Telegram Web Link
✏️ || በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ወቅታዊ መረጃዎች !


◼️ || በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በተለያዩ አጋጣሚዎች እንዲሁም አሁን ላይ የቁርጥ ልጆች እንደሆኑ እያስመሰከሩ የሚገኙት ዑመድ ኡኩሪ እና ሽመልስ በቀለ በግብፅ ሊግ እንዲሁም ቢንያም በላይ በስዊድኑ ኡመያ ክለብ እየተጫወቱ ይገኛሉ ::

የመሐል ሜዳው ፈርጥ ሽመልስ በቀለ ከቀናት በፊት ከኢትዮጵያ ወደ ግብጽ ያመራ ሲሆን ከክለቡ አል መካሳ ጋር ይፋዊ ልምምድ መስራት ጀምሯል ።

የግብፅ ሊጎች ከመጀመራቸው አስቀድሞ ክለቦች የወዳጅነት ጨዋታዎችን በማድረግ ላይ ሲገኙ የሽመልስ በቀለ ክለብ አል መካሳ በነገው እለት በቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ዲድዬ ጎሜስ በሚሰለጥነው እስማኤሊያ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል ።

ሌላኛው በግብፅ ሊግ እየተጫወተ የሚገኘው ዑመድ ኡክሪ በአስዋን ክለብ አንጸባራቂ ብቃቱን እያሳየ ቢቆይም ያለፉትን ወራት በከባድ ጉዳት ከሜዳ ተገሎ መቆየቱ ይታወቃል ። ከወደ ግብጽ በወጡ መረጃዎች ዑመድ ኡክሪ ከጉዳቱ በማገገም ቀለል ያሉ ልምምዶችን መስራት መጀመሩን ክለቡ አሳውቋል ።

አስዋን ክለብ በዛሬው እለት ከ አረብ ኮንትራክተርስ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ሊያካሂድ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ለሌላ ጊዜ መዘዋወሩ ተሰምቷል ።

በአውሮፓዊቷ ስዊድን የመጀመሪያ የውድድር ዓመቱን እያሳለፈ የሚገኘው የመስመር ተጫዋቹ ቢንያም በላይ ከሰዓታት በፊት በተጠናቀቀው የሊጉ መርሀ ግብር ኡመያ ክለብ ሶስት ለ አንድ በሆነ ውጤት ሲያሸንፉ በመጀመሪያው አሰላለፍ በመካተት 89 ደቂቃዎችን በመጫወት አሳልፏል ።

"SHARE" @Beakisport
ሮሜሉ ሉካኩ 2019-20 በሁሉም የውድድር አይነት 29 ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል። ይህም በፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ሂወቱ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

"SHARE" @Beakisport
የእንግሊዝ ፕርሜርሊግ የ2019/20 የውድድር አመት ሊጠናቀቅ የመጨረሻው ሳምንት ላይ ደርሷል
የእንግሊዝ ፕርሜርሊግን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ለመጨረስ 3ተጨዋቾች ተፋጠዋል

# 1_ጂሚ_ቫርዲ [23] ጎል
# 2_ዳኒ_ኢንግስ [21] ጎል
# 3_ኤምሪክ_ኦቦሚያንግ [20] ጎል

"SHARE" @beakisport
እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 38ኛ ሳምንት| 2019-20 የውድድር ዘመን የመጨረሻ ጨዋታዎች

#FULL_TIME 🕔

• ኒውካስትል 1-3 ሊቨርፑል
• ዌስትሀም 1-1 አስቶንቪላ
• ቼልሲ 2-0 ወልቭስ
• ሌስተር ሲቲ 0-2 ማን ዩናይትድ
• አርሰናል 3-2 ዋትፎርድ
• ማንችስተር ሲቲ 5-0 ኖርዊች
• በርንሌይ 1-2 ብራይተን
• ክሪስታል ፓላስ 1-1 ቶተንሀም
• ኤቨርተን 1-3 በርንማውዝ
• ሳውዛሀምፕተን 3-1 ሼፊልድ
በቀጣይ [2020-21] ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚሳተፉ የፕሪሚየርሊግ ክለቦች, ሊቨርፑል, ማን.ሲቲ, ቼልሲ, ማን.ዮናይትድ ሆነዋል።

"SHARE" @beakisport
2019-20 የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን, የሌስተር ሲቲው ጂሚ ቫርድ የወርቅ ጫማው አሸናፊ ሆኗል።

ይህንም ያሳካ በእድሜው ትልቁ ተጨዋች ሆኗል, 33 አመቱ ሲሆን 23 ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

"SHARE" @beakisport
ከፕሪሚየር ሊጉ ሚሰናበቱት 3ቱ ክለቦች፡ በርንማውዝ, ዋትፎርድ እና ኖርዊች ሆነዋል።

"SHARE" @beakisport
ዲብሮይኔ የቴሪ ሄነሪን ሪከርድ ተጋርቷል።

ይህም በዘንድሮ ፕሪሚየርሊግ ውድድር ዘመን 20 ጎል የሆኑ ኳሶችም አመቻችቶ በማቀበል ነው። 👑

"SHARE" @beakisport
📍 || ባርሴሎና በፊሊፔ ኮቲኖ ዝውውር ያሰባቸው ውሎች !

👉 ከአርሰናል ጋር በስፋት ስሙ እየተያያዘ ያለው ብራዚላዊው ጥበበኛ ወደ ሊጉ የመመለስ ዕድሉ ሰፊ ይመስላል ። ዋነኛ የተጫዋቹ ፈላጊ ደግሞ አርሰናል ነው ። ተጫዋቹ ግን በምን መልኩ ወደ አርሰናል እንደሚመጣ አልታወቀም ። ቀደም ብሎ ክለቡ ባርሳ ተጫዋቹን በውሰት መስጠት ቢፈልግም አሁን ደግሞ በተጫዋች ልዋጭ ማድረግ አስቧል ።

👉 || ከተጫዋቹ ልዋጭ ጋር ስሙ የተነሳው ደግሞ ታዳጊው ማቲዮ ጎንዶዚ ነው ። ባርሴሎናም አርሰናል ማቲዮ ጎንዶዚ+ 45.5 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲያቀርብ ይፈልጋል ። ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ውሉ አርሰናልን ላያስደስት ይችላል ። ነገር ግን ድርድሮች እንደቀጠሉ ናቸው ። #foot_mercato ትኩስ ብሎ ባወጣው ዜናም ባርሴሎና ይሄ ማይሳካ ከሆነ ኢቫን ራኪቲች እና አርቱሮ ቪዳልን በማቲዮ ጎንዶዚ ቅያሬ ማድረግ ይፈልጋል ።

👉 || አያይዞም ዘገባው የባርሴሎና ዳይሬክተር ኤሪክ አቢዳል አርሰናል ውሉን ሊቀበል እንደሚችል ያምናል ። ሁለቱም ተጫዋቾች ግን ዕድሜያቸው 30 አልፏል ። ባርሴሎናም ምን ያህል ተጫዋቹን እንደፈለገው የሚያሳይ ነው ። ውሉ ግን የማይመስል የሚችልበት መንገድ አለ ።

ምንጭ :- #foot_mercato , METRO
📍 || ባህር ዳር ከነማ ከተጨዋቾች ጋር ድርድር ጀምሯል.....

👉 || ባህር ዳር ከነማ ወደ ተጨዋቾች ድርድር ከመግባቱ በፊት የዋና አሰልጣኙን የፋሲል ተካልኝን ውል ለሁለት ዓመት ለማራዘም ቅድመ ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል።
አሁን ደግሞ ከተጨዋቾች ጋር ድርድር የጀመሩ ሲሆን አራት ነባር ተጨዋቾች ውላቸውን ለማራዘም መስማማታቸውን ለማወቅ ችለናል።

👉 || የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ልዑል ፍቃዱ እንደተናገሩት ውላቸውን "ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለማራዘም የተስማሙት አምበሉ ደረጀ መንግስቱ፣ ፍቅረ ሚካኤል አለሙ፣ ዜናው ፈረደ እና ከተስፋ ቡድን ያደገው ሃይለየሱስ ይታየው ናቸው" ብለውናል።

ምንጭ :- Sport 52
ኪሊያን ምባፔ ነሀሴ 6 ፒኤስጂ ከአትላንታ የሚያደርገው የቻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ እንደሚያመልጠው ታውቋል።

ባአጠቃላይ በአጋጠመው የእግር አልቦ ወለምታ እስከ 3ሳምንት ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ አስታውቋል።

"SHARE" @beakisport
ጀምስ ማዲሰን ከሌስተር ሲቲጋር ለተጨማሪ 5 አመታት የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ተፈራርሟል።

አዲሱ ውልም የሳምንታዊ ደሞዙን በእጥፍ የሚያደርግለት ነው። [Talk Sport]

"SHARE" @beakisport
ጁቬንቱስ የናፖሊውን አጥቂ አርካዲዝ ሚሊክን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል ሲል ዲማርዚዮ ዘግቡዋል።

በዚህ ሲዝን በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ 10 ፈጣን ተጫዋቾች፦

10 ፊል ፎደን - 23.07mph
9 ፍሬድ - 23.17mph
8 ሎንግ - 23.21mph
7 ሜትላንድ ኔልስ - 23.27mph
6 ሶንቹ - 23.33mph
5 አሮን ዋንቢሳካ - 23.36mph
4 ትሬዝጌት - 23.36mph
3 ግሪንውድ - 23.36mph
2 ትራዎሬ - 23.48mph
1 ወከር- 23.49mph

አርሰናል በፕሪምየርሊጉ ከ 25 አመታት ቡኃላ ዝቅተኛ ነጥብ ሰብስቦ ጨርሷል።

- በፕሪምየርሊጉ ታሪክ ዝቅተኛውን ነጥብ አስመዝግበዋል (56)
- በፕሪምየርሊጉ ከቶፕ 6 ውስጥ ወቶ አጠናቋል (8th)

አርሰን ቬንገር ባሰለጠኑበት ባለፉት 22 አመታት ከ 63 ነጥብ በታች አስመዝግበው አያቁም።

ከ 2010 ወዲህ በርካታ የማን ኦፍ ዘማትች ሽልማትን ያሸነፉ ተጫዋቾች፦

ሊዮናል ሜሲ - 228
ክርስቲያኖ ሰሮናልዶ - 127
ኤደነ ሀዛርድ - 94
ዛላታን ኢብራሂምኦቪች - 89
ኔይማር - 66
ሊውዝ ሱዋሬዝ - 65
ጋሬዝ ቤል - 62
አንቱዋን ግሬዝማን - 58
አርቱሮ ቪዳል - 53
ማርኮ ሩዊስ - 50

"SHARE" @beakisport
❗️በሀገራችን ተጨማሪ 653 በኮሮና መያዙ ተረጋግጧል

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ15 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,503 የላብራቶሪ ምርመራ 653 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 170 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 15,200 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 239 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 6,526
ዛሬ የቶትንሀሙ ኮከቡ አጥቂ ሀሪ ኬን የተወለደበት ቀን ነው።

⚪️ 287 ጨዋታ
⚽️ 188 ጎል
🎯 30 ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል

🎩 11 ሀትሪክ
🥇 2 የወርቅ ጫማ

"እኔ ቶተንሀም ሆትስፐር ነኝ ምክንያቱም ክለቡን እወደዋለው። የስፐርስ ደጋፊ መሆኔን ሁሉም ሰው ያውቃል"።

መልካም ልደት #Harry ..... ባለፉት 5 የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን እንደ ሀሪ ኬን ብዙ ጎል ያስቆጠረ የለም, 119 ጎሎችን ከመረብለይ ማሳረፍ ችሏል።
ቦሪሲያ ዶርትመንድ በዝውውር ሂደት እጅግ ስኬታማው ክለብ ነው። 👑💰

"SHARE" @beakisport
ላዚዬ ብሬሽያን 2-0 አሸንፍዋል

ሲሮ ኢሞቢሌ 1 ጎል ማስቆጠሩን ተከትሎ የ ሴሪያ ጎሉን 35 አድርሱዋል ⚽️ በ አውሮፓም ለ Golden boot የሚደረገውን ፍክክር ከ ሌዋንዶዊስኪ መብለጥ ችሉዋል፡፡ ሁለቱም በ 34 ጎል እኩል እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

ኢሞቢሌ 👏👏👏

@Beakisport
🔴 ከ10 አመት በፊት በ20 አመቱ ጁቬንቱስ ቤት ውስጥ ነበር ግን ማንም ልብ አላለውም ፣ በጀርመን ለዶርትሙንድ እንዲሁም በስፔን ለሲቪያ ቢጫወትም የጎል መረቡ ጠፍቶበት ነበር። በ2016 ላዚዮን ከተቀላቀለ በኋላ ግን በ41 ጫወታ 102 ጎል አስቆጥሮ ኮምፓሱን አግኝቷል።

🔵 በዚህ ሲዝን ደግሞ በጣልያን ሴሪ ኤው በ36 ጫወታ 35 ጎል በማስቆጠር ከአውሮፓ 5ቱ ታላላቅ ሊጎች ከፍተኛው በመሆን የወርቅ ጫማውን የማግኙቱ ዕድል በጣም ሰፍቷል።

🇮🇹 35 ⚽️ ሲሮ ኢሞቢሊ
🇵🇱 34 ⚽️ ሮበርት ሎዋንዶውስኪ
🇵🇹 31 ⚽️ ክርስቲያኖ ሮናልዶ

#ሲሮ_ኢሞቢሌ በመጨረሻው ሳምንት የጣልያን ሴሪ ኤ ጫወታ 1 ጎል ካስቆጠረ በ2015-16 በጎንዛሎ ሄጉዌን የተያዘውን በሴሪ ኤው ታሪክ በአንድ ሲዝን በርካታ ጎል የማስቆጠር ሪከርድን ይጋራል። ያሳካው ይሆን?


Soccer እግር_ኳስ_The_Beautiful_Game በልዩነት በጥራት
───────────────────────────

"SHARE" @beakisport
2020-21 የቶትንሀም አዲሱ ማልያ።

"SHARE" @MULESPORT
2025/10/27 14:45:09
Back to Top
HTML Embed Code: