Telegram Web Link
مسألة العذر بالجهل للشيخ أبي ذر .pdf
6.3 MB
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

መሰአለቱል ዑዝሪ ቢልጀህል

ዑዝር ቢል ጀህል ማለትአንድ ሰው እስልምና ውስጥ ሆኖ በጅህልና ( ባለማወቅ ) እስልምናን የሚፃረሩ ነገሮችን በሚሰራ ጊዜ ከእስልምና ወጣ ወይስ አልወጣም በሚለው ጉዳይ ዑለሞች የሚሰጡት ብይን ማለት ነው ። በዚህ ላይ የሰለፍ ዑለሞች ሁለት አይነት አቋም አላቸው ። ከፊሎች አንድ ሰው መሰረታዊ የተውሒድ ጉዳዮችን የሚያፈርስ ነገር ከሰራ ይከፍራል ምናልባት አዲስ ወደ እስልምና የገባ ወይም ከእስልምና አስተምሮ የራቀ አካባቢ ላይ ያለ ካልሆነ ይላሉ ። ሌሎች ደግሞ አንድ ሰው መሰረታዊ የተውሒድ ጉዳዮችን የሚያፈርስ ነገር ከሰራ ከእስልምና ወጥቷል ለማለት መስፈርቶች መሟላት ከልካይ ነገሮች መወገድና ሁጃ መቆም ( በሚገባው ቋንቋ መረጃው መድረስ ) አለበት ይላሉ ።
ይህ ኪታብ ሸይኻችን ሸይኽ አቡ ዘር የፃፈው ሲሆን መስፈርቶች ሳይሟሉ አይከፍርም ወይም አንድን ግለሰብን ማክፈር አይበቃል የሚለውን በመረጃ ያረጋገጠበት ሲሆን በሰለፍ ዑለሞች ንግግር አጭቆታል ። በመሆኑም ዳዒም ይሁን ኡስታዝ ወይም ዐሊም በዚህ ኪታብ በጣም ጠቃሚ እውቀት ያገኛል ።

ማስታወሻ
– መረጃ ማድረስ ወይም ተበዩን እስኪሆንለት ማለት መረጃውን በሚገባው ቋንቋ መንገር ማለት ነው ።
– መረጃውን መረዳት አለበት ሲባል መሰረታዊ ግንዛቤ እስኪፈጠርለት ማለት እንጂ እንደ ኹለፋኦች አይነት ፈህም ላይ ይድረስ ማለት አይደለም ።
– አንድ ሰው መረጃ ደረሰው ለማለት ልቡ ውስጥ ያለው ሹቡሃ መወገዱ ( ዘዋሉ አሽሹብሃ ) ወይም መረጃው ገብቶኛል ማለቱ መስፈርት አይደለም ።
ተክፊሮች አንድ ሰው የኩፍር ወይም የሽርክ ተግባር ላይ ከወደቀ ይከፍራል ይላሉ ። በዚህም ከአህሉ ሱና ይለያሉ ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
🔷 የደስተኝነት ምልክት

‏قال ابن القيم– رحمه الله – :

" علامة السعادة أن تكون حسنات العبد خلف ظهره، وسيئاته نصب عينيه، وعلامة الشقاوة أن يجعل حسناته نصب عينيه، وسيئاته خلف ظهره "

           مفتاح دار السعادة    (1/298)

     🟢  ኢብኑል ቀይም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላ : –

" የደስተኝነት ምልክት የአንድ ሰው መልካም ስራው ከጀርባው ሆኖ መጥፎ ስራው ከፊት ለፊቱ መሆኑ ነው ። የጥመቱ ምልክት ደግሞ መልካም ስራው ከፊት ለፊቱ አድርጎ ሀጢያቱን ከጀርባው ማድረጉ ነው "።

http://www.tg-me.com/bahruteka
  ለስኳር በሽታ መዳን ሰበቦች

    የስኳር በሽታ እንደማንኛውም በሽታ መዳን የሚችል በሽታ ነው ።
" አላህ በሽታን አልፈጠረም መድሃኒት ቢፈጥርለት እንጂ ያወቀው ያውቀዋል ያላወቀው አላወቀውም ከሞት በስተቀር "። ይላሉ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ስለሆነም የትኛውም በሽታ መድሃኒት አለው ።
     መድሃኒቶች ሁለት አይነት ናቸው ። የምግብ መድሀኒትና የክኒን ወይም መርፌ መድሃኒት ። በተለምዶ መድሃኒት ሲባል አእምሮራችን ወደ ሐከም የሚያዘው የክኒን አይነት ይሄዳል ። እንደ ሚታወቀው የዚህ አይነቱ መድሃኒት ምግብ አይሆንም ። ምግብ ግን መድሂኒት ሊሆን ይችላል ።
    ስለዚህ የምግብ አይነቶችን ለመድሀኒትነት መጠቀም ጥቅሙ ብዙ ነው ። በአግባቡ ከተወሰደ ተጓዳኝ ችግር ያስከትላል ተብሎ አይፈራም ። ከእነዚህ የምግብ መድሃኒት አይነቶች ለስኳር በሽታ መዳን ሰበብ የሚሆኑትን በአላህ ፈቃድ ለማየት እንሞክራለን ። 
     ለየአንዳንዱ ሰው በደሙ አይነትና በክብደቱ ልክ የሚታዘዝለት የምግብና የአመጋገብ ሁኔታ ያለ ቢሆንም ለሁሉም ሊሆኑ ከሚችሉት የተወሰኑትን ለመጥቀስ እሞክራለሁ ። አንዳንዶቹ በቁርኣንና ሐዲስ የተነገሩ ሲሆኑ አብዛኞቹ በዚህ ላይ ምርምር ያደረጉ ባለሞያዎች የሚመክሯቸው ናቸው ። ከእነዚህ ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል : –
– ማር = በቀን አንድ የሾርባ ማንኪያ ያክል መውሰድ ።
– ጥቁር አዝሙድ = አንድ የሻይ ማንኪያ ጥሬውን ለብቻው ወይም ዱቄቱን በቡና ካልሆ በሻይ በቀን አንድ ጊዜ መውሰድ ።
– አሳ  = በተቻለ መጠን እንደዋና ምግብ መመገብ ።
– ቀረፋ = በምግብ ውስጥ እንደ ቅመም ጨምሮ መጠቀም ።
– እንቁላል = ከተቻለ በቀን ሁለት የተቀቀለ እንቁላል መጠቀም ።
– እርጎ = በቀን አንድ ጊዜ አንድ ብርጭቆ እርጎ መውሰድ ።
– የአበባ ጎመን = ከተለያዩ የአትክልትና የጎመን አይነቶች ጋር መመገብ ።
– እንጆሪ = የተለያዩ የፍራፍሬ አይነቶች የሚመከሩ ሲሆን በዋነኝነት እንጆሪ ተጠቃሽ ነው ። ሳይበዛ በቀን አንድ ጊዜ መመገብ ።
– ነጭ ሽንኩርት = በጣም ጥሩ ነው ይባላል በምግብ ላይ ጨምሮ መመገብ ።
      እነዚህ ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው ሰበብ እንዲሆኑ በተቻለ መጠን አዘውትሮ መመገብ ያስፈልጋል እንደ ክኒን ለሳምንት ወይም ለወር አይደለም ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
📢 ሰበር ዜና 📢

🕰ዛሬ እለተ እሁድ ሰኔ 22/2017
ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ልዩ ሙሃዶራ አለ እንዳያመልጣችሁ!


👉 ልዩ ቆይታ
🎙ከሸይኻችን ሸይኽ አቡ ዘር (ሀፊዘሁላህ) ጋር

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
አዲስ አበባ አለምባንክ

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/DarASSunnah1444
https://www.tg-me.com/DarASSunnah1444
🔹እውነተኛው ጥመት

[وَعَنْ أَبِي مسعودٍ الأنصاريِّ أنَّه قَالَ لـحذيفةَ: أوْصِنِي! قَالَ: إنَّ الضَّلاَلَةَ حَقَّ الضَّلاَلَةِ أَنْ تَعْرِفَ مَا كُنْتَ تُنْكِرُ، وَتُنْكِرَ مَا كُنتَ تَعْرِفُ، وإيَّاكَ والتَّلَونَ في دِينِ اللهِ؛ فَإنَّ دِينَ اللهِ وَاحِدٌ].

አቡ መስኡድ አልአንሷሪ ሁዘይፋን "ምከረኝ" አለው።  የሚከተለውን ምላሽ ሰጠው:-

"እርግጠኛው እና እውነተኛው ጥመት : (ትናንት) ስታወግዘው የነበረውን (ዛሬ) እንደ መልካም  ማየትህ ፤ መልካም የምትለውን እንደመጥፎ ማየትህ ነው"  ፣ አስጠነቅቅሀለሁ ፣ በአላህ ዲን  ላይ (እንደእስስት) መቀያየርንም - የአላህ ዲን አንድ ነውና"

https://www.tg-me.com/alateriqilhaq

كن على بصيرة
👉 መሰአለቱል ዑዝሪ ቢልጀህል

https://www.tg-me.com/UstazAbuzarhassenAbutolha/12772
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉 መሰአለቱል ዑዝሪ ቢልጀህል

🌴 ዑዝር ቢል ጀህል ማለትአንድ ሰው እስልምና ውስጥ ሆኖ በጅህልና (ባለማወቅ ) እስልምናን የሚፃረሩ ነገሮችን በሚሰራ ጊዜ ከእስልምና ወጣ ወይስ አልወጣም በሚለው ጉዳይ ዑለሞች የሚሰጡት ብይን ማለት ነው። በዚህ ላይ የሰለፍ ዑለሞች ሁለት አይነት አቋም አላቸው። ከፊሎች አንድ ሰው መሰረታዊ የተውሒድ ጉዳዮችን የሚያፈርስ ነገር ከሰራ ይከፍራል ምናልባት አዲስ ወደ እስልምና የገባ ወይም ከእስልምና አስተምሮ የራቀ አካባቢ ላይ ያለ ካልሆነ ይላሉ። ሌሎች ደግሞ አንድ ሰው መሰረታዊ የተውሒድ ጉዳዮችን የሚያፈርስ ነገር ከሰራ ከእስልምና ወጥቷል ለማለት መስፈርቶች መሟላት ከልካይ ነገሮች መወገድና ሁጃ መቆም (በሚገባው ቋንቋ መረጃው መድረስ ) አለበት ይላሉ።
    
🌱 ይህ ኪታብ ሸይኻችን ሸይኽ አቡ ዘር የፃፈው ሲሆን መስፈርቶች ሳይሟሉ አይከፍርም ወይም አንድን ግለሰብን ማክፈር አይበቃል የሚለውን በመረጃ ያረጋገጠበት ሲሆን በሰለፍ ዑለሞች ንግግር አጭቆታል። በመሆኑም ዳዒም ይሁን ኡስታዝ ወይም ዐሊም በዚህ ኪታብ በጣም ጠቃሚ እውቀት ያገኛል።

🏝 ማስታወሻ
– መረጃ ማድረስ ወይም ተበዩን እስኪሆንለት ማለት መረጃውን በሚገባው ቋንቋ መንገር ማለት ነው።
– መረጃውን መረዳት አለበት ሲባል መሰረታዊ ግንዛቤ እስኪፈጠርለት ማለት እንጂ እንደ ኹለፋኦች አይነት ፈህም ላይ ይድረስ ማለት አይደለም።
– አንድ ሰው መረጃ ደረሰው ለማለት ልቡ ውስጥ ያለው ሹቡሃ መወገዱ (ዘዋሉ አሽሹብሃ) ወይም መረጃው ገብቶኛል ማለቱ መስፈርት አይደለም።
  
👉 ተክፊሮች አንድ ሰው የኩፍር ወይም የሽርክ ተግባር ላይ ከወደቀ ይከፍራል ይላሉ። በዚህም ከአህሉ ሱና ይለያሉ። 
     

📝 ኡስታዝ አቡ ዑበይዳህ ባህሩ ተካ አላህ ይጠብቀው!

https://www.tg-me.com/bahruteka
📢 ሰበር አስደሳች ዜና 📢

🕰ዛሬ እለተ ሰኞ ሰኔ 23/2017
ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ልዩ ሙሃዶራ አለ እንዳያመልጣችሁ!


👉 ልዩ ቆይታ ከባህር ዳር መሻይኾች
🎙ከሸይኻችን ሸይኽ ሐሰን ገላው እና ከሸይኽ ዩሱፍ አህመድ (ሀፊዘሁሙሏህ) ጋር

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
አዲስ አበባ አለምባንክ

https://www.tg-me.com/DarASSunnah
👉 ተሐዙብ ማለት

ተሐዙብ ማለት በዐረብኛ ቋንቋ ተለይቶ ወጥቶ የሆነን ቡድን በደገፍ በዛ ቡድን አመለካከትና አረዳድ እንዲሁም ዐቂዳ መጓዝ ማለት ነው ። ይህ ለጥሩም ለመጥፎም ይሆናል ።
ለጥሩ የሚሆነው የሆኑ ጭፍሮች ከባጢል አካላት አስተሳሰብ አመለካከትና እምነት ተነጥለው ወጥተው በቁርኣንና ሐዲስ በሶሐቦች አረዳድ በዑለሞች ስር ተሰባስበው ሲጓዙ ነው ።
ለመጥፎ የሚሆነው ደግሞ የሆኑ ቡድኖች በራሳቸው ተደራጅተው ወይም ከሐቅ ባልተቤቶች ተነጥለው በመውጣት በድብቅ የራሳቸውን አላማ ለማራመድ ተሰባስበው መሪ ሾመው ሲንቀሳቀሱ ነው ።
የመጀመሪያዎቹ ሒዝቡላሂ ሲባሉ የሁለተኞቹ ሒዝቡ ሸይጧን ይባላሉ ። ሒዝቡላሂ የተባሉት አላህ ባወረደው መመሪያ የሚሄዱና ዲኑን የሚረዱ በመሆናቸው ሲሆን ሒዝቡ ሸይጧን የተባሉት ስያሜው የተሰጣቸው የአላህን መመሪያ ትተው የሸይጧንና የነፍሳቸውን ጉትጎታ የተከተሉ በመሆናቸው ነው ። እነዚህ ሁለቱም በሚቀጥለው የተከበረው የአላህ ቃል ተወስተዋል :–
{ لَّا تَجِدُ قَوْمًا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ يُوَادُّونَ مَنْ حَادَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَوْ كَانُوا آبَاءَهُمْ أَوْ أَبْنَاءَهُمْ أَوْ إِخْوَانَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ ۚ أُولَٰئِكَ كَتَبَ فِي قُلُوبِهِمُ الْإِيمَانَ وَأَيَّدَهُم بِرُوحٍ مِّنْهُ ۖ وَيُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ ۚ أُولَٰئِكَ حِزْبُ اللَّهِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ اللَّهِ هُمُ الْمُفْلِحُونَ }
المجادلة ( 22)
" በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች ፤ አባቶቻቸው ፣ ወይም ልጆቻቸው ፣ ወይም ወንድሞቻቸው ፣ ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም ፡፡ እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል ፡፡ ከእርሱም በኾነ መንፈስ ደግፏቸዋል ፡፡ ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባቸዋል፡፡ አላህ ከእነርሱ ወዷል ፡፡ ከእርሱም ወደዋል ፡፡ እነዚያ የአላህ ሕዝቦች ናቸው ፡፡ ንቁ! የአላህ ሕዝቦቸ እነርሱ ምኞታቸውን የሚያገኙ ናቸው "፡፡
የሸይጧን ጭፍራ የተባሉት ደግሞ በዚሁ ምእራፍ ላይ አላህ የተቆጣባቸውን ሰዎች መንገድ የተከተሉ ሰዎችን አስመልክቶ ሲናገር በሚቀጥለው አንቀፅ እንዲህ ይላል : –

{ اسْتَحْوَذَ عَلَيْهِمُ الشَّيْطَانُ فَأَنسَاهُمْ ذِكْرَ اللَّهِ ۚ أُولَٰئِكَ حِزْبُ الشَّيْطَانِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ الشَّيْطَانِ هُمُ الْخَاسِرُونَ }
المجادلة (19)
" በእነርሱ ላይ ሰይጣን ተሾመባቸው ፡፡ አላህንም ማስታወስን አስረሳቸው ፡፡ እነዚያ የሰይጣን ጭፍሮች ናቸው ፡፡ ንቁ! የሰይጣን ጭፍሮች ከሳሪዎቹ እነርሱ ናቸው "፡፡
ተሐዙብ ወይም ሒዝቢያ የሚባለው በአብዛኛው የተወገዘ ሲሆን በቁርኣንና ሐዲስ ሐቅን በመቃረን በባጢል የተሰባሰቡ ጭፍሮችን ለማመልከት ነው የሚመጣው ለምሳሌ ለመጥቀስ የሚከተለውን የቁርኣንና ሐዲስ መረጃዎችን እንመልከት : –

{ فَاخْتَلَفَ الْأَحْزَابُ مِن بَيْنِهِمْ ۖ فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ كَفَرُوا مِن مَّشْهَدِ يَوْمٍ عَظِيمٍ }
مريم (37)
" ከመካከላቸውም አሕዛቦቹ በእርሱ ነገር ተለያዩ፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከታላቁ ቀን መጋፈጥ ወዮላቸው "፡፡
የአላህ መልእክኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – እንዲህ ይላሉ : –
عن عرفجة بن أسعد قال : قال – ﷺ –
" مَنْ أَتَاكُمْ وَأَمْرُكُمْ جَمِيعٌ عَلَى رَجُلٍ وَاحِدٍ يُرِيدُ أَنْ يَشُقَّ عَصَاكُمْ ، أَوْ يُفَرِّقَ جَمَاعَتَكُمْ فَاقْتُلُوهُ "
رواه مسلم
ዑርፉጃ የተባለ ሶሐብይ – ረዲየላሁ ዐንሁ – የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – እንዲህ ብለዋል ይላል : –
" ጉዳያችሁ በአንድ መሪ ላይ ተሳማምቶ እያለ ሊለያያችሁ ፈልጎ የመጣን ግደሉት ። "
እነዚህና የመሳሰሉ በጣም ብዙ ሐቅንና በሐቅ ላይ ያሉ ጀማዓዎችን ተቃርኖ ቡድን ፈጥሮ የሚንቀሳቀሱ አካላትን የሚያወግዙ መረጃዎች የመጡ ሲሆን እነዚህ አካላት የተገለፁት በውግዘት ነው ። በባጢል መሰባሰባቸውና አካሄዳቸው ተሐዙብ ይባላል ።
የሐቅ ሶዎች ቁጥራቸው ቢያንስም የአላህ ሕዝቦች ከመሆናቸውም ጋር ጀማዓዎች ተብለው ይጠራሉ ። በመሆኑም በሐቅ ላይ ካሉ ጀማዓዎች ተነጥለው በመውጣት ውስጥ ለውስጥ የራሳቸውን ጀማዓ የሚያደራጁ አካላት ሒዝቢዮች ይባላሉ ማለት ነውና መጠንቀቁ ጥሩ ነው ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
🔷 ከየትኛው ነህ ራስህን ተመልከት ⁉️

قال شيخ الإسلام ابن تيمية -رحمه الله -:
في ‏حديث :

" لا تزال طائفة من أمتي على الحق ظاهرين، لا يضرهم من خذلهم، ولا من خالفهم" .

فلينظر الرجل أيكون من الطائفة المنصورة، أم من الخاذلة، أم من المخالفة؟، فما بقي قسم رابع !.

مجموع الفتاوى ( 28/ 229 ).

ነብዩ – ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም –

" ከኡመቴ ውስጥ በሀቅ ላይ የበላይ የሆኑ ስብስቦች ከመኖር አይወገዱም ። እርዳታው በፈለጉ ጊዜ ወደኃላ ያለባቸውም ይሁን የተቃረናቸው የማጎዳቸው ሲሆኑ"

ብለው በተናገሩት ሐዲስ ላይ ሸኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ በዚህ ሀዲስ ማብራሪያው ላይ ሰውየው ይመልከት :– " ከተረዱት ስብስቦች ጋር ነው የሚሆነው ወይስ ወደኃላ ከሚሉት ወይስ ከሚቃረኑት ከዚህ በኃላ አራተኛ የለም " ! ይላል ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
ከበደሉህ ውስጥ በሆንኩኝ ኖሮ

‏كان الحسن البصري – رحمه الله – يدعو ذات ليلة :
(اللهم اعف عمن ظلمني)
فأكثر في ذلك،
فقال له رجل : يا أبا سعيد لقد سمعتك الليلة تدعو لمن ظلمك حتى تمنيتُ أن أكون فيمن ظلمك فما دعاك إلى ذلك ؟

قال: قوله تعالى :
﴿فمن عفا وأصلح فأجره على الله﴾

شرح البخاري لابن بطال (٥/٥٧٦)

🔹 ሀሰኑል በስሪ - ረሂመሁላሁ - አንድ ለሊት እንዲህ እያለ ዱዓእ ሲያረግ አንድ ሰው ሰማው

" አላህ ሆይ የበደለኝን ይቅር በልልኝ "

ሰውየውም የሰዒድ አባት ሆይ ማታ ለበደለህ ዱዓእ ስታደርግ ሰማሁህ ምናለ እኔም ከበደሉት ብሆን ብዬ እስከምመኝ ድረስ ምንድነው ለዚህ ያነሳሳህ ?
እሱም እንዲህ ብሎ መለሰ :–

" ይቅር ያለና መልካም የሰራ ሰው ምንዳው አላህ ላይ ነው "
የሚለው የአላህ ቃል ነው ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
👉 እህቴ ሆይ አላህን ፍሪ

ሜካፕ ተቀብተሽ ተኩለሽና ተቀንድበሽ ወይም በክት እንደነገነጠለ ውሻ ከንፈርሽን የምእራቦችን ቀይ ኬሚካል ለቅልቀሽ ፎቶሽን ፕሮፋይል የምታደርጊዋ እህቴ ሆይ ይህ ተግባር አላህ እርም ያደረገው ተግባር ነውና ራቂው ። እስኪ በዚህ ሁኔታ ተዘጋጅተሽ ፖስት ከማድረግሽ በፊት አላህ መለከል መውት ቢልክብሽ የሚሆነውን አስቢ !
አላህ ፊት ራቁትሽን እሱን ለማመፅ ተዘጋጅተሽ በነበርሽበት ሁኔታ ስትቆሚ ለመሆኑ
በዚህ መልኩ ፎቶ ተነስተሽ ፕሮፋይል የምታደርጊው የትዳር አጋር ፈልገሽ ነውን ? ከሆነ አላህን እያመፅሽ እንዴት አላህ መልካም ትዳር ይሰጠኛል ብለሽ ታስቢያለሽ ? አላህ ዘንድ ያለን ነገር አላህን በማመፅ መፈለግ ጤንነት አይደለም ። በዚህ መልኩ ከቤት ወጥተሽ መንገድ ላይ ስትውረገረጊ በሸይጣን ታጅበሽ መሆኑን አትርሺ ! ክብርሽንም ህይወትሽንም ልጣጪ ትችያለሽ ። የስሜት ማእበል የሚያናውጣቸውና በስሜት ፈረስ የሚጋልቡ ዋልጌዎች መጫወቻ ትሆኛለሽ ። ብዙ ጊዜ አባት ልጁን ደፈረ ፣ ልጅ እናቱን ተገናኘ የሚሉ ዘግናኝ ዜናዎች የሚሰሙት በዚህ አይነት ሸይጣናዊ አለባበስና በአስካሪ መጠጥ አማካይነት ነው ። ይህ ከአኼራ ቅጣት በፊት የቅርቢቱ ዐለም ውርደት ነው ።
ሌላዋ ቲቪ ፊት ለፊት ቁጭ ብለሽ በአጅ ነብይ ላይ የምታፈጪው ኡስታዝ እገሌ ማለት ይሄ ነው እንዴ ? እኔ እኮ እንዲህ ነበር የሚመስለኝ እያልሽ አይናይኑን እያየሽ በስሜት ጥልቅ ባሕር የምትዋኝው ተይው መላኢካም ይሁን ሸይጧን አይጠቅምሽም ግን ይጎዳሻል ።
ተይ ስትባይ ይህኮ ኺላፍ አለበት እያልሽ በጨለማ ወደ እሾካማ ዱር አትሩጪ !
ኺላፍ የሚሉት የሸረሪት ድር አይነት ማሰሪያ የማይሆን ሹቡሃት ፎቶ ወይም ቪዲዮ መቀረፅ ይበቃል አይበቃም ለሚለው መስአላ እንጂ ለሴት አጅነብይ ማየት አይደለም ። ይፈቀዳል የሚሉትም ሴት ልጅ ቲቪ ፊት ለፊት ቁጭ ብላ ምራቅዋን እየዋጠችና በሰራአካላትዋ እንደኤሌክትሪክ ሞገድ በሚሰራጭ ስሜት እየተናወጠች ትመልከት አይሉም ። ከሹቡሃት ሰመመን ውጪ !
ቢያንስ እንኳን አወዛጋቢ ነገርን መራቅ የራስንም የዲንንም ክብር መጠበቅ ነው የሚለውን መርህ ተከተይ !!
ወንድሜ ሆይ ከላይ ከተነሱት ነጥቦች አንተን የሚመለከቱትን ተጠንቀቅ ፕሮፋይል ፎቶ ማድረግ ራሳቸውን ሳይሆን ሌሎችን ለመምሰል የሚጥሩ ሰዎች ፈለግ ነውና ራቀው ! ፈለጋቸውን እንድትከተል የታዘዝከው ሶሓቦች አሉህና ተከተላቸው ። የለሁት ሀገር ስኬት ታገኛለህ ። ራስህንና ብርቅዬ ሞዴሎችህን ጥለህ እንሰሳዊ ስብእና የተላበሱ የምእራባዊያን ገፀባህሪን ለመላበስ አትዳክር ። አላህን በማመፅ እርካታ ሳይሆን ጭንቀት ነው የሚተረፈው ። የትኛውም አላህን የሚያምፅ ሰው ዱንያዊ ቅጣቱ ከወንጀሉ በኋላ ጭንቀት ውስጥ እንዲገባ መደረጉ ነው ።
ከቤትህ ውስጥ ቲቪ የሚባልን የስነምግባር ጠላት አስወግድ ! አደራህን ሳትጠብቅ አላህ ፊት ቀርበህ ከመጠየቅ ራስህን አድን ! ምእራባዊያኖች እኛን ከክብራችን አውጥተው ወደ እነርሱ ዝቅጠት ለማውረድ በዘረጉት መረብ ራስህን አትተብትብ ።
አላህ መልካሙን ሰምተው ከሚተገብሩት ያድርገን

http://www.tg-me.com/bahruteka
2025/07/01 04:20:00
Back to Top
HTML Embed Code: