Telegram Web Link
Audio
የሸርሑ ሱና ኪታብ ደርስ ክፍል 13
ሰዎች አዲስ ቢዳዓ አምጥተው አያውቁም በዛው ልክ ሱናን ቢተዉ እንጂ የሚለው ነጥብ የተብራራበት ።
Audio
የቁርኣን ትርጉም ማብራሪያ
የአል አዕራፍ ምእራፍ ክፍል 10
እነዚያ ጥጃን ( አምላክ) አድርገው የያዙት ከጌታቸው የሆነ ቁጣና ውርደት በቅርቢቱ ዐለም ያገኛቸዋል የሚለውና ሌሎቹም አንቀፆች የተብራሩበት ።
👉 ጌቶ ወረዳን ማን ነው የሚያስተዳድረው?

ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ይላል !!! የሀገሬ ሰው ። የጌቶ ወረዳ መጅሊስ የወ/ሮ ሂዳያን የቲም ልጆች እያከራዩ የሚያሳድጉበትን ቤት የሰጠሁት ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ አልተደረገም በሚል አሽጎታል ። !!! ገርሞ ገርሞ ይገርማል ። ለመሆኑ የወረዳ መጅሊስ የግለሰቦችን ቤት የሚያሽግበት ስልጣን ማን ሰጠው ? ነው ወይስ ወረዳውን እያስተዳደረ ያለው መጅሊሱ ነው ? ለመሆኑ የወረዳው የፍትህ አካላት ምን እየሰሩ ነው ? ዜጎች በንበረታቸው ላይ መጅሊስ ነው የሚያዘው ? የወረዳው መጅሊስ በሚገርም ሁኔታ ነው ወረዳውን እያስተዳደረና የበላይ የሌለበት መሂኑን ሀገር ይወቅ በሚል መልኩ ነው የወላጅ አልባ ህፃናትን ቤት ያሸገ መሆኑን በትልቁ ፅፎ ማህተም አድርጎ የለጠፈው ።
በሚቀጥለው ሊንክ ገብታችሁ የታሸገ መሆኑን ያሳወቀበትን ተመልከቱ : –
https://drive.google.com/file/d/1jT8Si-BeSKJXhYT8lNs483DcMDc0iYwi/view?usp=drivesdk

የመጅሊሶች የመብት ረገጣ ለከት ካልተደረገለት ጥሩ አይደለምና የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ በፅንፈኞች መብታቸው እየተረገጠ ላሉ ወላጅ አልባ ህፃናት መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል ። እነዚህን አባታቸው ነፍስ ከማወቃቸው በፊት የሞተባቸው ህፃናትን እያሳደጉ ያሉ እናት እንባ የሚያብስ ሊጠፋ አይገባም ።
የጌቶ ወረዳ የመንግስት ተቋማት ሀላፊነታችሁን ለመጅሊስ አስረክባችሁ ከሆነ ለህዝቡ ንገሩት ካልሆነ መጅሊሱ ማንዴቱ የት ድረስ እንደሆነ እንዲያውቅና በማይመለከተውና ስልጣን በሌለው ጉዳይ ገብቶ የዜጎችን መብት መርገጡን እንዲያቆም አድርጉት ። አይ ከኛ በላይ ነው ካላችሁ እኚህ እያለቀሱ እረፍት ያጡትን ወላጅ አልባ ህፃናት እያሳደጉ ላሉት እናት ከናንተ በላይ ወዳለ የመንግስት አካል እንዲሄዱ ንገሯቸው ።
አላህ ሆይ እነዚህን ቃልህንና የመልእክተኛህን ተልእኮ የሚዋጉ አካላትን የሚገባቸውን ስጣቸው ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
Audio
የሸርሑ ሱና ኪታብ ደርስ ክፍል 14
ከነገሮች ትናንሽ ፈጠራዎችን ተጠንቀቅ ከተተዉ ትላልቅ ይሆናሉና የሚለው ነጥብ

🌐 ▿▿▿▿▿▿▿▿
https://www.tg-me.com/bahruteka/5998
Audio
የቁርኣን ትርጉም ማብራሪያ የአል አዕራፍ ምእራፍ ክፍል 11
አላህ ለከሀዲያኖች እስከ ቂያማ ድረስ መጥፎ ቅጣት የሚያቀምሳቸው የሚልክባቸው መሆኑን ባሳወቀ ጊዜ ጌታህም ቅጣቱ ፈጣን ነው የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።

🌐                 ▿▿▿▿▿▿▿▿
https://www.tg-me.com/bahruteka/5999
ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም

የፊታችን እሁድ በቀን 17/09/2017  ታላቅ የሙሐደራ ፕሮግራም በመድረሳችን አልኢስላሕ ለየት ባለና ባማረ መልኩ አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል፡፡ 

🪑ተጋባዥ እንግዶች፡-

1ኛ.   🎙 አሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ኢብኑያሲን አልለተሚ (ሐፊዘሁሏህ)

2ኛ.   🎙 አሸይኽ ሙባረክ ሑሰይን አልወልቂጢ  (ሐፊዘሁሏህ)

👉 በተጨማሪ ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ይኖራሉ፡፡

አይደለም መቅረት ማርፈድ አይታሰብም።


📚 ከዚህ በተጨማሪ በሸይኻችን ሸይኽ ዐብዱልሐሚድ የሚሠጠው የ6ኛው ዙር ወርሃዊ ፕሮግራም ከፊታችን ጁሙዓህ ጀምሮ በሰአቱ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ እንደተለመደው ደርሱ ፕሮግራም የሚጀምረው ከአሱር ሰላት በኋላ ነው!!!

አድራሻ፡-  አልኢስላሕ መድረሳ ፉሪ ኑሪ ሜዳ ባጃጅ  ተራ መጨረሻ

🌐  https://maps.app.goo.gl/63WejUjbbkC1c6si7


ሰዓት፡- ልክ 2፡30 ይጀምራል፡፡

ለሴቶች በቂ ቦታ ተዘጋጅቷል!!!!!

ለበለጠ መረጃ 0951518383

https://www.tg-me.com/medresetulislah
ሰዎችን ሁሉ ማስደሰት አትችልም ።

قال الإمام الشافعي – رحمه الله –:

إنك لاتقدر أن ترضي الناس كلهم
فأصلح ما بينك وبين الله، ولاتبال بالناس.

‎ مناقب_الشافعي ٢٤/١

ኢማሙ ሻፍዕይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ : –

" አንተ ሰዎችን ሁሉ ማስደሰት አትችልም ። በአንተና በአላህ መካከል ያለውን አስተካክል ። ለሰዎች ( ትችት) ቦታ አትስጥ ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ወድ ወንድምና እህቶች ቴሌግራም በኔ ቻናል ላይ የለቀቀው ማስታወቂያ እንዳለ ወንድሞች ነግረውኛል ይህ ማስታወቂያ እኔን አይወክልም ። ማስታወቂያውን ሪፖርት አድርጋችሁ ለማስጠፋት ከጎን ያለውን ሶስት ነጥብ ነክታችሁ ምጫዎች ሲመጡ spam ብላች ላኩ ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
🔷   ከመልካም ነገር ምንንም አትናቅ

    قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم – :

   " لا تحقرن من المعروف شيئا "

              رواه مسلم 

      🔹 " ከመልካም ነገር ምንን በትንሽ አይን አትይ "

    በዚህ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ኡመታቸውን ወደ መልካም ነገር ሲያመላክቱ የመልካም ነገር ትንሽ እንደሌለው በማመላከት ነው ። ገንዘብ የማይከፈልበት መልካም ነገር ሞልቷል ። ጉልበት የማይፈልግ መልካም ነገር ሞልቷል ። ብዙ ኪታብ መቅራት የማይጠይቅ መልካም ነገር ሞልቷል ።
      ለወንድም ፈገግ ማለት ፣ መልካም ንግግር ፣ ከመንገድ ላይ ቆሻሻን ማስወገድ ፣ ምላስን ዚክር ማስለመድና በማንኛውም ሁኔታ ዚክር ማድረግ ፣ ቤት ስትገባ ፈገግ ብለህ ማናገር ፣ ልጆችህን መሳም ፣ ምግብ ሲበላ ባለቤትህን ማጉረስና የመሳሰሉ በቀላሉ የሚሰሩ መልካም ነገሮች እያሉ የመልካም ስራ ድሀ መሆን የለብንም ።
     
      https://www.tg-me.com/bahruteka
🔷      ዚክርና ቱሩፋቱ

قال ابن رجب الحنبلي – رحمه الله – :

" الأعمال كلها يفرغ منها،  والذكر لا فراغ له ولا انقضاء، والأعمال كلها تنقطع بانقطاع الدنيا،  ولا يبقى منها شيء في الآخرة. والذكر لا ينقطع
والمؤمن يعيش على الذكر ، ويموت عليه ، وعليه يبعث ."

لطائف المعارف  ص ( 365 ) 

    ↪️   ኢብኑ ረጀብ የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል: –

" ስራ ሁሉ ያልቃል,  ዚክር ግን አያልቅም መጨረሻም የለውም ። ስራ ሁሉ ዱንያ ሲያበቃ ያበቃል ። ከሷ አኼራ ላይ የሚቀር የለም ( የዱንያ ስራ)  ዚክር ግን አይቋረጥም ። ሙእሚን በዚክር ይኖራል ። በዚክር ይሞታል ። በዚክር ይቀሰቀሳል ። "

አላህ ከዛኪሮች ያድርገን ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
👉  የኢስቲጝፋር ጥቅም

    عن أبي سعيد الخدري – رضي الله عنه – أن رسول الله – صلى الله عليه وسلم –  قال :

" إن الشيطان قال : وعزتك يا رب، لا أبرح أغوي عبادك ما دامت أرواحهم في أجسادهم،  فقال الرب : وعزتي وجلالي،  لا أزال أغفر لهم ما استغفروني "

             المسند  ( 3/29 )

      🔹  አቡ ሰዒዲኒል ኹድርይ – ረዲየላሁ ዐንሁ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – እንዲህ ብለዋል ይላል : –

" ሸይጣን ጌታዬ ሆይ በአሸናፊነትህ ይሁንብኝ ባሮችህን ነፍሳቸው በአካላቸው እስካለች ድረስ ከማጥመም አልወገድም አለ ። 
   አላህም በአሸናፊነቴ በልቅናዬ ይሁንብኝ ኢስቲጝፋር እስካደረጉ ( ምህረት እስከጠየቁ ) ድረስ ምህረት ከማድረግ አልወገድም ።"

https://www.tg-me.com/bahruteka
🔹ሸይኽ ዑሰይሚን – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ: –

" በዙል ሒጃ 10 ቀኖች የሚሰሩ ሶደቃዎች በረመዳን 10 ቀኖች ከሚሰሩት የበለጠ አላህ ዘንድ ተወዳጅ ነው " ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
👉 የዘጠኙ ቀን ፆም

↪️ አላህ ለባሮቹ ከቸረው ከሰጠው በረከት ውስጥ አንዱ በዙል ሒጃ ወር የመጀመሪያዎቹ ዐስር ቀኖች ውስጥ ያደረገው አምሳያ የሌለው ምንዳና ቱሩፋት ነውእነዚህን ቀኖች አስመልክቶ ዐብዱላሂ ኢብኑ ዐባስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላሉ፦

عن ابن عباس– رضي الله عنهما –قال:- قال رسول الله صلى الله عليه وآله وسلم:-

"مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهَا أَحَبُّ إِلَى اللهِ مِنْ هَذِهِ الْأَيَّامِ" يَعْنِي أَيَّامَ الْعَشْرِ، قَالُوا :- يَا رَسُولَ اللهِ، وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللهِ؟ قَالَ:- "وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللهِ، إِلَّا رَجُلٌ خَرَجَ بِنَفْسِهِ وَمَالِهِ، فَلَمْ يَرْجِعْ مِنْ ذَلِكَ بِشَيْءٍ".

أخرجه أبو داود وابن ماجه وغيرهما.

"ከእነዚህ ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራ አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነበት አንድም ቀን የለም (የዙል ሒጃ ዐስሩ ቀኖች) አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ በአላህ መንገድ ላይ መታገልም ቢሆን?  አሉዋቸው። በአላህ መንገድ ላይ መታገልም ቢሆን, ምናልባት አንድ ሰው ነፍሱንና ገንዘቡን ይዞ ወጥቶ በምንም ነገር ካልተመለሰ እንጂ"

ይህ ሐዲስ መልካም ስራ የቱ እንደሆነ አልገደበም የትኛውም አይነት መልካም ስራ ያካትታል። ይሄኛው መልካም ስራ እዚህ ውስጥ አይገባም የሚል ሰው ማስረጃ ይጠየቃል ካላመጣ ተራ ወሬ ነው የሚሆነው። በእነዚህ ቀናቶች መፆም ከመልካም ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው። እያንዳንዱ ቀን ራሱ የቻለ ስለሆነ አንድ ላይ መፆም አይፈቀድም ማለትም ከልብ ወለድ መናገር ነው የሚሆነው።
  
ነብዩን አስመልክቶ እናታችን ሐፍሳ ይፆሙ ነበር ስትል እናታችን ዓኢሻ ደግሞ ፆመው አያውቁም ትላለች ዑለሞች በዚህ ዙሪያ የተለያየ ማስማሚያ (ማስታረቂያ) አቅርበዋል። ነገር ግን የሳቸው መፆምም ይሁን አለመፆም ንግግራቸውን አይፃረርም። አልፆሙም ቢባል እንኳን መፆም አይቻልም ማለት አይደለም። ምክንያቱም ለኡማቸው የሚጠቅመውን በቃላቸው አረጋግጠዋልና,  አብዛኛዎች የፍቅህ ሊቃውንቶች መፆሙ ሱና ነው ይላሉ። የዘመናችን ትላልቅ ዑለሞች እንደነ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፣ ዑሰይሚንንና ፈውዛን የመሳሰሉ መፆሙ ከመልካም ስራ መሆኑን አረጋግጠዋል ።
ስለዚህ በዚህ ጉዳይ በየአመቱ ንትርክ መፍጠርና አማኞችን ግራ ማጋባት አያስገልግም።
አላህ ለምልካም ስራ ያግራን።


http://www.tg-me.com/bahruteka
የዙል ሂጃ አስሩ ቀኖች

   የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - እነዚህን ቀኖች አስመልክተው እንዲህ ይላሉ :-

" ምንም ቀን የለም መልካም ስራ አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነበት ከእነዚህ ቀኖች የበለጠ
በአላህ መንገድ ላይ መታገልም ቢሆን ?
አሉዋቸው
አው ! በአላህ መንገድ ላይ መታገልም ቢሆን
ምናልባት አንድ ሰው በአላህ መንገድ ለመታገል በነፍሱና በገንዘቡ ወጥቶ በምንም ያልተመለሰ ቢሆን እንጂ " አሉ ።
ከዚህ ሀዲስ የምንረዳው በእነዚህ አስር ቀኖች ውስጥ የሚሰሩ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ ያላቸው ቦታ በጣም ትልቅ መሆኑ ነው ። የመልካሙ ስራ አይነት አልተገደበም ። ይህም እያንዳንዱ ሙእሚን በሚገራለት የመልካም ስራ አይነት እንዲበረታ መንገድ የከፈተ ነው ። ሁሉም በሚገራለት በመልካም ስራ ራሱን መሽጉል ማድረግ ይችላል ። ከእነዚህ ውስጥ ለምሳሌ : –
   ዚክር ማድረግ ፣ ቁርኣን መቅራት ፣ ሱና ሶላቶችን ማብዛት ፣ ዚያራ ፣ ሶደቃ ፣ ፆም ፣ የታመመ መጠየቅ ፣ የተጣላን ማስታረቅ ፣   በመልካም ማዘዝ ፣ ከመጥፎ መከልከል ፣
እና የመሳሰሉ መልካም ስራዎች ተጠቃሾች ናቸው ። በተለይ ምንም ገንዘብም ሆነ ጉልበት የማያስፈልገው ግን የመልካም ስራ ንጉስ የሆነው ዚክር አጅር ከሚዘረፍባቸውና ዋናው ሲሆን ቆሞም ፣ ተቀምጦም ፣ ተጋድሞም ፣ ቢሮም ሱቅም ፣ ተሳፍሮም ሆነ በእግር ሲጓዙ ፣ በየብስም ሆነ በባህር ወይ በአየር ፣ ገበሬም ሆነ ነጋዴ ፣
ሐኪምም ሆነ መሀንዲስ ፣ ተማሪም ሆነ አስተማሪ
በጓዳም ሆነ በማድ ቤት ፣ የትም መቼም በየትኛውም ሁኔታ ያለ ትጥበት ወይም ውዱእ ሊተገበር የሚችል የዒባዳ አይነት በመሆኑ መዘናጋቱ ትርፉ ፀፀት ነው ።

አላህ ከተጠቃሚዎች ያድርገን ።

http://www.tg-me.com/bahruteka
Audio
የሸርሑ ሱና ኪታብ ደርስ ክፍል 15
ካለህበት ዘመን ንግግሩን የሰማኸውን ሰው ሁሉ ለማሰራጨት አትቸኩል ! ከሰለፎች ማን እንደተናገረው እስክታረጋግጥ ድረስ ። ከሰለፎች ከመጣ ያዘው… የሚለው ነጥብ የተብራራበት ።
Audio
የቁርኣን ትርጉም ማብራሪያ የአል አዕራፍ ምእራፍ ክፍል 12
ከፈጠርናቸው ህዝቦዝች በሐቅ የሚመሩናበርሱ የሚያስተካክሉ አሉ ። የሚለውና ሌሎቹም አንቀፆች የተብራሩበት ።
ሰበር አስደሳች ዜና

ዛሬ እለተ ሰኞ ቀን 18/9/2017 ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

🎙 በአሸይኽ አብዱልሐሚድ ኢብኑ ያሲን አልለተሚ (ሐፊዘሁሏህ)

ርዕስ:- نُبْذَةٌ مِنْ دَعوةِ إِبْرَاهِيمَ (عليه السلام)
ከኢብራሂም አለይሂሰላም ደዕወህ የተወሰነ

https://www.tg-me.com/medresetulislah
👉 ማስታወሻ ለወንድሞች

የኩፍር የሽርክና የቢዳዓ አስተሳሰብና አመለካከት ተሸክመው እየዞሩ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚዘሩት አሕባሾች እየረጩት ያለውን ቁርኣን የአላህ ቃል አይደለም መኽሉቅ ነው የሚለውን መርዛቸው በአደባባይ እየረጩ መሆኑ ይታወቃል ። ይህ ሁሉም ዓሊምና ጧሊበል ዒልም ሊዋጋውና ባጢልነቱ በመረጃ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ግልፅ ሊያደርገው የሚገባውን የኩፍር አስተምሮ በምንም መልኩ ድምፁንም ይሁን ቪዲዮ በሚዲያ መልቀቅ አያስፈልግም ። ምክንያቱም ውዳቂ የሆነውን ፍልስፍናቸውንና ማስመሰያቸውን በማዳረስ መተባበር ስለሚሆን ።
ከሰለፍዮች የሚጠበቀው ቁርኣን የአላህ ቃልና ባህሪው መሆኑን በመረጃ ማስተማርና የአክፍሮት ተልእኮ አንግቦ ኢስላምን ለመናድ በምእራቦች የተላከውን ቡድን በቁርኣንና ሐዲስ እንዲሁም በሰለፎች ንግግር ድባቅ መምታትና አንገቱን እንዲደፋ ማድረግ ነው ።
በዚህ ጉዳይ ቅድሚያ ሊዙ የሚገባው ዑለሞች ሲሆኑ ጠንከር ያሉ የዲን እውቀት ተማሪዮችም ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ።
አሁንም ማስታወስ የምወደው በፍፁም የእነዚህን የኢስላም ጠላቶች ድምፅም ይሁን ቪዲዮ እንዳናስተላልፍ የሚለው ነው ። ምክንያቱም ሹብሃ ጠላፊና ዐቅል ደካማ በመሆኑ ሰለፎች ስላስጠነቀቁ ነው ።

http://www.tg-me.com/bahruteka
2025/07/02 01:30:02
Back to Top
HTML Embed Code: