አንበጣው እንዲስፋፋ ጥሩ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። እስካሁን የቀጠለው ዝናብ የፈጠራቸው እፅዋት ለአንበጣው መራባት ምክንያት ሆነዋል።

• በመጪዎቹ ሳምንታት ለበለጠ መራባት ምቹ የሆኑ ሁኔታዎች በምስራቃዊ ዩጋንዳ፣ በደቡባዊ ደቡብ ሱዳን፣ በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በሰሜን-ምዕራብ ኬንያ ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል፣ በቀጣይ የንፋስ አቅጣጫ አንበጣውን ወደ ሰሜን አፍሪካ እንደሚወስድ ተገምቷል።

• ከነፍሳት ዝርያ የሚመደበው የበረሃ አንበጣ በተለያዩ የእድገት ደረጃዎች ውስጥ የሚያልፍ እና አረንጓዴ አዘርቶችን በሙሉ የሚመገብ አውዳሚ ፀረ ሰብል ነፍሳት ነው፡፡ የበረሃ አንበጣዎች ከ3 እስከ 6 ወራት ያህል የእድሜ ቆይታ ሲኖራቸው በየቀኑ ከሰውነት ክብደታቸው በላይ የሆነ ምግብ ይመገባሉ፡፡ አንድ የአንበጣ መንጋ በቀን የሚያወድመው የሰብል መጠን ቢያንስ 2,500 ሰዎችን ለአንድ ቀን መመገብ የሚችል ነው፡፡

#በተመሳሳይ_ዜና "ስለ አንበጣው ከሚነገረው በላይ እጅግ አሳዛኝ እየሆነ ነው፣ ገበሬው የሚበላው እህል ብቻ ሳይሆን የእንስሳት ቀለብ የሆነውን አገዳ ጭምር እየበላ ነው። ለሞራል ካልሆነ በተአምር በሰው ሀይል የሚቆም አይደለም፣ ከሰው ሀይል ቁጥጥር ውጪ ነው።"- አርአያ መንገሻ ከራያ ያደረሰን መረጃ/ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት


@axumentertainment1 @axumentertainment1
DV 2022 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን?

በጥያቂያቹ መሰረት ዲቪ 2022 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ ጥቅምት ሀሙስ 07/2020 ጀምሮ ህዳር 10/2020 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።

DV-2022 Program Instructions
›የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች;-



↘️እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት ማለትም በ ፕሮግራሙ መሰረትም-

➡️ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት በሚገባ ያጠናቀቀ /ያጠናቀቀች። ወይም
➡️ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።

↘️የ DV አሞላል ሂደቶች:-

➡️ጉርድ ፎቶ ግራፍ በመቀጠልም
www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት
›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል
በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ ፎርም መሙያዉ መግባት።

↘️ፎርም አሞላል‼️
1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣
First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ
ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።

2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።

3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year ( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.

4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ

5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር

6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር
ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ

7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት - የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል
➡️ በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ
፣JPEG Format መሆን አለበት።

8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት

9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ

10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን
በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል

11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት

12. What is the highest level of education you have achieved,
as of today?
የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ

13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር
ሁኔታ መምረጥ

14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።

↘️በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን
ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን
DV-2022 ሲወጣ ማየት እንችላለን።
DV-2022 Submission Confirmation : Entry success
በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ
#አክሱም ENTERTAINMENT ን የቴሌግራም ቻናል ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ማረግ አይርሱ

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
ዮዳሄ ኢንተርቴይመንት #yodahe entertainment pinned «DV 2022 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን? በጥያቂያቹ መሰረት ዲቪ 2022 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ ጥቅምት ሀሙስ 07/2020 ጀምሮ ህዳር 10/2020 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው። DV-2022 Program Instructions ›የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች;- ↘️እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት /…»
በሊባኖስ መዲና ቤይሩት የነዳጅ ማጠራቀሚያ ፈንድቶ ቢያንስ አራት ሰዎች ሲሞቱ 20 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት ደረሰ።

ፍንዳታው የተከሰተው ታሪቅ አል ጂዲ በተባለ ጎዳና በርካታ ሰዎች በሚኖሩበት ሰፈር ነው።

በቴሌቪዥን የተሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ነበልባሉ በጠባብ ጎዳና ላይ በሚገኙ ቤቶች ጫፍ ላይ ደርሶ አሳይተዋል።

እስካሁን ድረስ እሳቱ እንዴት እንደተነሳ ያልታወቀ ሲሆን በአካባቢው የተሰማሩት የአደጋ መከላከል ሠራተኞች አሁንም ሰዎችን ከአደጋው የማዳን ሥራቸውን እንደቀጠሉ ናቸው።

ትላንትና ፍንዳታው ሲከሰት፤ እሳት አደጋ ተከላካዮች በመሰላል መኖሪያ ቤቶች ላይ ወጥተው በረዳቸው ላይ የነበሩ ሰዎችን ሕይወት ለመታደግ ሲጣጣሩ ነበር።

አንዲት ሴት "የፍንዳታው ድምጽ ሲሰማና ቤታችን ሲንቀጠቀጥ ደነገጥን። የምንኖርበት ሰፈር ያሉ ሰዎች ባጠቃላይ መጮህ ጀመሩ። ክስተቱ ወደኋላ መለሰኝ" ብላ ትዊት አድርጋለች።

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰
@axumentertainment1bot @axumentertainment1bot

#Join_As
👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1

👉 @axumentertainment1
2025/07/08 22:59:40
Back to Top
HTML Embed Code: