Telegram Web Link
👉በነብዩ ላይ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላዋት ማብዛት
¯¯¯¯¯¯

📜عن أبى بن كعب قال: قلت يارسول الله፡-

إنى أكثر الصلاة عليك . فكم أجعل لك من صلاتى
فقال : "ما شئت" ؛ قلت: الربع
قال :"ماشئت , فإن زدت فهو خير لك". 
قلت : فالنصف
,قال : ما شئت فإن زدت فهو خير لك" ,قلت :فالثلثين 
قال : "ما شئت ,فإن زدت فهو خير لك"
قلت : أجعل لك صلاتى كلها قال :
«إذن يكفى همك ويغفر لك ذنبك»

📚السلسلة الصحيحة 954

🔷ኡበይ ኢብኑ ከዕብዐረዲየላሁ ዐንሁ እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክኛ ሆይ እኔ በርሶ ላይ ሶለዋት አበዛለሁ ከሶለዋቴ (ከዱዓኤ) ምን ያክሉን ለርሶ ላድርገው አልኳቸው ይላል፦

☑️ «የፈለግከውን» አሉኝ
📝አንድ አራተኛውን ላድርግ? አልኳቸው "
🔖 የፈለግከውን ብትጨምር ላንተ መልካም ይሆንልሀል» አሉኝ
📜ግማሹን ላድርግሎት? አልኳቸው
የፈለግከውን ብትጨምር ላንተ መልካም ነው»።
🏖ሁለት ሶስተኛውን ላድርግሎት? 
🖼 «የፈለግከውን ብትጨምር ላንተ መልካም ነው» አሉኝ።
ሶለዋቴን (ለዱዓእ የወሰንኩትን ጊዜ) በሙሉ ላድርግሎት ወይ አልኳቸው?
📚የዛን ጊዜማ የሚያስጨንቅህን ነገር ሁሉ አላህ ይበቃሀል ወንጀልህም ይማርልሀል» አሉኝ።

↪️ ከዚህ ሐዲስ የምንረዳው ጠያቂው ለነብዩ ዱዓእ የሚያደርግበት የወሰነው ጊዜ እንዳለውና ምን ያክሉ በሳቸው ላይ ሶለዋት ለማውረድ እንደሚጠቀምበት ሲጠይቃቸው ያን ጊዜ በሙሉ  በሳቸው ላይ ሶለዋት በማውረድ እንዲጠቀምበትና ይህን ካደረገ የሚያገኘውን ምንዳ የነገሩት መሆኑን ነው። ይህ ማለት በነብዩ ላይ ሶለዋት ማውረድ ምን አይነት አጅር እንደሚያስገኝ የሚያሳይ በመሆኑ ጊዜያችንን በዚህ ወደ አላህ በሚያቃርበን ስራ እናሳልፈ።

ሶለዋት ሱቅ ላይ ፣ ቢሮ ውስጥ ፣ መኪና ውስጥ ፣ አየር ላይ ፣ ባሕር ላይ ተቀምጦም ፣ እየሄዱም ፣ ተጋድሞም ማድረግ ይቻላል እና እንጠቀምበት።

📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://www.tg-me.com/bahruteka
https://www.tg-me.com/bahruteka
👌 ሽርክ ወይስ የፍቅር ደብዳቤ?
      ◈¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯◉

🏝 አህባሾች እና ግብራበሮቻቸው ሳይቅሙም ጭምር የሚመረቅኑ ጉደኞች ናቸው። ወይስ የጫት ምርቃና አይለቅም?

➷➴➴➷➘
https://www.tg-me.com/AbuImranAselefy/10888
👆👆👆👆👆👆

🎤 ከላይ በድምፅ እንደምሰሙት በደበዘዘ አስተሳሰቡ አንዲህ ይላል፦ «መንዙማስ ማለት ምንድን ነው ብትባል? አዳምጠኝ! ቡኻሪ ላይ እንዳትፈልገው! ይሄን ❲መንዙማን❳ እዛ ❲ቡኻሪ❳ ላይ አታገኘውም።»

መልስ፦ ይህ አባባል የአህባሽን እምነት በግልጽ ያመላከተ አባባል ነው። አዎ አህባሽ ዲን ብላ የምትመራበት ከቁርኣንም ሆነ ከነብያችን ﷺ ሀዲስ የተያዘ አይደለም። ራሱ ሰውየው እንደመሰከረው መንዙማ ቡኻሪ አይገኝም። ቡኻሪ ማለት ከቁርአን ቀጥሎ አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ ሲሆን የውዱን ነብይ ﷺ ቃል ሰብስቦ የሚገኝ ኪታብ ነው። በዚህ ኪታብ አህባሾችና መሰሎቻቸው የዲን አካል አድርገው የያዙት መንዙሙ አይገኝም።
👌 وَشَهِدَ شَاهِدٌ مِّنْ أَهْلِهَا

◈ ምን ይሄ ብቻ
◦ መውሊድም አይገኝም።
◦ የሸዋል ዒድም አይገኝም።
◦ የቀብር አፈር በጥብጦ መጠጣትም አይገኝም።
◦ ሙታንን መማፀንም አይገኝም።

👌 ውጤት ፦ ስለዚህ አህባሾች እና መሰሎቻቸው የያዙት እምነት ከቡኻሪ (ከነብያችን ﷺ ሀዲስ) ሳይሆን ከግለሰቦች የመለጨ ሰዋዊ ቀመር እንጂ በአላህ የተደነገገው መለኮታዊ እምነት እስልምና አይደለም። ምንም እንኳን ቢሰግዱም ቢፆሙም ግን የያዙት እምነት በሽርክ በቢድዓ እና በመሳሰሉት ግፎች የበከሉት ዲን ነው።

🎤  ቀጥሎ እንዲህ ይላል፦ «መንዙማ ማለት ምንድን ነው? የፍቅር ደብዳቤ ነው። መንዙማን የማያውቀው ክፍል አፍቃሪም አይደለም ተፈቃሪም አይደለም። ታዲያ የማያውቀው ሀገር እሱ ስለዛ መናገር አይችልማ እኛ አፍካሪ ነን ተፈቃሪ ነን።»

መልስ፦ በዚህ ንግግር ከባባድ ንግግሮች ቀርበዋል። ሰውየው መርቅኖ ሳያስተውል የተናገረው ነው።

◈ ጥያቄዎችን ብቻ ላንሳ
⁉️ በመንዙማ ነብዩን ﷺ ማወደስ ብቻ ሳይሆን ሽርክም አለበት! ማንም አይክድም! ታዲያ እነዚያ የሽርክ ቃላት የፍቅር ደብዳቤ ናቸውን? ወይስ ፍቅራችሁ ከሸይጧን ጋር ነው? ያፈቀራችሁት ጀሃነምን ነውን?

⁉️ መንዙማን የማያውቀው ክፍል አፍቃራም ተፈቃሪም ካልሆነ
👌 መንዙማን
▣ ሶሃቦችም
▣ ታብዒዮችም
▣ አራቱ ኢማሞቻችንም
    ◈❲አል-ኢማሙ አህመድ 
    ◈❲አል-ኢማም አሻፊዒይ
    ◈❲አል-ኢማሙ ማሊክ
    ◈❲አል-ኢማሙ አቡ ሀኒፋ
▣ ሙሀዲሶቹም
    ◈❲ቡኻሪ
    ◈❲መስሊም ... ወዘተ
👌 እነዚህ ሁሉ መንዙማን አያውቁትም። ❨ቀደም ሲል ራሱ አህባሹ ቡኻሪ እንደማያውቁት መስክሯል።❩
👌 በዚህ መሰረት ይሄ ሁሉ የኢስላም እንቁ ትውልድ አፍቃሪም ተፈቃሪም አይደለም ማለት ነው? ወይስ ማፍቀር ሸይጧንን ሆኖ ነው? ከሆነ አዎ አፍቃሪም ተፈቃሪም አይደሉም። ነብዩን ﷺ ከሆነ ግን ከማናችንም በላይ አፍቃሪዎቹም ተፈቃሪዎችም መንዙማን የማያውቁት ሶሃቦች ናቸው።

🏝 مَّا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ وَلَا لِآبَائِهِمْ ۚ كَبُرَتْ كَلِمَةً تَخْرُجُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ ۚ إِن يَقُولُونَ إِلَّا كَذِبًا

🏝 ለእነሱም ለአባቶቻቸውም በርሱ ምንም እውቀት የላቸውም፡፡ ከአፎቻቸው የምትወጣውን ቃል ምን አከበዳት! ውሸትን እንጂ አይናገሩም፡፡
[ሱረቱ አል ከህፍ፥ - 5]

☔️ ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) በትኩረት ባልተሰጣት ወይም እኛ እንደ ቀላል በምንመለከታት ንግግር ምክንያት አንድ ሰው ወደ ጀሀነም ሊገባ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ይህን የሚያሳዩ በርካታ አስተማሪ ሀዲሶች አሉ።
ከእነዚህም መካከል፦

🌴 عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ: ((إِنَّ الْعَبْدَ لَيَتَكَلَّمُ بِالْكَلِمَةِ يَنْزِلُ بِهَا فِي النَّارِ أَبْعَدَ مَا بَيْنَ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ)).
🌴 "አንድ ባሪያ ሳያስብበት (ወይም ምንም ዋጋ የሌለው መስሎት) የሚናገረው ቃል አለ፤ በዚህ ቃልም ወደ ጀሀነም ከምስራቅና ምዕራብ ርቀት በላይ ይወርዳል።"
(ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት)

👉 ይህ ሀዲስ የሚያሳየው፣ የምንናገረው ቃል ምንም ያህል ቀላል ቢመስልም፣ በአላህ ዘንድ ክብደት ሊኖረውና ለከፋ ቅጣት ሊያደርስ እንደሚችል ነው። ብዙ ጊዜ ሰዎች ሲያወሩ ትኩረት ሳይሰጡት የሚናገሩት ነገር (ለምሳሌ፣ ሀሜት፣ ውሸት፣ ስድብ፣ ወይም ያለ አግባብ ሰውን መተቸት) ወደ ጥፋት ሊያመራ ይችላል።

🌱 እውነት ለመናገር ይህ አህባሽ በጫት ሞቅታ መንጫጫት የለመዱ አጃቢዎቹን ሰብስቦ በዚህ መልኩ እያንጫጫ የተናገረው ከንቱ ንግግር አደገኛ ነው። ገና ለገና ውሃብያ የሚላቸውን ሰዎች ለማናደድ በሚል ያለአግባብ ትችት በማንሳቱ ከባድ ንግግር ተናግሯል።

👌 ውድ ወንድም እህቶቼ አህባሾች ማለት የሙስሊሞችን ትክክለኛ ዲን የሚሸረሽሩ ሲሆን ዋነኛውና ትልቁ መሰላላቸው ደግሞ መንዙማ ነው። ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንደአይን ብሌኑ በሚቆጥራቸው ነብይ ﷺ ያወደሱ እየመሰሉ ሽርክን የሚያስፋፉ የሽርኽ መጓጓዣዎች ናቸው። ይህንን አውቀን ከልባችን እንቀሳቀስ!

📝 ወንድማችሁ አቡ ዒምራን

👌  👉  ☔️  🌱   👇👇👇
https://www.tg-me.com/AbuImranAselefy/10889
👉 እየአንዳንዱ የሚቀንሰው እስትንፋስ ያንተ ክፋይ ነው ! ።

قال ابن قدامة  – رحمه الله – :

    " فاغتنم رحمك الله حياتك النفيسة ، واحتفظ بأوقاتك العزيزة ؛ واعلم أن مدة حياتك محدودة ؛ وأنفاسك معدودة ، فكل نفس ينقص به جزء منك؛ والعمر كله قصير، والباقي منه هو اليسير ."

غذاء الالباب
في شرح منظومة الآداب    ( 448 )

  ➡️  ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ቁዳማ እንዲህ ይላል : –
" ውድ የሆነውን ሓያትህን ተጠቀምበት ,  አሸናፊ የሆነውን ጊዜህን ጠብቅ ,  የህይወትህ ጊዜ የተገደበ መሆኑን እወቅ, እስትንፋስህም የሚቆጠር ነው ። እየአንዳንዱ የሚቀንሰው እስትንፋስ ያንተ ክፋይ ነው ። እድሜ ሁሉም አጭር ነው ። ከዚህ የተቀረው ጥቂቱ ነው " ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
🔹 ዱንያ የትጋት ሀገር ናት ።

قال ﻳﺤﻴﻰ ﺑﻦ ﻣﻌﺎﺫ - رحمه الله - :

« اﻟﺪﻧﻴﺎ ﺩاﺭ ﺃﺷـﻐﺎﻝ ، ﻭاﻵﺧﺮﺓ ﺩاﺭ ﺃﻫـﻮاﻝ ، ﻭﻻ ﻳﺰاﻝ اﻟﻌﺒـﺪُ ﺑﻴﻦ اﻷﺷـﻐﺎﻝ ﻭاﻷﻫـﻮاﻝ ﺣﺘﻰ ﻳﺴـﺘﻘﺮَّ ﺑﻪ اﻟﻘـﺮاﺭ ، ﺇﻣَّـﺎ ﺇﻟﻰ ﺟﻨﺔ ﻭﺇﻣَّـﺎ ﺇﻟﻰ ﻧﺎﺭ ».

شذراة الذهب ج ( 3 )

🔷 የህያ ኢብኑ ሙዓዝ ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላል :-

" ዱንያ የትጋት አገር ናት
አኼራ ነገሮች የሚከሰትባት አገር ናት
አንድ ባሪያ በሁለቱ መካከል ነው
የሚያረጋጋ ነገር ወይ በጀነት ወይ በጀሀነም እስከ ሚያረጋጋው ድረስ "

https://www.tg-me.com/bahruteka
🚫 የስልክ ንግግርን ደብቆ መቅዳት

እንከን የለሹ ኢስላም ለሙስሊሞች የዘረጋላቸው የህይወት መስመር እንከን የማይወጣለት ነው ። በየትኛውም እንቅስቃሴያቸው አላህን እንዲፈሩና ራሳቸውን ሒሳብ እንዲያደርጉ ያሳስባል ። የእስልምና ሸሪዓ ይህንም ጭምር አውስቶታል ወይ በሚያስብል ልክ ለሁሉም መመሪያና ህግ አስቀምጧል ። ከእነዚህ አስገራሚ መመሪያዎች ውስጥ ሰዎች በመተማመን የሚለዋወጡዋቸውን ሐሳቦች ያለ ባለቤቱ ፈቃድ ወደ ሌላ አካል ማስተላለፍን አጥብቆ ይከለክላል ። ሐሳቡ በሁለት ሰዎችም መካከል ይሁን ከዛ በላይ ባሉ ሆኖ ከእነርሱ ውጪ እንዳይወጣ በማይፈልጉበት ጉዳይ ላይ የተነሳን ሓሳብ ከመካከል አንዱ ተነጥሎ ለሌሎች እንዲደርስ ማድረግ አማናን እንደመብላት ይቆጠራል ።
ከዚህ ውስጥ ሁለት ሰዎች በስልክ ያወሩትን ጉዳይ አንደኛው ሳያውቅ ቀድቶ ለሌሎች ማስተላለፍ ወሬ ማሳበቅና አማና መብላት ውስጥ ይገባል ። ከሁለቱ አንዱ የተነጋገሩበትን ነገር ወደ ሌላ መውሰዱ ሌላውን የሚገዳና አዛ የሚያደርገው ከሆነ የድርጊቱ ክልክልነት ደረጃ በዛው ልክ ይጨምራል ። የኢስላም ሊቃውንቶች ሸሪዓዊ ለሆኑ አገልግሎቶች ከአህሉል ቢዳዓ እንደማስጠንቀቅና ቃዲ ፊት ለመረጃ ማጠናከሪያነት ማቅረብን ለመሳሰሉት ካልሆነ የሚመለከተው አካል ሳይፈቅድ ወደ ሌላ አካል ማድረስ ክልክል መሆኑን ያስረዳሉ ። በዚህ ዙሪያ ከመጡ መረጃዎች ውስጥ በቀጥታ ተያያዥነት ያላቸውን የተወሰኑትን እጠቅሳለሁ ።
عن جابر بن عبد الله – رضي الله عنه – قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم –

" إذا حدث الرجل الحديث ثم التفت فهي أمانة" .
رواه أبو داود والترمذي وحسنه الألباني

وفي رواية " المجالس بالأمانة "

ጃቢር የተባለ ሶሓብይ ባስተላለፈው ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል : –

" አንድ ሰው ( ከሌላ ሰው ጋር ) በሆነ ጉዳይ አውርቶ ዞር ካለ ያ ወሬ አማና ነው "
በሌላ ዘገባ ደግሞ
" ሰዎች የሚቀማመጡበት ( ጉዳይ ) አማና ነው "
ምናልባት ያ የወጣው ወሬ ከሁለት አንዱን አዛ የሚያደርግ ከሆነ በሚከተለው የመልእክተኛው ንግግር ይገባል :–

عن عبد الله بن عمر – رضي الله عنه – قال
 صعد رسولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم المنبر فنادَى بصوتٍ رفيعٍ فقال :
" يا معشرَ من أسلمَ بلسانهِ ولم يُفضِ الإيمانُ إلى قلبهِ ، لا تُؤذُوا المسلمينَ ولا تُعيّروهُم ولا تَتّبعوا عوراتهِم ، فإنه من يتبِعْ عورةَ أخيهِ المسلمِ تتبعَ اللهُ عورتَهُ ، ومن يتبعِ اللهُ عورتهُ يفضحْه ولو في جوفِ رحلهِ "

أخرجه الترمذي بسند حسن

ዐብዱላሂ ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁማ የአላህ መልእክተኛ ሜምበር ላይ ወጡና እንዲህ አሉ
" እናንተ በምላሳችሁ የሰለማችሁና ኢማን ወደ ልባችሁ ያልደረሰ ስብስቦች ሆይ ሙስሊሞችን አዛ አታድርጉ … "

እነዚህ በጥቅልና በዝርዝር ከመጡ የቁርኣንና የሐዲስ አማናን ስለመጠበቅ መረጃዎች በጣም ጥቂቶቹ ናቸው ። የአማና ጉዳይ ኢስላም በጣም ትልቅ ትኩረት ከሰጣቸው ሸሪዓዊ ድንጋጌዎች ውስጥ ሲሆን ማጓደሉ የሙናፊቅነት ባህርይ መሆኑን በማስጠንቀቅ አስተምሯል ።
ሁለት ሰዎች አንዱ ሌላውን አምኖ ያወራውን ወሬ ለእኩይ አላማ ብሎ አማናውን ክዶ ወደ ሌላ ማስተላለፍ ያውም ሸርና ተንኮል አስቦ የረከሱ ሰዎች ተግባር ነው ። ከረከሰ ሰው እርካሽ ነገር እንጂ አይጠበቅም ። ነገር ግን እንዲህ አይነቱን ተግባር ሰለፍይ ነኝ ከሚል ያውም አስተማሪ ነኝ ብሎ ሰዎች በዲናቸው ከሚያምኑትና ከሚከተሉት አካል ሲሆን በጣም ያስፈራል ። ይህ የሚያሳየው አብዛኛዎች የሚሰሙትንና የሚያውቁት የኢስላም አስተምሮ ከህይወታቸው እንቅስቃሴ ጋር እያገናኙ ሳይሆን የሚኖሩት በራሳቸው የዝንባሌ ውቅያኖስ ውስጥ እየተናወጡ መሆኑን ነው ።
የኢስላም ሊቃውንቶች ከሙስሊሞች ውስጥ ያለ እውቀት የሚሰራ ከነሳራዎች ይመሳሰላል ። ባወቀው የማይሰራ ደግሞ ከአይሁዶች ይመሳሰላል ይላሉ ። ለማንኛውም ደብቀን የምናራምደው እርካሽ አላማ ሜዳ መውጣቱ አይቀርምና ሰው ፊት ማፈርን ከመፍራት ይልቅ አላህ ፊት ማፈርን ፈርተን መጠንቀቁ ይበጃል ።
ራሴንና ሰለፍዮችን አደራ ለማለት የምወደው ከድብቅ እኩይ አላማ ወጥተን ወደ ግልፅ የስኬት አላማ እንሸጋገር ። ለዲናችን ታማኝ ለመሆን መጀመሪያ ለራሳችን ታማኝ እንሁን ። አላህን መፍራት የሚባለው ምን ማለት እንደሆነ ቀደምቶች ሲገልፁ እሾሃማ በሆነ ጭቃ ላይ በባዶ እግር እንደ መጓዝ ነው ይላሉ ። በመሆኑም ለየአንዳንዱ ተግባራችን የሸሪዓ ልጓም እናብጅለት ። ከማንም በፊት ተጠቃሚዮቹ ራሳችን ስለምንሆን ። ከጎናችን ሆነው ወደተለያየ ነገር የሚገፋፉን ሰዎች ለምን እንደተጠጉንና ምን ፈልገው እንደሆነ ለማጤን እንሞክር አዛኝ መስለው ለውደት እንዳይዳርጉን መጠንቀቁ ጥሩ ነው ።
አብዛኞቹ ንፁሃንን ወደ እኩይ ተግባይ የሚያስገቡ አካላት ከኢብሊስ ስራ ድርሻ ያላቸው ናቸው ። ኢብሊስ ተረግሞ ከአላህ እዝነት በተባረረ ጊዜ ብቻዬን መሆን የለብኝም ብሎ ንፁዃንን ከጎኑ ለማሰለፍ ያለ እንቅልፍ ይለፋል ።
አላህ ከእኩይ አስተሳሰብና ተግባር ይጠብቀን ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
🌱 ወላሂ ምስጋና ደጋግም
      👌¯¯¯¯¯☔️¯¯¯¯¯👌

👉 በኩላሊት እጥበት ግዜ ደም ከሰውነታችን በቀዩ ቱቦ ይወጣና በ #dialysis machine አልፎ በሰማያዊው ቱቦ ተመልሶ ወደ ሰዉነታችን ይገባል።

እንዲህ እያለ ለ4 ሰዓታት ይቆያል። ይህ #dialysis በሳምንት 3 ጊዜ፣ በወር 12 ግዜ  ይደረጋል። በአጠቃላይ በወር ለ 48 ሰዓታት ታማሚው  ሳይንቀሳቀስ #dialysis ያደርጋል።

👉 እኔ እና አንተ ግን ኩላሊታችን ያለምንም ህመም እና ስቃይ በቀን 36 ግዜ ራሱን በራሱ ያጥባል።

👌 #እና_አላህን_እናመስግን!!!
ፈጣሪ የዋለልንን ፀጋ እናስታውስ።
በዚህ ህመም ለሚሰቃዩትም ሀያሉ ጌታ አላህ   ጤናቸውን ይመልስላቸው።

✉️ ምናልባት አንተ ሼር ባረከው አይቶ ቢያንስ 1ሰው አይቶ ይማርበታል። ሌሎችን ሼር በማረግ እናስተምር መልካም ቀን

©️𝕠py

🌱 ✉️ ✉️ 🌴 👇👇👇
https://www.tg-me.com/AbuImranAselefy/10901
🔹 ዐቅለኛ ማለት ኸይርና ሸርን የሚያውቅ ማለት አይደለም ። ነገር ግን ዐቅለኛ ማለት ኸይር ሲያይ የሚከተልና ሸር ሲያይ የሚርቅ ነው ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
ፊትና አላህ ያዘዘውን በመተው እንጂ አይመጣም ።

قال شيخ الإسلام ابن تيمية - رحمه الله -:

ولا تقع فتنة إلا من ترك ما أمر الله بـه

فإنـه سبحانه أمر بالحق وأمر بِالصّــبر

فالفتنة إما من ترك الحق

        وإما من ترك الصبر

           الاستقامة ( ١ /٣٩ )

        ↪️   አሁንም ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል  : –

"  ፊትና የሚከሰተው አላህ ያዘዘውን ነገር በመተው እንጂ በሌላ አይደለም ። አላህ ጥራት የተገባው ጌታ በሐቅና በሶብር አዟል ።
ፊትና የሚከሰተው ደግሞ ወይ ሐቅን በመተው ነው ወይም ሶብርን በመተው ነው " ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
🔹 ኸይር ያልተሰራበት እድሜ ፀፀት

‏قال الحسن البصري رحمه الله :

" يعرض على ابن آدم يوم القيامة ساعات عمره ، فكل ساعة لم يحدث فيها خيراً تقطعت نفسه عليها حسرات "

[حفظ العمر]

ሀሰን አል በስሪ ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላል :-

" ለአደም ልጅ የቂያማ ቀን የእድሜው ሰዓቶች ይቀርቡለታል ። እያንዳዱ መልካም ስራ ያልሰራበትን ጊዜ በፀፀት ነፍሱ ትቆረጥበታለች "

https://www.tg-me.com/bahruteka
🔷  አስገራሚ ቅናት

አቡ ዓብዲላህ ሙሀመድ ኢብኑ አህመድ ኢብኑ ሙሳ አልቃዲ የተባለ ሰው የቃዲ ሙሳ ኢብኑ ኢስሃቅ የፍርድ ሸንጎ ላይ በ286 የሂጅሪያ አቆጣጠር ተገኝቼ ነበር ይላል ።
አንዲት የተፈታች ሴት ወደ ቃዲው መጣች
ወልይዋ በባልዋ ላይ 500 ዲናር መህር አለበት ሲል ሞገተ ። ባልየው የለብኝም አለ ። ቃዲው ምስክር ጠየቃት ። ቀርበዋል ተባለ ። ቃዲው ከምስክሮቹ ውስጥ አንዱን ጠርቶ ቃሉን እንዲሰጥ ጠየቀው ። ምስክሩ ቀርቦ ሴትየዋን ጠርቶ እንድትቆም ጠየቀ ። ሚስቱን የፈታው ባል ምን ልታደርጉ ነው ሲል ጠየቀ ።
ወልይዋ ፊቷን ተከፍታ ሊያዩዋት ነው የምስክርነት ቃላቸው ካዩዋትና ካወቁዋት በኃላ ሊሰጡ አለው ።
ሰውየውም :– እኔ ቃዲውን በራሴ ላይ ምስክር አድርጌያለሁ ያለችው 500 ዲናር አለብኝ እከፍላለሁ ፊቷን እንዳትከፍት አለ ።
ከዛም ሴትየዋ ወደ ቦታዋ እንድትመለስና የፈታት ባልዋ ምን እንዳለ ተነገራት ። እሷም እንዲህ አለች :– እኔም ቃዲውን ምስክር አድርጌያለሁ ይህንን መህሬን ለሱ ስጦታ አድርጌለታለሁ ። በዱንያም በአኼራም ከሀቄ ነፃ እንዲሆን አድርጌዋለሁ አለች ።

ጂልባቡል መርአቲል ሙስሊማ
( 113 - 114) ሊሸይኽ አልባኒ

https://www.tg-me.com/bahruteka
👉 የነብያት ዳዕዋ ለምን ይተዋል ?

አላህ ከመላኢኮችና ከሰዎችም መልእክተኛን መርጧል ። የእነዚህ ከሰዎች ምርጦች ተልእኮ የሰውን ልጅ ፍጡርን ከማምለክ አውጥቶ አላህን ወደማምለክ ማሸጋገር ነው ።
ይህ የምርጦቹ ምርጥ ተልእኮ ነው በዱዓቶች ጫንቃ ላይ የተጣለው ። ዳዒ ማለት ተልእኮ የነብያት ተልእኮ ነው ። የሰዎችን ነፍስ ለማዳን ሰበብ መሆን ነው አላማው ። ሰው ምን ይለኛልን ቸል ብሎ ለሰው ልጆች የዘላለማዊ ስኬት መንገድ ማሳየት ፣ ወደ ሐቅ መጣራት ፣ ሐቅና ባጢልን ፣ ተውሒድና ሽርክን ፣ ሱናና ቢዳዐን ለይቶ ማስተማር ለዚህ ተልእኮ ነብያት የከፈሉትን ዋጋ መልክፈል የዳዒ ግብ መሆን አለበት ። ዳዒ የነብያቶች ወራሽ ከሆነ ነብያት ለተልእኳቸው ተርበዋል ፣ ተጠምተዋል ፣ ክብራቸው ተነክቷል ፣ ተሰደዋል ፣ ተደብድበዋል ፣ ተወግረዋል ፣ ከዚህ አልፎም በመጋዝ ለሁለት ተከፍሏል ፣ ተገድለዋል ። ይህ ነው ነብያቶች ክብራቸው ከፍ እንዲል ያደረገውና ትውስታቸው በአማኞች ልቦና ህያው ሆኖ እንዲኖር ምክንያት የሆነው ።
ዳዕዋው ተውሒድን ማወጅና ሽርክን ማውገዝ ግቡ የሰው ልጆችን ፍጡርን ከማምለክ አውጥቶ ፈጣሪን ወደ ማምለክ ማሸጋገር ያልሆ ዳዒ የነብያት ወራሽ አይደለም ። በዳዕዋው የአላህን ውዴታ የሚፈልግና ከዱንያዊ ጥቅም ርቆ አኼራን ከፊት ለፊቱ ያደረገ ዳዒ ዳዕዋው በሰዎች ልቦና ህይወት ይዘራል ። አላህ ክስረት የሻለት ካልሆነ ልቡ ለሐቅ ተከፍቶ በተውበት ብርሃን ወደ ስኬት ጎዳና ያመራል ። የዚህ አይነቱ ዳዒ አላማና ግቡን ተረድቶ ወደ ሂዳያው ሜዳ የወረደ ነው ።
በተቃራኒው በጌታው ያልተመካ ጫንቃው ከተቋሙ በሚደረግለት ድጎማ ግዞት ስር የሆነና ዳዕዋው በአለቆቹን የልብ ትርታ ላይ የተመረኮዘ ዳዒ ከዳዒነት ስሙ እንጂ አልወረሰም ። ጭንቀቱ አለቆቹ ምን ይሉ ይሆን ነው ። አላማው ሁሉንም ማስደሰት ነው ። የነብያቶች ዳዕዋ እሱ ዘንድ አላዋቂነትና ቂልነት ነው ። የዚህ አይነት ዱዓቶች ዛሬ በመላ ሀገሪቱ ተብራክተው ይታያል ። ድሮ የተብሊጎች ዳዕዋ ሲባል የነበረው ፈዳኢልና ረቃኢቅ ላይ ያተኮረ ዳዕዋ አላህ ካዘነለት ውጪ የሁሉም ሆኗል ።
የአላህ መልእክተኛ ቆመው ከሽርክና ቢዳዓ ያስጠነቀቁባቸው ሶሓቦች ፈለጋቸውን ተከትለው ተውሒድ እያወጁ ሽርክን ያንኮታኩቱባቸው መድረኮች ዛሬ መጅሊስ በሚያስተዳድራቸው መስጂዶች ላይ የዚህ አይነቱ ዳዕዋ እንደሰማይ ርቋቸዋል ። በየትኛውም ቋንቋ የሚደረገው ዳዕዋ የነሲሐዎች 30 የእንቅልፍ ክኒኖች አይነት ሆነዋል ። ሰዎች እየሰሙ እንቅፍ ይወስዳቸዋል ። በቀብር ላይ ጠዋፍ የሚያደርጉ ፣ አንዬ ፣ ዳንዬ ፣ ሾንክዬ ፣ ጌታው ሸይኽዬ ፣ አባድርዬ ፣ ሑሰይንዬ ፣ ጫልዬ ፣ አልከስዬ ፣ ቃጥባርዬ ፣ አብሬትዬ …… እያሉ ጉታዳቸውን ፣ ችግራቸውን ፣ ጭንቃቸውን ለሙታን የሚናገሩና ከእነርሱ ፈረጀት የሚለምኑ ጀለብያና ኮፍያ ውስጥ ያሉ ቀብር አምላኪዮች ፊት ለፊታቸው ተደርድረው ጥሩ መሰረት ላይ ካልቆሙ ንፋስ እንደበተነው ብናኝ የሚሆኑ እንደ ስለመልካም ፀባይ ፣ ስለ ወንድማማችነት ፣ ስለረመረዳዳት፣ ስለጎረቤት ሐቅና ስለሀሜት የመሳሰሉ ዳዕዋዎችን ያደርጋሉ ። የእንደነዚህ አይነት ዳዒዎች ምሳሌ አላህ በሰጠው እውቀቱ የሰዎችን ህይወት ለማዳን ሰበብ ለማስገኘት በሞያው ቃል ገብቶ ነጭ ገዋን ለብሶ አንገቱ ላይ ማዳመጫ አድርጎ ደረቱ ላይ ዶ/ር እገሌ የሚል ታፔላ ለጥፎ ከጠረዼዛ በስተጀርባ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ በሽተኛ ፊት ለፊቱ ሲቀመጥ ስለቀጠረው የሆስፒታል ባለቤት ጥቅም እንደሚያስብ ሐኪም ነው !!! ።
ዳዒ ነኝ ካልክ የነብያት ወራሽ ነህና የነብያቶችን ዳዕዋ አድርግ !

https://www.tg-me.com/bahruteka
🔹ዱንያ ፈልጎ አኼራ የለም


قال الحسن البصري  - رحمه الله  - : 

" يا معشر الشباب عليكم بالآخرة فاطلبوها ،
فكثيراً رأينا مَن طلب الآخرة فأدركها مع الدنيا ؛
وما رأينا أحدًا طلب الدنيا فأدرك الآخرة مع الدنيا ".

  الزهد الكبير للبيهقي ١٢

     🔷   አል ሐሰኑል በስሪይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" እናንተ የወጣት ስብስቦች አኼራን በመፈለግ አደራችሁን ።
ብዙ ያየነው አኼራን የፈለገ ከዱንያ ጋር ሲያገኛት ነው  ።
ዱንያን የፈለገ ከአኼራ ጋር ሲያገኝ አላየንም ።

https://www.tg-me.com/bahruteka
➡️ የአላህ ባሮችና ዱንያ

قال الحسن البصري – رحمه الله:-

"خطب عمر بن الخطاب وهو خليفة وعليه إزار فيه ثنتي عشر رقعة."


            حلية الأولياء (1/53)

👉 ሐሰኑል በስርይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል፦
"ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ከሊፋ በነበረበት ጊዜ 12 ቦታው የተለጠፈ (ተቀዶ) ሽርጥ ለብሶ ኹጥባ አድርጓል።"

https://www.tg-me.com/bahruteka
🎤  ሙስሊምና ወቅት

ጊዜ አላህ ለሰው ልጆች በእኩል ከሰጠው ፀጋዎች አንዱ ነው ። የሰው ልጅ ህይወቱ በጊዜ  የተገደበ ነው ። ጊዜ መቆሚያው እስከሚደርስ በረቀቀ ስርአት ከመጓዝ አይታቀብም ። ወደ ፊትም ሆነ ወደ ኃላ ማድረግ አይቻልም ። በተወሰነለት መስመር ወደ ተወሰነለት ፌርማታ ይጓዛል ። በጊዜ መርከብ ተሳፋሪዎች ብዙ ናቸው ። ነቅተው ጉዞዉን የሚከታተሉት ጥቂቶች ሲሆኑ የጉዞዉን እንቅስቃሴ አላይም ብለው የተኙት ግን ብዙዎች ናቸው ። እነዚህ ከእንቅልፋቸው የሚነቁት መውረጃችሁ ደርሳችኃል የሚል  ተጣሪ መጥቶ ድንገት ሲቀሰቅሳቸው ነው ።
      ኢስላም ጊዜ ማለት ምን ማለት እንደሆነና ሙስሊሞች ጊዜያቸውን በምን መልኩ መጠቀም እንዳለባቸው ትኩረት ሰጥቶ አስተምሯል ። ጊዜ የህይወት መርከብ መሆኑን በግልፅ መርህ አስቀምጧል ። ጊዜውን የተጠቀመ የህይወት ሚስጢር የገባው ሲሆን ጊዜውን ያልተጠቀመ የህይወት ትርጉም ያልገባው መሆኑን አስረድቷል ። ህይወት ማለት የሰከንዶች፣ የደቂቃዎች ፣ የሳአታት ፣ የቀናት ፣ የሳምንታት ፣ የወራትና የአመታት ውጤት መሆኑን በተጨባጭ ማስረጃ አረጋግጧል ።
    ቀደምት የኢስላም ሊቃውንት ሰለፎች ይህን ተገንዝበው ጊዜያቸውን በአግባቡ ተጠቅመዋል ። የአላህ መልእክተኛን " ሁለት ፀጋዎች ብዙ ሰዎች ይሞኙባቸዋል , ጤንነትና ክፍት ጊዜ "
ብለው በአግባቡ አስገንዝበዋል ። ከዚህ በመነሳት ነው ታላቁ ሊቅ አል ሐሰኑል አል በስሪ እንዲህ የሚለው : –

" ሰዎችን አግኝቻለሁ አንዳቸው በእድሜው ከወርቁና ከብሩ የበለጠ ስስታም ሆኖ " ።

       ኢማሙ አሽሻፍዕይም – ረሒመሁላሁ እነዲህ ይላሉ :–
" ከሱፍዮች ጋር በቆየሁበት ጊዜ የተጠቀምኩት " ጊዜ ሰይፍ ነው ። ካልቆረጥከው ይቆርጠሃል" ። የሚለውን ነው "። 
ታዲያ እኛ ለጊዜ ያለን ቦታ ምን ይመስላል ? ጊዜ ህይወታችን ነው ወይስ ጠላታችን ? ምክንያቱም ብዙ ሙስሊሞች ጊዜ እናጥፋ ብለው አልባሌ ተግባር ሲከውኑ ይታያል !!! ። ከላይ እንዳልኳችሁ ጊዜ አለህ ለሰዎች እኩል ከሰጣቸው ፀጋዎች አንዱ ነው ። አንዳንዱ  ጊዜውን ተጠቅሞ የሁለት ሀገር የስኬት ማማ ላይ ሲወጣ ሌላው ጊዜውን አጥፍቶ የጀሀነም አዘቅት ይወርዳል ። 
      ጊዜ ሶስት ነው ይላሉ ጠበብቶች ።
🔹 ትላንት   አልፏል ።
🔹 ነገ  መድረሳችን አይታወቅም ።
🔹 ዛሬ  እንጠቀምበት ።

http://www.tg-me.com/bahruteka
🔖        አስደሳች ዜና ለሁሉም 

🎙 በተወዳጁ ሸኻችን በሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን (አቡጦልሀ)

🕌ኮምቦልቻ ከተማ ሰላም መስጂድ በተከታታይ ከመግሪብ እስከ ኢዕሻ የሚሰጡትን ደርሶችን በቀጥታ ስርጭት (በቴሌግራም ላይቭ ) በሰላም መስጂድ ገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕላይ የምናስተላልፍላችሁ መሁንን በታላቅ ደስታ እናሳውቃለን።

📚የሚሰጡት የደርሶች አይነት እና ፕሮግራም

1⃣,  ጁሙአ፣ ቅዳሜ እና እሁድ = ቁረአን ተፍሲር

2⃣,  ሰኞ እና ማክሰኞ = ኢዕላሙ ዱአት ቢሲማቲል ሙመይአቲ ወል ሀዳዲየቲል غُላት

(إعلام الدعاة بسمات المميعة والحدادية الغلاة)

3⃣,  እረቡዕ አና ሀሙስ = ፈትሁል መጂድ (የኪታቡ ተውሂድ ሸርህ )

💧ሁላችሁም ሸር ማድረግና ከታችያለውን ሊንኩን እየተጫናችሁ በመግባት የድሉ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ጋብዘነዎታል።

⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

https://www.tg-me.com/kombolcha_selam_mesjd

https://www.tg-me.com/kombolcha_selam_mesjd

https://www.tg-me.com/kombolcha_selam_mesjd
ከሱና ለመውጣት ሰበብ የሚሆኑ ነገሮች

  يقول الإمام ابن بطة - رحمه الله -

" إعلموا إخواني أني فكرت في السبب الذي أخرج أقواما من السنة والجماعة ، واضطرهم إلى البدعة والشناعة ، وفتح باب البلية على أفئدتهم وحجب نور الحق عن بصيرتهم ، فوجدت ذلك من وجهين : أحدهما : البحث والتنقير ، وكثرة السؤال عما لا يغني ، ولا يضر العاقل جهله ، ولا ينفع المؤمن فهمه ، والآخر : مجالسة من لا تؤمن فتنته ، وتفسد القلوب صحبته ....." 

الإبانة الكبرى  ( 1/390)

🔷  ታላቁ ሊቅ ኢብኑ በጣህ - ረሒመሁላሁ - እንዲህ ይላል :-

" ወንድሞቼ እወቁ እኔ ሰወችን ከሱናና ጀማዓህ ያወጣውና ወደ ቢዳዓና ጥፋት ያስገባቸው በልባቸው ላይ የበላእ ፈተና የከፈተባቸው የሐቅን ብርሃን ከቀልብ አይናቸው የጋረደባቸው ነገር ምን እንደሆነ አሰብኩ ። ( ከዛም) በሁለት ነገር አገኘሁት :–

አንደኛ  -  
መፈላፈል ስለማይጠቅም ነገር
ዓቂል የሆነን ሰው አለማወቁ የማይገዳው አማኝንም የሱ ግንዛቤ የማይጠቅመው የሆነን ነገር ጥያቄ ማብዛት ።

ሁለተኛ   -
  ፈተናው የማይታመንና  ጓደኝነቱ ልብን የሚያበላሽ ሰው ጋር መቀማመጥ ነው "

http://www.tg-me.com/bahruteka
  🔷 ባወቁት እውቀት አለመስራት መጨረሻው

قال علي – رضى الله عنه – :

" سيأتي على الناس زمان لا يبقى من الإسلام إلا اسمه، ولا من القرآن إلا رسمه، مساجدهم يومئذ عامرة وهي خراب من الهدى، علماؤهم شر من تحت أديم السماء، منهم خرجت الفتنة وفيهم تعود ". 
موسوعة ابن أبي الدنيا (4/431)

ዐልይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ – ረዲየላሁ ዐንሁ – በዒልማቸው የማይሰሩ ሰዎችን ሁኔታ ሲነግረን እንዲህ ይላል : –

" በሰዎች ላይ ጊዜ ይመጣል ። ከእስልምና ስሙ እንጂ አይቀርም ። ከቁርኣንም ፁሑፉ እንጂ አይቀርም ። መስጂዶቻቸው በዛ ዘመን ያጌጡ ናቸው ። ነገር ግን ከትክክለኛው መንገድ የፈረሱ ናቸው ። ዑለማኦቻቸው ከሰማይ ስር ካሉ ( ኸልቆች ሁሉ ) ሸረኞች ናቸው ። ፈተናው ከእነርሱ ነው የወጣው በእነርሱም ላይ ይመለሳል " ።

http://www.tg-me.com/bahruteka
የአላህን ሐቅ አቅልሎ ማየት ውጠ ት

قال حذيفة – رضى الله عنه – قال :

" ما استخف قوم بحق الله - عزَّ وجلَّ - إلا بعث الله - عزَّ وجلَّ - عليهم من يستخف بحقهم. 

موسوعة ابن أبي الدنيا ( 4/441 )

ሑዘይፋ – ረዲየላሁ ዐንሁ – እንዲህ ይላል : –
" ሰዎች የአላህን ሐቅ ቀለል አያደርጉም አላህ በእነርሱ ላይ ሐቃቸውን የሚያቀልባቸው ቢልክባቸው እንጂ " ።

http://www.tg-me.com/bahruteka
2025/06/27 21:20:14
Back to Top
HTML Embed Code: