Telegram Web Link
ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
Photo
ዘንድ ይገባሃልን?” አለው። እርሱም “እስከ ሞት ድረስ እቈጣ ዘንድ ይገባኛል” አለ። እግዚአብሔርም “አንተ ትበቅል ዘንድ ላልደከምህባት ላላሳደግሃትም፣ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፣ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው ቅል አዝነሃል። እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” አለው፡፡›› (ዮናስ ፬፥፩-፲፩)

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ፈጣሪያችን በአርአያውና በአምሳሉ ለፈጠረን ለእኛ ለሰዎች እንደሚያዝን፣ ተጸጽቶ ለሚመለስ ደግሞ ምሕረትን እንደሚያደርግ በዚህ ለነቢዩ ዮናስ በምሳሌ አድርጎ በነገረው መሠረት እንረዳለን፡፡ አምላከ ምሕረት እግዚአብሔር በከፋ ደረጃ ለበደሉት ለነነዌ ሰዎች ምሕረትን ያደረገው በሦስት ቀን ጾም ብቻ ነው፡፡ እኛም በሦስቱ ቀናት ጾም እግዚአብሔር ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ባሕርይውን ዝቅ አድርጎ፣ ሥጋን ለብሶ፣ በምድር እንደ ሰው ተመላልሶ፣ መከራን ተቀብሎና ተሰቅሎ፣ በሦስተኛ ቀን በትንሣኤው ትንሣኤን የሰጠን በሦስተኛው ቀን ነውና ይህን ድንቅ ጥበብና የአምላክ ሥራ በዘመከርና በማመን በእውነት መንገድ ተጉዘን በምጽአት ቀን ሕይወትን ልናገኝ እንዲሁም መንግሥተ ሰማያትን ልንወርስ ይገባናል፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶ፣ ልመናችንን ተቀብሎና ጾማችንን አስቦ ምሕረትን ያድርግልን፤ አሜን!!!
👍1🥰1
ጸሎት ዘአረጋዊ ዮሐንስ

“ከእኔ የተሰወርክና የተሸሸግህ ጌታዬ ሆይ! አንተነትህን ግለጥልኝ፡፡ ከእኔ ውስጥ ያለውን ያንተን ውበት አሳየኝ፡፡ ሰውነቴ ለአንተ ማደሪያ ቤተ መቅደስ ይሆን ዘንድ የሠራኸው ጌታዬ ሆይ! (፩ቆሮ.፫፥፲፮-፲፯፤፪ቆሮ.፮፥፲፮)የክብርህ ደመና ቤተ መቅደስህ የሆነውን ሰውነቴን ይክደነው፤ የመሠዊያህም አገልጋይ የሆነችው ነፍሴ በፍቅር በመሆን አንተን ቅዱስ እያሉ በአድንቆትና በአግርሞት፣ በፍጹም ትጋትና ቅድስና እንደሚያገለግሉህ ሕያዋንና መንፈሳውያን ኃይላት ታመሰግንህ ዘንድ እርዳት፡፡
የይቅርታ ውቅያኖስ የሆንክ ክርስቶስ ሆይ! ካንተ የሆነውን ብርሃናዊ ልብስ ተጎናጽፌ እንዳንጸባርቅ ባንተ ውሃነት በኃጢአት ያደፈውን ሰውነቴን እንዳጥብ ፍቀድልኝ፡፡ ሕቡዕ በሆኑ ምሥጢራት የተሞላው የክብርህ ደመና (መንፈስ ቅዱስ) እኔን ይከድነኝ ዘንድ (በእኔ ያድር ዘንድ) በዐይኔ
ከማላያቸው ጀምሬ ወደ አንተ ውበት የሚወስዱኝን የጽድቅ ጎዳናዎች አስተውል ዘንድ ባንተ ግርማ ተማርኬ ያለማቋረጥ ክብርህን አደንቅ ዘንድ እንዲሁም በዓለም ጉዳይ ዐይኖቼ ከመባከን ያርፉ ዘንድ ምንም ቢሆን ምን ከአንተ ፍቅር የሚለየኝ እንዳይኖር ከዚህ ይልቅ አንተን በመናፈቅ እንድኖር ያለማቋረጥ ፊትህን እመለከት ዘንድ የልቡናዬን ዐይኖች ግለጥልኝ የልቡናዬንም እርሻ አለስልሰው፡፡”
V solomon
14👍4🙏3
«በመንፈስ ቅድስና ያለው ሰው በላዩ የሚያበራው ብርሃን ከቅድስት ሥላሴ ስለሆነ፥ መንግሥተ ሰማያት በልቡ አለች፡፡ የሚተነፍሰው አየር፥ አጽናኝ የሆነ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ወዳጆቹም ሰማያውያን መላእክት ናቸው፡፡ ደስታውና እርካታውም የብርሃን አምላክ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው»::
ቅዱስ የሐንስ ሳባ
18👍1
"እኔ የእግዚአብሔር ስንዴ ነኝ የክርስቶስም ንጹሕ ኅብስት እሆን ዘንድ በጥርሳቸው የተፈጨሁ ነኝ።"
አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ
17👍1
ከአባቶቻችን በረከትን ያድለን:: አሜን::
👍12🥰4
በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ አንቺ ደግሞ ለጸሎቴ መጨመሪያ የወርቅ ጽንሐሕ ሁኚ ልመናዬን ባንቺ ወደ ልጅሽ ኢየሱስ ክርስቶስ አቀርብ ዘንድ፡፡ ካህን ዕጣኑን ከወርቅ ማዕጠንት እንዲጨምር እንዲሁም ጸሎቴን ከጆሮሽ እጨምራለሁ ካፌ የወጣውንም ቃል ተቀበይው በልቡናሽም ያደረ ይሁን፡፡
የልቡናሽም ትጋት ወደ ልቡናዬ ትጋት ይሁን፡፡ የልቡናሽም አሳብ ወደ ልቡናዬ አሳብ ይሁን፡፡ ልጅሽንም ለምኝው እንዳያሳፍረኝ፡፡ ተስፋም እንዳያስቆርጠኝ፡፡ የልቤንም ግዳጅ እንዲፈጽምልኝ፡፡ ዘወትርም የተመኘሁትን እንዲሰጠኝ፡፡
በመንፈስ ቅዱስ በረከትም ይባርከኝ የእጄንም ሥራ ሁሉ ያቅናልኝ፡፡ በልቡናዬም የሰው መውደድ ያሳድርብኝ፡፡ በሰውም ልቡና እኔን መውደድ ያሳድርበት፡፡ የርሱንም ቸርነት በልቤ ይጨምር በመለኮት ጨው የጣፈጥሁ ያድርገኝ፡፡ የጥበብ መብራትንም በልቡናዬ ያብራ፡፡ የዕውቀት መንፈስም ከኔ ላይ አይራቅ፡፡
ይህንን ነገር ከልጅሽ ከወዳጅሽ እሽልኝ ከክርስቲያን ልጆች ጋራ ሁሉ አስማሚኝ፡፡ ልጅሽንም ከሚወዱ ሁሉ ጋራ በፍቅር ባንድነት አኑሪኝ፡፡
ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቂኝ ከጠላቶቼም ወጥመድ ካሽክላው አድኚኝ ለጽድቅ መገዛትን የተገዛሁ አድርጊኝ፡፡ ከኃጢአት ሸክም ነፃ አድርጊኝ ኃጢአትን የሚሠራት ሁሉ የኃጢአት ባሪያዋ ነውና (ሮሜ፣ ፮፣ ፲፮፣ ፳)
በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ በላዬ ይሰለጥን ዘንድ ሰይጣንን አታሰናብችው፡፡ በምውልበትና በማድርበትም የልጅሽ ሠራዊቶች የሚሆኑ መላእክት ይጎብኙኝ ከጠላት ጦርነት ያድኑኝ ዘንድ፡፡ በልጅሽ መስቀል አጥርነት እጠሪኝ እኔ ባለሁበት ሥፍራ ሁሉ ርኩሳን መናፍስት እንዳይገቡ በቅድስናሽ መጎናጸፊያም ሠውሪኝ በልብስሽ መዓዛ እሻተት ዘንድ፡፡
ከእንቅልፍም በነቃሁ ጊዜ ያለ ስንፍና እንዳመሰግንሽ ጸሎት ለማስታጎል እንቅልፍ በመጣብኝ ጊዜ የልጅሽ የመለኮትነቱ ኃይል ከቅንድቤ ከሽፋሽፍቴም ያርቀው፡፡ አንደበቴም አንቺን ለማመስገን የተጋ የነቃ ይሁን፡፡ እግሮቼም በፊትሽ ሳይናወፁ ይቁሙ፡፡ ግዳጄን ካንቺ ዘንድ እስክፈጽም ድረስ ለጸሎቴም እጆቼ የተዘረጉ ይሁኑ ከጌታው ደመወዙን እንደሚቀበል ሰው ሁሉ፡፡ ዐሥሩ ጣቶቼም እንደፋና መብራት ይሁኑ ጠላቴን ይወጋው ዘንድ የእሳት ሰይፍም ከአንደበቴ ይውጣ፡፡ የሚቃረነውን ይቆርጠው ዘንድ በጸሎት ሳለሁ በላዬ አሳብ ማብዛትን እንግዲህ ወዲህ አይድገም፡፡
የሚወላውልም ልቡና አያምጣብኝ፡፡አባቶቼ ቅዱሳን መነኮሳት እንዲህ ይላሉ ከእግዚአብሔር ፊት የሚጸልይ ሁሉ የልቡናው ሀሳብ ከቤተክርስቲያን ውጭ ቢሆን ወይም ወደ ሥራው አንድ ልጅ ያለው ከርሱም ሌላ የሌለው ሰውን ይመስላል፡፡ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የሠዋው እርሱ ደግሞ ስለ ሥጋዊ ነገር የሚደክም የነፍሱን ነገር ቸል የሚል ይመስላል፡፡

አርጋኖን_ዘሰሉስ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
7👍6
ገነት መንግሥት ሰማያት (እንዲህ ከታች በሥዕሉ ላይ እንዳለው) ከአንበሳና ነብር፤ ከዘንዶና ድኩላ ጋራ የምንላፋበት፤ በሞት ያጣናቸውን ዘመዶች ከነጂንስ ሱሪያቸው አግኝተን የምንተቃቀፍበት፣ በአበባ ያጌጠ የመናፈሻ ቦታ አይደለም። ይህ ጉዳይ የሀገራችን ፖለቲካ ምን ያህል በእምነት ideolgy የተተበተበ መሆኑ አንድ ጥሩ ማሳያ ነው::
@Kesis_Ephrem_Eshete
4👍2
"ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ።
  ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና፦ አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥  ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ"

ሉቃ.15:17
6👍2
Forwarded from ግጻዌ
🙏 እንኳን ለታላቁ ዓቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ 🙏

⛪️ ዕለተ ሰንበት ምስባክ ⛪️

  ❤️ 1ኛ ሳምንት ዘወረደ ❤️

@gitsawe
@gitsawe
@gitsawe
👍64
#ስትጾሙ_እንደ_ግብዞች_አትጠውልጉ

የአዋጅ ጾም ስለሆነ "ትጾማለህ ወይ?" ስንባል "አዎ እጾማለሁ" ማለት መታበይ አይሆንም ውዳሴ ከንቱንም አያስከትልም።

ውዳሴ ከንቱ ሆኖ ዋጋችን የሚያስቀርብን አጿጿም ግን አለ፦

➺ ስንጾም እንደ ግብዞች በመጠውለግ፣

➺ "እስከ ምሽት" ለመጾማችን በአንድም በሌላም መልኩ ማሳወቅ፣

➺ "ከቤተክርስቲያን አሁን አስቀድሰን መመለሳችን ነው" ዓይነት የፎቶ፣ የቪድዮ፣ የጽሑፍ ማስታወቂያዎች፣

➺ የሌላውን አጿጿም በመንቀፍ (ለማስተካከል ከሆነ ክፋት ባይኖረውም) ከራሳችን ጋር እያነጻጸርን ማቅረብ (ይቺ በውስጧ 'እኛኮ ቀላል ሰው አይደለንም'ን አዝላለችና)

➺ ለሌላው ትምህርት በሚል የራስን 'ጽድቅ' ማስጣት (ግዴለህም ወንድማችን ባትነግረንም ከፍሬህ መማር ስለምንችል ነግረኸን ዋጋ ከምታጣ አንተ ከብረህልን በጸሎት ብታሳስብልን ይሻለናል)

➺ የግድ መነገር አለበት ለሌላውም ትምህርት ይሆናል ብለን ካሰብን እኛ የሚያውቁን እንኳ ሳይቀሩ እንዳይገምቱ አድርገን በሌላ ሰው ስም ብንነግር (ለካስ የሌላ ሰው ተሞክሮ እያስመሰለ የሚነግረን የራሱን ነው በሉኝ አሉ፤ ታዝቤአችሁ ዝም የምል ብቻ እንዳይመስላችሁ wisdom teeዜ እስኪታይ ድረስ ነው የምስቅባችሁ 😂😂😂 ብዬ!!! መጨረሻ ላይም አንድ ገጠመኝ እነግራችኋለሁ የራሱ ነው በሉ አሉ ሆ! አላናግር ልትሉኝ ነው እንዴ!)

➺ የታዘዘልንን የጾም ሰዓት ጠብቀን እንመገብ። ከዚያ በፊት የሚመገብ ብናገኝ በሆዳችን አንንቀፍ። ምን እንደገጠመው፣ ምን ዓይነት ችግር ላይ እንዳለ አናውቅምና። እኛ የምናየው የሰውዬው ሁለት ዲናር ነው (እኛ ብዙ ዲናር ስላለን) ጌታ የሚያውቀው ደግሞ ያለውን ሁሉ እንደሰጠ ነው። አንተ ብዙ ዲናር አለህ ከሱ እጥፍ አራት አድርገህ ሰጠህ፤ ቀሪ ግን ዐሥር አለህ። ባታውቅ ነው እንጂ እሱ ያለውን ትዳሩን በመስጠቱ ካንተ ተሽሏል። ምናልባትም እያላገጥክ ያለኸው ካንተ በተሻለው ላይ ሊሆን ይችላልና አንደበትህን ከፍ ሲልም አእምሮህን ጠብቅ።

➺ ጭራሽ የማይጾም ደግሞ ሊገጥመን ይችላልና አንማው፣ አንፍረድበት በሆዳችን ወደ አምላካችን እናመልክትለት እንጂ። እሱም የፍቅር አምላክ ነውና ስለ ወንድማችን ያቀረብነውን ልመና ይሰማናል (ውለታ የማይዘነጋ አምላክ ነውምና በእኛ ችግር ጊዜም ስለኛ የሚለምን ሰው አዘጋጅቶና ጸሎቱን ሰምቶ ይምረናልና። 'ሰው የዘራውን ያጭዳል' አደል ያለው?!)።

#ገጠመኝ

አንድ የሰ/ት/ቤት ወንድሜ ነው የነገረኝ። ወቅቱ የፍልሰታ ጾም መግቢያ ነው። "አንድ ሰው መጣና" አለ።
"አንድ ሰው መጣና 'ዘንድሮኮ ሽንብራ በጣም ተወደደ' አለኝ" አለ።

ሆ! ጀርመንኛው ገብቷችኋል አደል?! አይጠፋችሁም!

በሾርኔ'ኮ 'እኔ በሽንብራ ነው የምጾመው ቀላል ሰው እንዳልመስልህ' ነው። እና ሌላ ምንድነው ነው? እንጂ ታድያ ጉዳዩ ወደ ሥራ አመራር ቀርቦ "ለእገሌ ሽንብራ ስለ መግዛት" ብሎ አጀንዳ እንዲያዝለትኮ አይደለም።

መልካም የበረከት ጾም ያድርግልን!!!
👍173🙏3
➦'' ከመብል ከመጠጥ ታቅቦ የሚጾም አንድ ሰው በሐሜት የሰዎችን ሥጋ መብላት ከቀጠለ ይህ ጾም የግብዝነት ነው።"
ማር ይስሕቅ በመጽሐፍተ መነኮሳት

➦እስመ በጾም ኤልያስ ሰማያተ ዐርገ ዳንኤል ድኅነ እምአፈ አናብስት ወሶስና ድህነት እምእደ ረበናት
ኤልያስ በጾም ወደ ሰማይ ዐረገ ዳንኤልም ከአናብስት አፍ ዳነ ሶስናም በጾም ከሐሰት ምስክሮቹ ከረበናት እጅ ዳነች (ቅዱስ ያሬድ)

#ጾመኢየሱስ
👍122
"በጾምና በጸሎት ኃጢአት ይሠረያል በደልም ኹሉ ይደመሰሳል።"
ጾመ-ድጓ ዘወረደ
12😢6👍3🙏2
ጥያቄ ነበረኝ

አንዱ ነው ቀረብ ብሎኝ "ጥያቄ ነበረኝ" አለኝ? ምንድነው አልኩት። አሳ በጾም ይበላል ወይ አለኝ። አይበላም ሳልለው  "ብላ" ብዬ መለስኩለት። መምህር አሳ በጾም አይበላም የሚልኮ ተምሬ ነበር አለኝ።
ከተማርክ ለምን ጠየከኝ አልኩት። አይ ለማረጋገጥ ብዬ ነው አለኝ። ያኔ ስትማር እርግጠኛ አይደለም ብለውኽ ነበር? አልኩት። አላሉንም አለኝ።  በራሱ የሳቀ ይመስለኛል ሳቁ መጣ እኔ ጠንከር ባለ ቃል ነው የመለስኩለት። መንገዱን ቀጠለ። ኹለተኛ ሰው ይጠይቃል ብዬ አልገምትም።
👍25🤣41
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ዳዋ ጥሳ ፣ ተራራ ቧጣ ፣ ቋጥኝ ፈልፍላ ፣ የእምነት እና የታሪክ ቦታዎችን የመሥራት ብቃት ፣ ችሎታ ፣ መንፈሳዊነት እና መለኮታዊ ኃይል አላት ።

መስቀል አደባባይ እንዲህ ዛሬ ያም እየተነሳ የእኔ ነው ያም እየተነሳ የእኔ ነው ከማለቱ በፊት ጉቶውን ነቅላ አረሙን አርማ ስትጠቀምበት የኖረችው ይኸችው መከረኛዋ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ናት ።

አሁንም ቤተ ክርስቲያናችን የሆነ በረሃ ላይ ሄዳ እንደ መስቀል አደባባይ ዓይነት በዓላቶቿን የምታከብርበት ቦታ ብታዘጋጅ ይኸንኑ ያዘጋጀችውን ቦታ ሊቀራመቷት የሚመጡ አይጠፋም ።

ዝንጀሮ እና ጦጣ ሁል ጊዜ ያልዘራውን ያጭዳል ያላበቀለውንም ያለ ይሉኝታ ይበላል ። ቅድስት እናታችን ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችንም ይኸ ነው የገጠማት ።

ጊዜ የሚባል ፍትሐዊ ዳኛ አለ !

Zekaryas Kiros
14👍2
#"ሰላም ለእሌኒ ንግሥት ዘከሠተት መስቀለ
በጎልጎታ:ለክርስቲያን ዘይከውን ወልታ፤እምኀበ ወጽአ ጢስ በሃይማኖታ፤ወዓዲ ረከበት ቅንዋተ መስቀሉ ለክርስቶስ፤ወአግበረት ልጓመ ፈረስ በከመ ይቤ ዘካርያስ" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
2025/07/09 22:10:15
Back to Top
HTML Embed Code: