Telegram Web Link
"እኔ በስምሽ አምናለሁ፥ አንቺም ስለእኔ ትማልጃለሽ፥ ልጅሽም ስለአንቺ የልመናዬን ዋጋ ይሰጠኛል።"
— ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ማኅሌተ ጽጌ

ተአምርኪ ማርያም ተሰብከ በኦሪት
አመ ተሰነዓውኪ ጳጦስ ምስለ መለኮት
ዘርእየኪ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
ጸልልኒ በአዕፁቅኪ ሐመልማላዊት ዕፀት
ሦከ ኃጢአትየ ያውዒ ጽጌኪ እሳት፡፡

-ትርጉም- “ማርያም ሆይ ነበልባል ከሐመልማል ተዋሕዶ ሙሴ በደብረ ኮሬብ ባየ ጊዜ ተአምርሽ በኦሪት ተሰበከ ተነገረ፡ ፡ ምሳሌሽ በሐመልማልና በእሳት አምሳል የታየ ማርያም ሆይ ጽጌ ልጅሽ ኃጢአቴን ያጠፋልኝ ዘንድ በጥላሽ ሥር አስጠጊኝ፡፡” (አንድ ሊቅ እንደተረጎሙት)

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ፡፡
🌕🌖🌗እንኳን #ለወርኃ_ጽጌ በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ!🌓🌔🌕

በሀገራችን የመስከረምና የጥቅምት ወራት የአበባ ወራት /ዘመነ ጽጌ/ ናቸው፡፡
ይህም ወቅት ተራሮች በአበባ የሚያጌጡበትና ለዓይን ማራኪ የሚሆኑበት ጊዜ ነው፡፡

በዚህም ዘመን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ......

✟...... “ስለልብስስ ስለምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፡፡ አይደክሙም፣አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡ እግዚአብሔርን ዛሬያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህየሚያለብሰው ከሆነ እናንተ እምነት የጐደላችሁ እናንተንማይልቁን እንዴት እንግዲህ ምን እንበላለን ምንስ እንጠጣለን?ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ ..."....✟
/ማቴ.5፡28-33/

በማለት የተናገረውን ቃል በማሰብ መጨነቅ የሚገባንመንግሥተ ሰማያት ለመግባት እንጂ በዚህ ዓለም ስላለው ነገር እንዳልሆነ፤ ተራሮችን በአበባ ያለበሰ አምላክ በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረንን እኛን ለኑሮ የሚያስፈልገንን ምግብና ልብስ እንደማይነሳን እያሰብን የምንዘክርበት ወቅት ነው፡፡

እንዲሁም ክቡር ዳዊት
👉 ✟.....«ተዘከር እግዚኦ ከመ መሬት ንሕነሰብእሰ ከመ ሳዕር መዋዕሊሁ ወከመ ጽጌ ገዳም ከማሁ ይፈሪ፤አቤቱ እኛ አፈር እንደሆን አስብ ሰውስ ዘመኑ እንደሣር ነውእንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል ነፋስ በነፈሰበት ጊዜያልፋልና».....✟
መዝ.1ዐ2፤14-16


በማለት እንደ ተናገረው የሰውሕይወት በሣር ይመሰላል፡፡ ሣር አድጐ አብቦ ከዚያ በኋላይደርቅና በነፋስ አማካኝነት ያ የረገፈው ሣር እየተነሣየነበረበት ቦታ ስንኳ እስከማይታወቅ ድረስ ይሆናል፡፡

ሰውም ከአደገ በኋላ በሕማም ፀሐይነት ይደርቅና በሞተ ነፋስነት ይወሰዳል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ መቃብር ሲወርድ የነበረበት ቦታ ይዘነጋል፡፡

#ስለዚህ_ዘመነ_ጽጌ_ሰው_ዘመኑ_እንደ_አበባ_በቶሎ_የሚረግፍ_መሆኑን_በማሰብ_ይህ_ዘመን_ሳያልፍ_መልካም_ሥራ_ለመሥራት_ትንሣኤ_ኅሊና_የሚነሣበት_ጊዜ_ነው፡፡

ቅዱስ ያሬድ ለዘመነ ጽጌ የሠራው ድጓም ይህንኑ የሰውን ዘመን አጭርነት የሕይወቱን ኢምንትነት በዚህ ሕላዌ የተፈጠረ ሰው በዚህ ዓለም ክፉ ሥራ መሥራት እንደሌለበት ሁልጊዜ
#በተዘክሮተ_ሞት_እንዲኖር የሚያስረዳ ነው፡፡

✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
ሁላችንም በመቅረብ እንድናውቅና ማኅሌተ ጽጌ በመጸለይና ማኅሌቱን በመቆም በመጾም የእመቤታችንን በረከትና ረድኤት የልጇን የክርስቶስን ምሕረት ለማግኘት ያድለን!

✥ እመ አምላክ ድንግል ማርያም በረድኤቷና በበረከቷ አትለየን!


በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
ከሐመር መፅሄት የተወሰደ፣ መስከረም 25 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.
የዓለም ሁሉ መድኃኒት የምትሆን ብላቴና እግሯ የተመላለሰበቱን ምድር እስም ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡ ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡ የብርሃን ልጅ ወደ ሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን በከፈለኝ የእግሯንም ጫማ እሸከም ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡

መጽሐፈ አርጋኖን - ዘሰኑይ
Forwarded from Ortoodoksii ishee dhugaa
Channaloota barumsa Amantaa Ortoodoksii Afaan Oromoottiin itti baranuu.

በአፋን ኦሮሞ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርቶችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና ብሒላተ አበው  ወይም የአበውን ምክር ለመከታተል እነዚህ Channels  ይቀላቀሉ።

Ortoodoksii Ishee Dhugaa
(እውነተኛይቷ ኦርቶዶክስ )
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @Ortodoksiidhugaa 👈
👉 @Ortodoksiidhugaa 👈


https://www.tg-me.com/+UE8OsP4gdv93PxwT
“አንድ ምንም እውቀቱና ልምዱ የሌለው ሰው ዝም ብሎ መሬት ስለ ቆፈረ ብቻ ወርቅ አያገኝም፡፡ ከዚያ ይልቅ ምንም ረብሕና ጥቅም የሌለውን ድካም ያተርፋል እንጂ፡፡ ባስ ካለም የቆፈረው ጉድጓድ ተደርምሶበት ሕይወቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደሚነበብና እንዴት መረዳት እንዳለበት ያለወቀ ሰውም ይህን ሰው ይመስላል፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ  አፈወርቅ
"የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን።"
መጽሐፈ ሚስጢር
የምንጸልየው እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለበት ለመንገር ሳይሆን እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲነግረን ነው።
        ቅዱስ አውግስጢኖስ
“እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤”
(ቆላ. 1፥18)
***
ነገረ ቅዱሳን በትክክል ለመረዳት ነገረ ክርስቶስን ርቱዕ በሆነ መንገድ መረዳት ይገባል። ራሱ የተበላሸ ከሆነ ግን አካሉ ሁሉ የተበላሸ ይሆናል። (አረዳዱን ነው።)
አዲስ ኪዳን በአብዛኛው ስለ ክርስቶስ የሚናገር ሆኖ ሳለ ስለ ድንግል ማርያም እና ሌሎች ቅዱሳን 'ከተባለው በላይ' ለምን ታስተምራላችሁ? የሚል ትችት በተደጋጋሚ እንሰማለን። በርግጥም ወንጌል ዋናው መልእክቱ ስለ ክርስቶስ ማንነት፣ የማዳን ግብራት እና ትምህርት ነው። ነገር ግን ከጥቅስ ቆጠራ ባለፈ ወደዚህ የወንጌል ትምህርት መንፈስ ጠልቀን ስንገባ ክርስቶስን ከሞተላት፣ ከተዋሐዳት እና ሕያው ትምህርቱን ከሰጣት ከቤተ ክርስቲያን ለመለየት መሞከር መቀነስ (reductionism) ነው። መቀነስም ብቻ ሳይሆን ማዛባት ነው። የቅዱስ ጳውሎስን ስለ ክርስቶስ እና ቤተ ክርስቲያን መዋሐድ ጥቅስ ሳይመርጥ የሚመረምር ክርስቶስ ከቤተ ክርስቲያኑ (ከቅዱሳኑ ኅብረት) ጋር ያለውን ምሥጢራዊ ተሳትፎ ሊያቃልል አይችልም። የቅዱስ ጳውሎስ ተወዳጅ የቅድስና አንቀጽ "በክርስቶስ ውስጥ (in Christ) ሆናችሁ" የምትል ናት። (ሮሜ. 6፥3፣ 8፥1፣ 8፥39፣ 12፥5፤ 1ኛ ቆሮ 1፥13፣ 1፥30፣ 4፥10፣ 12፥12፣ 15፥22፣ 16፥24፤ 2ኛ ቆሮ. 1፥21፣ 2፥14፣ 5፥17፤ ገላ. 2፥20፣ ወ.ዘ.ተ...)
ወደ ወንጌል ጠልቀህ ግባ፤ የክርስቶስና የቤተ ክርስቲያኑ ዘርፈ ብዙ አንድነት ግልጽ ይሆንልሃል። ክርስቶስን የበለጠ ለማወቅ በሞከርሽ መጠን ከቅዱሳኑ ጋር ያለውን ጥልቅ የፍቅር አንድነት አለማየት ስህተት ይሆናል።
ይህም ይታወቅ ዘንድ ከጥንት ጀምሮ ቅዱስ ሄረኔዎስን በመሳሰሉ አበው ሲብራራ የነበረው የነገረ ማርያም ጉዳይ በእጅጉ ጎልቶ የወጣው ታላቁ የተዋሕዶ ነገረ ክርስቶሳዊ ጉዳይ ከመ*ናፍ*ቃን ለመጠበቅ ተጋድሎ በነበረበት በ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱስ ቄርሎስ ዘመን ነው።
የወንጌል ማዕከል የሆነው የቁርባን ምሥጢር የግድ ወደ ነገረ ቅዱሳን ይወስዳል፤ የክርስቶስና የቤተ ክርስቲያኑ የአንድነት ምሥጢር ነውና። (ማቴ. 26፥26፣ ዮሐ 6፣ 1ኛ ቆሮ. 11)
#Dn_Bereket_Azmeraw
አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሷል፤ ያበሰብሷልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
          በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመክራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይናገራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይፈፅማሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይሠራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስማማሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከናውናሉ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይልካሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያሰለጥናሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ምስክር ይሆናሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሰውን ይስባሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያለምዳሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመክራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያነጻሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከብራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸናሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስጨክናሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስተምራሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይጋርዳሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያለብሳሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ባለምዋል ያደርጋሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይቀመጣሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይፈርዳሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመረምራሉ ።
እንዲህ እናምናለን እንዲህም እንታመናለን አንድነትን ሳንለይ የተለየ እንዳይሆን ። የተቀላቀለ እንዳይሆን እንለይ።

እንደ አብርሃምና እንደ ይስሐቅ እንደ ያዕቆብም ሦስት የምንል አይደለም በገጽ ሦስት ሲሆን አንድ ነው እንጂ ።
ከፍጥረት ሁሉ እንደሚቀድም እንደ አዳም አንድ የምንል አይደለም በባሕርዪው አንድ ሲሆን ሦስት ነው እንላለን እንጂ ።

ክፉዎች አይሁድ ባለማወቃቸው የእግዚአብሔርን ገጽና አካል አንድ ነው የሚሉ በደለኞችን የይስማኤል ወገኖችንም እነሆ እንሰማቸዋለን ልቦናቸውን ያሳወሩ ናቸው ።

አምላኮቻቸውም ብዙ አጋንንቶቻቸው ብዙ የሆኑ በጣዖት የሚያመልኩ አረማውያንን እነሆ እናያቸዋለን ። እኛ ግን በጎ ጐዳና የሚያስተምሩትን እንከተላለን ። ሐዋርያት እንዲህ እያሉ እንዳስተማሩን ።

አብ ፀሐይ ነው ወልድ ፀሐይ ነው መንፈስ ቅዱስም ፀሐይ ነው ። ከሁሉ በላይ የሚሆን አንድ የእውነት ፀሐይ ነው ።

አብ እሳት ነው ወልድ እሳት ነው መንፈስ ቅዱስም እሳት ነው ። በልዕልና ያለ አንድ የሕይወት እሳት ነው ።
አብ ጎሕ ነው ወልድ ጎሕ ነው መንፈስ ቅዱስም ጎሕ ነው ። በብርሃኑ ፀዳል ጨለማ የራቀበት አንድ የጧት ጎሕ ነው ።

አብ ጒንደ ወይን ነው ወልድ ጒንደ ወይን ነው መንፈስ ቅዱስም ጒንደ ወይን ነው ። ዓለሙ ሁሉ የጣፈጠበት አንድ የሕይወት ወይን ነው ።

አብ ሐሊብ ነው ወልድ ሐሊብ ነው መንፈስ ቅዱስም ሐሊብ ነው ። ጭማሪ የሌለበት አንድ ሐሊብ እርሱ ነው ።

እንዲህም እናምናለን እንዲህም እንታመናለን ።

ምንጭ: – ቅዳሴ ማርያም
"እግዚአብሔር አምላክ የለመኑትን አይነሳምና ሁላችሁም ስለ ሀገር ሰላም፣ስለ ቤተክርስቲያን አንድነት፣ስለ ሕዝብ ደህንነትና አብሮነት ጸልዩ፤"

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
"መጥፎ ቀን እና ጥሩ ቀን የሚባል ነገር የለም። ያለው ጸሎት አድርገህ የወጣህበት ቀን እና ጸሎት ሳታደርግ የወጣህበት ቀን ነው። ያልጸለይክባቸው ቀናት በክፉ ምኞትና የሥጋ ፍላጎት የተሞሉ ስለሆኑ ክፉ ቀናት ናቸው።"
— ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ
የጌቴሴማኒ እናቶቻችንን ጥያቄ መመለስ የክብር ጉዳይ ነው
CBE 1000003777689
--
ገዳሙን የተሳላሚ ያህል አውቀዋለሁ፡፡ የሰው ፊት ማየት አይወዱም፡፡ አንድ ገዳም እንዴት መኖርና ማኖር እንዳለበት ብሔራዊ ማሳያ ናቸው፡፡ ይሠራሉ፡፡ ያስተምራሉ፡፡ ያሳድጋሉ፡፡ ይጦራሉ፡፡ በልመና አይታዩም፡፡ የሠሩትን ሲሸጡ ብቻ አይተናል፡፡ አሁንም ፊታችን የቆሙት የነበረውን ለማስቀጠል እንጅ ልመናን የማይቋረጥ ዘላቂ ተግባር አድርገው አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ … ያልታሰበ ቀን የሰው ፊት ያቆማል፡፡ እናቶቻችን ሰው ፊት መቆም አልለመዱም፡፡ ጊዜ ጥሏቸው እንጅ ኩሩዎች ሠርቶ አዳሪዎች ነበሩ፣ ናቸው፡፡ በነበሩበት የመንፈስ ልዕልና እንዲቀጥሉ ማስቻል የክብር ጉዳይ ነው፡፡ የሽግግር ጊዜያቸውን አሳጥረን በነበሩበት የትሩፋት ተግባር ማስቀጠል ግዴታችን ነው፡፡
ነገ ረቡዕ በጥናታዊ ጽሑፍ መድረክ ከቻሉ ይሳተፉ።

-ርዕስ- Mystical Theology: Insights from Spirituality -ምሥጢራዊ ነገረ መለኮት ከኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት እይታ አንጻር''

-ነገ ረቡዕ ጥቅምት 20 /02/2017 ዓ.ም

-ሰዓት 11:00

-አቅራቢ አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ(ፕ/ር)

-ቦታ 4 ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ
2025/07/03 23:09:28
Back to Top
HTML Embed Code: